ኢህአዴግ ላይ ሲቀርቡበት ከነበሩት ሪፖርቶች በተለየ ጥቅሞቹ ላይ ያነጣጠሩ አስደንጋጭ መረጃዎች እንደወጡበት ተሰማ።

ዓለም ባንክ ርምጃ ለመውሰድ ጫፍ ደርሷል ኢህአዴግ ላይ ቀደም ሲል ሲቀርቡበት ከነበሩት ሪፖርቶች በተለየ ጥቅሞቹ ላይ ያነጣጠሩ አስደንጋጭ መረጃዎች እንደወጡበት ተሰማ። መረጃው የኢህአዴግን አንገት የማነቅ ያህል እንደሚቆጠርና ለተግባራዊነቱ የተንቀሳቀሱትን አካላት “የአስተዋይነት” ትግል ውጤት እንደሆነ ተጠቁሟል…
ኢህአዴግ በህዝብ ስም በብድርና በርዳታ የሚያገኘውን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለፖለቲካ ስራ እንደሚያውለውና ለአፈና ተቋማቱ ማጠናከሪያ እንደሚጠቀምበት የተከሰሰበት ሪፖርት መጠናቀቁን የገለጹት የጎልጉል ታማኝ ምንጮች ናቸው። ምንጮቹ እንዳሉት ሪፖርቱ የቀረበለት የዓለም ባንክ በቅርቡ መረጃውን ተቀብሎ ርምጃ ይወስዳል ተብሎ ይጠበቃል። ኢህአዴግ ርምጃው ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ለማክሸፍ የተለመደውን ሩጫ መጀመሩ ተሰምቷል።
በኢህአዴግ ላይ የቀረበው ሪፖርት የመፍትሄ ሃሳብም ያካተተ እንደሆነ የተናገሩት የጎልጉል ምንጮች፣ የዓለም ባንክ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሪፖርቱን ሙሉ በሙሉ እንደሚቀበለውና ይፋ እንደሚያደርገው አስረድተዋል። የምርመራ ዘገባውን ስላጠናውና ስላቀረበው የኢንስፔክሽን ተቋምና የስራ ተሞክሮ በቂ ግንዛቤ ያላቸው እነዚህ ክፍሎች እንደሚሉት የዓለም ባንክ ቦርድ ይህ ተቋም ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ያቀረባቸውን ሪፖርቶች ላለመቀበል አንገራግሮ እንደማያውቅ ያስረዳሉ።
በሚመሩት ህዝብ ላይ ግፍ የሚፈጽሙ መንግስታትና በልማት ስም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚያካሂዱ አገራት የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በስፍራው በመገኘትና መረጃዎችን ከመሠረታቸው ዘልቆ በመመርመር  አጥንቶ ተጠያቂ የሚያደርገው ኢንክሉሲቭ ዴቨሎፕመንት ኢንተርናሽናል Inclusive Development International (IDI) የሚባለው ተቋም ከኢትዮጵያውያኑ ሰለባዎች ውክልና በመውሰድ ስራውን ለማከናወን እንቅስቃሴ መጀመሩን ጎልጉል ምንጮቹን በመጥቀስ መዘገቡ ይታወሳል። ተቋሙም በውክልናው መሰረት ለኢንስፔክሽን ፓናል በዝርዝር የሰለባዎቹን በደል በማተት አሳውቆ ነበር።
ኢህአዴግ በርዳታና በብድር የሚያገኘውን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለፖለቲካ ስራ፣ ለአፈና፣ ለወታደራዊ አቅም ግንባታ፣ ለተለያዩ የአፈና ተቋም ሰራተኞቹ ደሞዝና ህዝብን በመርገጥ ስርዓቱን ለሚንከባከቡ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን በመክፈል ገንዘቡን ለመጠቀም ከታለመለት ዓላማ ውጪ እንደሚያውለው በበርካታ መረጃዎች ያረጋገጠው የኢንስፔክሽን ቡድን ለዚሁ ስራው ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳንና ኢትዮጵያ በቅርቡ አቅንቶ ነበር።
ምርመራው ያስደነገጠው ኢህአዴግ በተለያየ መልኩ ሰለባዎች በደላቸውን እንዳይናገሩ፣ በጥቅም የተደለሉ ሰዎችን በየቦታዎቹ በማዘጋጀትና በማስፈራራት አፈና ማካሄዱን የጎልጉል የመረጃ ምንጮች በወቅቱ ቢያስታውቁም ጎልጉል መረጃውን ለስራው መሳካት ሲባል ይፋ ከማድረግ ተቆጥቧል።
ከቀናት በፊት ሪፖርቱን አጠናቆ ለዓለም ባንክ ቦርድ ያቀረበው የኢንስፔክሽን ቡድን (ፓናል) በማያወላዳ መንገድ ተጽኖ ፈጣሪ ተቋም መሆኑንን ያስረዱት ለስራውና ለተቋሙ ቅርበት ያላቸው ክፍሎች፣ ሪፖርቱን ከቦርዱ አባላት አንዱ እንኳ አልቀበልም ቢሉ ምን ሊከሰት እንደሚችልም አብራርተዋል።
“አንድ ወይም ከአንድ በላይ የቦርድ አባላት የፓናሉን ሪፖርት ውይይት እንዲደረግበት እስካልጠየቁ ድረስ ፓናሉ ባቀረበው መሠረት እንዳለ ይጸድቃል። ከጸደቀም በኋላ ሪፖርቱ በዓለም ባንክ ስም ይፋ ይሆናል። ሪፖርቱ ታምኖበት ይፋ ከሆነ በሪፖርቱ የቀረቡት የመፍትሄ ጭብጦች ተግባራዊ ከማድረግ ውጪ ሌላ አማራጭ የለም። እስካሁን ባለው አሰራር የፓናሉ ሪፖርት ተቃውሞ አጋጥሞት አያውቅም” ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።
“ይህ ታላቅ ውጤት የተገኘው በእቅድና አስተውሎ በመራመድ ነው። ወደፊትም በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራቶች አሉ። የአገዛዙን ትምክህትና ማን አለብኝነት የሚያረግቡ፣ ብሎም የሚያተኑ ስራዎች ለመስራት ለተጀመረው ስራ ይህ ውጤት ከፍተኛ መነቃቃት ይሆናል” ሲሉ ጉዳዩን በቅርበት በመከታተል እዚህ ያበቁት ክፍሎች አስረድተዋል።
ጉዳዩ እንዴት እዚህ ደረጃ ደረሰ? ለሚሉት ጥያቄዎችና ኢህአዴግ ስለተከሰሰባቸው ዝርዝር ጉዳዮች  October 12, 2012 አስቀድሞ የዘገበውን  ማጣቀስ አግባብ ሆኖ በመገኘቱ ከዚህ በታች እንዳለ አቅርበነዋል።

ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!!  ብያኔው ከጸና ኪሣራው በቢሊዮን ዶላር ሊደርስም ይችላል!

ኢህአዴግ ከዓለም ባንክ ያገኘውን 600 ሚሊዮን ዶላርና በተመሳሳይ ፕሮጀክት ወደፊት ሊያገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ገንዘብ በተመለከተ አደጋ ውስጥ መውደቁ ተሰማ። ኢንስፔክሽን ፓናል (Inspection Panel – IP) የተሰኘ ተቋም ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው ኢህአዴግ የቀረበበት ውንጀላ ከተረጋገጠ የሚያጣው ገንዘብ በቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ታውቋል። ይፋ የሆነውን መረጃ አስመልክቶ ከኢህአዴግ ወገን እስካሁን በይፋ የተሰጠ ምላሽ የለም።
ግፍ የሚፈጽሙ መንግስታትን፣ በልማት ስም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጽሙ ወንጀሎችን መረጃዎችን በስፍራው በመገኘትና ከመሠረቱ ዘልቆ በመግባት አደራጅቶ ተጠያቂ የሚያደርገው ኢንክሉሲቭ ዴቨሎፕመንት ኢንተርናሽናል Inclusive Development International (IDI) ከሰለባዎቹ ውክልና ተሰጥቶታል። ተቋሙም በውክልናው መሰረት ለኢንስፔክሽን ፓናል በዝርዝር የሰለባዎቹን በደል በማተት አሳውቋል።
የኢህአዴግ መከላከያ ሠራዊት የሚያደርሰውን እስራት፣ ግርፋት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ከመኖሪያ ቦታ ማፈናቀል፣ የግዳጅ ሰፈራ ወዘተ በማምለጥ ወደ ኬንያ የተሰደዱ የጋምቤላ ነዋሪዎች ይህ ሁሉ ግፍ የሚፈጽምባቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በልማት ስም ከዓለም ባንክ በሚያገኘው የዕርዳታ ገንዘብ በመሆኑ ለባንኩ በላኩት የአቤቱታ ደብዳቤ አመልክተዋል።
አቤቱታውን መሠረት በማድረግ የሚደረገው ምርመራ ውጤት ይፋ ሲሆን፣ በሌሎች አገሮች እንደተደረገው በዕርዳታ ስም የሚገኝን ገንዘብ ኢህአዴግ ለፖለቲካ ተግባር መጠቀሙ ሲረጋገጥ፣ በመስከረም ወር መጀመሪያ አካባቢ ከዓለም ባንክ ተፈቅዶ የነበረው 600ሚሊዮን ዶላር ሊከለከል ይችላል፡፡
የዛሬ ዘጠኝ ዓመት አካባቢ በሟቹ ጠ/ሚ/ርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ መለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትዕዛዝ በጋምቤላ ክልል በተለይ የተማሩ ወንዶች ላይ በማተኮር 424 ንጹሐን የአኙዋክ ተወላጆች በተገደሉበት ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩት ወደ ጎረቤት አገር ኬንያ መሰደዳቸው ይታወሳል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ክልሉ ሰላም የለም፡፡ በየጊዜውም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሲካሄዱበት ቆይቷል፡፡ በተለይም ለም የሆነውን እጅግ ሰፋፊ መሬት ለውጪ ባለሃብቶች በሳንቲም በመሸጥ ላይ የሚገኘው የኢህአዴግ አገዛዝ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቀድሞው የደርግ ዘመን ሲካሄድ ከነበረው ባለፈ መልኩ እጅግ በሚያሰቅቅ ሁኔታ በመንደር ምስረታና አስገድዶ የማስፈር ፖሊሲ ከመኖሪያ ቀዬ የማፈናቀል ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን የኦክላንድ ተቋም፣ ሂውማን ራይትስ ዎች፣ … የመሳሰሉ ድርጅቶች ያወጧቸው ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡
ከ1998ዓም ጀምሮ የመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) በሚል በአራት ተከታታይና ሁለት ተጨማሪ የገንዘብ ድጎማ የሚደረግባቸውን ፕሮግራሞች የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ ይህ መሠረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን ለማሟላት ተወጥኖ የሚካሄድ ፕሮጀክት በትምህርት፣ በጤና፣ በእርሻ፣ በንጹህ ውሃ አቅርቦት፣ በገጠር መንገድ ሥራ፣ ወዘተ መስኮች ላይ እንዲውል (PBS I, PBS I-AF (Additional Financing), PBS II, PBS 11-AF, PBS-Social Accountability Program and PBS III) በማለት በተለያዩ ደረጃዎች ለተከፋፈለው ኦፐሬሽን ማስፈጸሚያ የሚውለው ገንዘብ ከ13ቢሊዮን ዶላር የሚበልጥ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛው የዓለም ባንክ ድርሻ 2ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የተቀረው በሌሎች ለጋሽ መንግሥታት እና ድርጅቶች የሚሸፈን ነው፡፡ PBS III የተሰኘውን በሦስት ንዑሳን ፕሮግራሞች የተከፋፈለውን ፕሮጀክት ለማስፈጸም በአጠቃላይ የሚፈጀው 6.3ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ የባንኩ ድርሻ የሆነውን 600ሚሊዮን ዶላር ቦርዱ መስከረም 5ቀን 2005ዓም አጽድቋል፡፡
በአስገድዶ ማስፈር፣ መንደር ምስረታና ሌሎች በርካታ የሰብዓዊ መብቶቻቸው የተጣሱባቸው በኬንያ የሚገኙ ሦስት የአኙዋክ ስደተኞች ተወካይ ድርጅቶች በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ ሌሎች የሰብዓዊ ድርጅቶች ጋር በመሆን ባንኩ ሊሰጥ የወሰነውን ገንዘብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም ከመዋል ይልቅ ለኢህአዴግ የፖለቲካ ዓላማ ማስፈጸሚያ እየዋለ መሆኑን በመጥቀስ ለባንኩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጂም ዮንግ ኪም መስከረም 6፤ 2005ዓም ደብዳቤ ልከዋል፡፡ በጥያቄያቸውም መሠረት በዓለም ባንክ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የሚፈሰው ገንዘብ “በልማት ስም የኢትዮጵያ መንግሥት በጋምቤላ ክልል ለሚያካሂደው የመንደር ምስረታ እየዋለ ነው” በማለት ይከሳል፡፡ ሲቀጥልም የአኙዋክ ሕዝብ ለዘመናት ከኖረበት መንደር በማፈናቀል “የተሻለ አገልግሎት ይሰጣችኋል” በማለት በግድ የማስፈር ተግባር እየተፈጸመ ሲሆን “የተባለው አገልግሎትም ሆነ ለእርሻ የሚሆን በቂ ቦታ እንዲሁም ለከብቶች የሚበቃ የግጦሽና የውሃ ቦታ የላቸውም” በማለት ሰፈራውን የተቃወሙ ሁሉ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ረገጣ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡ ይህንን ግፍ የሚፈጽሙት ደግሞ የዓለም ባንክ ለመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) ስም ለልማት እንዲውል ከሚሰጠው የዕርዳታ ገንዘብ በመንግሥት ተቀጥረው ደመወዝ የሚከፈላቸው ሠራተኞች መሆናቸውን ገልጾዋል፡፡ ይህንን ጉዳይ ከዓለም ባንክ ጋር እንዲነጋገሩላቸው Inclusive Development International (IDI) የተባለውን ድርጅት መወከላቸውን አስታውቀዋል፡፡ (የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)
ተመሳሳይ ጉዳዮችን በዓለምአቀፍ ደረጃ በመከታተልና በማስፈጸም የታወቀው IDI በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከተው የመልሶ ማቋቋምና ልማት ዓለምአቀፍ ባንክና (International Bank for Reconstruction and Development (IBRD)) የዓለምአቀፍ ልማት ማኅበር (International Development Association (IDA)) ሥር ለሚገኘው የኢንስፔክተር ፓናል ባለ 18ገጽ ደብዳቤ ጽፏል፡፡ (የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል) ይህ የኢንስፔክተር ቡድን ከፍተኛ ሥልጣን ያለው መ/ቤት ሲሆን የዓለም ባንክ የሚሰጠውን ገንዘብ በትክክለኛ ቦታ ላይ አለመዋሉን በመጥቀስ ክስ የሚያቀርቡ ወገኖችን ጉዳይ በመከታተልና ቦታው ድረስ የራሱን ምርመራ በማካሄድ ውጤቱ ተግባራዊ እንዲሆን የባንኩን እጅ የማስጠምዘዝ ዓቅም ያለው እንደሆነ ከዚህ በፊት ያካሄዳቸው የምርመራ ውጤቶች ይጠቁማሉ፡፡
ይህ የመርማሪ ቡድን የቀረበለትን አቤቱታ መቀበሉንና በጉዳዩ ላይ የማንም ተጽዕኖ የማይደረግበትን የራሱን ምርመራ እንደሚያደርግ ከትላንት በስቲያ ባወጣው ባለ 8ገጽ መግለጫ ላይ አሳውቋል፡፡ ይህ የአቤቱታ ፋይል ቁጥር የተሰጠው ጉዳይ በግልባጭ ለባንኩ ፕሬዚዳንትና ለከሳሽ ተወካይ ድርጅት (IDI) እንዲደርስ ተደርጓል፡፡(የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)
የሰሜን አሜሪካ ዘጋቢ ባጠናከረው መረጃ መሠረት ቡድኑ ከያዝነው ዓመት የጥቅምት አጋማሽ በኋላ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ያቀናል። ቡድኑ ስደተኞቹ የሚገኙባቸውን፣ እንዲሁም ጉዳዩን በሚመለከት አስፈላጊ የሚላቸውን ቦታዎችና ግለሰቦች ሙሉ በሙሉ ያነጋግራል። ለስራው መሳካት የሚሆነውን ሁሉ በሚፈለግበት ቦታ በመገኘት በግንባር እንደሚያከናውን ለማወቅ ተችሏል።
በተለያየ ጊዜ ኢህአዴግ የሚፈጽመውን ግፍና በደል በማደራጀት ሥርዓቱ ላይ ከትጥቅ የጠነከረ ትግል ማካሄድ እንደሚቻል አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል:: አያይዘውም በመላው አገሪቱ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣና የመብት ጥሰት በማሰባሰብ የኢህአዴግን የገንዘብ ምንጭ የማድረቅ፣ ብሎም በእርዳታ ገንዘብ የሚገነባቸውን የአፈና ተቋማት ማስለል እንደሚቻል አስታውቀዋል። ይህንን ታላቅ ስራ የሰሩትን አካላት ልምዳቸውን ለሌሎች በማካፈል አስፈላጊውን ስራ ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል።
Source: http://ethioandinet.wordpress.com

ራዲዮ ድምጻችን ይሰማ ስርጭቱን ጀመረ:የመጀመሪያው የራዲዮ ድምጻችን ይሰማ ፕሮግራም ይህ ነው ያዳምጡት ::

የመጀመሪያው የራዲዮ ድምጻችን ይሰማ ፕሮግራም ይህ ነው ያዳምጡት ::
 http://www.bilaltube.com/dimtsachin-yisema-radio-july-172013-1st-day-video_dadb7deb0.html#sthash.OGD1WvBg.dpbs

ያስታውሱ !!!
http://www.bilaltube.com/watch.php?vid=dadb7deb0
ሬዲዮ ድምፃችን ይሰማ በሳምንት ሰባት ቀናት ከምሽቱ 4.30 እንስክ 5.00 አብረን ነን በመንግስት ጃም እንዳይደረግ መፍትሄ ተዘጋጅቷል!
የኢትዮጵያ ሙስሊሙችን አመት ከመንፈቅ ያለፈ ሰላማዊ ትግል መነሻና ሂደትን እንዲሁም አሁን ያለበትን ተጨባጭና ቀጣይ ጉዞውን አስመልክቶ ህዝብ ለህዝብ መረጃ የሚለዋወጥበት የሬዲዮ ስርጭት መጀመር ከተበሰረ ጥቂት ቀናት ብቻ ነው ያለፈው፡፡ ሬዲዮ ስርጭቱ መረጃ በበቂ መልኩ ለማይደርሳቸውና በተለይም ሚዛናዊነት በጎደላቸው ዘገባዎች ለተሳሳተ አመለካከት የተዳረጉ ዜጎችን ከመታደግና በሰፊው ሊንሸራሸሩ የሚገባቸውን አጀንዳዎች ከህዝብ እንዲደርሱ የሚያስችል በመሆኑ በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል እንደ ትልቅ እድል ነው የተቆጠረው፡፡
ሬዲዮ ድምፃችን ይሰማ  በሳምንት ሰባት ቀናት ከምሽቱ 4፡30 እስከ 5፡00 አጭር ሞገድ በ 19 ሜትር ባንድ በ 15550፣ 15555፣ 15560፣ 15570፣ 15575፣ እና 15580 ኪሎ ኼርዝ (KHZ) ስርጭቱን ይጀምራል፡፡ ሬዲዮ መስመሩ ላይ ሊኖር የሚችል የስርጭት መታወክን (ጃሚንግ) ለመከላከል ታሳቢ በማድረግም የስርጭት አማራጮቹ እንዲበዙ ተደርገዋል፡፡ አድማጮችም ከላይ ከተጠቀሱት የስርጭት መስመሮች በአንዱ ፕሮግራሙን ማድመጥ ይችላሉ፡፡ የሬዲዮ ፕሮግራሙ የራሱ የሆኑ ውስን አላማዎች የሚኖሩት ሲሆን እነዚህም በስርጭት ወቅት ይፋ የሚደረጉ ይሆናሉ፡፡ የዚህን የሬዲዮ ፕሮግራም ተደራሽነት ለማስፋት በተለይ በገጠሩ የሃገራችን ክፍል ለሚኖሩ የየትኛውም እምነት ተከታይ ወገኖቻችን የስርጭት ወቅትና መስመሩን ማለትም ከምሽቱ 4፡30 እስከ 5፡00 በ 19 ሜትር ባንድ በ 15550፣ 15555፣ 15560፣ 15570፣ 15575፣ እና 15580 ኪሎ ኼርዝ (KHZ) አጭር ሞገድ ሳምንቱን በሙሉ እንደሚሰራጭ በስልክ፣ በአጭር መልዕክት (SMS) እና አመቺ በሆኑ ዘዴዎች ሁሉ ያስተላልፉ፡፡ ሬዲዮ ድምፃችን ይሰማ - የሕዝብ ድምፅ፡፡

Where you from? ‹‹ከየት ነህ?››


(ምኒሊክ ጥቁር ሰው)  

ምኒልክ  ሳልሳዊ ብሎግ  

አሜሪካን ሀገር በተለያየ አጋጣሚ የምተዋወቃቸው አብዛኞቹ ነጮች የሚጠይቁኝ ጥያቄ “Where you from?” የሚል ነው፡፡ ታዲያ አሁን እንደበፊቱ ደረቴን ነፍቼ ኢትዮጵያዊ ነኝ ለማለትና ማንነቴን ለመግለፅ አንገቴን የሚያስደፉኝ በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ የኢትዮጵያን መልካም ገፅታዋን ሳይሆን የረሃብና የድርቅ ተምሳሌትነቷን፤ ፖለቲካዊ ኪሳራዋን፣ ኢኮኖሚያዊ ድቀቷን፣ የዜጎቿን ዓለም-አቀፋዊ ስደተኝነት እና ሌሎችም ውጥንቅጥ የሞላባቸውን አስቀያሚ ገፅታዎቿን ሳይቀር አብዛኞቹ ያውቁታል፡፡ አንዳንዶቹ በሚገርም ዓይነት ሁኔታ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር መኖሯንም በፍፁም አያውቁም፡፡ አረ አንዳንዴስ ሳስበው ክፉ ክፉ ነገራችንን ብቻ እያነሱ ከሚያሸማቅቁን ጭራሽ ባያውቁን ነው የሚበጀው፡፡
ታዲያ ከአስገራሚ ጥያቄዎቻቸው ውስጥ በከፊል፡-

• ‹‹ሀገራችሁ ምግብ የለም፤ ሕዝቡ አሁንም ድረስ ይራባል?››
• ‹‹መንግሥታችሁ ጎሪላ ፋይተር (ሽምቅ ተዋጊ) ነው አይደል?››
• ‹‹ለመሆኑ ዋሻ ውስጥ ነው የምትኖሩት ወይስ ቤት አላችሁ?››


የመሳሰሉት ጥያቄዎች በተደጋጋሚ ከሚያጋጥሙኝ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹማ ስለ ኢትዮጵያ መልካም ነገሮቿን ልነግራቸው በሞከርኩ ቁጥር ‹‹ታዲያ አገራችሁ አንተ እንደምታወራላት ደህና ሀገር ከሆነች ለምን እዚህ መጣህ?›› በሚል ጥያቄ ያፋጥጡኛል፡፡ በዚህ ምክንያት አሁን አሁን ኢትዮጵያዊ ነኝ ከማለት ይልቅ የተለመደው ‹‹ከየት ነህ?›› ጥያቄ ሲመጣ ‹‹Somewhere in Africa›› ‹‹ከአፍሪካ አካባቢ›› ማለትን መርጫለሁ፡፡ ታዲያ ምንቦጣኝ? ለምን ልሳቀቅ? አንጋፋዋና ዝነኛዋ ድምፃዊት አስቴር አወቀ ስለሀገር ባዜመችው አንድ ዜማዋ ላይ ‹‹ከየት ነሽ ጥያቄ ሆዴን ያስብሰኛል›› ያለችው ለካንስ ወዳ አይደለም፡፡

በነገራችን ላይ እዚህ አሜሪካ ያሉ አንዳንድ ኢትዮጵውያን ልጆቻቸውን ለመቆጣት ሲፈልጉ ‹‹ዋ! እምቢ ካልክ ኢትዮጵያ ነው የምወስድህ!›› ይሏቸዋል፡፡ አሜሪካ የሕፃንትና የሴቶች መብት በጣም የተከበረበት ሀገር ስለሆነ ከዚህ በላይ ምንም ሊሏቸውና ሊያደርጓቸው አይችሉም፡፡ ታዲያ እነዚህ ሕፃናት ገና በለጋ አዕምሯቸው ስለኢትዮጵያ ምንድነው ተቀርፆባቸው የሚያድጉት? ኢትዮጵያ ማለት ‹ሲዖል›፣ ‹የገሃነም ደጃፍ›፣ ወይም ለነሱ ቀረብ በሚል ቋንቋ ‹ጓንታናሞ ቤይ›?

በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ራሳችን የገዛ ልጆቻችንን ዛሬ እንደዚህ ካበላሸናቸው ነገ መልሰን እናቃናቸው ብንል እንዴት ይሆንልናል? አንድ ዛፍ መቃናት የሚችለው ገና በችግኝነቱ እንጂ ትንሽ ከፍ ካለ አበቃለት፡፡ መቼም እኛም ሆንን አሁን ያለው ታሪክ ተወደደም ተጠላ ጊዜውን ጠብቆ ያልፋል፤ ነገርግን በነገይቱ ኢትዮጵያ ላይ የራሳችን የሆነ ምን ዓይነት አሻራ ነው ጥለን የምናልፈው? በእንዳንዳችን ሕሊና ውስጥ ሊታሰብበትና መልስ ሊሰጥበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ ቸር ይግጠመን፡፡ምንልክ ሳልሳው ብሎግፖስት 

 

የኢትዮጲያ ሙስሊሞች ትግል ጃዋር ሙሃመድ እና ዘረኝነት

ስራጅ ታንጎ/ምንሊክ ሳልሳዊ ብሎግፖስት
ሁለት ዓመት እየያ'ዘ ባለው የኢትዮጲያ ሙስሊሞች ትግል የዲያስፖራው ድርሻ ቀላል የሚባል' አይደለም ። ሀገር ውስጥ ያለን ሰዎች እንደተከታተልነው እና በአሁኑ ሰዓት እስር ቤት በሚገኙት የሙስሊሙ ማህበረሰብ ችግረ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ምስጋና እንደተቸረው ከሆነ በውጭ የሚገኘው የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤ/ን አባላት ጳጳሱን ጨምሮ ይሄን እንቅስቃሴ በቀናነት እና በፍፁም ኢትዮጲያዊነት ሲደግፉ ተስተውሏል። ይህም የሆነበት ዋና ምክኒያት የሙስሊሙ ጥያቄ የፍትህ የህግ መንግስት ይከበር ስለነበር ነው። በእርግጥ እነዚህ ጥያቄዎች ተነስተው ንፅሁ ህሊና እና አስተዋይ አዕምሮ ላለው ሰው ከመደገፍ ውጭ ምን አማራጭ አለው?ኢትዮጲያውያንም የደረጉት ይሄንኑ ነው ለዚህም ሊመሰገኑ ይገባቸዋል። በመቀጠል የጃዋርን ንግግር ከሙስሊሙ ጥያቄ እና ከእስልምና መርህ ጋር ለማየት እንሞክራለን….ምንሊክ ሳልሳዊ ብሎግፖስት
 • #የሙስሊሙ ጥያቄ
  ሙስሊሙ ማህበረሰብ አሁን እያደረገ ያለውን ሠላማዊ የመብት ትግል የጀመረው ሁላችንም እንደምናውቀው ሦስት መሰረታዊ ጥያቄዎችን በማንገብ ነበር። ለማስታዎስ ያክል
  1. የመጂሊሱን(የኢትዮጲያ እስልምን ጉዳዮች ምክር ቤት አመራር) አመራሮች በራሳችን እንምረጥ
  2. አወሊያ በቦርድ ይተዳደር
  3. አህባሽ የተሰኘ ከእስልምን ውጭ የሆነ አስተሳሰብ በሃይል አይጫንብን።
  እነዚህ ጥያቄዎች ሲጠቃለሉ ህገ መንግስቱ ይከበር ወደ ሚል አንድምታ ይወስዱናል በእርግጥ በኋላ ላይ ሌሎች ጥያቄዎች ቢመጡም ልክ የታሰሩትይፈቱ ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ ሁሉም ነገር የሀገሪቱ የህግ የበላይየሆነው ህገ መንግስት ይከበር ከሚል አያልፍም ።
  #ስለጃዋር
  ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ጃዋር ያለው ነገር ሳይሆን የሚያሳስበው ስንትጃዋሮች አሉ የሚለው ነው የሚያስጨንቀን ሲል ጽፏል።
  እኔ ደግሞ እውን ጃዋር የኢትዮጲያ ሙስሊሞችን እና ኦሮሞዎችን ይወክላልን እላለሁ? ወንድም ፋሲል በመላምት ደረጃም ቢሆን ኦሮሞን ጠቅልሎ የጃዋር ሃሳብ አቀንቃኝ አድርጎ የማሰብ ነገር ይታያል(ቢሆን እንኳ ስሌት ይጠቀማል )ይሄ ደግሞ ጨርሶ ስህትት ነው ምክኒያቱም የኦሮሞ ህዝብ የጃዋርን ሃሳብ ከጥንቱም አይደግፍው ቢደግፈው ሃሳቡ እንዲህ ባልተንኮታኮተ ነበር።
  ወደ ጥያቄየ መልስ ስመጣ ጃዋር ሙስሊሙንም ሆነ ኦሮሞውን አይወክልም ባይ ነኝ። እንደ አንድ ግለሰብ የመሰለውን ተናግሯል ። መብቱ ነው። እኛም ተው ይሄ ሃሳብ ትክክል አይደላም እንላለን ። ታዲያሀገር ሲፈርስ ዝም እንበል እንዴ!?
  ይህ ሲባል ግን ጃዋር ለሙስሊሙ ትግል አስተዋጽኦ አላበረከተም ማለቴ አይደለም ብዙ ነገር አድርጓል እናመሰግናለን ደግሞ መታወቅ ያለበት ጃዋር ወይም ሙስሊሙ ዲያስፖራ ብቻ አይደለም እየታገለ ያለው ከነ ታማኝ ጀምሮ ሁሉም የኢሳት ጋዜጠኞች እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጲያውያን ዲያስፖራ ተሳትፈዋል ለምን ህገ መንግስት ይከበር ስለነበረ ጥያቄው።
  አሁን አሁን ጃዋር ጥያቄውን ጠቅልሎ ወዴት እየወሰደው ነው ያስብላል እንዲህም ይላል “የኦሮሞ ህዝብ መብት መከበር የሙስሊሙ መብት መከበርነው” ምክኒያቱም አብዛኛው ሙስሊም ኦሮሞ ስለሆነ እንቀጥል….
  የኦሮሞ ትግል Vs የሙስሊሙ ትግል
  እዚህ ላይ ስለ ኦሮሞ ትግል ብዙ ማለት አልፈልግም ግን ትግላቸው እነ ጃዋርም ሆኑ ሌሎች የኦሮሞ ታጋዮች ለፍትህ ለዴሞክራሲ እና ለህግ የበላይነት ከሆነ አዎ ከኢትዮጲያ ሙስሊሞች ትግል ጋር አንድ ነው። ካልሆነ ጃዋር እንደሚለውን የኦሮሞን የበላይነት ለማረጋገጥ ከሆነ የሙስሊሙ ትግል አላማው እሱ አይደለም እንለዋለን። እዚች ላይ የማዲባ ንግግር ትምጣ ታዋቂው የፀረ አፓርታይድ ታጋይ ማዲባ ማንዴላ እንዲህ ይላሉ “ እኛ የምንታገለው የነጭን የበላይነት አስወግደን የጥቁሩን የበላይነት ለማምጣይ አይደለም፤ እኛ የምንታገለው ነጩም ጥቁሩም በእኩል የሚኖርባት ደቡብ አፍሪካን ለመፍጠር ነው” እኛም እንዲህ እንላለል ‘እኛ የምንታገለው የኦሮሞን እና የሙስሊሙን የበላይነት ለማንገስ ሳይሆን በኢትዮጲያ የህግ የበላይነትን ለማስፈን ነው!”
  #ኢትዮጲያችን ወዴት ወዴት
  የሰው ልጆች ታሪክ እንደሚያስረዳው የጭቆናና የበደል መዓት አንደኛው በአንደኛው ላይ ሲጭን እንደነበረ ነው። ነጩ በጥቁሩ፤ብዝሃው በዓናሳው፤ካቶሊኩ በፕሮቴስታንቱ(በአውሮፓ የሆነ ነው) ግልባጩም ሰርቷል አጼዎቹ በሙስሊሙ እና በሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች (በኛ ሀገር) ይሄ ግን በህዝቦች እና ጨቋኞች በሚከተሉት እምነት ቡራኬ የተሰጠው አልነበረም በትቂት ግለሰቦች እና ለሆዳቸው ባደሩ የእምነቱ መሪዎች እንጂ። እነደዚህ አይነት የታሪክ ጠባሳ ያረፈባቸው የዓለማችን ህዝቦች ችግሩን የፈቱት በእርቅ እና በሰላም እንጂ ታሪኩን እየመዘዙ ለበቀል በመነሳሳት አይደለም። ከእርቅ እና ይቅር ከመባባል የተሻለም ትክክልኛ መንገድ ሊኖር አይችልም ምክኒያቱም በጊዜው የነበሩትን ጨቋኞች በአሁኑ ዘመን አግኝቶ መጠየቅ እና ለፍርድ ማቅረብ ሰለማይቻል። አክቲቪስት ታማኝ በየነ በአንድ ንግግሩ (ሁሉም ማህበረሰብ የትም ሃገር በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ተጨቁኗል እኛም ሀገር እንዲሁ በጊዜው ብንኖር እና ብናስተካክለው ደስ ባለን ግን አልሆነም እኛም አልነበርነም )ብሏል ስለዚህ ፍቅር ይሻለናል። የሁለቱም እምነቶች መጽሃፍ ይህንኑ ሃሳብ ያጠናክሩልናል።
  ቅዱስ ቁርዓን በምዕራፍ 17፤15 “….Nor can the bearer of a burden bear the burden of another… “ (ተሸካሚም ነፍስ የሌላኛውን ሃጢያት አትሸከምም)
  መፅሃፍ ቅዱስ በዘዳግም 24፤16” The fathers shall not be put to death for the children neither shall the children be put to death for the fathers every man shall be put to death for his own sin” (አባቶች ስለ ልጆች አይገደሉ ልጆችም ስለ አባቶች aይገደ..  • ለኔ ይሄ ትግላችን ለማደናቀፍ የሚደረግ ጥረት ነውና ድምጻችን ይሰማ (አሚራችን) ተገቢወን መግለጫ መስጠት አለበት ብዬ አምናለው ፡፡ እንተስ??
   #የጃዋር ሞሀመድ እብደት "እኔ ባለሁበት 99% ሙስሊም ነው ማንም ሰው ደፍሮ ቀና አይልም #በሜንጫ ነው አንገቱን የምንለው " በአሜሪካ በተደረገ ስብሰባ ላይ ከተናገረው(ሜንጫ የማጭድ ቅርፅ ያለው ረዘም ያለ ባለስለት የቁጥቋጦ መቁረጫ መሳሪያ ነው)
   እንደ አባባሉ ከሆነ ሆድ ያባውን ብቅል ነበር የሚያወጣው የጃዋር ነገር ግን ግራ የሚያጋባው አድማጭ እና መድረክ ባገኘ ቁጥር ነው ከውስጡ ደብቆ የኖረውን ለማንም የማይጠቅም መርዘኛ አስተሳሰብ አደባባይ እያወጣ ያለው።የነ ኢሳያስ አፈወርቂና የሟች መለስ ዜናዊ የመንፈስ ልጅ ለመሆን እየተንደረደረ የሚገኘው ጃዋር የጎሳና የዘር ፖለቲካ ኋላቀርና ተቀባይነቱ እጅግ እየደከመ መሆኑን ሲረዳ ብዙ ለውጥ ናፋቂ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ልቡ ሲደግፈው የነበረውን እንዲሁም ዘረኝነት የሌለበትን በኢትዮጵያዊነት መንፈስ የተቃኘውን የሙስሊሞች ትግል ላይ ተፈናጦና አቅጣጫውን አስቶ ፀሐይ የጠለቀችበትን የወረደ የፖለቲካ አስተሳሰቡን በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ለመጫን እይተፍጨረጨረ ይገኛል በስመ መሐል ሰፋሪነት የጃዋርን ደም አፋሳሽ እብደት መታገስ ግብዝነት ነው ብዙሀን ሙስሊሙም ጃዋርን በስማችን አትነግድ ሊለው ግድ ይላል።እኔ በበኩሌ እንደ ጃዋር ያሉ ግልገል መለስ ዜናዊና ኢሳያስ አፈወርቂ ኢትዮጵያችንን በደም ለማጨቅየት ሲቋምጡ እያየሁ ዝም አልልም።እውነትም ትምህርት ቀናን እንጅ ጠማማን እንደማያቀና ጃዋር አብይ ምስክር ነው።

በዋልድባ ገዳም የሚገኝው የሥኳር ፕሮጀክት ነዳጅ ማራገፊያ የመሬት መንሸራተት አጋጠመው ::

(አንድ አድርገን ሐምሌ 8 2005 ዓ.ም)፡- መንግሥት በአምስት አመቱ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዘመኑ ውስጥ በ32 ቢሊየን የኢትዮጵያ ብር በላይ  አስር የሥኳር ፋብሪካዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ውስጥ እገነባለሁ ብሎ በእቅድ መያዙ ይታወቃል ፤ መንግሥት ከፍተኛ አትኩሮት ከሰጣቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ በኋላ የሥኳር ፕሮጀክቶቹ በሁለተኝነት ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ የስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ ብዙ ውዝግብ ያስነሳው ፤ ብዙ ዋጋ ያስከፈለው አሁንም እያስከፈለ ካለው የሥኳር ፋብሪካ ውስጥ በዋልድባ ገዳም የሚገነባው አንዱ ነው፡፡ እነዚህን ፕሮጀክቶች በበላይነት የሚመራው መቀመጫው መሀል ካሳንቺስ ያደረገው በአቶ አባይ ጸሀዬ የሚመራው የስኳር ኮርፖሬሽን መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከፕሮጀክቶቹ አንዱ እና ዋንኛው የሆነውን የዋልድባን የስኳር ፋብሪካ ግንባታን በመቃወም ብዙ መነኮሳት ከበአታቸው በመሰደድ በያሉበት ሆነው ስራውን እየተቃወሙ ይገኛሉ ፤ ፕሮጀክቱን ለመስራት በየጊዜው የሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የመጡ ኮንትራክተሮች ውል በመቋጠር እንደገና በመፍታት አሁን ላይ ሶስተኛው ስራ ተቋራጭ ስራው እያካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ 
መንግሥት በትላልቅ ፕሮጀክቶች ስራቸው እንዳይተጓጎል ለማድረግ ከየትኛውም ፕሮጀክቶች በተለየ መልኩ ከብሔራዊ ነዳጅ ማከማቻ ጋር የተለየ ውል መያዙን የውስጥ ሰዎች ይገልጻሉ ፤ ለአንድም ቀን ይሁን እነዚህ ፕሮጀክቶች ላይ የሚሰሩ መኪናዎችና የተለያዩ በነዳጅ የሚሰሩ መሳሪያዎች ስራቸው እንዳይስተጓጎል በመጀመሪያ ደረጃ በተለየ ምልከታ የነዳጅ ፍላጎታቸው በየጊዜው እንደሚቀርብላቸው ምንጮች ያስረዳሉ፡፡
ይህ በእንዲህ እያለ ከሳምንታት በፊት በዋልድባ ገዳም እየተሰራ ለሚገኝው የሥኳር ልማት ፕሮጀክት አንድ ከነተሳቢው ነዳጅ የጫነ መኪና ከአዲስ አበባ ወደ ዋልድባ የጫነውን ነዳጅ ለማራገፍ ወደ ቦታው ያመራል ፤ ቦታው ላይም ነዳጅ የጫነው መኪና በጊዜው መድረስ ችሎ ነበር ፤  ነገር ግን ነዳጅ የጫነው መኪና በጊዜው ቢደርስም ነዳጁን ለማራገፍ በሚሞክርበት ጊዜ ከመሬት ስር የተቀበረው ነዳጅ ማራገፊያ በመሬት መንሸራተት ምክንያት ከዋናው ቦታ መሸሹን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህ ምክንያትም ነዳጁን የያዘው መኪና በመሬት መንሸራተት ምክንያት ቦታውን ያጣውን ነዳጅ ማከማቻ ወደ ቦታው የመመለስ ስራ እስኪሰራ እና ለመገልበጥ ሁኔታዎች እስኪመቻቹ ድረስ ለ21 ቀናት በቦታው ላይ መቆሙን ለማወቅ ተችሏል፡፡ እግዚአብሔር በአንድም በሌላም መንገድ ይናገራል ፤ በዋልድባ ከፕሮጀክቶቹ ጋር ተያይዙ ብዙ ምልክቶች እየታዩ ይገኛሉ ፤ ላስተዋለ አንድም ምልክት በቂ ነበር ላላስተዋለ እንደ ፈርኦን አስራ አንድ ምልክት ቢከታተል ልቡ ደንድኗልና የመጨረሻውን ምልክት እስከሚያይ ድረስ ፤ ባሕረ ኤርትራ ተከፍቶ እስኪውጠው ድረስ ከጥፋት ስራው ሊመለስ አይችልም ፤ መጽሀፉ ‹‹ ማንም የቆመ ቢመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ›› ይላል፡፡
እግዚአብሔር ዋልድባ ገዳምን ይታደግልን፡፡