መንግስት አላዋጣ ሲለው ጥሎት የነበረውን ካርታ ዳግም መዘዘው

እውን ይህ ካርታ ይሳካለት ይሆን?

የኢትዬጲያ ሙስሊሞች መብታችን ይከበር በማለት አሃዱ ብለው ከተነሳንበት ጊዜ አንስቶ በመንግስት አካላቶች በተደጋጋሚ በሚዲያቸው፣በጋዛጣ እንዲሁም በሚያዘጋጁት መፅሄቶች ላይ ሙስሊሞች ኢስላማዊ መንግስት ሊመሰርቱ እየተንቀሳቀሱ ነው በማለት ትግላችንን ለማሸማቀቅ እና ለዘመናት ተቻችለን እና ተከባብረን ከሌላ እምነት ተከታዬች ጋር የመኖር ባህላችንን አጣብቂኝ ውስጥ ለመክተት ብዙ ሲዳክር ቆይቷል፡፡

ሆኖም ኢስላማዊ መንግስት ሊመሰርቱ ነው በማለት የክርስቲያን ወገኖቻችንን ድጋፍ ለማግኘት ቢጣጣርም እውነታውን ግን እየዋለ እና እያደረ ለሁሉም እየተገለጠ በመምጣቱ መንግስት አስቦት የነበረው ኢስላማዊ መንግስት የምትለዋ ካርታ አላዋጣ ብላ ብሎም ኪሳራ ውስጥ ከተተችው፡፡

ሟች ጠ/ሚኒስተር አቶ መለስ ዜናዊ በመሰናበቻ የፓርላማ ንግግራቸው በኢትዬጲያ ውስጥ የሙስሊሞች ቁጥር ይበልጣል፡፡ መንግስት ያንሳል ማለቱ ስህተት ነወ፡፡ ከሃገሪቱ ካለው ህዝበ ብዛት የሙስሊሙ ቁጥር
ስለሚበልጥ ኢስላማዊ መንግስት መመስረት አለብን በማለት ከፍተኛ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው እነዛ ጥቂት ሰለፊዬች በማለት የኢትዬጲያን ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ በሃሰት መዳመጣቸው የሚታወስ ነው፡፡

የሆኖ ሆኖ የኢትዬጲያ ሙስሊሞች የእምነት ወኪሎቻችንን እኛው እንምረጥ ነው ያልነው አይደለም ሸሪአዊ መንግስት ለመመስረት ማሰብ ይቅርና የሸሪአ ፍርድ ቤታችን እንኳን ይስተካከል ብለን አልጠየቅን በማለት በመላው ሃገሪቱ አንድ አቋም መያዙን ያስተዋለው መንግስት ስቦት የነበረው ካርታ ለጊዜው አላወጣኝም በማለት መልሶ ለመክተት ተገዶ ነበር፡፡ ኮሚቴዎቻችንም ኢስላማዊ መንግስት ሊመሰርቱ ነበር በማለት ክስ ያቀረበባቸውን በማንሳት ጨዋታውን አክራሪነትን ለማንገስ የሚደረግ ሩጫ በሚል ቀይረውት ነበር፡፡

ህዝበ ሙስሊሙም ከጊዜ ወደ ጊዜ ለመብቱ መከበር ያለውን ቁርጠኝነት እየጨመረ መምጣቱን የተመለከተው መንግስት የውስጥ ሰዎችን ልኮ ትግሉን ለማቀዛቀዝ ሞከረ፡፡አሁንም ዳግም አልሳካ አለው፡፡በሙስሊሙ እና በመንግስት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት በዚሁ ሁኔታ መቀጠሉ አብዛሃኛው ማህበረሰብ ችግሩ ምኑ ጋር እንዳለ ለመረዳት አስቻለው፡፡የመንግስት የቅርብ ወዳጅ የሆኑት እነ አሜሪካም እንኳን ሳይቀሩ ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች አሸባሪዎች እንዲሁም ፅንፈኞች አይደሉም ሲሉ በአንደበታቸው ተደመጡ፡፤

በምስራቅ አፍሪካ የሽብር ስጋት ቀጠና መሆኑ በአለም አቀፍ ደረጃ ቢታወቅም በኢትዬጲያ በኩል ግን ከውስጥ አንዳችም ፅንፈኝነት ምልክት አለመታየቱን አለም አቀፍ ድርጅቶች መሰከሩ፡፡

መንግስት በቻለው አቅም አላማውን ለማሳካት የቀደዳቸው በሮች በሙሉ ለመንግስት ሽንፈትን እንጂ ድልን ሊያስገኙለት አልቻለም፡፤በተደጋጋሚ ሙስሊሙን እርስ በእርስ ለመከፋፈል ሱፊ ሰለፊ ብሎ ቁማር ተጫወተ፡፡ አልተሳካም ዞር በል ተባለ፡፡ ቀጠለ ፅንፈኛ አክራሪዎች መጡላችሁ ብሎ ሰበከ፡፡የሚሰማው ጠፋ፡፡ ድራማ ሰርቶ አቀረበ፡፡ሁሉም ህዝብ በተውኔቱ ደካማነት ሳቀበት ብሎም አላገጠበት፡፤አተርፋለው ብሎ ያላሰበው ኪሳራ ውስጥ ከተተው፡፡

በመንግስት በኩል ተሰልፈው የነበሩት አካላትም ጥያቄ አለን በማለት ገሸስ ማለትን አስቀደሙ፡፡ ይህ አልወጥልህ ያለው መንግስት የመጨረሻ የሚለውን ካርድ ለመሳብ ተገደደ፡፡

በደሴ ከተማ ዋና አጋሩን ሼህ ኑሩን አስከወዲያኛው አሰናበታቸው፡፡ሰውየውን በሂወት እያሉ ከጌታቸው ከአላህ ጋርም ከህዝብ ጋርም አጣልቶ ተጠቀመባቸው፡፤ ግብአተ መሬታቸውንም ካፋጠነ ቡሃላም ከፍተኛ ጥቅም ለማጋበስ ሩጫውን ቀጠለ፡፡፡፤

ሙስሊሙን እና ክርስቲያኑን ማህበረሰብ ለመለያየት እና ለማጋጨት ሼህ ኑሩ ጥሩ አጋጣሚ ፈጠሩ፡፤አክራሪዎች ገደሏቸው፡፡ እኔ መንግስት ፅንፈኞች አሉ ስላችሁ አልሰማ አላችሁኝ በማለት ተቋርጦ የነበረውን አስትንፋሱን ለመመለስ መፍጨርጨር ጀመረ፡፡ሼህ ኑሩን ወደ ቀጣዩ አለም አሰናብቷቸው መንግስት ግን የራሱን ቀጣይ የትግል ሜዳ አመቻቸባቸው፡፤

ከሼህ ኑሩ ሞት ቡሃላም ሌላ አንድ ተጨማሪ ካርታ ተመዘዘ፡፡ ባንዲራ(ሰንደቅ አላማ!!!!!!!). ይህን ሰንደቅ አላማ አዋረዱት አለ፡፡ በመቶሺዎች የሚቖጠሩ ሙስሊሞች በተገኙበት ቦታ አንድ ወጣት ልጅ ከአንዋር መስጂድ ጣሪያ ላይ ያገኛትን በዝናብ እና በፀሃይ የተበጣተሰች ባንዲራ ከወደቀችበት በማንሳት አውለበለባት፡፡ይህ ድርጊቱ በኢቲቪ ካሜራ ስር ገባች፡፤በሚዲያም አቀረቧት፡፡

በእርግጥ የባንዲራው ካርታ ቀደም ተብሎ የታሰበባት ጉዳይ ናት፡፡ ከዚህ ቀደም ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የኢትዬጲያ ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ እንዳይታይ ሲደብቁ ተስተውለዋል በማለት መወንጀሉ የሚታወስ ነው፡፡ ከዚህ ሁላ ሩጫ ቡሃላ በኑር መስጂድ በተካሄደው አስገራሚ ተቃውሞ ልቡ የደነገጠው መንግስት ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንዲሉ ባንዲራ አቃጠሉ በማለት ድራማ ሰርቶ በሚዲያ አቀረበ፡፡የክርስትና እምነት ተከታዬችን ለመኮርኮር እና በሙስሊሞች ላይ ለማነሳሳት ከፍተኛ ስራ ሰራ፡፡በሁሉም ሚዲያዎቹ ይህን ድራማ በሙስሊሞች ስም ሰርቶ ካራገበ ቡሃላ በፊት መዞት ወደነበረው ካርታ ተንደርድሮ ተመለሰ፡፡

የኢትዬጲያ ሙስሊሞች ተቃውሞ እያሰሙ ያሉት ኢስላማዊ መንግትስት ለመመስረት ነው ሲሉ በድጋሚ አወጁ፡፡በኢድ አደባባይ ያን ሁላ ሺህ ህዝብ ደብድበው ጥቂት ሰለፊዬች ኢስላማዊ መንግስት መመስረት አለብን በማለት ባስነሱት ግርግር እና ሁከት ችግሩ እንደተፈጠረ በመግለፅ ለሚሊዬኖች ሙስሊሞች ንቀታቸውን አሳዩ፡፡

በግብፅ የጠፈጠረውን የፖለቲካ ትኩሳት በመመርኮዝ የኢትዬጲያ ሙስሊሞች ከግብፅ እርዳታ እንደሚያገኙ እና ኢስላማዊ መንግስትም ለመመስረት እየሰሩ እንደሚገኙ መስበኩን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡

በኢድ ሰላት በመላው ሃገሪቱ የተካሄደውን ተቃውሞ ለመግታት ሙሉ ሃይሉን ተጠቅሞ ለማቀዘቀዝ ቢሞክርም ሳይሳካለት የቀረው መንግስት የፈጸመውን አሳፋሪ ድርጊትም ለመሸፋፈን እና ትቶት የነበረውን ካርታ ዳግም በመምዘዝ በሚዲያ በመቅረብ ክርስቲያኖች ሆይ ንቁ ሙስሊሞች ኢስላማዊ መንግስት ሊመሰርቱባችሁ እየታገሉ ነው የሚል እንድምታ ያለው መልዕከት ከጠ/ሚኒሰተሩን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ ባለስልጣናት በዚህ ሁለት ቀናቶች ውስጥ መግለጫቸውን ለሚዲያ ሰተዋል፡፡

ውድ ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች ሆይ መንግስት እንደ አዲስ የመዘዛት ካርድ እንደዚህ ቀደሙ ሁሉ ኪሳራን እንጂ ትርፍን እንደማያጋብስለት እሙን ነው፡፡ አዲስ በተጀመረው ፕሮፖጋንዳ ላይ ከሌላ እምነት ተከታዮች ጋር መንግስት ለመፍጠር የፈለገውን እኛን የማጋጨት ስራ ለማክሸፍ ቆርጠን መነሳት ይኖርብናል፡፡ ከዚህ ቀደም ባዳበርነው ልምድ በመነሳት ይህን ርካሽ ፕሮፖጋንዳ ለማክሰም ይከብደናል ብዬ አልገምትም፡፡በመሆኑም ሁላችንም በኩላችንን ለክርስቲያን ወገኖቻችን የትግላችንነ እውነታ እና የመንግስትን ቅጥፈት በማጋለጡ ስራ ላይ ለመሳተፍ ቆርጠን መነሳት እንደለብን መልዕክቴን በማቅረብ ሃሳቤን እዚህ ላይ እቋጫውው፡፡

አላህ እውነታውን የምናሳውቅ እና ከሁሉም እምነት ተከታዬች ጋር ኢስላም ባስተማረን መልኩ ተከባብረን የምንኖርባት ሀጋር ያድርግልን፡፡
አቡ ዳውድ ኦስማን ኦስማን
To get more information like this page

https://www.facebook.com/abudawdosman
https://www.facebook.com/abudawdosman

የጀርመን ድምጽ ራዲዮ በቅጥረኞች የተሞላ የአምባገነኖች አለቅላቂ

በጥቅም የተገዙ እና የሙያ ስነምግባርን ያልተከተሉ ጋዜጠኞች አምባ
በምንሊክ ሳልሳዊ
"ከዽምጽ ጩኸት በስተቀርና ተደበደቡ ከሚባለው ውጭ ..የሰማነው ያየነው የለም"ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ የወያኔ አለቅላቂ

"የሙስሊሙ ወጣቶች በሰላም ወደ ቤት ሲመለሱ ነው ያየሁት ...ፖሊሶች መንገድ ዳር ከመፍሰሳቸው ውጪ ሲተናኮሉ አላየሁም....ደረሰ የተባለው ድብደባ እና እስር ሲባል ከመስማት ውጪ አላየሁም::..."ዮሐንስ ገብረእግዚአብሄር የሕወሓት አባልና የጀርመን ራዲዮ ዘጋቢ (እጅግ ዘረኛ)


የጀርመን ራዲዮ ጋዜጠኞች የወያኔን መውደቅ ተከሎ ከኢቲቭ እኩ ለፍርድ የሚቀርቡ መሆኑን ልንነግራቸው እንወዳልን::
በኢድ አልፈጥር በአል ወቅት በአዲስ አበባ መንግስት በሃይማኖታችን ጣልቃ አይግባ ጥያቄያችን ይመለስ ብለው በይፋ ተቃውሞ ያሰሙትን ሙስሊም ወገኖቻችንን የአምባገነኑ የወያኔው ፖሊሶች የጭካኔ ዱላቸውን ተጠቅመው ለሞት ለመቁሰል እና ለከባድ አደጋዎች ዳርገዋቸዋል ገለዋል ደብድበዋል አስረዋል አንገላተዋል::የጀርመን ድምጽ ጋዜጠኞች ሊያውቁት የሚገባ ጉዳይ ቢኖር የሙስሊሙ ጉድይ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ጉዳይ ነው ዘር ሃይማኖት እና ማንጛውንድ ደረጃ ሳይለይ የሙስሊሙ ጥያቄ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥያቄ ነው:: እናንተ ብትዘባበቱበት እኛ ድፍን ኢትዮጵያውያን ግን የውስጣችን የደም ማንነታችን ያስተሳሰረን ስለሆነ አብረን በጋራ እንታገላለን እናሸንፋለን::

እውነታውን አለም አውቆት እየመሰከረ ባለበት ወቅት የአለም ሚዲያዎች ይህንንን እያስተጋቡበት ባለበት ጊዜ የቅጥረኞች ስብስብ የሆነው የጀርመን ድምጽ ራዲኦ ውሻ በበላበት ይጮሃል እንደሚባለው ጥያቄውን በአደርባይ የሆዳም ቋንቋ በመጠቀም ሊያልከሰክሰው ሞክሯል::ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ተብሎ ራሱን የሚጠራው ሆዳም አደርባይ ጋዜጠኛ ባቀረበው ዘገባ ላይ በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ የተካሄደውን ጭፍጨፋ አቅልሎ በወያኔ የመጅሊስ ሹመኞች እና በካድሬዎቻቸው ቃለምልልስ ለመሸፈን ዳድቶታል:: የበላበትን የአምባገነኖች ወጪት ላለመስበር ኢሕኣዲጋዊ ሲቃ እየተናነቀው የዘገበው ጌታቸው ተብየው ሙስሊም ወገኖቻችን መደብደባቸው እና መታሰራቸው 'ደግ ኣደረገ መንግስት' በሚል ኢንተርቭው ዘግቶታል::/ http://www.dw.de/popups/mediaplayer/contentId_17007641_mediaId_17008051

ከዚህ ቀደም ማንተጋፍቶት(ማሙሽ ስብሃቱ) የተባለ የዚሁ ራዲዮ የወያኔ አለቅላቂ  በፌስ ቡክ ባለፉት ሁለት አመታት የመጡ ኢትዮጵያውያን ጥያቄያቸው ፖስታቸው አግባብ አይደለም ያፈነገጠ ወዘተ በሚሉ ድፍን ሃሳቦች ሲወላገድ ነቅተንበት እጅ እና እግሩን እንዲሰበስብ አድርገነዋል የሱ ተከታይ የሆነው ሌላኛው የወያኔ አለቅላቂ በአረብ አገር ተደብቆ ሂጃብ የዘራፊ እና የዱርየ መከለያ ነው በማለት እንዲሁም ባለፉት አመታቶች አክራሪነት እየተስፋፋ ነው በሚል እደምታ የወገናችንን የሙስሊሙን ማንነት ከመዳፈርም አልፎ በትላንታው እለት የተደረገውም ተቃውሞ በሃገሪቱ ሙስሊሙ እየተደበደበ እየተገደለ እየታሰረ ባለበት ሰአት ይህ ግለሰብ በአረብ አገር ውስጥ ተደብቆ የፖሊስን ዱላ ወደ ጎን በመተው በድሬዳዋ እና በሌሎች...የኢድ ዝግጆቶች በሰላም ተጠናቀዋል በማለት የጻፈ ሲሆን የህዝብን የተቃውሞ ድምጽ ለመደበቅ ፈልጎ አልተሳካለትም::

በትላንትናው የኢድ በዓል በሺዎች ድምጻቸውን ያሰሙት በአንዋር እና በበኒን መስኪድ አይደለም ሙስሊሙ ህብረተሰብ የተመመው ወደ እስታዲየም ነበር ይህንን እያወቁ የጀርመን ጋዜጠኞች አንዋር እና በኒን መስኪድ ምን ሊያደርጉ ሄዱ? ሙስሊሙ የተደበደበው የታፈሰው የታሰረው በስታዲየም እና በአከባቢ እንጂ በሌላው መንገድ ላይ አልነበረም::እውን በአሉ የተከበረው ኢስታዲየም ነው ወይንስ በእነዚህ መስኪዶች ነው??ከዘገባዎቹ ብዙ ጥያቀዎች ማንሳት እንችላለን:: ሆዳሙ የሕወሓት አባል የሆነው ዮሃንስ ገብረእግዜር ተብሎ የሚጠራው ጋዜጠኛ ሙስሊሙ በሰላም ወደቤቱ ሲመለስ ተመልክቻለሁ በማለት ተራ የሆኑ ቃላቶችን ተጠቅሞ የፈሰሰውን ደም እንደውሃ ሊነግረን ፈልጓል:: http://www.dw.de/popups/mediaplayer/contentId_17007641_mediaId_17008432 ይህ ዮሃንስ ተብሎ የሚጠራው የሕወሓት አባል በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ዘንድ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰ እና ደረሰ የተባለውንም ከመስማት ውጪ እንዳላየ ዘግቧል::የጋዜጠኝነት ስራ ምን ያህል ድረስ ነው ብለን እንድንጠይቅ አድርጎናል::ፖሊሶች በየመንገዱ ዳር ከመፍሰሳቸው ውጪ ወንጀል ሲፈጽሙ እንዳላየ ተናግሯል:: ዮሃንስ የተባልከው ሆዳም ቅጥረኛ የተገደሉት የታሰሩት የተደበደቡት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ደም ይፍረድብህ ወያኔ ነገ አፈር ይበላል ጀርመን ተደበቅ አሜሪካ ሁን ኢትዮጵያ ጆሮህን ይዘን ለፍርድ እናቀርብሃለን::ምንሊክ ሳልሳዊ

የተፈናጠረው 11ኛ ሰአት - የወያኔ የመጨረሻው የጥላቻ አጣብቂኝ


    የታሰሩትን መፍታት ለኢሕኣዴግ የፖለቲካ ኪሳራ ያስከትላል::

ለሊቱን በስብሰባ ተወጥሮ ያደረው ወያኔ መስማማት ተስኖታል:: አደርባዮች እና የድል አጥቢያ አርበኞች ጨንቋቸዋል::ከየተኛው ወገን እንደሚለጠፉ ግራ ገብቷቸዋል:: የደህንነት እና የህወሓት ወታደራዊው ክንፍ በተጠንቀቅ ላይ ነው:: ባለስልጣናቱ ከውጪው አለም እየተደረገባቸውን ጫና እና ግፊት በፍጹም አንቀበለም የሚል ድምዳሜ ላይ ለመድረስ እርስ በእርስ ሲላተሙ አድረዋል::

ሃገራችን የጥበበኛ ህዝቦች እና የጥበበኛ መሪዎች ሃገር የምትሆንበትን ጊዜ የምንፈልግ እኛ ለውጥ ፈላጊ ልጆቿ ዛሬ ላይን ተቀምጠን ትላንትን የምንመኝ ለነገው ትውልድ የማናስብ በፍርሃት ድባብ ተውጠን ስደትን እና ገንዝእብን የምናሳድድ መሆናችን በመታወቁ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ስልጣኑንን እንዴት አስረዝሞ ሃገር ወዳድ የሆኑ ጠላት የሚላቸውን ኢትዮጵያውያንን ነቃቅሎ የሚያጠፋበት ስልት በቡድናዊ አምባገነንነት እየዶለተ እና በስልጣን ሽኩቻ እርስ በእርሱ እየተባላ ባለበት ወቅት እኛ አንድነት አጥተል በጋራ ዘመም በቀኝ አክራሪ እና ባፈጀ ባረጀ የፖለቲካ ግራውንድ እየተሽከረከርን ህዝብዊ መቆላለፍን ልንፈጥር አለመቻላችን ለአገዛዙ አመቺ አድርጎታል:: እስኪ የወያኔን ስጋት ያነቡ ዘንድ ጋብዘናል::

ከትላንት ሃምሌ 28 ሊነጋ የተበተነው የወያነው የውጥረት ስብሰባ በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ ነበረ ለሊቱን የተጓዘው::እንደቀድሞው እቅዳችን ትራንስፎርሜሽናችን ልማታችን ምናምናችን ዲሞክራሲያችን ሰላማችን የጼረ ህዝቦቻችን ...ምናምን የሚል አልነበረም ..በአተካሮ የተሞላ ውጥረት የነገሰበት አድርባዮች ፍራቻ ይነበብባቸው የነበረበት የነባር ታጋዮች ጩሐት ውይይቱት ደበላልቆት ያደረበት እንደነበር በስብሰባው ላይ የነበሩ የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጭ ተናግረዋል::

የት ከርሞ ከየት እንደመጣ ወዴትስ ሄዶ እንደነበር በማይታወቀው የአምባገነን ቡድን አስተባባሪ በደብረጽዮን የተመራው ይህ አተካራዊ ስብሰባ የወያኔ አባላቱን ለከፍተኛ ፍጥጫ ከመዳረጉም አርፎ ዘለፋ እና ዛቻ እንዲሁም የቀድሞ ጉዳዮች ወቀሳ ያካተተ የነበረ ሲሆን በብኣዴን ነባር አባላት እና በጫካው ሕወሓት እንዲሁም በሕወሃት የከተማ ህዋስ እና በጫካው ሕወሓት መካከል ከፍተኛ የሆነ ጭቅጭቅ ተስተናግዷል:: ዋናው አትኩሮት የነበረው ይላሉ የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ወቅታዊው የአንድነት ፓርቲ እንቅስቃሴ;የሙስሊሙ ጥያቄ; የምእራባውያን ጫና;እና የዲያስፖራው ድጋፍ በተመለከተ ነበር::

የስብሰባው ላይ አነጋጋሪ የነበረው የአንድነት ፓርቲ ጉዳይ በስፋት መንቀሳቀስ በዚሁ ከቀጠለ ካለው የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ችግር አኳያ ህዝቡ ሆ! ብሎ ሊነሳ ስለሚችል ከዚህ ቀደም እንደተለመደው ፓርቲውን በወከባ እና በጥቅም ማክሰም ወይንም ከፓርቲው ጋር መደራደር እስከሚሉ ጨከን ያሉ ሃሳቦች ተንጸባርቀዋል:: ከፓርቲዎች ጋር መደራደር የሚባል ነገር አይዋጥልኝም የሚሉት አለቃ ጸጋዬ በቁጣ እና በጩኽት ይህንን የመደራደር ሃሳብ ያቀረበችውን የሕወሓት የከተማ ህዋስ አባልን ያመጣንሽ እኮ እንድትጦሪን እንጂ ጠላት እንድትሆኚን አይደለም በማለት በቋንቋቸው አይሆኑ ዘለፋ ዘልፈዋታል::ቤቱ በዝምታ ድባብ እንዲዋጥ ያደረጉት የጫካው ሕወሓቶች የታገልነው ለድርድር አይደለም ሲሉ ተደምጠዋል:: ሰማያዊ ፓርቲ ቢነሳም ብዙም አያሰጋንም በሚል ታልፏል::

ከኦህዴድ ሙክታር ብቻ የተካፈለበት ይህ ስብሰባ 16 የህወሃት ጄኔራሎች የተመከሩ ይመስል ጂንስ በጃኬት ለብሰው ነበር በስብሰባው ላይ የተገኙት :: በአሁን ሰአት የደህንነቱ እና የወታደሩ ክፍል በተጠንቀቅ ሊሆን ይገባዋል በሚል የሚያሳዝን አንደበት መናገር የጀመሩት አቶ በረከት አትኩረውት የነበረው በሙስሊሙ እና በዲያስፖራው ጉዳይ ነበር :: ሙስሊሙች ጥያቄያቸው ሰፍቶ አለምም ጆሮ ሰቷቸዋል እንሱን ዝም ማሰኘት አሊያም ለፖለቲካ ስልት መጠቀም አስፈላጊ ነው ቢሉም የታሰሩትን መፍታት ለኢህኣዴግ የፖለቲካ ኪሳራ ስለሆነ ያለንን ሃይል መጠቀም አለብን ብለዋል:የዲያስፖራው ጥላቻ ከ60% ወደ 90% አድጓል:: 10% ደሞ ንብረት አገር ቤት ያፈሩ ወይም ከፖለቲካ ነጻ ነን የሚሉ ግለሰቦች ሲሆኑ ይህ ደሞ 10% ደጋፊ ሳይሆን የምንላቸው ለንብረቶቻቸው እና ለቤተሰቦቻቸው ደህንነት የሚለማመጡ ብንል ይቀላል :: በዲያስፖራው ዘንድ ያለው ጉዳይ ብዙም ተስፋ ሰጪ ስላልሆነ ሊታሰብበት ይገባል ብለዋል:: ይህ የራሳችን የፖሊሲ ውጤት ነው ብለው ደፍረው የሚናገሩ አባላት አልተገኙም::

የህወሃት አንጋፋ ታጋዮች የተሳተፉበት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ያልተጠሩበት ጥቂት ብኣዴኖች እና አንድ ኦህዴድ የፈጠጡበት ይህ ስብሰባ የምእራቡን ጫና በተመለከተ ሰፋ ያለ የዲፕሎማቲክ ስራ እና ዝርዝር ሪፖርት ይዞ የማስረዳት ስራ እንዲሰራ የሕወሓት የውጪ ጉዳይ አትኩሮት እንዲሰጥበት ያደረገ ሲሆን ለአንድ አገር የውጪ ፖሊሲ የአንድ ፓርቲ ሰዎችን እንዲሰሩ ማዘዝ በአንዳንድ ተሰብሳቢዎች ላይ አግራሞትን ፈጥሯል::ምንም አይነት ስምምነት ያልታየበት ይህ ስብሰባ በፍጥጫ በአተካሮ እና በጩኽት የተሞላ ቢሆንም አብዛኛዎቹ አንጋፋ ታጋዮች ማስታውሻቸው ላይ ሲቸከችኩ ተስተውለዋል::

ወደማይፈታ ችግር ራሱን እየወሰደ ያለው ቡድናዊው አምባገነን ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ እንዳለ የሚያሳየው ይህ ጨለማ የሚደረግ ስብሰባ አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን ሰዎች እየተመረጡ ደጋፊዎች እየታዩ እየተጠራሩ በጎጥ እና በመንደር በመሰባሰብ ሃገርን ወደማትወጣበት አዘቅት ቁልቁል እየከተቷት ነው:: በመጪው ቀናቶች የሚጠሩ ስብሰባዎች በእነዚሁ ወቅታዊ ጉዳዮን ላይ አተኩርው እንደሚወያዩ ይጠበቃል መልካም የለሊት ስብሰባ::  ምንልክ ሳልሳዊ ብሎግፖስት