የህግን የበላይነት ማረጋገጥ የተሳነው ስርኣት የወለዳቸው ስብርባሪ መንግስታት

ምንሊክ ሳልሳዊ

በሃገሪቱ የተፈጠሩ ስብርባሪ ህወሓት መራሽ መንግስታት የህዝቦችን የመኖር መብት ደፍጥጠዋል::በሃገራችን ውስጥ ላለፉት 22 አመታት ተንሰራፍቶ ያለው የአንድ ፓርቲ ህገወጥ አገዛዝ ለህዝቦች ነጻነት የሚከፈለውን መስእዋትነት እንደ መንግስት ሳይከፍል ህዝብን በማሸበር እና በማወናበድ የህግ የበላይነትን ደፍጥጦ ለስልጣኑ ብቻ እየተራወጠ ይገኛል::በሃገሪቱ የህግ የበላይነት የተከበረ ጊዜ ስልታንህ ያበቃል የተባለ ይመስል ከበላይ ባለስልጣናት ጀምሮ እስከ በታች ካድሬዎች ድረስ የህግን የበላይነት ክደዋል:: ማንም ማንንም ማዘዝ በማይችልበት እና የተሰባበሩ ትንንሽ በንግስታት በራሳቸው ሂደት የተፈጠሩባት ኢትዮጵያ ባለስልጣናቱ መናበብ አለመቻላቸው ህዝቡ በፍትህ ላይ ተስፋ ከቆረጠ ውሎ አደረ አድሮም ኖረ::

የአንድ ሃገር ህግ የህዝብን ትኩሳት እና ጥያቄዎች ይዞ መጓዝ ሲኖርበት በሃገራችን ግን የህግ የበላይነትን የፖለቲካ ትኩሳቶች እያሽመደመዱት እንዳይከበር እና እንዲደፈጠጥ እያደረጉት ይገኛሉ:; አንድ ህዝብ ባላረቀቀው እና ባላጸደቀው ህግ ሲገዛ የህግን ትርጉም እንደማያውቅ ታሳቢ አድርጎ በህዝብ ነጻነት ላይ የሚደረጉ የፖለቲካ ጨዋታዎች እንኳን በበሰለው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ይቅር እና በሌላውም ባልሰለጠነ ህዝብ ላይ ሊተገበር መድፈር ራስን እንደመናቅ ይቆጠራል:: ወያኔ ራሱ አርቅቆ እና አጽድቆ ህጎችን በማውጣት ከፈለገም በመሻር በመቀየር በመገለባበጥ በመተርጎም ህዝቦች የራሳቸውን መብት እና ነጻነት እንዳያገኙ በከፍተኛ ደረጃ መሸራረፎችን እየፈጠረ ነው::

ባለስልጣናት የወንበር ግዝፈታቸውን ተጠቅመው የተለያዩ ውሳኔዎችን ትእዛዞችን ተግባራትን በስልክ በደብዳቤ በቀላጤ ወዘተ የህግን ስርኣት ባልተከተለ መልኩ እያሽከረከሩት ከህግ የበላይነት ላይ በድንፋታና በትእቢት በመጓዝ ላይ ሲሆኑ ይህንን ያየ የበታች ካድሬ እንዲሁ ህግን እና ስራትን ባልትየከተለ መንግድ የህዝቦችን ህልውና ገደል ከቶታል:: ከበላይ ባለስልጣናት ባልተናነሰ እንዲሁም በበለጠ ማለት ይቻላል የወያኔ ካድሬዎች እና ተባባሪዎቻቸው በአገሪቱ ላይ ስርኣት አልበኝነት እና ህገወጥነት እንዲሰፍን እየሰሩ ነው::ይህ ደግሞ ህዝብ በስርኣቱ ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ አድርጎታል::

በከፍተኛ ደረጃ ህግን እየበረዙ አድርገው በሙስና የተዘፈቁ የወያኔ ባለስልጣናት እና ደጋፊ ታዛዥ ካድሬዎቻቸው በሃገሪቱ ራሳቸው ያወጡትን ህግ ራሳቸው እየጣሱ የሚገኙ ሲሆን በራሳቸው ህግ ራሳቸው እንደሚጠየቁበት እየዘነጉ መሆኑን አለማወቃቸው ለህዝብ ያላቸውን ንቀት ያመለክታል::የምናነበው ሕጉና የምንመለከተው ተግባሩ የተለያየ ነው፡፡በሙስና ከተዘፈቁበት አንዱ የመሬት እደላ እና አሰጣጥ ነው መሬትን በተመለከተ ህጉ የሚለውን የሚከተል ባለስልጣን ማግኘት አስቸጋሪ ነው ህጉን የሚያስፈጽም ካድሬ ሹመኛም ማግኘት አይታሰብም::ይህ ማለት ደሞ ሁሉም ከመሬት እደላ ጋር በተያያዘ ህጉን ተከትለው የሚሰሩት ሳይሆን የግለሰቡ ብሄር እና የፋይናንስ አቅም ተመልክተው ይፈጽሙለታል:; ለእውነት እና ለሃገር የሚሰራ ኢንቨስተር ከአከባቢው ይነቀላል ሌባው እና ሙሰኛው ኢንቨስተር በአደባባይ በመንግስት ባለስልጣናት እንክብካቤ ይደረግለታል አፋሽ አጎንባሽ ካድሬዎችን ይበዙለታል::

የህግ የበላይነት በሃገሪቱ አለመስፈኑ ኢኮኖሚውን ከማንኮታኮቱም በላይ ባለስልታናት በዝርፊያ እና በሽሽት ላይ እንዲያተኩሩ አድርጓቸዋል::ህዝቡም ይህን ተከትሎ እንዲሁም በፖሊሶች በደህንነት አባላት በቅጥረኛ የመንግስት አሸባሪዎች በጥቂት የከተማ ወታደራዊ ኮማንዶዎች ህግ ሲጣስ እየተመለከተ ስለሆነ አንድም መንፈሱ ሲጎዳ ሌላም አለው ስርኣት ላይ አመኔታ በማጣቱ ድምጹን እንዲቋጥር አስገድዶታል::በሃገሪቱ የፍትህ አካላት ላይ የመንግስት ባለስልጣናት ጣልቃ ገብነት የፖለቲካ የበላይነት መከሰቱ ህዝቦች አንገታቸውን በፍትህ አካላት ፊት እንዲሰብሩ እንዲሸማቀቁ አድርጎታል::

በየመንግስት ተቋማት፣ ከሚኒስቴር ጀምሮ እስከ ተራ የቀበሌ ካድሬ ቢሮ ጠረጴዛ፣ በፍርድ ቤቶች እና በፍትህ አካላት ፍትሕ የተነፈጉ፣ ሕገ መንግሥትና ሥርዓት እንዲከበር የሚጠይቁና አቤት የሚሉ በርካታ መዝገቦች ሰሚ ጆሮ አጥተዋል፡፡ ለሕግና ለሥርዓት ቅድሚያ የሚሰጥ አዕምሮ፣ ጆሮና ዓይን ተነፍገዋል፡፡ ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ሕገ መንግሥቱና ሕግ ያስገድዳሉ፡፡ቢሆንም ምንም አይነት መልስ ሲሰጣቸው ይሁን ሲገመገሙ ታይቶ አይታወቅም በተዋረድ የመንግስት አሰራር አለመኖር በስልክ እና በቀላጤ ህግ እየተጣሰ ከህዝብ በሚሰበሰብ ግብር የሚተዳደሩት ፖሊስ እና የፍትህ አካላት በግለሰቦች ትእዛዝ ህዝባዊ ሂደቶችን ሲያመክኑ ህግን ሲጥሱ ህገወጥ እርምጃዎች ሲፈጸሙ ከህግ ውጭ የህዝቦችን መብት ሲደፍሩ እየታየ መንግስት ነኝ የሚለው አካል ዝምታን መርጧል::ይህ ደግሞ የሚያመለክተው በሃገሪቱ ውስጥ ስብርባሪ ትንንሽ መንግስታት መፈጠራቸውን ነው::ባለስልጣናት ለህግ እና ለስርኣት ተገዢ አለመሆናቸው ህግእና ስርኣት ለእነሱ ተገዢ እንዲሆን ማድረጋቸው ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ነው;: እነዚህ ስርኣቱ የወለዳቸውን ባለስልጣናት እና ካድሬዎች ከኢትዮጵያ ምድር ወደ ከርሰ መቃብራቸው ከቶ ህዝብን ለነጻነት ለማብቃት በጋራ መታገል ግዴታችን መሆኑን አውቀን በአንድነት ስርኣቱን ማስወገድ ማንኛውም ሃገሬን እወዳለሁ የሚል ዜጋ ሊነሳለት እና ሊተገብረው የሚገባ መሆኑን ለማስገንዘብ እወዳለሁ::

የመንግሥት አመራር በኢትዮጵያ ውስጥ የለም::ሃገሪቱ ካለፈው የባሰ አደጋ ተጋርጦባታል:: MUST READ !!!

"አገሪቱ በልማት ጎዳና ላይ እየነጎደች ...." ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ በትእዛዝ የካዱት
"የመንግሥት አመራር በኢትዮጵያ ውስጥ የለም::ሃገሪቱ ካለፈው የባሰ አደጋ ተጋርጦባታል::" ሪፖርተር ርእስ አንቀጽ 
የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የሕወሓት ሪፖርተር መግለጫ ግጭት #1 ምንሊክ ሳልሳዊ

ኖሚናል የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የተባሉት እና በህገመንግስት የተሰጣቸውን ስልጣን በትእዛዝ ብቻ የሚሰሩበት ምንም አይነት አገራዊ ፋይዳ የማያደርጉት ሃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እና የሕወሓት ታማኝ የሆነው ሪፖርተር ጋዜጣ ያሰፈረው ርእስ አንቀጽ የሃገሪቷ ላይ የሰፈነው አብዮታዊ ዲሞክራሲ አምባገነንነት እያደረሰ ያለውን ችግር እና መጪውን አደጋ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሃገሪቱ ምንም አይነት ችግር እንዳሌለ እና ሁሉም ነገር በመንግስት ቁጥጥር ስር እንዳለ በዲሞክራሲ እና በልማት እየነጎድን ህዝባዊ ድሎችን እየተጎናጸፍን ..ምናምን...የሚሉ እና ሃሰትን የተሞሉ የማደናገሪያ እና የማስፈራሪያ ቃላት ፍርሃት በሚነበብበት ፊታቸው እያስገመገሙ ደስኩረዋል:: የእርሳቸው ንግግር እንደተጠበቀ የሕወሓት ሪፖርተር ጋዜጣ ደሞ እንዲህ ብሎናል::የኢሕኣዴግ ባለስልጣናት ፕሮፓጋንዳ እና የሚከተለውን የሪፖርተር ወቀሳ ይመዝኑት::ሪፖርተር እንደውስጥ አዋቂነቱ ያየውን እና የታዘበውን ሃይለማርያም ደሳለኝ ግን በትእዛዝ የካዱት እኛ ደሞ ያነበብነውን የተከፋፈልነው የታዘብነውን እንደራሳችን እይታ እንደሚከተው በዝርዝር ለማየት እንፈቅዳለን::

ሰብሰብ፣ ጠንከርና ነቃ ያለ የመንግሥት አመራር በኢትዮጵያ ውስጥ እንዳሌለ እና እንደሚያስፈልግ በግልጽ አስቀምቷል:: የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በሞት ሲለዩና አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሰየሙ ምንም ችግርና ብጥብጥ እንዳልነበር ይህ ማለት መሪ አልተተካም ሳይሆን ሰብሰብ፣ ጠንከርና ነቃ ያለ መንግሥትና አመራር ስላሌለ አገራችን ያያስፈልጋል እያልን ዓለም የኢኮኖሚ ቀውስ እኛንም እየጐዳን ነው፡፡ ትላልቅና በርካታ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ሲደረጉ በደመነፍስ ባጀት ተመድቦ ከፍተኛ ፋይናንስ ሳይኖር ወደ ላማት ይገባል ፡፡ ከዚህ በፊት ያልነበረ የሃይማኖት ግጭትና ልዩነት እየታየ ነው፡፡ ችግሩ ካልተፈታ አስጊ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ዕድገት የማይሹና የማይመኙ ጠላቶች በእጅጉ እየተፈታተኑን ናቸው፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ጠንካራ መንግሥትና ጠንካራ አመራር የግድ ይላል፡፡በኢትዮጵያ ውስጥ ተንካራ መንግስት እና አመራር እንደሌለ በግልጽ ሪፖርተር አስቀምጧል::

ገዥው ፓርቲ እርስ በኤርሱ እየተዋከበ እና እየተፈረካከሰ በውስጡ መተማመት እንደጠፋ በገሃድ መካሪ መስሎ የመሰከረው ሪፖርተር ኢሕኣዴግ ውስጣዊ አንድነቱን ማጠናከር አለበት፡ሲል በአደረጃጀቱ ምክንያት አራት አባል ድርጅቶች ቢኖሩትም ሲሠራና ሲንቀሳቀስ እንደ አንድ መሆን አለበት፡፡ኢሓዴግ አራት ድርጅቶችን አክፎ በተለያዩ አሰራሮች በመጠመድ እርስ በራሱ እየተዋጋ እና እየተሸበር መሆኑን ሪፖርተር ፍንትው አድርጎ አሳይቶናል::ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን የጠላት ወሬ ሲሉ ክደዋል::በኢሕኣዴግ ድርጅቶች መካከልመራራቅ እና መፈረካከስ እየታየ ነው የሚለው ይሄው ዘገባ እንኳን እየተራራቁ አንድ ተሁኖም ለመፍታት የሚያስቸግሩና የሚፈታተኑ ችግሮች እያጋጠሙ ናቸው፡፡ሲል ጠላቶችና አንዳንድ ተቃዋሚዎች እንደሚሉት ተጣሉና ተሰነጣጠቁ እንደሚባለው ሳይሆን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ ተገቢና የሚጠበቅ አንድነት፣ መቀራረብ፣ የዓላማ ፅናትና ለመስዋዕትነት ዝግጁነት እየታየ አይደለም፡፡በማለት መክሯል ሆኖም ያለው ገዢ ፓርቲ እየሞተ እየተበታተነ እና እየተልፈሰፈሰ መሆኑን ሰብሰብ ነቃ እና ጠንከር በሚሉ ቃላቶች ተክቶ አቅርቦታል::


የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የሕወሓት ጋዜጣ ሪፖርተር ግጭት === #2 ምንሊክ ሳልሳዊ
 
-ገዢ ፓርቲ እየሞተ እየተበታተነ እና እየተልፈሰፈሰ መሆኑን የሚያሳብቁ ተተኪ ቃላቶች ሰብሰብ ነቃ እና ጠንከር
-ሙሰኞችን ማደን - ‘እንትና ይደናገጣል እከሌ ያኮርፋል’ ተብሎ የሚቆምና የሚቀዘቅዝ ትግል
-የትም ሥፍራ፣ የትም መሥሪያ ቤት በማንኛውም ጊዜ መልካም አስተዳደር እየተጣሰ፣ ፍትሕ እየጠፋ፣ የሕዝብ ጩኸትና ጥሪ ተቀባይ አልባ ሆኗል፡፡

ገዥው ፓርቲ እርስ በእርሱ እየተዋከበ እና እየተፈረካከሰ በውስጡ መተማመት እንደጠፋ በገሃድ መካሪ መስሎ የመሰከረው ሪፖርተር ኢሕኣዴግ ውስጣዊ አንድነቱን ማጠናከር አለበት፡ሲል በአደረጃጀቱ ምክንያት አራት አባል ድርጅቶች ቢኖሩትም ሲሠራና ሲንቀሳቀስ እንደ አንድ መሆን አለበት፡፡ኢሕኣዴግ አራት ድርጅቶችን አቅፎ በተለያዩ አሰራሮች በመጠመድ እርስ በራሱ እየተዋጋ እና እየተሸበር መሆኑን ሪፖርተር ፍንትው አድርጎ አሳይቶናል::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን የጠላት ወሬ ሲሉ ክደዋል::በኢሕኣዴግ ድርጅቶች መካከል መራራቅ እና መፈረካከስ እየታየ ነው የሚለው ይሄው ዘገባ እንኳን እየተራራቁ አንድ ተሁኖም ለመፍታት የሚያስቸግሩና የሚፈታተኑ ችግሮች እያጋጠሙ ናቸው፡፡ሲል ጠላቶችና አንዳንድ ተቃዋሚዎች እንደሚሉት ተጣሉና ተሰነጣጠቁ እንደሚባለው ሳይሆን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ ተገቢና የሚጠበቅ አንድነት፣ መቀራረብ፣ የዓላማ ፅናትና ለመስዋዕትነት ዝግጁነት እየታየ አይደለም፡፡በማለት መክሯል ሆኖም ያለው ገዢ ፓርቲ እየሞተ እየተበታተነ እና እየተልፈሰፈሰ መሆኑን በሚያሳብቁ ተተኪ ቃላቶች ሰብሰብ ነቃ እና ጠንከር በሚሉ ተክቶ አቅርቦታል::

ሙስናው በስፋት ተንሰራፍቷል ያልው የሪፖርተር ጋዜጣ "አገር በሙስና እየተጨማለቀች ናት" ሲል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተናገሩት በተቃራኒ ጎኑ መጭውን አደገኛ የሃገር ኢኮኖሚ የዳግም ስርኣተቀብር ሙስናው እያሳየን መሆኑን ጠቁሟል:: ሙስናን ለመዋጋት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የውስጥ የፖለቲካ ባላንጣዎችን ለማፈን እና ለማስወገድ የእጅ አዙር መጥረቢያነት ከማገልገል ውጭ ምንም አይነት እርምጃ በሙሰኞች ላይ ሲወሰድ አልታየም ይባስ ሙስና በሃገሪቱ እየተስፋፋ እና እያበበ ነው::‘እንትና ይደናገጣል እከሌ ያኮርፋል’ ተብሎ የሚቆምና የሚቀዘቅዝ ትግል እንደሆነ ይጠቁማል::ሙስና ኢትዮጵያን እያጨማለቀ ሲሆን ከስርቆትና ከዝርፊያ በፊት ሙስናን የሚያስቆሙና የሚያጋልጡ አሠራሮች፣ ሕጐች፣ መዋቅሮችና የሥነ ምግባር ደንቦች እንዳይወጡ የመንግስት ባለስልጣናት እንቅፋት ሁነዋል::የመንግስት ባለስልጣናት በራሳቸው ለሙስና የሚያመች ሁኔታ እየፈጠሩ ሙስናን እንዋጋለን ማለት አያስኬድም፡፡ ከአሿሿም ጀምሮ፣ ከቁጥጥር ጀምሮ፣ ከቅጥር ጀምሮ አሠራሩ ሁሉ ሙስናን የሚያስወግድ ሳይሆን የፖለቲካ ታማኝነትን የጠበቀ ነው፡፡

አገሪቷ በሙስና መጨማለቋ የመልካም አስተዳደር እጦት ፈጥሯል:: ጠቅላያችን እንዳሉን ማንጫውንም ነገር መልካም አስተዳደርን ጨምሮ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች መኖራቸው እና በሂደት እየተሻሻሉ እንደሚሄዱ ነግረውናል ይህ ነገር ላለፉት 22 አመታት ሲነገረን የነበረ እና ምንም አይነት ለውጥ ከማየት ይልቅ በካድሬዎች ብልሹ አሰራር እና ቢሮክራሲ የመልካም አስተዳደሩ እየተበላሸ ገደል መግባቱን ብቻ ነው::የመልካም አስተዳደር እጦት ሕዝቡን ተስፋ እያስቆረጠ ነው ብሎናል ለገዢው ፓርቲ ቅርብ የሆነው ሪፖርተር- አዎን ገዥው ፓርቲ መልካም አስተዳደር አለመኖሩን እያመነ ነው፡፡ ዕርምጃም እወስዳለሁ ቢባልም ለስልጣኑ ማራዘሚያ የሚጠቀምባቸው በጥቅም የተተበተቡ ካድሬዎቹ ይገለበጡብኛል በሚል ፍራቻ ምንም አይነት ርምጃ ሳይወስድ የመልካም አስተዳደር እጦቱ እንደቀጠለ ነው ፡፡

መልካም አስተዳደር ይኑር ይስፋፋም የሚሉ የመንግስት ሚዲያዎችም ይሁኑ ፕሮፓጋንዲስቶች ቃላቶችን ህዝብን ለማጭበርበር እየተጠቀሙበት ነው ፡፡ በቃላት ላይ ችግር የለም፡፡ በተግባር ግን መልካም አስተዳደር እውን ሊሆን አልቻለም፡፡ የትም ሥፍራ፣ የትም መሥሪያ ቤት በማንኛውም ጊዜ መልካም አስተዳደር እየተጣሰ፣ ፍትሕ እየጠፋ፣ የሕዝብ ጩኸትና ጥሪ ተቀባይ አልባ ሆኗል፡፡ ሕገ መንግሥቱና የተለያዩ ሕጎች ተግባር ላይ የሚያውላቸው አጥተዋል፡፡ የሙስና ተጠርጣሪዎች ታሰሩ ቢባልም ፈጥረውታል የተባለው በደል ግን ሲስተካከል አይታይም፡፡ ይህ ችግር በእጅጉ አደገኛ ነው፡፡ ዜጋ አገሩን እንዲጠላና ተስፋ እንዲቆርጥ እያደረገ ያለ ችግር ነው፡፡ #3 ምንሊክ ሳልሳዊ 
በአንድ አገር ላይ ሁለት አገር የለም ሃይለማርያም ደሳለኝ ስለ የትኛው አገር መግለጫ እንደሰጡን አሁንም አልገባንም::ሪፖርተር ጋዜጣ ደሞ የታዘብኩት ያየሁት የሰማሁት በሚል አበይት ብሎ ያለውን የሃገርቱን እውነታዎች በከፊት አስቀምጧል:: በርግጥ የተሸፋፈነ ቢሆንም ፍንጭ ግን አገሪቷ አደጋ ላይ እንዳለች ጋዜጣው መስክሯል:: እኛም ያየነውን የምናውቀውን ጤቅላይ ሚኒስትሩን እና ጋዜጣውን ይዘን ተንትነናል ::

የሃይለማርያም ደሳለኝ መግለጫ እና የሪፖርተር ጋዜጣ ግጭት
- የመንግስት የጥንቃቄ ጉድለት እና የፖለቲካ አጀንዳ ሃይማኖቶችን እየበረዘ ነው:;
- የኢኮኖምው ድቀት አገሪቷን ወደማትወጣበት አደጋ ውስጥ የከተተ ሲሆን ከፍተኛ ስራ አጥነት ፈጥሯል::
- በወያኔ መንግስት የመወያየት የመነጋገር የመቀራረብ መንገዶች ስለተዘጉ ችግሮች እየበረከቱ ነው::

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የድርጅታቸው የበላይ አካሎች በሰጧቸው ኦረንቴሽን መሰረት አጥንተው ገብተው በሃገሪቱ የተከሰቱ የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄዎችን እና መሰረታዊ የዲሞክራሲያዊ መብት ጥያቄዎችን በተለመደው አሸባሪ አክራሪ እና ጽንፈኛ በሚሉ ወያኔያዊ ቃላት ተጠቅመው ሲያስፈራሩ ... ይህን መሰል የመንግስት ማስፈራሪያ በህዝቦች መብት ላይ መስጠት በሃገሪቱ ያሉ ሃይማኖቶች ነጻነታቸውን መጋፋት ሲሆን ዋናው የችግሩ ፈጣሪ ወያኔ የፈጠረው የስልጣን ማስረዘሚያ የወንጀል ቃላቶች መሆናቸውን ፍንትው አድርጎ ያሳያል :: ሃይማኖቶች በመርሃቸውም ይሁን በተግባራቸው አይጋጩም፡፡ ሁሉም ፍቅርን፣ መተሳሰብንና ሰላምን የሚሰብኩ ናቸው፡፡ ችግሩ ያለው እምነት ላይ አይደለም፡፡ ችግሩ ያለው የዚህ ሃይማኖት ጠበቃና አለኝታ እኔ ብቻ ነኝ፣ አንተ ወይም ያኛው አይደለም በሚል ሃይማኖትን ተገን በማድረግ በሚደረግ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ስለዚህ የችግሩ መንሴ የሆነው ወያኔ የሃይማኖቶ ጠበቃ በመምሰል በህገመንግስት ንግድ ውስጥ ተጀቡኖ እጁን ወደ ሃይማኖቶች በማስገባት ራሱን የሃይማኖት አለኝታ በማስመሰል ሃይማኖቶችን ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋሉ የህዝብ ጥያቄዎች በአደባባይ መሰማት ከጀመሩ አመታት ተቆጥረዋል::
የክርስትና፣ የእስልምናና የአይሁድ እምነቶች በጋራ በሚኖሩበት አገር ውስጥ፣ ጋብቻ ፈጽመውና ተፋቅረው መኖር የሚችሉ የተለያዩ የሃይማኖት እምነት ተከታዮች ያሉበት አገር አለን እያልን፣ የወያኔ መንግስት በፈጠረው የፕሮፓጋንዳ እና የከፋፍለህ ግዛ ድርጊት ተጋጨ፣ ጠንካራ የነበረን ሕዝብ ተፋጀ ወደሚል አሳፋሪ ታሪክ እየቀየርነው ነው፡፡ ወያኔ ለስልጣን ማስረዘሚያ ብሎ የተጤቀመበት ስልት ነገ ለቁጭት የሚዳርገን እና ወደማንወጣበት ውድቀት የሚከተን ሲሆን ታሪካችንን፣ ማንነታችንና ደኅንነታችንን ለአደጋ እያጋለጠ ነው::

የሃገሪቷ ኢኮኖሚ በወያኔ ባለስልታናት እና በብሄራዊ ጥቅም በታወሩ ምእራባውያን እንደሚወራል ሳዮን እጅግ በጣም እየተንኮታኮተ መሆኑ እሙን ነው::በመንግስት ካዝና ውስጥ ከባድ የሆነ የገንዘብ ችግር አለ:: የመንግስት ካዝና ባዶ ነው ቢባል የሚያስኬድበት ደረጃ ላይ ተኩኖ የሃገሪቷን በጀት ማጽደቅ እንደት እንደሚቻል ግራ እየገባን ነው:: በጀት ሲጸድቅ እንጂ ሲለቀቅ የማይታይባት ኢትዮጵያ አስደንጋጭ የኢኮኖሚ ውጥንቅጥ ውስጥ እየዳከረች ነው:: የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች ብቻ ከጥቂት ነጋዴዎች እና ብሄርተኞች ጋር በሙስና ተጨማልቀው የሚሰሩት የአየር በአየር ንግድ የሃገሪቷ ኢኮኖሚ አይደለም የመንደር ኢኮኖሚ ሊባይ አይችልም::ክፍያ አፈጻጸም ላይ እንኳን ግለሰብ መንግሥትም እየተቸገረ ነው፡፡ የግል ባንኮች እየተዳከሙ ናቸው፡፡ የብድርና የውጭ ምንዛሪ ችግርና እጥረት አለ፡፡ ግሽበትን ለመቆጣጠር የሚወሰደው ዕርምጃ የራሱን ችግር እየስከተለ ነው፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ፣ የውኃ መጥፋት፣ የኔትወርክ አለመኖር፣ በሁሉም ዘርፍ ችግር እያስከተለ ነው፡፡ ገንዘብ ማሸሽና መደበቅ እየታየ ነው፡፡ ሌባው ሲፈራ ባይገርምም፣ ንፁኃን ሲሸማቀቁና ብታሰርስ እያሉ በመፍራት ከቢዝነስ እንቅስቃሴ ሲቆጠቡ እየታየ ነው፡ ይህንን ወያንኤ አምኖ ሊቀበለው አይደለም ጭራሽ በጠላይ ሚኒስትር ደረጃ መካድ ተጀምሯል:: ከሕዝብ ብዛትና ከሚመረቁ ተማሪዎች አንፃር በቂ የሥራ ዕድል አልተፈጠረም፡፡ ሥራ ለማግኘት ወደ ዓረብ አገሮች የሚደረገው ስደት በአስፈሪ ሁኔታ እየታየ ነው፡፡ ወደ ወንጀል እየተገባ ነው፡፡ ለባለ ገንዘብ ራስን ለሽያጭ ማቅረብ እየተስተዋለ ነው፡፡ ይህ ችግር ካልተፈታ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ያሰጋል፡፡ ልዩ ትኩረትና መፍትሔ ይደረግበት፡፡ የተራበ ሆድ አደገኛ ነውና፡፡

በወያኔ መንግስት የመወያየት የመነጋገር የመቀራረብ መንገዶች ስለተዘጉ ችግሮች እየበረከቱ ነው:: በኢትዮጵያ እየታዩ ያሉ ችግሮች ኢትዮጵያዊያን ሊፈቱዋቸው የሚችሉ ናቸው፡፡ በመንግሥትና በሕዝብ፣ በመንግሥትና በተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ፣ በመንግሥትና በሲቪል ማኅበረሰቡ፣ በመንግሥትና በተለያዩ የሙያ ዘርፎች መካከል መቀራረብ፣ መወያየትና መመካከር ስለሌለ በቀላሉ የሚፈቱ ችግሮች እየተባባሱ ናቸው፡፡ ችግሮችን ለመንግሥት ማቅረብ አልተቻለም፡፡ መንግሥትም የሕዝብን ችግርና ስሜት ማወቅ አልቻለም፡፡ በዚህ ምክንያት ቀላል ችግሮች እየተካበዱና ወደማያስፈልግ አቅጣጫ እየተሸጋገሩ ናቸው፡፡ መንግሥት በአስቸኳይ ቲንክ ታንክ ያቅድ፣ የጋራ መድረክ ይፍጠር፣ የሕዝብና የመንግሥት፣ የመንግሥትና የባለሙያዎችን ግንኙነት ያጠናክር፡፡ መጠራጠርንና መራራቅን ወደ መቀራረብና መተማመን ይቀይር፡፡ አድዮስ ዲሞክራሲ!!! 

ከቀይ ሽብር ተፅዕኖ ያልተላቀቀው ፖለቲካ‹‹የምን ይቅርታ? ለሕዝብና ለአገር ዕድገት ነው የተነሳነው፡፡ በትግሉ ሒደት ስህተት ፈጽመናል፤ ስህተቱ የትግሉ አካል ነው፡፡ ዘውዳዊ ሥርዓቱን ጥለናል፤ የኢትዮጵያንም ሕዝብ ነፃ አውጥተናል፡፡
የደቡብና የምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ይናገሩ፡፡ ከወላይታ የመጣውና ከአናሳ ሃይማኖት የመጣው ግለሰብ አገር የሚመራው በእኛ ትግል ምክንያት ነው፡፡ በማያውቀውና ባላነበበው ታሪክ የበሰበሰ ይለናል? የመጀመሪያ ዘመቻችን የዕውቀት ዘመቻ መሆን አለበት፡፡››
ከቀይ ሽብር ተፅዕኖ ያልተላቀቀው ፖለቲካይህን የተናገሩት የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ ሲሆኑ መልስ እየሰጡ የነበረው ደግሞ ፓርቲያቸው ኢሕአፓንና የትግል አጋሮቻቸውን አስመልክቶ ትችት ላቀረበ አንድ ወጣት ነበር፡፡ ወጣቱ፣ ‹‹በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ ዘግናኝና ሰቅጣጭ ጭፍጨፋ ተፈጽሟል፡፡ መድረክ ላይ ያላችሁት ሰዎች በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ በተለያየ መስመር ተሰማርታችሁ ባመናችሁበት አቋም የአገሪቱን የፖለቲካ እመርታ ለማስለወጥም ሆነ ለማሳደግ የራሳችሁን ሚና ተጫውታችኋል፡፡ የ60ዎቹና 70ዎቹ ትንታግ ትውልድ ዳፋ አሁንም ባለንበት የፖለቲካ ተግባራዊ ሁኔታ ላይ በእጅጉ ሲንፀባረቅ ነው የምናየው፡፡ መጠላላቱና ጥቅመኝነቱ እንዳለ ነው፡፡ እዚህ አዳራሽ ውስጥ በመኢሶን፣ በኢሕአፓና በሌሎች ድርጅቶች ውስጥ የታገላችሁ ሰዎች አላችሁ፡፡ ያ የከሰረ፣ የበሰበሰ፣ የተቀበረና የሞተ የትግል ውጤት እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡ ግን አሁንም ሰንኮፉ አልለቀቀንም፡፡ በምትጽፏቸው መጽሐፎችና በምታቀርቧቸው ፕሮግራሞች ላይ አሁንም የቀይ ሽብር ትውስታዎች እንዳሉ እናያለን፡፡ መቼ ነው ኢሕአፓዎችና መኢሶኖች በአደባባይ ወጥታችሁ የሠራነው ስህተት፣ የፈጸምነው በደል ይኼ ነበር፤ ትውልድ ከእኛ ተምሮ እዚህ ላይ ትኩረት ያድርግ በማለት ይቅርታ የምትጠይቁት? አሁንም እየተታኮሳችሁ ነው፣ ዛሬም ኢትዮጵያን የምትተረጉሙት በተለያየ መንገድ ነው፤›› በማለት ነበር አስተያየት የሰጠው፡፡ 
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ተማሪ መሆኑን የገለጸው ወጣት አስተያየት ቁጣን የቀሰቀሰው በፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ ላይ ብቻ አልነበረም፡፡ መድረኩ ላይ የጥናት ሥራዎቻቸውን ያቀረቡትን ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ፣ ዶ/ር ካሳሁን ብርሃኑ፣ ፕሮፌሰር ሽፈራው በቀለ፣ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴን ጨምሮ ከታዳሚዎቹ ውስጥ “Tower in the Sky” በተሰኘ መጽሐፏ በአጭር ጊዜ ዝነኛ የሆነችው የኢሕአፓ የቀድሞ ታጋይ ሕይወት ተፈራና ከኢሕአፓ መሥራቾች አንዱ የሆነው የብርሃነ መስቀል ረዳ ባለቤት አምባሳደር ታደለች ኃይለ ሚካኤልን ጨምሮ፣ የ1960ዎቹ እና የ1970ዎቹ ትግል አካል የነበሩ በርካታ ሰዎች ተገኝተው ነበር፡፡ 
መስከረም 19 ቀን በደሳለኝ ሆቴል የተዘጋጀው ሕዝባዊ መድረክ በአፍሪካ ኅብረት የሰብዓዊ መብት መታሰቢያ፣ በኢንተር አፍሪካ ግሩፕና በጀስቲስ አፍሪካ ትብብር ሲሆን፣ ዋነኛ ዓላማው ቀይ ሽብር በኢትዮጵያ ዳግም እንዳይከሰት ምን ማድረግ ይገባል? በሚለው ጥያቄ ላይ ውይይት ለማድረግ ቢሆንም፣ በመድረኩ ላይ የተንፀባረቁት የሐሳብ ልዩነቶች የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዛሬም ከቀይ ሽብር ተፅዕኖ ያልተላቀቀ መሆኑን ያረጋገጠ ነበር፡፡ 
ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግን ጨምሮ በ1960ዎቹና በ1970ዎቹ የፖለቲካ ትግል ተሳታፊ የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች አባላት የዛሬዋ ኢትዮጵያን የመንግሥትና የተቃውሞ ፖለቲካ መዋቅርን ጨምሮ በአገሪቱ ያሉ ወሳኝ ዘርፎችን በበላይነት በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡ በዕድሜና በጤና ምክንያት ከመድረኩ ሲገለሉም ከማርክሲስታዊ ሌኒኒስታዊ ርዕዮተ ዓለም የተቀዳውን አካሄዳቸውን ለአዲሱ ትውልድ እያወረሱ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ይገልጻሉ፡፡ ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግም ዲሞክራሲን የሚሰብከውን ሕገ መንግሥት፣ ከሕገ መንግሥት ጀርባ ያለው ሌላው ሕገ መንግሥት በሚባለው አብዮታዊ ዴሞክራሲ እንዲሸረሸር ያደረገው ከዚሁ ከማርክሲስታዊ ሌኒኒስታዊ ርዕዮተ ዓለም ጋር ካለው ጥብቅ ቁርኝት አንፃር እንደሆነም ይጠቁማሉ፡፡ የቡድኖቹ ቅርበትና ልዩነት ርዕዮተ ዓለምን መሠረት ያደረገና ከኋላ ታሪክ መቀዳቱ በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ለውጥ እጅግ አዝጋሚ እንዲሆን የበኩሉን አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ 
በመድረኩም የተስተዋለው ይኼው እውነታ ነው፡፡ የወጣቱ ትውልድ አባላት ጥያቄ በአላዋቂነት ነው የተዘጋው፡፡ አንድ የመኢሶን አባል የነበሩ ግለሰብ ጥያቄም በተቃውሞ ነው የተመለሰው፡፡ ለነገሩ ግለሰቡም ውስብስቡን ፖለቲካ እጅግ አቃለው ኢሕአፓ ለኤርትራ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ማሰቡ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለውጭ ኃይል አሳልፎ ከመስጠት ጋር ነው ያያያዙት፡፡ ኤርትራ በወቅቱ የኢትዮጵያ አካል ነበረች፡፡ የኢሕአፓ አባል የነበሩ ምሁራን የፓርቲውን ስህተት ይደፋፍናሉ ለሚለው ጥያቄም ምላሽ አልነበረም፡፡ ለዘመኑ ወጣት አክብሮት አትሰጡም ተብለውም ሲተቹ አንድ ዕድሜያቸው ገፋ ያለ ግለሰብ፣ ‹‹የዘመኑ ወጣት እንደያኔው በቀላሉ አይነዳም›› ሲሉ፣ የአብዮቱ ተሳታፊዎች በጥቂት ወራት ባዕድ የሆነ የሌላ አገር ርዕዮተ ዓለምን ወደ ኢትዮጵያ አውድ ለመቀየር እንኳን ሳይሞክሩና በጥልቀት ሳይረዱት በመከተላቸው አገሪቱ መታመሷን ሲገልጹም ድጋፍ አላገኙም፡፡ 
ወጣቱ ትውልድ ከእናንተ ምን ይማር? በሚል ለቀረበው ጥያቄ ከመድረክ ጥናት አቅራቢዎቹና ከታዳሚዎቹ መካከል የተለያዩ ምላሾች ቀርበዋል፡፡ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ‹‹የዕውቀትን አስፈላጊነት መማር ይቻላል፡፡ የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታና የሕዝቡን ሁኔታ በማርክስ ጽሑፎች መመለስ አይቻልም ነበር፡፡ መቻቻልና መደማመጥ መማር ይቻላል፡፡ ስህተትን መቀበል መማር ይቻላል፤›› በማለት መልሰዋል፡፡ ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ በበኩላቸው፣ ‹‹የኢትዮጵያን ታሪክ በብቸኝነት ልንይዝ እንደማይገባ ልንማር ይገባናል፡፡ ታሪካችን ከሌሎች አገሮች ጋር ተመሳሳይነት ነበረው፡፡ እያነፃፀርን ልንረዳው ይገባናል፤›› ብለዋል፡፡ 
በአብዮቱ ዕጣ ፈንታ ላይ የዳያስፖራው ሚና ምን ነበር? የመኢሶንና የኢሕአፓ ልዩነት ምን ያህል ሰፊ ነበር? መኢሶን ወይም ኢሕአፓ ከሕዋሓት ጋር የነበራቸው ግንኙነት ምን ይመስል ነበር? ከመኢሶን ወይም ከኢሕአፓ አንዳቸው በደርግ ቦታ ሥልጣን ቢይዙ ቀይ ሽብር እንደማይኖር ምን ማረጋገጫ አለ? በአሁኑ ወቅት የአደባባይ ምሁራን የጠፉት ከቀይ ሽብር ጋር በተያያዘ ነው ወይ? ቀይ ሽብር ለመንግሥትና ለሕዝብ አሉታዊ ግንኙነት እንዴት ነው አስተዋጽኦ ያደረገው? በኢትዮጵያ አዲስ የፖለቲካ ባሕል እንዴት መፍጠር ይቻላል? የሚሉ ጥያቄዎችም ከተሳታፊዎች የተሰነዘሩ ሲሆን የተወሰኑት ብቻ ምላሽ አግኝተዋል፡፡ 
ዶ/ር ካሳሁን ብርሃኑ መኢሶንና ኢሕአፓ ‹እናሸንፋለን› እና ‹እናቸንፋለን› ከሚለው እጅግ የዘለለ ልዩነት እንደነበራቸው በመጥቀስ ልዩነታቸው ጥቃቅን እንዳልነበር ያመለከቱ ሲሆን፣ ሁለቱም ድርጅቶች በትክክል ማርክሲስታዊ ሌኒኒስታዊ ነበሩ ለማለት እንደማይቻልም አስረድተዋል፡፡ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ልዩነቱ የፖለቲካ ሥልጣን ጉዳይ እንደነበር አስገንዝበው፣ ደርግም ሆነ እሱን ለመፋለም የተሠለፉት ኃይሎች ጥፋተኞች እንደነበሩ ተናግረዋል፡፡ ፕሮፌሰር ሽፈራው በቀለ መኢሶንና ኢሕአፓ በጊዜያዊ ሕዝባዊ መንግሥት ምሥረታ ጉዳይ እስከ ጥር ወር 1967 ዓ.ም. ድረስ አንድ የነበሩ ቢሆንም፣ መኢሶን ‹ሒሳዊ ድጋፍ› በሚል ከደርግ ጋር ለመሥራት መወሰኑ በሥልጣን አያያዝ አካሄድ ላይ መሠረታዊ ልዩነት እንዲኖራቸው ማድረጉን አስታውሰዋል፡፡ 
የመኢሶንና የኢሕአፓን የአደባባይ ይቅርታ በተመለከተ ዶ/ር ካሳሁን በግለሰቦችና በመጻሕፍት ውስጥ ይቅርታቸው ቢታይም፣ በአሁኑ ወቅት ድርጅቶቹ ሕልውና ስለሌላቸው ያን ማድረግ አስቸጋሪ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡ ዛሬ ላይ ሆኖ በስሜት መናገር እንደማይጠቅም የገለጹት ፕሮፌሰር ባህሩ፣ ድርጅቶቹ ይቅርታ የመጠየቅ ፍላጎት የሌላቸው መነሻቸው ለኢትዮጵያ በጎ ነገር ለመሥራት መሆኑን በመጥቀስ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡ ፕሮፌሰር ባህሩ የያኔውን የዳያስፖራ ተፅዕኖ በተመለከተ አስተያየት ሲሰጡ የያኔው የዲያስፖራ ተፅዕኖ እንዳሁኑ ጠንካራ እንዳልነበር አስገንዝበዋል፡፡ 
አንድ አስተያየት ሰጪ የቀይ ሽብር ተጎጂዎችን ለመደገፍና በእነሱ ዙሪያ የተሟላ መረጃ የመስጠት ችግር እንዳለም ጠቁመዋል፡፡ በተመሳሳይ አምባሳደር ታደለች ኃይለ ሚካኤል በቀይ ሽብር ሕይወታቸውን ያጡ ዜጎች ቁጥር በውል ሊታወቅ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ 
ቀይ ሽብር እንዳይደገም
የአፍሪካ ኅብረት ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ሲመረቅ የአፍሪካ ኅብረት የሰብዓዊ መብት መታሰቢያ ስብሰባ አዳራሹ ላይ የመሠረት ድንጋይ ተጥሏል፡፡ የመታሰቢያው ጊዜያዊ የአመራር ቦርድ ሊቀመንበር የሆኑት ፕሮፌሰር አንድሪያስ እሸቴ እ.ኤ.አ. ጥር 28 ቀን 2012 ዓ.ም. መሠረት ድንጋይ ሲጣል የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የቦታውን ልዩ አብነት አስመልክቶ በበዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር በጥሞና ማውሳታቸውን አስታውሰዋል፡፡ ቦታው የቀድሞው የከርቸሌ እሥር ቤት እንደነበርና ‹ዓለም በቃኝ› የተሰኘ በጣልያን ወረራ ጊዜና በኋላም በደርግ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተሰቃዩበትና የገደሉበት ቦታ እንደነበርም ፕሮፌሰሩ ጠቁመዋል፡፡ 
መታሰቢያው ቀይ ሽብርን ጨምሮ በሩዋንዳና በደቡብ አፍሪካ የተፈጸሙትን የዘር ማጥፋትና የአፓርታይድ ጭቆና፣ ባርነትና ቅኝ ግዛት የሚታወሱበት እንደሚሆንም አክለው ገልጸዋል፡፡ ‹‹በመታሰቢያው ብዙኃን ጉዳተኞችን ከማስታወስ አልፎ በአፍሪካውያን መሠረታዊ ለውጦች ላይ መሰል አደጋ መቼም በማንም ላይ ተፈጻሚነት እንደማይኖረው በአፍሪካ ኅብረት ውስጥ ያሉ ሕዝቦች አቋም የሚያንፀባርቁበት ነው፤›› በማለትም ዋነኛ ዓላማውን አመልክተዋል፡፡ 
የመጀመሪያው ዙር ስብሰባ በሩዋንዳ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 10 እስከ 12 ቀን 2012 መካሄዱን የጠቆሙት ፕሮፌሰር አንድሪያስ፣ በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ሰለባዎችን ለማስታወስ በየዓመቱ የ100 ቀን የሐዘን ጊዜ መኖሩን አስታውሰው፣ በኢትዮጵያም ለቀይ ሽብር ሰማዕታት የሐዘን ጊዜ መመደብ ያስፈልግ ይሆን ወይ? ብለው እንዲጠይቁ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ የተደረገው የመታሰቢያው ስብሰባ ስለ ቀይ ሽብር የሚመለከታቸው አካላት ሐሳብ በመለዋወጥ የተሻለ መግባባት ለመፍጠር ያለመ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ 
የቀይ ሽብር ፖለቲካዊ አንድምታዎች
የ1966 ዓ.ም. ሕዝባዊ አብዮት ሒደት የተጀመረውና አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖዎቹን እያሳደረ የተጓዘው የዳበረ ሰላማዊ ፖለቲካ ሽግግር ባሕልም ሆነ የነቃ የኅብረተሰብ ተሳትፎ ባልተለመደበትና ባልዳበረበት አጠቃላይ ማዕቀፍ እንደነበር የገለጹት ዶ/ር ካሳሁን ብርሃኑ፣ አብዮቱ ተስፋ እንደተደረገው ሰላማዊና ከደም መፋሰስ የፀዳ እንዳልነበር አስታውሰዋል፡፡
ለቀይ ሽብር መከሰት ዋነኛው ምክንያት በለውጡ እንቅስቃሴ መፍትሔ በሚያስፈልጋቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ዙሪያ በቂ የሐሳብ ልውውጥ ተደርጎ ብሔራዊ መግባባት ላይ ለመድረስ የአብዮቱ መቀጣጠል ድንገተኛነትና ግብታዊነት፣ እንዲሁም ብሔራዊ ፍላጎቶችን አቀናጅቶ ሒደቱን መምራት የሚችል ግንባር ቀደም ድርጅት ተዘጋጅቶ አለመቆየቱ እንደሆነ ዶ/ር ካሳሁን አስረድተዋል፡፡ 
የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) የተባለው ድርጅት በርካታ አባላትና ደጋፊዎችን አፍርቶ የጀመረው የከተማ ሽምቅ ውጊያ የበርካታ ሺሕ ዜጎችን ሕይወት የቀጠፈውንና በአጠቃላይ የኅብረተሰቡን ሕይወት ያናጋውን ቀይ ሽብር ተብሎ የሚታወቅ ክስተት ማስከተሉን የጠቆሙት ዶ/ር ካሳሁን፣ ይህ አሉታዊ ውጤት በአገሪቱና በዜጎቿ ላይ ያደረሰውን ፈርጀ ብዙ ጉዳት ተቋቁሞ በትክክለኛ መስመር ላይ የተመረኮዘ ግንባታና ተሃድሶ ለማካሄድ እስካሁንም ድረስ እጅግ ሰፊ ልፋትና ጥረት የሚጠይቅ ዓብይ ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ 
ዶ/ር ካሳሁን ብርሃኑ በቀይ ሽብር የተነሳ ሦስት መሠረታዊ የፖለቲካ አንድምታዎች መድረሳቸውን ያስረዳሉ፡፡ የመጀመሪያው ተፅዕኖ ከመንግሥትና ከሕዝብ ግንኙነት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ‹‹በኢትዮጵያ በአብዛኛው የኅብረተሰቡ ክፍል ባሕልና እምነት መንግሥት ሕዝብን ከአደጋና ክፉ ነገሮች የሚጠብቅ፣ የሚከላከልና የሚታደግ አካል ተደርጐ ሲወሰድ የነበረበት ሁኔታ ቀይ ሽብር ባደረሳቸው ጥፋቶችና መናጋቶች የተነሳ ተቀይሮ የሕዝብ አስተዳዳሪ የሆነው መንግሥት በአጥፊነት፣ በግፈኝነትና በመከራ ምንጭነት በሚታይበት ሁኔታ የመተካት ዝንባሌ በብዙዎች ዘንድ አሳድሯል፡፡ የኅብረተሰቡና የመንግሥት ግንኙነት የጥርጣሬ፣ የፍርኃትና ያለመተማመን ገጽታዎች እንዲላበስ አስገድዷል፤›› ብለዋል፡፡
ሁለተኛው ተፅዕኖ ከዜጎች የፍርኃት ስሜት ጋር የተያያዘ እንደሆነም ዶ/ር ካሳሁን ገልጸዋል፡፡ “ቀይ ሽብር በአብዛኛው የኅብረተሰብ ክፍል ውስጥ ያሳደረው የፍርኃትና የጭንቀት ድባብ በርካታ ዜጎች በአገሪቱ የፖለቲካ ዋና ዋና ጉዳዮች በንቃት የመሳተፍና የየበኩላቸውን ገንቢ አስተዋጽኦ የማድረግ አስፈላጊነትን በርቀት እንዲሸሹና በገለልተኛነት እንዲያዩት የሚያደርግ አዝማሚያ አስፍኗል፤” በማለት አስረድተዋል፡፡
ሦስተኛው ተፅዕኖ ከዜጎች ባሕሪ መለወጥ ጋር የተያያዘ መሆኑን ዶ/ር ካሳሁን ጠቁመዋል፡፡ “በቀይ ሽብር ሳቢያ ብዙዎች የፖለቲካ አስመሳይነት፣ የአድርባይነትና የለዘብተኝነት ባህሪያትን ተላብሰው ነገሮችን ከአጭር ጊዜና ግላዊ ጥቅምና ፍላጎት ማሟያ አንፃር ብቻ የመመልከት አጉል ባሕሪ እንደ ዓላማ እንዲይዙ አድርጓል፡፡” 
ዶ/ር ካሳሁን ስለ ቀይ ሽብር በተደጋጋሚ ከማውሳትና የድርጊቱን ተዋናዮች ከማውገዝና ከመኮነን በዘለለ፣ ለወደፊቱ ተመሳሳይ ድርጊቶች እንዳይደገሙ በተለያዩ ጎራዎች ተሰልፈው ደም የተቃቡና ቂም የተያያዙ ወገኖችን በማገናኘት ከቁርሾ ከመራራቅ ተቆጥበው የየግላቸውና የጋራ ስህተቶቻቸውን የሚገመግሙባቸውን መድረኮች በማመቻቸት፣ ለጋራ ጥቅምና አብሮነት በትብብር የሚሠሩበትን ሁኔታ ማገዝና ማበረታታት አስፈላጊ እንደሆነ አመላክተዋል፡፡ የተፈጸመውን ሳይረሱ ይቅር መባባል እንዳለባቸውም ዶ/ር ካሳሁን መክረዋል፡፡
የቀይ ሽብር ታሪካዊ ዳራዎች
ፕሮፌሰር ሽፈራው በቀለ ለቀይ ሽብር የዳረገው አብዮት በ1966 ዓ.ም. ሲከሰት አገሪቱ ለአብዮት ፈጽሞ ዝግጁ እንዳልነበረች አስረድተዋል፡፡ በዓለም ታሪክ እጅግ ጥቂት የሆኑት ማኅበራዊ አብዮቶች የኅብረተሰቡን የፖለቲካ ሥርዓትና ማኅበራዊ መዋቅር ሙሉ በሙሉ የሚቀይሩ፣ ኅብረተሰቡን የሚመራውን ገዥ ርዕዮተ ዓለም ቀይረው በሌላ የሚተኩና በኅብረተሰቡ በኩል ትልቅ ምስቅልቅል የሚያመጡ ክስተቶች በመሆናቸው እንደሆነ አመልክተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከእነዚህ ጥቂት ማኅበራዊ አብዮቶች መካከል አንዱን በ1966 ዓ.ም. ማስተናገዷንም ገልጸዋል፡፡
ከ1933 ዓ.ም. እስከ 1966 ዓ.ም. ባለው ጊዜ አገሪቱ በግንባታና በለውጥ ላይ የነበረች ብትሆንም፣ የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት የራሱ ለውጥ የፈጠራቸውን የለውጥ ኃይሎች ሊቆጣጠራቸውና ሊቀድማቸው እንዳልቻለ ፕሮፌሰር ሽፈራው አስታውሰዋል፡፡ ከአራት እስከ አምስት በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት በ1950ዎቹ ሲመዘገብ በዓለም ባንክ ጭምር የተከበረ የኢኮኖሚ አፈጻጸም እንደነበር የገለጹት ፕሮፌሰር ሽፈራው፣ የኢኮኖሚ ዕድገቱ የሕዝብ ብዛት እንዲጨምር ገዳይ በሽታዎችን በመቆጣጠር አስተዋጽኦ ቢያደርግም፣ የሕዝቡ ብዛት ግን ቤት አልበኝነትንና ፍፁም ድህነትን በማምጣት የተማረው የኅብረተሰብ ክፍል ጥያቄ እንዲያነሳ መጋበዙን ያስረዳሉ፡፡ “መንግሥት መዋቅር ቢለውጥም ንጉሣዊ አገዛዙ ስላልተለወጠ በአዲሱ የመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያለው ኃይል ከንጉሣዊ አገዛዙ ጋር ሊሄድ አልቻለም፡፡ የመንግሥት መዋቅሩ ለውጥ በጣም ፈጣን ሲሆን፣ ንጉሣዊ አገዛዙ የሚያደርገው ለውጥ እጅግ ዘገምተኛ ነበር፡፡ አዲሱ ኃይል በጣም ትዕግሥት ያጣ፣ መሄድ መወርወር አለብን የሚል ነበር፡፡ አባቶቹ የነበሩትን ጊዜ ጨርሶ አያመዛዝንም ነበር፤›› ብለዋል፡፡
አዲስ የፖለቲካ ባሕል
የተማሪዎች ንቅናቄ ብዙ በጎ ጎኖች ቢኖሩትም በርካታ አሉታዊ አሻራዎች እንዳሉት ያስታወሱት ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ፣ አብዮቱ በውስጡ ቀይ ሽብርን የፈጠሩ መሠረታዊ ምክንያቶች እንደነበሩትም አመልክተዋል፡፡ ‹‹የመጀመሪያው ምክንያት ቀኖናዊ የሆነ የማርክሲዝም ሌኒኒዝም አስተሳሰብ ማስረፅ ነው፡፡ ሁለተኛው የአመፅ ባሕል ፈጥሯል፡፡ ሦስተኛው የተፈጠረው ነገር ተፈጥሮአዊ ክፍፍል ነው፤›› ሲሉ ገልጸውታል፡፡
ሌላው የቀይ ሽብር ምንጭ የአመፅ ባሕል እንደሆነ ፕሮፌሰር ባህሩ ያስረዳሉ፡፡ ‹‹የአመፅ ባሕል የተለያዩ ዘርፎች አሉት፡፡ የመጀመሪያው የሃይማኖት ዘርፍ ነው፡፡ ሁለተኛው ወታደራዊ ዘርፍ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በአብዛኛው ጦርነት የተደረገው እርስ በርስ ነው፡፡ በዚህ የተነሳ ገለን መሸለል ባሕላችን ነው፤›› ብለዋል፡፡
ሦስተኛው የቀይ ሽብር ምንጭ የ1953 ዓ.ም. የእነ ብርጋዴር ጄኔራል መንግሥቱ ንዋይ መፈንቅለ መንግሥት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ‹‹የመፈንቅለ መንግሥቱ ሙከራ ሁለት አንድምታዎች አሉት፡፡ ሙከራው በመክሸፉ ከመንግሥት ይልቅ የተማሩት ተቃዋሚዎች ናቸው፡፡ ወታደሮቹ በተለይ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ መክሸፍ ማለት ሞት መሆኑን ተምረውበታል፡፡ ሌላው ሙከራው ከከሸፈ በኋላ ተሳትፎ አድርገዋል በተባሉት ሰዎች ላይ የተፈጸመው ግድያ ከቀይ ሽብር ጋር የተገናኘ ነበር፤›› በማለት አነፃፅረዋል፡፡
የቀይ ሽብር ውጤት ብሩህ አዕምሮ ያላቸውን ወጣቶች በመፍጀት፣ አምባገነናዊ ሥርዓት በመፍጠርና ኅብረ ብሔራዊ ተቃውሞን በማክሰም እንደሚገለጽ የጠቆሙት ፕሮፌሰር ባህሩ፣ ቀይ ሽብር እንዳይደገም ከዝክር ባሻገር አዲስ ፖለቲካዊ ባሕል መፍጠር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡ ‹‹ጃፓንና ጀርመን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፅልመት መጥተው ብሩህ የሆነ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ገንብተዋል፡፡ ያ ታሪክ ሆኖ ቀርቷል፡፡ በጀርመን በየጊዜው የሒትለር ሥራ በኤግዚቢሽን ይታያል፡፡ አዲሱ ትውልድ ያን እያየ ወላጆቹን ‹ይኼ ሁሉ ሲሆን ምን ታደርጉ ነበር?› ብሎ ይጠይቃል፡፡ በኢትዮጵያም በተመሳሳይ ይህን ለማምጣት አዲሱ ትውልድ ከሥር ከሥርዓተ ትምህርቱ ጀምሮ ቀይ ሽብርን እንዲያውቀው ማድረግና ዲሞክራሲን በተላበሰ መንገድ እንዲያድጉ መደረግ አለበት፤›› ብለዋል፡፡
በውይይቱ ጥናት አቅራቢዎቹም ሆኑ ተሳታፊዎቹ አገሪቱ ወደፊት ልትሄድበት የሚገባው ጎዳና ሙሉ በሙሉ ከቀይ ሽብር የፀዳ እንዲሆን የተስማሙ ቢሆንም፣ በቀይ ሽብር ተፅዕኖ ስሜታዊነት ተስተውሎባቸዋል፡፡ ቢያንስ ግን በአንድ መድረክ መነጋገርና ሐሳብ መለዋወጥ (በአብዛኛው ራስን በመከላከል መንፈስ ቢሆንም) አንድ የሚበረታታ ተግባር መሆኑን ተሳታፊዎች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ 


አክራሪነት የመሽገው በቤተመንግስት አብዮታዊ ዲሞክራሲን ተላብሶ ነው::

በቤተ መንግስት ውስጥ የሚራመድ ሃዋርያዊ/ፕሮቴስታንታዊ አክራሪነት እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል::
 

ምንሊክ ሳልሳዊ
የወያኔው ጁንታ አሻንጉሊት የሆኑት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በተለያዩ ጊዜያት እሳቸው እና ቤተሰቦቻቸው ጸረ ማርያም አቋም ሲያሳዩ እንደነበር እና ይህም የሕወሓት ማርኪሲስቶችን ተከትሎ የተፈጠር ክፍተት አሁንም ባለቤታቸው ወይዘሮ ሮማን ተስፋይ ስልጣንን ተገን በማድረግ ከፍተኛ የሆነ የፕሮቴስታንት አክራሪነት ለማስፋፋት ደፋ ቀና እያሉ መሆኑን በአንደበታቸው አስመስክረዋል::

እንዲሁም ሰማያዊ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ ላይ ""ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በምስራቅ ጎጃም በአዋበልና አነደድ ወረዳ የሚገኙ ስምንት አብያተ ክርስትያናት ከሚያዚያ እስከ ነሐሴ 2005 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ብቻ በእሳት ተቃጥለው በቤተክርስቲያናቱ ውስጥ የሚገኙ ነዋየ ቅድሳት፣ ልዩ ልዩ አልባሳት፣ ብዙ መጽሐፍትና ንብረት ወድሟል፡፡""ብሎናል:: ይህንን ንብረት ያወደመ ማነው?? መንግስት ዝምታም መርቷል:; በሌሎች ላይ ለማላከክ እና ለማሳበብ በለመደው የአሸባሪነት ድርጊቱ ራሱ አድርጎት መንግስታዊ አክራሪነቱን በሌላው ላይ ለመላከክ ምክንያት ስላጣ አድበስብሶታል:: ይህ የተደረገው ደሞ ቤተመንግስት ውስጥ በመሸጉ ለኢትዮጵያ እና ለህዝቧ አንድነት ደንታ በሌላቸው ባለስልጣናት ትእዛዝ መሆኑ የተደበቀ ነገር አይደለም:: በታሪክ ተሳስረው እጅና እጅ ተያይዘው የመጡ ሃይማኖቶችን በመጤዎች ለመተካት የሚሰራው ወያኔያዊ ደባ የትም አያደርስም ህዝኡ ስለነቃ እውነታው ሊጋለጥ ይገባል::

የዛሬ አመት ገደማ የሃይለማርያምን እና የቤተሰባቸውን ቤተመንግስት መግባት ዱካቸውን ተከትሎ በቤተ መንግስት ውስጥ ክከፍተኛ የሆነ የሃዋሪያዊ ቀኖና ሰበካ ሲካሄድ የሕወሓት ማርኪሲስቶች ለቤተመንግስቱ የፕሮቶኮል ደህንነት አያመችም በሚል አግተውት ነበር ሆኖ በጊዜው በሃይለማሪያም ቤተሰቦች እና በቤተመንግስቱ የጸጥታ ሃይሎች መካከል አለመግባባቶች ተከስተው እንደነበር አይረሳም:: በቤተመንግስት ስብሰባ ብለው የመጡ ሰዎች ከመመለሳቸውም በላይ ለጸሎት የደረሱ የሃዋርያ ቤተክርስቲያን ፓስተሮች በከፍተኛ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ተመልሰው እንዳይደርሱ ተደርጓል::

ይህ በኢንዲህ እንዳለ በቅርቡ አንድ ጋዜጠኛ የሃይለማርያምን ሚስት አላማቸውን እና እቅዳቸውን ሲጠይቃቸው አክራሪነት የተሞላ አንደበታዊ ትምክህት ተናግረዋል::ኢትዮጵያ በሃይማኖቶች መካከል በመቻቻል በመተሳሰብ እና በመፋቀር ለለዥም ዘመናት የኖረች አገር ከመሆኗም በላይ ከጥንት ጀምሮ እያንዳንዱ ሃይማኖት ዘልቆ ገባ እንጂ ኢትዮጵያዊ ማለት ሃይማኖት ሳይኖረው በፈሪሃ እግዛብሄርነት የሚኖር ህዝብ ነበር::ምንም አይነት ሃይማኖታዊ መጽሃፎች በኢጁ ሳይኖሩት በመተባበር በመፈቃቀር እና በመተሳሰብ የሚኖር ህዝብ ነው እንጂ በአክራሪነት የሚኖር ህዝብ እንዳልሆነ ቤተመንግስት የመሸጉት አክራሪዎች ሊረዱት ይገባል::

ህዝባዊ ስልጣን ይዣለሁ ከሚሉ ወገኖች የማይጠበቅ ሃገሪቷን የመጽሃፍ ቅዱስ አገር ማድረግ ነው አላማዬ ብሎ መናገር ጭልጥ ያሉ አክራሪዎችን ታቅፈን እንዳለን ያመለክታል :;ኢትዮጵያ ማንኛውም ሃይማኖት ተቻችሎ እና ተፋቅሮ የሚኖርባት ህብረ ብሄር ሃገር ነው:: ኢትዮጵያን የመጽሃፍ ቅዱስ አገር አደርጋታለሁ ብሎ መዘላበድ ነገ ለሚመጣው ችግር ሃላፊነት መውሰድም ያስፈልጋል:: እኛ ኢትዮጵያውያንን እያሰጋን ያለው የኢስልምና አክራሪነት እና አሸባሪነት ሳይሆን የባለስልታናት አክራሪነት እና አሸባሪነት መሆኑን ከተረዳን ስለቆየን ስልጣንን መከታ አድርገው ከሚፈጸሙ አክራሪያዊ አንደበቶች ራሳችንን መጠበቅ የሁል;አችን ድርሻ ነው::ኢትዮጵያዊነት ያሸንፋል::

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለቤት ለተናገሩት ነገ ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚገባ ማወቅ አለባቸው:: ለሁሉ ለውጥ አለው እንደዚህ አይነት ባለስልጣናትን ያፈራችው የሃዋርያት ቤተክርስቲያን ራሷ ከተጠያቂነት አትተርፍም:: ማንም የሚያልፋቸው የለም::ይህች አገር የጋራ ናት ሌላውን እምነት ማጥፋት አይደልም አንድ ፐርሰንት ማክሰም እንደማይቻል አስረግጠን ለመናገር እንደፍራለን::ጥንቃቄ!!!!

አሜሪካን የበጀት ቀውስ ውስጥ የከተተው ከአሜሪካ ሕዝብ ይልቅ በፓርቲ ፖለቲካ ሽኩቻሁለት ሚሊዮን የመንግሥት ሠራተኞች ባሉባትና በዓለም ላይ ከፍተኛ የቱሪስቶች መዳረሻ በሆነችው አሜሪካ፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ይዘጋሉ ብሎ ለማሰብ ያዳግታል፡፡

ሆኖም ከማሰብም ባለፈ በአሜሪካ ይህ እውን ሆኗል፡፡ በአሜሪካ ሴኔት ውስጥ ያሉት ዴሞክራቶችና ሪፐብሊካኖች ሰሞኑን የቀረበውን የበጀት ሰነድ ማፅደቅ ላይ ባለመስማማታቸው፣ አገሪቷን ከ17 ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የመንግሥት በጀት ቀውስ ውስጥ ከተዋታል፡፡ 

አሜሪካን የበጀት ቀውስ ውስጥ የከተተው የፖለቲከኞች ውሳኔ

ለመንግሥት መሠረታዊ አገልግሎቶች አዲስ በጀት ለማፅደቅ የተቀመጡት የዲሞክራቱና የሪፐብሊካኑ ኮንግረስ አባላት ባለመስማማታቸው ሳቢያ፣ ማክሰኞ መስከረም 21 ቀን 2006 ዓ.ም. 800,000 የአገሪቱ የመንግሥት ሠራተኞች ቤታቸው ያለ ሥራ ቁጭ እንዲሉ ተገደዋል፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው ከማክሰኞ ጀምሮ ቤታቸው እንዲቀመጡ የተነገራቸው የመንግሥት ሠራተኞች ከሥራ ለቀሩባቸው ቀናት የኋላ ክፍያ የማሰቡ ነገርም የሞተ ነው፡፡ የአሜሪካ ውሳኔ ሰጪ ፖለቲከኞች ልዩነታቸውን ማጥበብ ባለመቻላቸውም የመንግሥት ሠራተኞች ያለዋስትና ቀርተዋል፡፡ በአሜሪካ ምክር ቤት ከፍተኛ መቀመጫ ያላቸው ሪፐብሊካኖችና በሴኔቱ ከፍተኛ መቀመጫ ያላቸው ዲሞክራቶች አንዱ የአንዱን ድምፅ በመጣልና ለመደራደሪያ በማቅረብ ከአሜሪካ ሕዝብ ይልቅ በፓርቲ ፖለቲካ ሽኩቻ በመጠመዳቸው፣ ሁለት ሚሊዮን የሚደርሱ የመንግሥት ተቀጣሪዎችን አደጋ ላይ ጥለዋል፡፡ 

የአሜሪካ መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ለቀጣዩ ሦስት ሳምንታት በከፊል መዘጋት በመንግሥት ሠራተኞች ላይ ከሚፈጥረው የኑሮ ቀውስ በተጨማሪ፣ የአገሪቱን ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (ኢኮኖሚ) በተያዘው ሩብ ዓመት ብቻ በ0.9 በመቶ እንደሚቀንሰው ጎልድማን ሳክስ ገምቷል፡፡

ጤናና ትምህርትን ለመሳሰሉ መሠረታዊ አገልግሎቶች የተቀመጠውን አዲስ በጀት ሪፐብሊካኑ ላለማፅደቅ በወሰኑበትና ከዲሞክራቶቹ ጋር መግባባት ባልቻሉበት መሠረታዊ የመንግሥት አገልግሎቶች በጀት ምክንያት፣ የዋይት ኃውስ በጀት ቢሮ የመንግሥት ኤጀንሲዎች ቢሮዎቻቸውን በከፊል እንዲዘጉ አዟል፡፡ 

ይህንን ተከትሎ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በትዊተር ገጻቸው ‹‹በምክር ቤቱ ውስጥ የሚገኙት የሪፐብሊካን ቡድኖች ትክክለኛውንና ዋናውን በጀት ከማፅደቅ ይልቅ፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እንዲዘጉ ጫና አድርገዋል፤›› ሲሉ አስፍረዋል፡፡

የአሜሪካ ምክር ቤት የሪፐብሊካን አፈ ጉባዔ ጆን ቦህነር ሴኔቱ በአዲሱ በጀት ላይ ከስምምነት እንደሚደርስ ተስፋ እንዳላቸው በመግለጽ፣ ‹‹የአሜሪካውያን ችግር ይፈታል፤›› ብለዋል፡፡

‹‹አሜሪካውያን የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እንዲዘጉ አይፈልጉም፡፡ እኔም አልፈልግም፡፡ ሆኖም አዲሱ የጤና ኢንሹራንስ ሕግ የሚፈጥረው ተፅዕኖ አዋጭ አይደለም፡፡ መስተካከል ያለበት ጉዳይ አለ፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡ 

የቢቢሲ ዋሽንግተን ዘጋቢ ማርክ ማርዴል በአሜሪካ የተከሰተውን የመንግሥት በጀት ቀውስ አስመልክቶ፣ ‹‹የአሜሪካ ፖለቲከኞች ጥላቻ ውስጥ መግባት መንግሥት ሥራውን በአግባቡ እንዳይሠራ እስከመድረስ ተካሯል፤›› ሲል ተናግሯል፡፡ 

የአሜሪካ ሴኔት አባላት አዲሱን የመሠረታዊ አገልግሎት በጀት ማፅደቅ ባለመቻላቸው 19 ያህል ሙዚየሞች፣ ጋለሪዎች፣ ብሔራዊ የእንስሳት መጠለያዎችና ፓርኮች ተዘግተዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም ከመከላከያ ክፍል 400,000፣ ከንግድ ክፍል 30,000፣ ከኃይል ክፍል 12,700፣ ከትራንስፖርት ክፍል 18,481 ሠራተኞች ተጐጂ ሆነዋል፡፡ 

የአየር ትራፊክ ቁጥጥር፣ ብሔራዊ ደኅንነትና የኑክሌር ጦር መሣርያና ኃይልን ሳይጨምር ሁለት ሚሊዮን ሠራተኞችን ያቀፉትን የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በከፊል መዘጋት አሜሪካና አሜሪካውያንን ዋጋ ያስከፍላል ተብሏል፡፡ 

የአዲሱ በጀት አለመፅደቅ የትምህርት ክፍሉ ለመንግሥት ትምህርት ቤቶች የያዘውን 22 ቢሊዮን ዶላር በቀጣይ ለማከፋፈል ቢያስችለውም፣ ሠራተኞችን ግን በከፋ ደረጃ ተጐጂ ያደርጋቸዋል፡፡ የፖስታ አገልግሎት እንደነበረ ቢቀጥልም፣ የጡረታ ክፍያና የባለሙያዎች ጥቅማ ጥቅም ይዘገያል ተብሏል፡፡ የፓስፖርትና የቪዛ ማመልከቻዎች ደግሞ አይስተናገዱም፡፡

በጀቱ ባለመፅደቁ ሪፐብሊካኖች እየተወቀሱ ቢሆንም፣ በአጠቃላይ የሴኔቱ አባላት ‹‹እንደ ሦስት ዓመት ሕፃናት ስብስብ ይቆጠራሉ›› ሲል አንድ የኬንታኪ ነዋሪ ተናግሯል፡፡

አሜሪካውያንና ባለሥልጣኖቻቸው በሰላም ተንፍሰው ለመንቀሳቀስ የወታደራዊ ክፍሉን ጨምሮ የመንግሥት ሠራተኞች ሚና ከፍተኛ ቢሆንም፣ ‹‹ፖለቲከኞቹ በጀቱን አለማፅደቃቸው የሚያበሳጭ ነው፤›› ብሏል፡፡ 

የኦባማ የጤና ኢንሹራንስ ሕግ ተፈጻሚ እንዳይሆን የሚፈልጉ የሪፐብሊካን ሴኔት አባላት ለመሠረታዊ አገልግሎቶች የተያዘውን የመንግሥት በጀት ባለማፅደቅ እንደመደራደሪያ መያዛቸውም እያስተቻቸው ነው፡፡ 

ፕሬዚዳንት ኦባማም ‹‹የጤና ኢንሹራንስ በጀት አለ፡፡ ይህንን ማስቆም አትችሉም፡፡ እናንተ የማትፈልጉት ሕግ ስላለ ብቻ የምታሳልፉት ያልተገባ ውሳኔ አያሸልማችሁም፤›› ብለዋል፡፡ 

እ.ኤ.አ. በ1995 በተመሳሳይ 96 ያህል የአሜሪካ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በከፊል ለ21 ቀናት በመዘጋታቸው፣ ሪፐብሊካኑ በምርጫ የአሜሪካን ሕዝብ ድምፅ እንዲያጡ ማድረጉን አልጄዚራ ዘግቧል፡፡