የየካቲት አብዮትን ልዩ አስተዋጽኦ ክዶ ‹ኢትዮጵያዊነት›ን መላበስ አይቻልም፡፡

Image ምኒልክ ሳልሳዊ ብሎግ

የዘውዱ መንግሥት ከውስጡ በስብሶ የሚገፋው ብቻ እንደሚያሻው ሁሉም የለውጥ ወገኖች ባወቁበት ወቅት፣ ከተማሪውና ከምሁራኑ መካከል ቀርቶ ከታጠቀው ወታደር በኩል እንደሚታወቀው ለጊዜው መፍትሔ ተገኘ፡፡ ንጉሡ ከዙፋናቸው ተባረው፣ መሳፍንቱ ከየመንበራቸው ተወርውረው፣ ቀጥሎም ባለርስቱ ከንብረቱ ተላቆ አገሪቱ ወደ ሌላ ደረጃ ተሸጋገረች፡፡ ሕዝቡ የሚመኛቸውና ታጋዮች በየአቅጣጫው ሲጣጣሩላቸው የነበሩት ጥያቄዎች ሙሉ በሙሉ ባይፈቱም አገሪቱ ከዘውድና ከባላባታዊ ሥርዓት ተላቀቀች፡፡

የቅርብ ጊዜ የኢትዮጵያ ታሪክ እጅጉን ሊጠናና ሊመረመር የሚገባው መሆኑ የማያከራክር ቢሆንም፣ በመጪው የካቲት 2006 ላይ 40ኛ ዓመቱን የሚሞላው አብዮት በተመለከተ ግን በታላቅ ክብረ በዓል ልንቀበለው የሚገባ ነው፡፡ በተለይ ውድ ሕይወታቸውን ሳያቅማሙ ላበረከቱት ወገኖች፣ ተሰውተውም ቢሆን በሕይወት ተርፈው ባሉበት ሁኔታ፣ ይህ ታሪካዊ ዕለት የራሳቸው የግል የሕይወት ምዕራፍ ተደርጐ ሊታሰብላቸው ይገባል፡፡ በሕይወት ያሉትም ሆኑ ተወላጆቻቸው እንዲሁም ወጣቱ ትውልድ በአጠቃላይ የራሱን ወገን መብት፣ ክብርና ህልውና በአዲስ መልክ ማዋቀሪያና ማቀፊያ ሆኖ የተነሳውን የካቲት 1966ን መልሶ ሊዘክረው፣ ሊያውቀውና ሊያቅፈው ይገባል፡፡

አብዮት የከበደ፣ መራርና በደም የተለወሰ ማኅበራዊ ነውጥ ነው፡፡ ጥቂቶች ተመልሶ የማይገኝ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደረጃቸውን ያጣሉ፡፡ ብዙኃኑ ግን እግር ተወርች ተጠፍረው ከሚኖሩበት ሥርዓትና ሕይወት ተላቀው ወደ አዲስ ጐዳና ይገባሉ፡፡ ለውጡ ወዲያውኑ ለብዙኃኑ ሕዝብ ገነትን አይፈጥርም፡፡ ይህ ዓይነት አካሄድና ሁኔታ የመጀመሪያው ሕዝባዊ አብዮት በተካሄደባት በሃይቲም፣ ከዚያ በቀጠለው በፈረንሳይም፣ በሜክሲኮም፣ በሩሲያም፣ በካሜሩንም ታይቷል፡፡ የየካቲት የኢትዮጵያ አብዮት ከእነዚህ ሁሉ በአነሳሱም ሆነ ባቀፋቸው ኃይሎች ስብጥር በጣም የሚለይባቸው ምክንያቶች ስለነበሩ በሒደቱም በውጤቱም እንደዚያው ነበር፡፡

አንዳንዶች የየካቲት አብዮትን ሲያነሱ ያንገፈግፋቸዋል፡፡ በዜና ማሰራጫዎች በተለይ የማጥላላት ዘመቻ ሲካሄድ ውሎ አድሯል፡፡ የየካቲት አብዮትን ከደርግ አስተዳደር ጋር በማምታታት ይመስላል አንዳንዶች ይህ የሚሰማቸው፡፡ ነገር ግን የዛሬዋ ኢትዮጵያ መሠረት የተጣለው የየካቲት አብዮት ባስገኛቸው ድሎች ወይም በፈጠራቸው አማራጭ የለሽ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ መዋቅሮች ላይ ነው፡፡ ደርግ ተገዶ የየካቲትን አብዮትን ቃላትና አልባሳት ተውሶ የሕዝቡን ብሶትና ጥያቄዎች በከፊል መልሶ በአምባገነንነት አገሪቱን በጦርነትና በደም ቢያጥባትም የየካቲት አብዮት ጥፋት አይደለም፡፡ የሕዝብ ወገኖች ነን ባዮች ኃይላቸውን አስተባብረው አብዮቱን እንዳነሳሱ  ሁሉ ወደ ግቡ ሳያደርሱት ቢቀሩ ተጠያቂው ያው አብዮት ሊሆን አይችልም፡፡ በተለይ ደግሞ ደርግን በመደገፍና በመቃወም ዙሪያ የተከሰተው መተላለቅ ያንኑ አብዮት በተከሳሽነት አያስመድበውም፡፡

ለማንኛውም የየካቲት 1966 ዓ.ም 40ኛ ዓመት ይከበር ሲባል ከደርግ ጭፍጨፋ በፊት ገና ደርግ የሚባል ነገር ባልታሰበበት ወቅት የተከሰተውን ሰማይ ሰበር ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ትርዒት ነው፡፡ በወቅቱ በሕይወት የነበሩም ሆኑ ገና ያልተወለዱ ይህን የአገራችንን የታሪክ ጉልላት መለስ ብለው ሊያስታውሱት፣ ሊያስቡት፣ ሊመረምሩትና ሊያወድሱት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የራሳቸውን ማንነት የገነባውን ታላቅ ታሪካዊ ምዕራፍ እንዳልነበረ ወይም የጥፋትና የእልቂት ምልክት አድርጐ በአንዳንድ ወገኖች የሚነፋውን የውሸት ትረካ ማመን የለባቸውም፡፡ እውነተኛው መንገድ የአገሪቱን የገነገነ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ሥርዓት ከሥሩ እንዲነቀል ያስቻለውን ታሪካዊ ዕልልታ መቀበልና ማወደስ፣ ድክመቱንና ጥንካሬውን መርምሮ ትምህርት መቅሰም ነው፡፡

ነገር ግን ይህንን የፈጠጠና በታሪክ መዝገብ የሰፈረ ትርዒት ተረግጠው ዘለው ሄደው፣ ያልነበረ የውሸት ሀተታ እየበዘበዙ የ1966 አብዮትን እንዳልነበረ ከአዕምሯቸው አውጥተው ጥለው፣ የአገሪቱ ወጣት ትውልድም ማንነቱን እንዳያውቅ ማድረግ ምሕረት የማይሰጠው ጥፋት ይሆናል፡፡ የየካቲት አብዮትን ልዩ አስተዋጽኦ ክዶ ነገር ግን ባዶነትን ሸፋፍኖ ‹ኢትዮጵያዊነት›ን መላበስ አይቻልም፡፡ ምን ላይ ተቁሞ የራስን ታሪክ በተውሶ ታሪክ፣ የራስን ባህል በተቀዳ ባዕድ ባህል ለመተካት ለሚሹ ምርጫቸውን መተቸት አይቻል ይሆናል፡፡ ሆኖም አገሬና እናቴ እያሉ ለሚዘፍኑ፣ ለሚቀኙ፣ ለሚሟገቱ፣ ትንታኔ ለሚያቀርቡና በየመድረኩ ለሚፎክሩ ሁሉ የወቅቱ አንድ ትልቅ ፈተና ይኸውና እፊታችሁ ተደቅኗል እንላቸዋለን፡፡ የየካቲት 1966ም 40ኛ ዓመት በዓል ለማክበር መነሳሳት፡፡

በዓሉን ለማክበር የሚሹ ሁሉ በየፊናቸው መደራጀት ይችላሉ፡፡ ሁሉም በአንድ አዳራሽ፣ በአንድ መድረክ፣ በአንድ አገር መሆን የለበትም በዓሉን ለማክበር፡፡ ዋናው ነገር ማክበሩ ነው፡፡ በየዘርፎችና በየመገናኛ ብዙኃኑም እንደዚሁ ለየብቻቸው ወይም በተባበረ መልክ ማክበር ይችላሉ፡፡ ሬዲዮ ጣቢያዎች፣ ጋዜጦች፣ ቴአትር ቤቶች፣ ወዘተ ወቅቱን ተንተርሰው የየራሳቸው ዝግጅት ማድረጋቸው የማይቀር ነው፡፡ ለበዓሉ ዝግጅት የሚነሱትንና በተግባር የሚሠለፉትን ሁሉ ይበል፣ እሰይ እንላቸዋለን::
 የየካቲት 1966 አብዮት 40ኛ ዓመት ክብረ በዓልን በተመለከተ  ምኒልክ ሳልሳዊ  ብሎግ ለሚነሱ አስተያየቶች ጸሐፊውን አስፋ አሰፋ አንደሻው በኢሜይል አድራሻቸው etfeb74@gmail.com ማግኘት ይቻላል፡፡

በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው ጥቃት እና የፈዘዘው ስርኣት የፖለቲካ ክስረት መፍትሄው ኢሕኣዴግ የማይደፍረው ስር ነቀል ለውጥ ነው:

ምንሊክ ሳልሳዊ:-ኢትዮጵያውያን በመካከለኛው ምስራቅ በስፋት መሰደድ የጀመሩት ባለፈው 20 አመታት የወያኔው ጁንታ መንግስት ስልጣኑን ተቆጣጥሮ በህዝቦች ላይ በተለየ መልኩ የፈጠረውን አደገኛ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ቀውስ ተከትሎ መሆኑ እሙን ነው::ይህ ቀውስ የደረሰባቸው ወገኖቻችን ከተሰደዱባት ሃገር አንዷ ሳኡዲ አረቢያ ተጠቃሽ ናት::ሳኡዲ አረቢያ ከሃብቷ ብዛት የመጣ የስራ ፍቅር ባሌለው ወጣት ዜጋ የተሞላች እና ፔትሮ ዶላር ባሰከራቸው ቱጃሮች የምትተዳደር አገር መሆኗ እና የዜጎቿ የስራ አለመስራት የስራ እድሎችን ስላሰፋ የወያኔ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ተጠቂዎች ወደዚሁ መሰደድን መርጠዋል:: ይህንን ተከትሎም ይህን ሰሞን የአለም ዋና አጀንዳ የሆነው የኢትዮጵያውያን በሳኡዲ አረቢያ እየደረሰባቸው ያለ ስቃይ ነው::
ምንሊክ ሳልሳዊ ብሎግ
ሰቆቃው ያደረሰው የሰብኣዊ መብት ጥያቄ ከሳኡዲ መንግስት ላይ ይልቅ ወደ ወያኔው ጁንታ ላይ እንዲተኮር ያደረገ ሲሆን የወያኔው ጁንታ ለከፍተኛ የፖለቲካ ኪሳራ ተዳርጓል::በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው አስደንጋጭ እና ሰብኣዊነትን ያለፈ ድርጊት በመንግስት ባለስልጣናት መሃከል የፈጠረው መረበሽ እስከአለመግባባት አድርሷቸዋል::ይህንን የወያኔን አቋም የተመለከተችው ሳኡድ አረቢያ በአለም አቀፍ ደረጃ የፖለቲካ የበላይነት ተቀናጅታለች::የወያኔ ተቃዋሚ በሆኑት እና በአገር ውስጥ በውጪ በሚኖሩት ድርጅቶች  እንዲሁን በከፍተኛ ደረጃ በአለም አቀፍ ደረጃ ባሉ ኢትዮጵያውያን እና እርትራውያን ዘንድ ከፍተኛ የሆነ አትኩሮት አግኝቶ የአለም ጎዳናዎች ሳኡዲን እና ወያኔን በሚቃወሙ በሰላማዊ ሰልፍ እየተጥለቀለቁ ነው::

ከወያኔው መንግስት የሚንጸባረቁ አጀንዳዎች ለዘብተኛ አቋሞች በስህተት እንደተፈጠሩ ወቅታዊ ሁኔታኦች እያሳዩ ሲሆን ስርኣቱ አጣብቂኝ ውስጥ እና የፖለቲካ ኪሳራ ውስጥ እንደገባ ተረጋግጧል:: የሌላ ሃገር እምባሲዎች ዜጎቻቸውን በመጠበቅ ላይ ሲያተኩሩ የወያኔው ዲፕሎማቶች የዜጎች ንብረት የሆነውን ኤምባሲ በመዝጋት አገልግሎት አቁመዋል::
የደረሰውን ሰቆቃ ተከትሎ ስርኣቱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመተባበር ለሉአላዊ የዜግነት ክብር መነሳሳት ሲኖርበት እና ህዝብን ማቀፍ ሲኖርበት ለብሄራዊ ውርደት ዜጎችን ዳርጓል::የፖለቲካ ፓርቲዎች የጠሩትን ሰልፍ በሃይል እና በደብዳቤ በትኗል::የወያኔው ስርኣት የህዝቡን ቁጣ ባለማንበቡ በችኮላ ያልበሰለ ሃሳብ በማራመዱ የፖለቲካ ኪሳራውን አስፍቶታል::ህገመንግስታዊ መብቶችን አለመከበሩን እና ለዜጎች አለመቆርቆርን በማሳየቱ በአለማቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያውያንን ቁጣ ቀስቅሷል::ሚዲያዎች ከዜጎች የሳኡዲ ሰቆቃ ይልቅ የወያኔን ስርኣት ጋጥወጥነት አትኩሮት ሰተውታል::

ለዚህ ሁላ ችግር መንስኤው ስርኣቱ በልማት ሽፋን የሚከተለው የፖለቲካ እና እና የኢኮኖሚ ፖሊሲ ችግሮች እንደሆኑ አግጥጦ ገሃድ ከመውጣቱም በላይ የአደባባይ ሃቅ ሆኖ ለለውጥ እንትጋ የሚሉ ድምጾች በመላው ሃገሪቱ ተንጸባርቀዋል:; የወያኔ ስርኣት ህዝብን የሚያሳትፍ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ፖሊሲ እስካልተከተለ ድረስ እና አሁን ባለው ሂደት ላይ ለውጥ እስካላደረገ ድረስ የስደት ችግሩ በስፋት እየቀጠል ይሄዳል:;ዛሬ ሳኡዲ ላይ የደረሰው ሰቆቃ ነገ በሌሎች ሃገራትም ይቀጥላል::ይህ ብሄራዊ ውርደት በታሪካችን አይተነው የማናውቅ ነው:;ኢትዮጵያውያን ከቀድሞው ጀምሮ በፖለቲካ ቢሰደዱም እንደዚህ አይነት ውርደትን አስተናግደው አያውቁም::የአሁኑ ውርደት ያለው ስርኣት ለዜጎቹ ደንታ ቢስ በመሆኑ የተወለደ ችግር ነው::በሃገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ተመዘገበ ከመባል ውጭ የተባለው እድገት ምንም አይነት ህዝባዊ ጠቀሜታ እንዳላሳየ በይፋ አስመስክሯል::የተማረው እና የሚሰራው ሃይል መሰደዱ ኢኮኖሚው እንደኮላሸ እንጂ እንዳደገ አያሳይም::የዚህ ሁላ መንስኤው ስርኣቱ የሚከተለው አፋኝ የፖለቲካ እና የእኮኖሚ ፖሊሲ ስለሆን ድጋሚ ሊከለስ እና ሊፈተሽ ይገባዋል::

የነቃ እና የተደራጀ አዲስ ፖሊሲ አስፈላጊ መሆኑ እሙን የሆነበት ጊዜ ላይ ደርሰናል::ስርኣቱ የሚከተለውን ፖሊሲ በአስቸኳይ ካልቀየረው የሚመጣው አደጋ ከፍተኛ ነው::በሃገሪቱ በልማት ስም እና በፖለቲካ ባላንጣነት በዜጎች ላይ የሚደርሰው ችግር የሙስና መንሰራፋት ሚዛናዊነት የጎደለው የምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴ የግሉን ሴክተር የማዳከም ውስጣዊ ሴራ ዘር ተኮር የሆነ ፖለቲካ እና አድሎኣዊ አሰራር የትምህርት ጥራት መውረድ እና የስራ አጡ ቁጥር እንዲስፋፋ የሚደረጉ ደባዎች ዜጎች ምንም አይነት ጥያቄ እንዳያነሱ የሚደረጉ የፖለቲካ ዱላዎች ለድህነት መፈጠር እና የስደት መስፋፋት ምክንያት ሆነዋል::የህዝብ ቁጥርን ተከትሎ የሚደረግ የእድገት ፖሊሲ አለመመጣተን የሃገሪቱ ዜጎች ተዘዋውረው እንዳይሰሩ የተደረገ የጎሳ ፖለቲካ የተማሩ ዜጎችን የስራ እድል አጥብቦታል::አለ ተብሎ የሚወራለት የኢኮኖሚ እድገት ጥቂት የስርኣቱን ካድሬዎች ተጠቃሚ ያደረገ በመሆኑ ማንኛውም ነገር በካድሬዎች ዙሪያ እና በፓርቲ ስራዎች ዙሪያ ያተኮረ በመሆኑ ዜጎች በሃገራቸው ላይ ተስፋ እንዲቆርጡ አድርጓቸዋል::

ያለው ስርኣት ስርነቀል ለውጥ ለማምጣት ፖሊሲዎቹን እና የደረሱ የዜጎችን ችግር ከስሩ መሰረቱ መመርመር አለበት:: በፓርቲው አመራር ደረጃ ያሉ የስርኣቱ ባለስልጣናት ለስርነቀል ለውጥ ራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው::በግል የንግድ ተቋማት ላይ ስርኣቱ ያለው አቋም ከመጀመሪያ ለውጦች አንዱ ነው የግል የንግድ ተቋማት መዳከም ምክንያቱ የስርኣቱ መራሽ የንግድ ድርጅቶች እና አድሏዊነት የፈጠረው የኢኮኖሚ ችግር ሲሆን መፍትሄውም የተዳከመውን የግሉን የንግድ እንቅስቃሴ እንዲያንሰራራ ማድረግ እና ለዜጎች በርካታ የስራ እድሎች እንዲከፍት ማበረታታን አንዱ ሲሆን የተለየ የፖለቲካ አቋም ያለው ዲያስፖራው በሃገሩ ጉዳይ እንዲሳተፍ እድሎችን ማመቻቸት እንዲሁ ለፖሊሲ ለውጥ ጅማሮ ሊሆን ስለሚችል ስደትን በስፋት ለመቀነስ እና ዜጎች ከሃገራቸው እንዳይወጡ ለማድረግ ይችላል::

በአሁን ሰአት ስርኣቱ እየተተቀመበት ያለው የኢኮኖሚ ፖሊሲ በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ የተገነባ ከመሆኑም ባሻገር ባልተማሩ እና ባልሰለጠኑ የፖለቲካ ታማኞች ስለሚተገበር በአግባቡ እየተተረጎመ ባለመሆኑ ውድቀትን አምጥቷል::የሃገሪቱ አጠቃላይ ሃብት እና የኢኮኖሚ ምሶሶ በጥቂት የፓርቲ ድርጅቶች እና ባለስልጣናት እጅ በቁጥጥር ስር ስለሆነ የግሉ ኢንቨስትመት በመዳከሙ እና ስርኣቱ ከዚህ አይነት የንግድ እንቅስቃሴ ካልወጣ በቀር ምንም አይነት ለውጥ መምጣት እንደማይቻል እሙን ሲሆን መፍትሄው የተቆጣጠረውን እና በግል መያዝ ያለባቸውን የንግድት ተቋማት እና የአገልግሎት ዘርፎች መልቀቅ ካልቻለ ችግሩ እየከፋ ዜጎችን ምንም ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ያደርጋል::በአለም አቀፍ ደረጃ እንደሚታየው መንግስታት ህግ የማውጣት እና የማስፈጸም አቅም እንጂ ከትልቅ እንስከተራ ንግድ ድረስ እጃቸውን አስገብተው ሲሰሩ አይታይም::ያለው ስርኣት ወደ ቸርቻሪ ነጋዴነት በመቀየሩ ለዜጎች የስራ እድሉን አጥብቦታል::

ኢኮኖሚውን ከፍተኛ የጦር ጄኔራሎች እና የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች በሞኖፖል ስለተቆጣጠሩት ዜጎች በስርኣቱ ፖለቲካ ካልተጠመቁ ድረስ ስራ የማግኘት እድል የላቸውም::ይህ ኢኮኖሚውን የመቆጣጠር የፖለቲካ ጭብርብሮሽ የኢንቨስትመት ሂደቱን ከማዳከሙም በላይ ዜጎች በሃገራቸው እና በስርኣቱ ላይ እምነት እንዲያጡ አድርጓል::ስርኣቱ ከነጋዴነት መውጣት ሰፊ የስራ እድሎች እንዲፈጠሩ እና ስደት እንዲቀንስ የሚረዳ ሲሆን ዜጎች በሃገራቸው ተሳፋ እንዳይቆርጡ ያደርጋል:: እንዲሁም የመንግስት የመገናኛ ቡዙሃን በሃሰት የተሞሉ መሆናቸው እና አስፈላጊውን መረጃ መስጠት አለመቻላቸው ሌላኛው የኢኮኖሚ ድቀት እና የስደት መንስኤ ናቸው:: በነጻነት የማይሰሩት እና ለፖለቲካው የእድሜ ማስረዘሚያ የሆኑት የመገናኛ ብዙሃን ቀረጥ የሚከፍላቸውን ህዝን እንዳያገለግሉ ከመደረጉም በላይ በሃሰት የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ወንጀሎችን በመፈብረክ የታወቁ ሆነዋል::

 ሕዝቡ ስርኣቱ እስካልተመቸው ድረስ ስደትን ማቆም አይቻልም ጊዜአዊ እገዳውም ውጤታማ አይሆንም:: ሀገሪቱ ብዙ ሴቶች ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሊሰደዱባት የቻለውም ከሴቶች እኩልነት ጋር በተያያዘም ችግር በመኖሩና ብዙ ስራ አለመሰራቱን የሚያሳይ ነው::በዚህ ዙሪያ የሚሰሩ ድርጅቶችም በነፃነት አለመቋቕውማቸው ሴቶችም እንደሰው አለመታየታቸው ነው::የፓርቲ ፖለቲካ መስበክ ሳይሆን በሴቶች እኩልነት እና ተሳትፎ ዙሪአ ኢኮኖሚው መዳበር ሲኖርበት አስፈላጊውን ኦረንቴሽንም መስጠን የስርኣቱ ግዴታ ነው::አሁን ባለው ሁኔታ ወደ ስራ የሚገባውን ወጣት የሚሸከም ኢኮኖሚ አልተፈጠረ:: የግል ሴክተሩም በርካታ ዜጎች እንዳይፈጥር ሆኖ እየሞተ መሆኑን ከዓለም ባንክ ሪፖርቶች ማየት ይቻላል::በዓለም ደረጃ በመንግስት ኢንቨስትመንት ኢትዮጵያ በዓለም ሦስተኛ ስትሆን፤ በግል ኢንቨስትመንት ከመጨረሻዎቹ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ነን። ስለዚህ የግል ሴክተሩ ካልተስፋፋና ካላደገ ስራ ሊፈጠር አይችልም። በየዓመቱ ከዩኒቨርሲቲ የሚመረቀው ወጣት በዓመት ወደ መቶ ሺህ ሊጠጋ ነው። ይሄንን ኃይል መጦ የሚያስቀር  የሚያደርግ ኢኮኖሚ መፈጠር የሚቻለው የግል ሴክተሩ ሲነቃቃ ነው። አሁን የግል ሴክተሩ በኮንስትሪክሽን ዘርፍ ላይ ውር ውር እያለ ነው። ይሄም ሴክተር ቢሆን፤ የቀን ሰራተኛ ከመሳብ ባለፈ ሙያተኛውን መቅጠር አልቻለም። ለዚያውም ትንሽ ሲሚንቶ መለሰን ሲጀምሩ ወደ መካከለኛው መስራቅ በተከበረ ወርሃዊ ደመወዝ ሲቀጠሩ ይታያል። ሀገሪቱ የተማረ የሰው ኃይል የላትም። ያሉዋትም ለባዕድ አገር እያገለገሉ ነው። በአንፃሩ የአገሪቱን የባቡር መንገድ እና ግድብ የሚሰሩት ቻይናና ሕንድ ናቸው። ስኳር ፋብሪካውንም የሚሰሩት ሕንዶች ናቸው። በሚያሳዝን መልኩ ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን የተማሩም ሆነ ያልተማሩ ችሎታቸውን እየሸጡ ያሉት ለባዕድ ሀገር ነው። ከአፍሪካ እስከ ደቡብ ሱዳን፣ ቦትስዋና እና ደቡብ አፍሪካ ሳይቀር በርካታ ኢትዮጵያውያን ችሎታቸውን በጥሩ ዋጋ እየሸጡ ነው። ይሄን አሳዛኝ ታሪክ ለመቀየር የግል ሴክተሩ ማደግ ወሳኝ ነው ።

የግል ዘርፉ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ይረከብ ማለት ግድብ ይገንባ፣ የባቡር መንገድ ይዘርጋ ማለት አይደለም  ነገር ግን የግል ዘርፉ ሊሰራቸው የሚችሉ ስራዎች ተለይተውና ተጠንተው መሰራት አለባቸው።  የኅብረተሰብ ችግርም እየተበራከተ ስለሆነ ችግሩን መመርመር ያስፈልጋል ። የግል ዘርፉ ከካፌና ሆቴል ላይ ብቻ የሚሯሯጠው ለምንድነው? የቀጥታ የውጪ ኢንቨስትመንት ችግር በገፍ የማይመጣው ለምንድነው፣ አነስተኛና ጥቃቅን አደረጃጀት ምን ያህል ውጤት አምጥቷል? የተደራጀ ጠንካራ የግል ዘርፍ መፍጠር ነው ወይስ አነስተኛ ጥቃቅን ድርጅቶች የሚለው መታየት አለበት። የትኛው ነው ብዙ ኀሳብ የሚያመነጩት፣ የገበያ ሁኔታስ? ባንኮች አካባቢ ያለው ችግር ምንድነው? ለምን አያበድሩም ይሄ ሁሉ መፈተሽ አለበት ።ኢትዮጵያ የአረብ ገረድ አምራች ሆና መቅረት አለበት ። ምንሊክ ሳልሳዊ ብሎግ


የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ስደተኛ እንጂ ህገወጥ/ወንጀለኛ ዜጋ የለንም:ምንሊክ ሳልሳዊ :- ይህ በአለም ላይ የማይካድ እውነት ነው:: ምንም ከሃገሩ ካለምክንያት አይሰደድም የአንድን ሃገር ድንበርም ጥሶ ካለምክንያት አይዘልቅም:: ኢትዮጵያውያን በተለያዩ መንገዶች ወደ አረብ አገራት ገብተዋል:: የይልፍ ወረቀት ገዝተው በአየር የወጡትን ጉዳይ ለጊዜው ተወት እናድርገው እና በዛሬው ወቅት ህገወጥ እየተባሉ በአረቦቹ እና በስርኣቱ መሪዎች ስለሚወነጀሉት ኢትዮጵያውያን አጠር ያለ ነገር እናንብብ::

ወደ አረብ አገራት የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን በሁለት ይከፈላሉ እነዚህ ስደተኞች አብዛኛዎቹ በባህር አቋርጠው እና አስቸጋሪ ፈተናዎችን አልፈው በሰላም ወደ ፈለጉበት የደረሱ የሸሹ የተደበቁ እጅግ አሳዛኝ ዜጎች ናቸው:: በሁለት ከፍለን ስናያቸው የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ስደተኞች ብለን እናስቀምጣቸዋለን :; እነዚህ የሁለት ፈርቅ ስደተኞች በጅቡቲ እና በሱማሌላንድ ወደቦች  በጀልባዎች ተጭነው የተረፈ ተርፎ የገባ ገብቶ አሁን ላሉበት ሁኔታ ደርሰዋል::እስኪ ከፍለን እንመልከታቸውምንልክ  ሳልሳዊ

የፖለቲካ ስደተኞች
እንዚ የፖለቲካ ስደተኞች በብዛት የተሰደዱት ከኦሮሚያ ክልል ሲሆን እነዚህ ኢትዮጵያዊ ስደተኞች በተለያየ ጊዜ የእነግ አባላት ናችሁ የኦነግ ጦር ረዳቶች ናችሁ ኦነግን ትደግፋላችሁ በሚል የተለያዩ ችግሮች እና መከራዎች ሲደርሱባቸው ድብደባ እና እስር ሲፈጸምባቸው ይህንን በመሸሽ እንዲሁም የቤተሰቦቻቸውን እና የራሳቸውን የእርሻ መሬት ሲነጠቁ የስራ እድላቸው በፖለቲካ እምነታቸው ሲጋረድባቸው ስርኣቱ በፈጠረው የፖለቲካ ጫና ቤተሰብ ማስተዳደር ሲሳናቸው ወደ የመን ሳኡድ አረቢያ ደቡብ አፍሪካ  እና የተለያዩ አገሮች በምድር ጉዞ ይሰደዳሉ:; እንዲሁም ሴት ልጆች በቤተሰባቸው ላይ ፖለቲካው የፈጠረን ጫና ለማሸነፍ ሲሉ እንዲሁ ይሰደዳል:: እንዚህ የፖለቲካ ስደተኞች ራሳቸውን ለማሸነፍ ሲፍጨረጨሩ ህገወጥ ወይንም ወንጀለኛ አድርጎ ማየት ሃላፊነት የጎደለው አስተሳሰብ ነው::

የኢኮኖሚ ስደተኞች
በሃገሪቱ የተንሰራፋው የዘረኝነት ጁንታ አብዛኛው ህብረተሰብ እንዳይሰራ ግሬጣ ከመሆኑም በላይ የፖለቲካው አናት የንግድ ድርጅቶቹን በማስፋፋት በሃገሪቱ አንጡረ ሃብት እየተጫወታ ዜጎችን ለድህነት አገሪቱንም ለድቀት ዳርጓል::የሃገሪቱ የትምህርት ጥራት ትውልድ እንዳያፈራ ተደርጎ አመድ ከተለወሰ በኋላ የስራ አጥ ቁጥሩ በእጥፍ ጨምሯል:: የምእራባውያኑ የገንዘብ ተቋማት የአፍሪካን እድገት ስለማይፈልጉ አምባገነንነትን በማበረታታት የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ይነዛሉ::እንዲሁም እንደ ቻይና የመሳሰሉት አገራት ከቀን ሰራተኛ ጀምሮ በተለያዩ ለውጪ ዜጎች በማይፈቀድ የስራ ዘርፍ ተሰማርተው የአገሪቱን ወጣት በስራ አጥነት እጁን አጣጥፎ እንዲቀመጥ አድርገውታል:: ይህ አይነቱ መንግስት ባለስልጣናት ነጋዴነት ሙሰኝነት የውጪ ዜጎች ካለደረጃቸው ዝቅ ብለው የሚበጠብጡት የስራ እድል አሻሚነት ተደማምሮ በአመት ከ 800.000 በላይ ስራ አጥ ስለሚፈጠር የስደት መንስኤ ሊሆን ችሏል::ወደ አረብ አገራትም የሚሰደዱ ዜጎች የዚህ እና የተያያዥ የኢኮኖሚ ችግሮች ሰለባ ከመሆናቸውም በላይ ይህ ደግሞ የስርኣቱ ለዜጎች የኑሮ እድገት ግዴለሽነት ያመለክታል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ የብሄራዊ እፍረት መንስኤ የሆነው ስርኣት በሚከተለው የፖለቲካ እና የእኮኖሚ ፖሊሲ ምክንያት ዜጎች አገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ እና ለሞት ለእስር ለስቃይ እና ለመንገላታት እንዲዳረጉ ሚናውን ተጫውቷል:: ይህንን መፍትሄ ለማምጣት የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልገናል በጋራ አገር ላይ በጋር እንድንሰራ እኛ እናውቅላቹዋለን የሚል ስርኣት ከነአካቴው ሊቆም እና ሃይ ሊባል ይገባዋል: ኢትዮጵያውያን በአረብ አገራት እየደረሰ ያለው መከራ የምን ውጤት ነው መፍትሄውስ ምንድነው ብለን ቆም ብለን የምናስብበት ጊዜ ነው:: ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር ስርኣቱ አሁንም ካለው እኩይ አድራጎቱ ሊቆጠብ ስለማይችል ነገ በሌላም አገር የምንኖር ኢትዮጵያውያን ችግሮች ቢደርሱብን የገዛ ዜጎቼ ሳይሆን የሚለው አብሮ ህገወጥ እና ወንጀለኛ ብሎ በመፈረጅ ለሞት እና ለስቃይ ከመዳለግ ወደኋላ ስለማይል የትግል አድማሳችንን በማስፋት ወንጀለኛው ህገወጡ በሃገሪቱ የተንሰራፋው ስርኣት መሆኑን የማጋለጥ ግዴታ አለብን;;ጎን ለጎንም የመፍትሄ ሰዎች እየሆንን ባለው ስርኣት ላይ ጫና በማሳደር መትጋት ድርሻችን ነው::

ኢህአዴግን በግልጽ በቃህ የምልበት የመጨረሻው ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡ አዎ!

beka2-300x168
ኢትዮጵያዊ ባልሆነ መንግስት መገዛት ይብቃን!

አንድ የኢህአዴግ ታጋይ አሊያም ሲቪል ካድሬ ሲሞት በቴሊቪዥን ሳይቀር ይለፈፍለታል፡፡ በሳውዲ እየሞቱ ለሚገኙት ኢትዮጵያውያን ግን አንድም ነገር አልተደረገም፡፡ ሌላው ይቅርና መሰሎቹ አጭበርብረው ‹‹ምርጫ አሸነፍን›› ሲሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ለማጉረፍ ማንም የማይቀድማቸው እነ ኃ/ማሪያም አሁን ምንም አላሉም፡፡ በተቃራኒው ድምጽ ለማሰማት የወጡትን በጨካኝ ፖሊሶቻቸው አስደበደቡ፡፡

ወደ ጣሊያን ሲያቀኑ ያለቁት የአፍሪካ ስደተኞችን ሞት አስመልክቶ ሰንደቅ አላማው ዝቅ ብሎ ተውለብልቧል፡፡ የኢትዪጵያውያንን ነፍስ ምን ያህል አርክሰው ቢያዩት ነው? ለአንድ ቀን ሀዘን፣ ለአንድ ቀን ሰንደቅ አላማውን ዝቅ ለማድረግ አልፈቀዱም፡፡ ስለዛ አምባገነን መሪያቸው ግን ሁሌም ይቆዝሙብናል፣ ይለምኑብናልም፡፡ ኢትዮጵያን እንደነጠቁን ሰላማዊ ሰልፉን በመከልከል ዳግመኛ አረጋግጠውልናል፡፡ በተቃራኒው ከኤስያ፣ እስከ አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ የእኛዎቹ ወገኖች እንደልባቸው ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉ ነው፡፡

እንዲያውም ድጋፍ እየተደረገላቸው፡፡ ትናትና ፌስ ቡክ ላይ እንዳነበብኩት አንድ የአውሮፓ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርጉ ሲያሳውቁ የድምጽ ማጉያ የመሳሰሉ መሳሪያዎች ከሌሏቸው ማዘጋጃ ቤቱ ሊያውሳቸው እንደሚችል አረጋግጦላቸዋል፡፡ እንደ ሳውዲ ካሉት ውጭ ለኢትዮጵያውያን አገራቸው ካለው ይልቅ የተሰደዱበት መንግስታት ደግና ርሁሩሆች ናቸው፡፡ ለእኔ ኢህአዴግ ኢትዮጵያዊ ላለመሆኑ ከዚህ ውጭ አስረጅ አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡ የግድ እንደ ግራዚያኒ በየ ቤታችን ገብቶ በቆጨራ እስኪቆርጠን መጠበቅ የለብንም፡፡ ካድሬ ሆነ ተቃዋሚ፣ አማራ ሆነ ኦሮሞ፣ ትግሬ ሆነ ወላይታ ኢህአዴግ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን እስካለሰበ ድረስ ከስቃዩ ሊያመልጥ አይችልም፡፡ መለስ ከሞተበት ጊዜ ጀምሮ ኢህአዴግ ገንዘብ ሲያሰባስብ የነበረው እንደ ሳውዲ ባሉ አገራት ከሚገኙት ዜጎቻችን ጭምር ነው፡፡ የልመና ጊዜ በሮ የደረሰው የውጭ ጉዳይ አሁን በቲውተር ከሚቀልደው ያለፈ ሊፈይድ አልቻለም፡፡ ካድሬም ብትሆን አይቀርልህም፡፡


በጊዜያዊ ጥቅም ከሆነማ ጣሊያንም ለባንዳዎቹ ከፍተኛ ጥቅም ሰጥታለችኮ፡፡ እነ ራስ ሀይሉ በወር 175 ሺህ ሊሬ ይከፈላቸው ነበር፡፡ የፋሽስቱን ስርዓት ያልተቃወመ ወጣት አሁን ኢህአዴግ ከሚያደርገው በላይ ተከፍሎታል፡፡ እናቶች፣ ካድሬ ቄሶችና ሌሎችም ኢህአዴግ አሁን ከሚያደርግላቸው በላይ ጣሊያንን እንዳይቃወሙ ጥቅማጥቅም ተሰጥቷቸዋል፡፡ በኋላ ግን በጅምላ ተጨፍጭፈዋል፡፡ እናም ይህን ኢትዮጵያውይ ያልሆነ መንግስት ኢትዮጵያዊ ማድረግ አይቻልም፡፡ በቃ! ከዚህ በላይ በደል መሸከም አንችልም፡፡ ከዚህ በላይ ባይተዋር መሆን አንፈልግም፡፡ ከዚህ በላይ ማንባት አንሻም፡፡ ኢህአዴግን በግልጽ በቃህ የምልበት የመጨረሻው ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡ አዎ! ኢትዮጵያዊ ባልሆነ መንግስት መገዛት ይብቃን!