ፍትሕ የሚያስፈልጋቸው የሕገወጥ ስደት ሰለባዎች


(ምንሊክ ሳልሳዊ)

በአሁኑ ጊዜ ሳዑዲ ዓረቢያ በስደት የነበሩ ከ100 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን አገራቸው ለመግባት በቅተዋል፡፡ አሁንም በርካታ ወገኖች የመሄጃ ጊዜያቸውን በማጎሪያ ጣቢያዎች ወይም በቤታቸው ሆነው እየተጠባበቁ ነው፡፡
ሰሞኑንም የሳዑዲ መንግሥት ኢትዮጵያዊያኑን ‹‹ለጊዜው ማቆያ ቦታዎቻችን ከመጠን በላይ ስለተጨናነቁና ሁላችሁንም ልናስተናግድ ስለማንችል በየቤታችሁ ሆናችሁ ድጋሚ ጥሪ እስክናደርግ ተጠባበቁ፤›› የሚል መልዕክት ‹‹ወደ አገራችን አሳፍሩን›› ለሚሉት ኢትዮጵያዊያን እያስተላለፈ ነው፡፡ በዜና ዘገባዎች ላይ የተጠቀሰው ቁጥር እነዚህን በቤታቸው ሆነው የሚጠባበቁትንም ያጠቃልል እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ የተረጋገጠ መረጃ ማግኘት አልቻልንም፡፡
ይሁንና ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ሲታይ፣ የተጠቀሰው ቁጥር አሁንም ገና የሚቀረው ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ በቅርቡ በጅዳ አካባቢ ማረፊያ ጣቢያዎች ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያዊን ቁጥር በጥቂቱ ከ20,000 በላይ እንደሆነ ተገምቷል፡፡ ከሃምሳ በሚበልጡ የተለያዩ ማጎሪያ ቤቶች ውስጥ የተሰበሰበው ሕዝብ ደግሞ ቢያንስ 20,000 ይሆናል፡፡ በየቤቱ የሳዑዲ መንግሥትን ዳግም ጥሪ የሚጠባበቀው በሪያድ፣ በጅዳ፣ በመካ፣ በደማምና በሌሎች ከተሞች የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ ደግሞ ለመቁጠር እጅግ የሚያስቸግር ነው፡፡
ከላይ የዘረዘርኩት እንግዲህ ይተልቅም ይነስም በከተሞች አካባቢ የሚኖረው መሆኑ ነው፡፡ በሌላው በኩል ደግሞ በየበረሃው በበግ፣ በፍየልና በግመል ጥበቃ ወይም በሌሎች ሥራዎች የተሰማራውና ለመገናኛ ብዙኃን ቅርበት የሌለው ኢትዮጵያዊ ቁጥሩ ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ አይቻልም፡፡ ሁሉም ለማለት ይቻላል፤ የየመንን ድንበሮች በመከራና በስቃይ ሕይወታቸውን፣ አካላቸውን፣ ሴትነታቸውንና ሰብዓዊ ክብራቸውን እየገበሩ፣ ካንዱ ቦታ የሚቀጥለው ቦታ የሚያደርሳቸውን የኮንትሮባንድ ትራንስፖርት ገንዘብ እስኪያሟሉ ይቆዩና ወደ ሚቀጥለው መዳረሻቸው ጉዞ የሚጀምሩ እንዳሉ በደንብ ይታወቃል፡፡ በሳዑዲ እንደሚታወቀው አንድ ሰው ከየመን ከምትዋሰነው የሳዑዲ ድንበር ከተማ ጀዛን አንስቶ በቀጥታ ሪያድ ወይንም ጅዳ ለመግባት ቢያንስ 1,000 የአሜሪካ ዶላር ስለሚፈጅ፣ በድንብር ከተሞች ያለው ፍተሻም ከረር ያለ በመሆኑ ማንም ስደተኛ በድንበር ከተሞች መቆየት አይፈልግም፡፡
(ምንሊክ ሳልሳዊ)
በዋና ዋና ከተሞች የሚኖር ሌላ አጋዥ ኢትዮጵያዊ ወገን ከሌለው ሁሉም አቆራርጦ መድረስ ነው የሚፈልገው፡፡ ይህም ከድንበር ከተማዋ ጀዛን ወደ ዋና ከተሞች ለመድረስ የሚፈጀውን ገንዘብ ለማሟላት ጉዞውን እያቆራረጡ ማድረግ የግድ ይላል፡፡ ለምሳሌ ከጀዛን ሪያድ ርቀቱ ወደ 1,800 ኪሎ ሜትር ገደማ ነው፡፡ ስለዚህ በዋና ከተሞች ወጪውን የሚሸፍንለት ወገን የሌለው ስደተኛ ይህንን 1,800 ኪሎ ሜትር ለመሸፈን ቢያንስ ቢያንስ ከስምንት ወር እስከ አንድ ዓመት ይፈጅበታል፡፡ አንድ ቦታ አንድ ወር ይሠራና ባገኘው ገንዘብ የተወሰኑ መቶ ኪሎ ሜትሮችን ይቀንስና ገንዘቡ ባደረሰው ቦታ ሌላ የእረኝነት ሥራ ይጀምራል፡፡ ከዚያም እንደመጀመሪያው እያደረገና እያቆራረጠ ዋና ከተሞች ይደርሳል፡፡
ስደተኞች ዋና ከተሞችን የሚመርጡበት ዋናው ምክንያት ደግሞ የተሻለ ክፍያ ፍለጋ፤ አነስተኛ ፍተሻና በርከት ያለ አቅርቦት ስላለ ነው፡፡ ለምሳሌ በጀዛን አካባቢ መንደሮች ለአንድ የጉልበት ሠራተኛ እረኛ የሚከፈለው ገንዘብ ከ100 ዶላር በታች ሲሆን፣ በሪያድ አካባቢ ደግሞ ላንድ ሙያ ለሌለው የጉልበት ሠራተኛ የሚከፈለው 500 ዶላር ይደርሳል፡፡ ታዲያ ጉዞውን ከጀዛን ከዓመት ወይም ከስድስት ወር በፊት የጀመረው ስደተኛ አሁንም መንገድ ላይ ነው ማለት ነው፡፡ እንዲያውም ባለፉት አሥራ ሁለት ወራት ባብዛኛው ለሥርዓት አልበኞች ጥቃት አብልጦ ሲጋለጥ የነበረው ስደተኛ እንዲህ ዓይነቱ ነበር፡፡ ካለፈው ዓመት አንስቶ በኢትዮጵያዊያን ላይ ሲሰነዘር የተስተዋለውና በየማኀበራዊ ድረ ገጾች ሲለቀቅ የነበረው ፎቶና ቪዲዮም ላይ የተመለከትናቸው ኢትዮጵያዊያን የመከራ ገፈት ቀማሾች እኚሁ መንገደኞች ናቸው፡፡
ምንም እንኳን በመንግሥታችን በኩል እየተደረገ ያለው ወገኖችን ወደ አገራቸው የማስገባት ጥረት የሚበረታታና የሚያስደስት ቢሆንም፣ ተደራሽነቱ አሁንም ለኔ እጅግ በጣም አጠያያቂ ነው፡፡ እንደ አገር ያሉትን ወገኖች በተቻለ መጠን ጠቅልለን እስካላወጣን ድረስ መሞታቸውን እንኳን የማናውቃቸው ኢትዮጵያዊያን ቁጥር እየጨመረ እንደሚሄድ የሚያውቀው አገር ቤት ያለው ቤተሰባቸው ብቻ ነው የሚሆነው፡፡
ለመሆኑ ይኼን ያህል ኢትዮጵያዊ ወገን በሕገወጥ መንገድ ከአገር ሲወጣ ለምን ተመልካች አልነበረም? በአፋር በረሃዎች ለግመል እረኞች የዒላማ መለማመጃ ሆኖ ሕይወቱ ያለፈውን፣ በጂቡቲ በረሃዎችና የባህር ዳርቻዎች በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ቱጃሮች ወንድና ሴት ሳይለይ ጾታዊና አካላዊ ጉዳት እየደረሰባቸው፣ የሚላስና የሚቀመስ እያጡ በረሃ ወድቀው የቀሩት፣ በሶማሊላንድ በረሃዎች እስከ ቦሳሶ ወደብ ድረስ እየተደበደቡ፣ እየተዘረፉ፣ እየተደፈሩና ክብራቸው እየተዋረደ ሕይወታቸው ያለፈው፣ ቀይ ባህር ሰጥመው ለአሳነባሪ እራት የሆነው፣ ዕድል ቀንቶአቸው የመን ደርሰው በየመን ሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ከባህር ጀምሮ እንደ ሽቀጥ ካንዱ አዘዋዋሪ ወደሚቀጥለው አዘዋዋሪ ሲቸበቸቡ፣ በሳዑዲ ከተሞች የሚኖር አንድ ወገን በችግር ሠርቶ ያጠራቀመውን ገንዘብ ከፍሎ አለዚያም አገር ቤት የሚኖር ቤተሰብ መሬቱን ሸጦ ወይንም አከራይቶ በሚልከው ገንዘብ ነፍሱ ያልተዋጀችለትና በሚነድ ፌስታል ተለብልቦ፣ በሚስማር ተቸነካክሮ፣ በስለት ተተልትሎ፣ በብረት በትር እንደ እባብ ተቀጥቅጦ፣ በፕላስቲክ ገመድ ደሙ እስኪቆም ድረስ ብልቱና የዘር ፍሬውን ታስሮ እየተንጠለጠለና እጆቹን የፊጥኝ ተጠፍሮ፣ በጥይት አረር አሮ፣ ያውም በገዛ ወገኖቹ ኢትዮጵያዊያን ከየመን በረሃዎች እስከ መንፊሃና ነሲም በተዘረጋው የደም ንግድ ደሙ ደመ ከልብ የሆነበትን ኢትዮጵያዊ ከቶ ማን ሊቆጥረው ይችላል? በጀማ እየተደፈሩ ሕይወታቸው ያለፈ ኢትዮጵያዊያት እህቶችንስ ማን ይቆጥራቸዋል?
መቼም አንዱን ካንዱ ማበላለጥ ቢያስቸግርም እንደ ከብት ኢትዮጵያዊያን የተቸበቸቡባቸውና የታረዱባቸው የስደተኛ ንግድ ሸሪኮች ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ማወቅ ደግሞ ሐዘኑን የከፋ ያደርገዋል፡፡ ከየመን በረሃዎች አንስቶ በሳዑዲ ዋና ዋና ከተሞች ድረስ የተዘረጋው የግፍ ንግድ ምንም እንኳን በየመናውያኑና በሳዑዲያውያኑ ቢመራም በየመን በረሃዎች ውስጥ የነበሩት ገራፊዎችና በየከተሞቹ የሚገኙት ገንዘብ አቀባባዮች ግን በሙሉ ኢትዮጵያዊያን ነበሩ፡፡
ምን ይኼ ብቻ? በኢትዮጵያ ካሉ ከተሞችና የገጠር ቀበሌዎችስ እነኚህን ተስፈኞች እየደለሉና እያባበሉ ወደ ሞት የነዷቸውስ እነማን ነበሩ? ‹‹የሌላ አገር ዜጋ ኢትዮጵያ ውስጥ በየመንደሩ ገብቶ ዜጎችን ለስደት መለመለ›› ብሎ የሚከራከር ያለ አይመስለኝም፡፡ በዚህ የምልመላ ሥራ ላይ ለመሳተፍ ደግሞ የግድ ባይሆንም የተመልማዩ ወገን አካባቢ ነዋሪ መሆን ያስፈልጋል፡፡ ከዚያ ባሻገር ደግሞ በአዲስ አበባ ዋና ዋና መንገዶች ለዘመናት ተለጥፈው ስናነባቸው የከረምናቸው ‹‹ወደ ዓረብ አገር በነፃ እንልካለን›› የሚሉት ማስታወቂያዎች እማኞች ናቸው፡፡
በዚህ ጹሑፌ ትኩረት ላደርግበት የፈለግኩት እነዚህን የዚህን ሁሉ ኢትዮጵያዊ ነፍስ የበሉትንና ለዚሁ ሁሉ መከራ የዳረጉትን ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ነው፡፡ እንዲያውም ከወር በፊት አዲስ አበባ ሄጄ የታዘብኩት ነገር ቢኖር፣ አንዳንድ ኤጀንሲዎች ቢሯቸውን ወደ ካርቱም ማዛወራቸውን ነው፡፡ ዜጎችን በመመርያ ወደ ካርቱም ከዚያም ወደ ዓረብ አገር ኤክስፖርት ለማድረግ!
አይግረማችሁና በሳዑዲ የዚህ የብዙዎችን ሕይወት የቀጠፈውንና ስንቶችን የአካል ጉዳተኛና የአዕምሮ በሽተኛ ያደረገው ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ገንዘብ አስተላላፊዎች፣ ሱቆቻቸውን እየዘጉና ሚኒባሶቻቸውን እያቆሙ ከነዚሁ መከረኞች ጋር ወደ አዲስ አበባ እየተሳፈሩና የመሳፈሪያ ጊዜያቸውን እየጠበቁ ነው፡፡ በየመንም ያሉት ኢትዮጵያዊያኑን ሲያሰቃዩ የነበሩት ኢትዮጵያዊያንም እንዲሁ፡፡ አገር ቤት ያሉት ደላሎችና ኤጀንሲዎች ባለ በርካታ ፎቆችና መኪኖች ባለቤት መሆናቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡
ታዲያ እነዚህን ሁሉ ወንጀለኞች እያወቅናቸውና በመካከላችን አቅፈናቸው እየኖርን፣ ወገንን ለባርነትና እንደ መኪና መለዋለጫ አካላቸውን እየተተለተሉ በመቸብቸብ ንግድ ሀብትና ንብረት ያለማንም ከልካይ አፍርተው በእነዚህ ተበዳዮች አገር ሲንፈላሰሱ እያስተዋልን ‹‹ይኼ ነገር ገነ አይቀጥልም›› ብለን የምናስብ ከሆነ መቼም ምን እንደምንባል አላውቅም፡፡ እስኪ ለመሆኑ የትኛው ደላላ ወይም ኤጀንሲ ነው ለኮፍ ለኮፍ ሳይሆን ለተከሰተው የሕይወት መጥፋት፣ ያአካል መጉደልና ያአዕምሮ መታወክ ተመጣጣኝ ቅጣት የተቀጣና ተመጣጣኝ ካሳ የካሰ?
ተበዳዮች ደማቸውንና የሚያስመልስላቸውና በደላቸውን የበላይ አካል በጠፋ ጊዜ ራሳቸው በራሳቸው ፍትሕ ማግኘታቸውን ትናንት ወይም ዛሬ የተጀመረ ሀቅ አይደለም፡፡ ለዘመናት የኖረና አሁንም የሚኖር ነው፡፡ ዘመናችን በከሰተው በዚህ የባሪያ ፍንገላና የሰው ልጅን ለዕርድ የማቅረብ አሰቃቂ ወንጀል በቀጥተኛም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ግንኙነት ያላቸውና በዚሁ ኢሰብዓዊ ወንጀል እጃቸውን በንፁኃን ደም ያጠቡ ደላሎች፣ የሕክምና ተቋማት፣ ኤጀንሲዎች፣ በየመን የነበሩ አሰቃዮችና በሳዑዲ የነበሩና የሚገኙ ገንዘብ አስተላላፊ ግለሰቦች ከያሉበት ታድነው የሚገባቸውን ፍርድ እስካላገኙና ወደፊትም በዚህ ዓይነቱ አሰቃቂ የደም ንግድ ለመግባት ላሰቡ ሰዎች መቀጣጫ የሚሆንና በቂ ቅጣት ካልተቀጡ በቀር፣ አሁን ያየነው ዓይነት አሰቃቂ ክስተት ላለመከሰቱ ምንም ዓይነት ዋስትና የለም፡፡ እዚህ ላይ በቅርቡ አሜሪካ ውስጥ ኢትዮጵያዊቷን ልጅ እስርበው ለሞት አብቅተዋታል በሚል ወንጀል የተከሰሱት አሜሪካውያን ባልና ሚስት፣ ሦስት ሴቶችን ለዓመታት እቤቱ አግቶ የወሲብ ጥቃት ሲፈጽም ነበረ የተባለው አሜሪካዊ ላይ የተበየኑትን ብይኖች ስናስታውስ ‹‹መቼ ይሆን በኛስ አገር ተበዳይ ፍትሕ የሚያገኘው?›› ብዬ እንድጠይቅ ብቻ እገደዳለሁ፡፡
 ጸሐፊው ነዋሪነታቸው በሳዑዲ ዓረቢያ ሪያድ ከተማ  ነው፡፡ (ምንሊክ ሳልሳዊ)

የነገ ታህሳስ 3 ቀጠሮና የትግላችን የወደፊት አቅጣጫ!

የነገ ታህሳስ 3 ቀጠሮና የትግላችን የወደፊት አቅጣጫ!
ረቡእ ታህሳስ 2/2006

በማዕከላዊ ከህግ አግባብ ውጪ ለወራት ኢሰብዓዊ የሆነ ስቃይና ቶርቸር ሲፈጸምባቸው በቆዩት ኮሚቴዎቻችን ላይ የተከፈተውን የሀሰት ክስ በማየት ላይ ያለው ችሎት የዐቃቤ ህግ ምስክሮችንና መረጃዎችን ከተመለከተ በኋላ ‹‹ተከሳሾቹ ከክሱ ነጻ ናቸው ወይስ መከራከር ይጠበቅባቸዋል›› የሚለውን ብይን ለማሰማት የሰጠውን የህዳር ቀጠሮ ኢመደበኛ በሆነ መልኩ አዛውሮ ለነገ ታህሳስ 3/2006 ቀጠሮ የያዘ ሲሆን ህዝበ ሙስሊሙ ደግሞ ‹‹የሚፈረደው በኮሚቴዎች ላይ ሳይሆን በእኛ ነው! በእነሱ መታሰር ታስረናልና ችሎቱ እደህዝብ የሚፈርድብንን እንጠብቃለን›› እያለ ይገኛል፡፡

መንግስት በእፎይታው ጊዜ ሲፈጽም የቆያቸው ተግባራት ሙስሊሙ ህብተሰብ የመንግስት ፍላጎት ምን እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ እንዲያይ ያስቻለው ሲሆን ቀጣይ የትግሉ አቅጣጫ ምን መምሰል እንዳለበትም ያመላከተ ነበር፡፡ የእፎይታው ወቅት እንቅስቃሴው እጁን አጣጥፎ ከመንግስት የሚመጣን መፍትሄ ብቻ ሲጠብቅ የነበረበት ሳይሆን ራሱንም ቆም ብሎ የገመገመበት፣ መንግስት በተገቢው መንገድ ምላሽ ባይሰጥ ቀጣይ የትግሉ አቅጣጫ ምን መሆን እንዳለበት አማራጮችን የፈተሸበት ነበር፡፡ በድምጻችን ይሰማ አማካኝነት በተደረገው የህዝብ አስተያየት ስበሰባ በርካታ ጠቃሚ አቅጣጫዎች የተጠቆሙ ሲሆን በእነዚሁ አቅጣጫዎች ላይ ሰፊና ጥልቅ ውይይቶች የተደረጉ ሲሆን የተለያዩ አማራጭ አቅጣጫዎችና ማስፈጸሚያ ስልቶችም ጭምር ተዘጋጅተው እየተጠናቀቁ ይገኛል፡፡ 

ያለጥርጥር የዚህን ህዝባዊ እንቅስቃሴ የወደፊት አቅጣጫ የሚወስኑ በርካታ ጉዳዮች አሉ፡፡ መንግስት በእፎይታው ጊዜ ከተከተለው መንገድ በተጨማሪ ነገ ታህሳስ 3 በመሪዎቻችን ላይ የሚሰጠው ብይን ደግሞ ለዚህ ትልቅ ግብዓት ይሆናል፡፡ መንግስት የእስከዛሬውን ግትር አቋሙን ገፍቶ እየቀጠለ መሆን አለመሆኑንም በማያሻማ ሁኔታ ያሳያል፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብም ቢሆን ኮሚቴዎቻችንን በሙሉ በነጻ ከማሰናበት ውጭ ያለን ማንኛውም ውሳኔ አይቀበልም፡፡ እንደተለመደው ኮሚቴዎቻችንን በማን አለብኝነት በቀጠሮ ማጉላላት ወይም ጥፋተኛ ብሎ መወሰን መንግስት እየተከተለ ያለውን ፀረ-ኢስላም ፖሊሲ ገፍቶ መቀጠሉን በድጋሚ የሚያረጋግጥ ተግባር ስለሚሆን ይኸው ውሳኔ እንቅስቃሴያችን የወደፊት ጉዞውን አስመልክቶ ካስቀመጣቸው አማራጭ አቅጣጫዎች የመምረጥ ሂደት ላይ ጉልህ ሚና ይኖረዋል!!!

ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ነጻነት በህግ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው::

 

ኮሚቴዎቻችን አሸባሪ እና አክራሪ ሳይሆኑ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት የተገሩ የሃይማኖት ምሁራን ናቸው::ምንሊክ ሳልሳዊ:- የወንድሞቻችን የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በገዛ አገራቸው አፈራቸው እና በነጻነታቸው ላይ የተቃጣ አደገኛ መንግስታዊ ሴራ ካለተግባራቸው ተወንጅለው የህሊና እስረኛ ከሆኑ ጀምረው ድምጻችንን እያሰማን እንገኛለን ;;አሁንም እስከመጨረሻው ድረስ ነጻነታቸው ተረጋግጦ ጥያቄቸው እንዲመለስላቸው አጥበቀን በመጠየቅ በኢህኣዴግ መራሹ መንግስት ላይ ሕዝባዊ ጫናዎቻችንን ከመፍጠር ወደኋላ የምንልበት እና የምናፈገፍግበት አንዳችን ምክንያት ስለሌለ የሙስሊሙ ወገናችን መብት በይፋ የሃይማኖት ነጻነት በአደባባይ በተግባር እንዲውል አጥብቀን እንጠይቃለን::

የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ለመንግስት ያቀረቡት ጥያቄ ግልጽ እና የማይገሰስ የመሰረታዊ ዲሞክራሲያዊ መብቶች ጥያቄ መሆኑ እየታወቀ እና በመንግስታዊ ስርኣቱ እውቅና ከተሰጠው በኋላ የፖለቲካ ዝማሬውን በሃይማኖት ውስጥ አጥልቆ ማስገባት የሚፈልገው የአብዮታዊው ዲሞክራሲው ባላባት ኢሕኣዴግ ባልታሰበ እና ባልተጠበቅ ሁኔታ ንፁሃኑን በአሸባሪነት ፈርጆ በእስር በማንገላታት ትክክለኛውን ህጋዊ ፍርድ እንዳያገኙ በማድረግ ፖለቲካዊ ውሳነ ለመስጠት አሰፍስፏል::

የኢትዮጵያውያን ሙስሊም ወገኖቻችን ትግል የፖለቲካ ጥያቄ ያለው በማስመሰል የተለያዩ ፕሮፓጋንዳዎችን በመንዛት ተግባር የተሰማራው ስርኣት የኮሚቴዎቻችንን በግፍ ማሰሩን ተከትሉ ሙስሊሙን ህብረተብ በማፈስ በመግደል በማሰር በማንገላታት በመዝረፍ እና ተመሳሳይ ችግሮችን አስከፊ በመፈጸም በህዝቦች ላይ ከአንድ መንግስት ነኝ ከሚል አስተዳደር የማይጠበቅ ሽብር በመፈጸም ላይ ይገኛል::በህገወጥ መንገድ ያስቀመጣቸውን ታማኝነታቸው ለፓርቲ ተጠሪነታቸው ለአሸባሪ ባለስልጣናት የሆኑ ዳኞችን በመጠቀም በኮሚቴዎቻችን ላይ የፖለቲካ ውሳኔ ለመስጠት ታህሳስ 3 2006 አውሬያዊ አፉን ከፍቶ ንጹሃንን ለመዋጥ ተዘጋጅቶ ይገኛል::

ታህሳስ 3 2006 በንጹሃን ላይ ሊሰጥ የታሰበው የፖለቲካ ፍርድ ዘር ቀለም ሃይማኖት ሳይለይ በ80 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሊደረግ የታቀደውን ፖለቲካዊ ጣልቃገብነት ያለበትን ፍርደገምድልነት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በይፋ ይቃወመዋል::
ኮሚቴዎቻችን እያንዳንዳቸው በኢትዮጵያዊ ጨዋነት የተገሩ እና ምንም አይነት የሽብር ተግባር ያልፈጸሙ መሆናቸውን ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን አለም ያረጋገጠው ጉዳይ ስለሆነ እንዲሁም እነሱን ተከትሎ በየእስር ቤቱ የታጎሩ ወገኖቻችን ሙስሊሞች ሁሉ በነጻ እንዲለቀቁ እና ሃገሪቱ አላት በተባለው ህገመንግስት መሰረት ነጻነታቸው እንዲከበርላቸው አጥብቀን እናሳስባለን::በሀገሪቱ እስርቤቶች የታሰሩ ሙስሊም ወንድሞቻችን ካለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቀ በህግ መስመር መሰረት ደግመን አጥብቀን እንጠይቃለን:;ምንሊክ ሳልሳዊ
ድል ለመላው ኢትዮጵያውያን!!!

መፍትሄ ያጣው ህዝብን ተስፋ ያስቆረጠው የፍትህ አካላቱ ፖለቲካዊ ንቅዘትምንሊክ ሳልሳዊ - ላለፉት ሃያ አመታት በሃገሪቱ የተንሰራፋው የእሓዴግ መራሹ መንግስት የፍትህ ስራቱ እንዲቀበር እና በፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እንዲሞት በማድረግ ህዝቦች በፍትህ አካላት ላይያላቸው እምነት ተስፋ እንዲያጣ አድርጓል::የፍትህ አካላት ለሃገሪቱ ዜጎች ማገልገል ሲገባቸው ለጥቂት ባለስልጣናት እና ለጥቅማ ጥቅም በመገዛት ህጎች እንዲፋለሱ በማድረግ ላይ ይገኛሉ :;ሊሻሻል እና ሊለወጥ በማይችልበት ደረጃ ላይ የደረሰው ይህ የፍትህ አካላቱ ንቅዘት አለኝታነቱን እና ታማኝነቱን በማጉደል ከፍተኛውን ወንጀል በመፈጸም ላይ ይገኛል::

በጥቅም የነቀዙት የፍትህ አካላቱ በሙስና ላይ እርምጃ እንዲወስዱ መቀመጣቸውን ዘንግተው በፓርቲ ካድሬነት ብቻ የሰለጠኑ እና ታማኝነታቸው ለአንድ አካል እና ተጠሪነታቸውም ለገዢው በመሆኑ ህዝብ ትክክለኛ ፍትህ እንዳያገኝ በማድረግ ላይ ሲገኙ ይህንንም ላላቸው የፓርቲ ቀረቤታ በማናለብኝነት በሙስና ተዘፍቀው ፍትህ በማጓደል ህገመንግስቱን እና ተከታይ ህጎችን እያጣመሙ በመተርጎም የዜጎች መንፈስ እንዲበላች እና በፍትህ ሂደት ላይ እምነት እንዳይጣል እያደረጉ ይገኛል:: የፖለቲካ ታማኝነታቸውን መከታ በማድረግ ከፍትህ ማጓደል በተጨማሪ በጉቦ ቅሌት ላይ ተሰማርተው የሙስና ሰለባ የሆኑት የፍትህ አካላቱ በሚያገኙት ጥቅማጥቅም መዝገቦችን በመዝጋት እና ሰነዶችን በማጥፋት በተዘዋዋሪ ፍትህ ፈላጊዎችን በህገወጥ መንገድ በሃይል በማስደንገጥ በአጭሩ ሊፈቱ የሚችሉ እና ውስኔ የሚገባቸውን ጉዳዮች ቀጠሮ በማስረዘም እና የፍርድ ውሳኔዎችን በማዛባት ፍትህ ከቁጥጥር ውጪ ወቶ ህገወጥነት እንዲስፋፋ አድርገዋል::

በዳኝነት ወንበር ላይ መቀመጥ የፖለቲካ ደላልነት የሚመስላቸው የእሕኣዴግ ካድረዎች ካለምንም በቂ የህግ እውቀት በፖለቲካ ፓርቲ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ፕሮግራም ተገርተው የገረፍ ገረፍ ህግን ሰልጥነው በህግ ባለመብሰል ካለ አቅማቸው ወንበሩን ስለያዙት ከፍተኛ የፍትህ መበላቸት በመስፋፋቱ ህዝቦች ላይ ከፍተኛ የስነ ልቦና ችግር እያደረሱ ነው:: እነዚህ በህግ እውቀት የአቅም ማነስ የተጠለፉ የፖለቲካ አገልጋዮች ተቆጣጣሪ አካል ሳይሆን ፍርድ እንዲያዛቡ ያስቀመጣቸው አካል የስልታን እድሜው እንዲረዝም ምንም አይነት እርምጃ ባለመውሰዱ ዜጎችን እያስለቀሱ ይገኛሉ::

ለፍትህ አረም የሆኑት የኢሕኣዴግ ባለስልጣናት እጅግ በወረደ መልኩ ከአንድ ህዝብ አስተዳድራለሁ ከሚል አካል በማይጠበቅ አካሄድ በፍትህ ስርኣቱ ላይ ጣልቃ በመግባት ሕግ አውጪው፣ ሕግ አስፈጻሚውና ሕግ ተርጓሚው ነፃ ሆነው እንዳይንቀሳቀሱ እንዳይሰሩ በየፍርድ ቤቱ ዳኞች ላይ በስልክ እና በተለያዩ ዘደዎች ትእዛዝ በማስተላለፍ አደገኛ ሽብር እየፈጸሙ ይገኛሉ::የፖለቲካ ጣልቃ ገብነትን እና ጫና በመሸሽ ሽብር ስጋት እና ፍርሃት ስለተፈጠረባቸው ቁጥራቸው ብዙ የሆነ እና በቂ የህግ እውቀት ያላቸው ዳኞች ተሰደዋል-ከስራ ተባረዋል-በገዛፍቃዳቸው ስራ ለቀዋል-ታስረዋል..::ይህ ማስፈራራት እና ሽብር በፍትህ አካላት ላይ የሚፈጠረው በባለስልታናት ብቻ ሳይሆን ባለስልጣናቱን መከታ ባደረጉ ሰዎችም ጭምር ነው::ባለስልጣናቱ በየፍርድ ቤቱ ዳኛ አድርገው የመደቧቸውን ካድሬዎቻቸውን በማዘዝ በህሊና እና በፖለቲካ እስረኞች ላይ ካለምንም ማስረጃ እንዲፈረድ የወዳጅ ዘመዶቻቸው መዝገብ እንዲዘጋ ሰነድ እንዲበላሽ እንዲቃጠል በማድረግ ጫና እየፈጠሩ የፍትህ ስርኣቱ እንዲነቅዝ አድርገውታል::

አቶ ሙሐመድ ኢብራሒም ማእከላዊ እስር ቤት አስገብቶ መግደሉ ለመንግስቱ አሳፋሪ ከመሆኑም ባሻገር የስርዓቱን መላሸቅ አመላካች ነዉ

አቶ ሙሐመድ ኢብራሒም ማእከላዊ እስር ቤት ዉስጥ በደረሰባቸው ድብደባ ህይወታቸዉ ማለፉ፤ ሆድ-እቃቸዉ ተከፍቶ ኩላሊታቸዉ መሰረቁ ታወቀ 

“አስክሬን ምንሊክ ሆስፒታል ሄደን እንድንወስድ ስልክ ተደወለልን፤ ለሞቱ ከደነገጥነዉ በላይ አስክሬኑን ስንመለከት ፍጹም ተረብሸናል፤ ከአዉሬ አፍ የተረፈአስክሬን ነበር ሚመስለዉ…ሰዉነቱ ተቦጫጭቋል!” ጓደኞች


 በአዲስ አበባ ዉስጥ በቦሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪ የነበሩት አቶ ሙሐመድ ኢብራሒም ቀደም ሲል በጥቅምት 4/2006 በአካባቢዉ ላይ ፈንድቶ ከነበረዉ ቦንብ ጋር በተያያዘ መልኩ ለምርመራ ማእከላዊ እስር ቤት መግባታቸዉ እና በማእከላዊ ቆይታቸዉ ምግብ እንዳይገባላቸዉ ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸዉ መከልከሉም ለማወቅ ተችሏል።
እንደ አቶ ሙሐመድ ጓደኛ አገላለጽ ግለሰቡ ለተጠረጠሩበት ወንጅል የሚያበቃቸዉ ጉዳይ ባይኖርም፤ከገቡበት ማእከላዊ እስር ቤት በደረሰባቸዉ ከፍተኛ ድብደባ በህይወት መዉጣት አልቻሉም።
ለሐያ ዘጠኝ ቀናት ማእከላዊ እስር ቤት የታሰሩት አቶ ሙሐመድ ምን ያህል ድብደባ እንደደረሰባቸዉ ባይታወቅም ጭንቅላታቸዉ በጣም መጎዳቱን፣ሰዉታቸዉ እንደበለዘ፣ብዙ ሰንበሮች መታየታቸዉ፣ሆድ እቃቸዉ ተከፍቶ ኩላሊታቸዉ መሰረቁን ለአስራ ሁለትአመታት የሚያዉቋቸዉ ጓደኛቸዉ በሐዘን ይገልጻሉ።የዱር አዉሬ ቦጫጭቆ የገደለው ይመስላል በማለት ሁናቴዉን የሚገልጹት ጓደኛ ከመንግስት አካላትም ይሁን አስክሬኑ ከመጣበት የሚኒሊክ ሆስፒታል ስል አቶ ሙሐመድ አሟሟት የተሰጠ መረጃ አለመኖሩን፤ በደም በተጨማለቀ ከፈን የተከፈነ አስክሬን ብቻ መመለሱን ገልጸዋል።
ቤተሰቡ ጉዳዩን ለሰብአዊመብት ተሟጋች ለሆኑ ድርጆቶች እንዳያመለክት ከፍተኛ ዛቻ ደርሶበታል፤በቅርበት የሚያዉቋቸዉ እንኳ በሞታቸዉ ከማዘን በስተቀር ስለ አሟሟታቸዉ ከፍርሃት የተነሳ መናገር አይችሉም በማለት የሚያስረዱት ጓደኛቸዉ ሁሉም ለሞቱ ከደነገጠዉ በላይ አስክሬኑን በማየት ተሸማቋል ይላሉ።
በጥሩ ስነምግባራቸዉ የሚታወቁት አቶ ሙሐመድ ኢብራሒም ሐማኖትን ተግባሪ፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪ ከመሆን በስተቀር አገርን ወገንን ሊጎዳ በሚችል የአሸባሪ ተግባር የሚጠረጠሩ አይደልም በማለት በሐዘን የሚናገሩት ጓደኛ ሟቹ የሰባት ልጆች አባት እንደነበሩ ቤተሰቡም ለአደጋ መጋለጹንም አስረድተዋል።
በጥቅምት 4/2006 መንግስት በቂ መረጃ ለህዝብ ማቅረብ ባልቻለበት፤ የመንግስት ደህነነቶች አለም አቀፋዊ ትኩረትን ለመሳብና ፖለቲካዊ ጥቅምን ለመጎናጸፍ በቦሌ ክፍሌ ከተማ አደርሰዉታል ተብሎ በሚነገረዉ የቦንብ ፍንዳታ፤ ማመካኛን ለማግኘት የሱማሌ ብሔር ተወላጅ የሆኑትን የአቶ ሙሐመድ ህይወትን መንግስት መስዋዕት አድርጓል በማለት አስተያያት የሚሰጡ ወገኖች አሉ።በትላንትና እለትዉ የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን በጅጅጋ ከተማ ድረስ ባሸበረቀ መልኩ አከበርኩ ለሚለዉ መንግስት፤ የአገሩን ዜጋ በብሔር ነጥሎ ማእከላዊ እስር ቤት አስገብቶ መግደሉ ለመንግስቱ አሳፋሪ ከመሆኑም ባሻገር የስርዓቱን መላሸቅ አመላካች ነዉ የሚሉም አሉ።
የአቶ ሙሐመድ ኢብራሒም ታስሮ ለህልፈት መብቃት፤ የሆድ እቃቸዉ ተቀዶ የኩላሊታቸዉ መሰረቅ ከፍተኛ ምርመራ የሚያሻዉ ቢሆንም፤በሟች አስክሬን ላይ የተፈጸመው ወንጀል ስርዓቱ በህይወት ባሉ ብቻ ሳሆን በሙታንም ላይ ግፍ እንደሚፈጽም የሚያረጋግጥ ነዉ፤ በሐሰት አስሮ በመደብደብ፣በመግረፍ፣እስር ቤት ዉስጥ ከማሰቃየት አልፎ፤ ታሳሪዎች እስር ቤት ዉስጥ ሲሞቱ ሆድ እቃ ተከፍቶ የሰዉነት አካል መቸርቸር ተጀምሯልና!.. ኢትዮጵያ ወዴት እያመራች ነዉ? የሚለዉ ጥያቄ የብዙሐኑ ነዉ።

በአፈና ትግልን ማስቆም አይቻልም::

አይቶ ጸጋይ በርሄ ሆይ - የታፈነው ጌታነህ ባልቻ በአስቸኳይ እንዲለቀቅ እንጠይቃለን::

ወያኔ ኢሕኣዴግ ይህንኑ የአፈና ስራውን በመቀጠል በአይቶ ጸጋይ በርሄ በሚመራው የአፈና ቡድን እና ረሱን መንግስት አድርጎ በሚወስደው የማፊያ ሴረኛ ደህንነቶች እየተመራ የተለያዩ እኩይ ተግባራትን በመፈጸም ላይ ይገኛል:: የወያኔ ኢሕኣዴግ ጁንታ እንደሱ ማሰብ ያልቻሉት በጥቅማጥቅም የማይደለሉትን ህዝባዊነትን መሰረት አድርገው ለሃገር እና ለወገን ነጻነት የሚታገሉትን የፖለቲካ ፓርቲ አባላትም ማፈን የጀመረው ገና ሲፈጠር ጫካ እያለ ነው::ከማፈንም ባለፈ በማሰቃየት በመግደል በማጉላላት በማሰር ተስተካካይ ያልተገኘለት አምባገነን እና አሸባሪ መሆኑ ምስክር የማያሸው እና እየታየ ያለ ነገር ነው::

በጫካው ትግል ወቅት የራሱን እና የሌሎች ፓርቲዎችን ታጋዮች ካለርሕራሄ ሲበላ የነበረው የአብዮታዊ ዲሞክራሲው ነብር የሃገሪቱ ስልጣን ከተቆጣጠረ ጀምሮ በአደባባይ እንደ አሰፋ ማሩ የመሳሰሉት በመግደል እንዲሁም የኢሕኣፓ ጀግኖችን አፍኖ እንደ ባዶ ሽድሽተ እና አለባቸው ጫካ እስር ቤት ውስጥ ካለፍርድ በጭካኔ በማሰቃየት ላይ ይገኛል:: እንዲሁም የተለያዩ ዜጎችን ከቤታቸው ከመንገድ እና ከስራቸው ቦታ በማፈን የት እንዳደረሳቸው አይታወቅም::

ወያኔ ኢሕኣዴግ ይህንኑ የአፈና ስራውን በመቀጠል በአይቶ ጸጋይ በርሄ በሚመራው የአፈና ቡድን እና ረሱን መንግስት አድርጎ በሚወስደው የማፊያ ሴረኛ ደህንነቶች እየተመራ የተለያዩ እኩይ ተግባራትን በመፈጸም ላይ ይገኛል:: አይቶ/አለቃ ጸጋይ የሚመሩት ይህ የደህንነት ቡድን ሰላማዊ ሰልፎችን በማገድ ተሰላፊዎችን በማስደብደብ ከፍተኛ ባለስልጣናት የማያውቁትን ትእዛዝ በመስጠት ሃገሪቱን እየበጠበጠ ይገኛል::

ከቅዳመ ህዳር 26 2006 ጀምሮ በደህንነቶች ታፍኖ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ የአደረጃጀት ጉዳይ ሃላፊ ጌትነት ባልቻም የዚህ ቡድን ሰለባ ነው:: ስለዚህ ይህ የሃገሪቱን ለውጥ ጠያቂዎች በማፈን እያሰቃየ የሚገኘው የደህንነት ቡድን ያፈነውን ጌትነት ባልቻን በ24 ሰአት ውስጥ በአስቸኳይ እንዲለቅ አጥብቀን እንጠይቃለን::