በዜጎች ላይ የሚፈጸመው የባለስልጣናት ግፍ እና እብሪት አላባራም !!!

‹‹ከአገር እንድወጣ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶኛል›› አቶ አስመላሽ ሀዲሽ ወልዱ


‹‹ከአገር እንድወጣ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶኛል››  አቶ አስመላሽ ሀዲሽ ወልዱ

የዛሬው ‹‹ምን እየሠሩ ነው?›› ዓምድ እንግዳችን አቶ አስመላሽ ሀዲሽ ወልዱ ይባላሉ፡፡ ተወልደው ያደጉት በትግራይ ክልል አጋሜ አውራጃ አዲግራት ከተማ ውስጥ ነው፡፡
ትምህርታቸውን እስከ ዘጠነኛ ክፍል በተወለዱበት አዲግራት ከተማ ተከታትለው፣ ወደ አሰብ ራስ ገዝ በመጓዝ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል፡፡ የደርግ መንግሥት መውደቅን ተከትሎ በ1983 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ ከተማ መምጣታቸውን የሚናገሩት አቶ አስመላሽ በንግድ ሥራ ተሰማርተው ስኬታማ ሥራ እየሠሩ የነበሩ ቢሆንም፣ ባልታሰበ ድንገተኛ ገጠመኝ ከፍተኛ ችግር ውስጥ መውደቃቸውን ተናግረዋል፡፡ ስለገጠማቸው አስቸጋሪ የሕይወት ፈተናና አሁን ስላሉበት ሁኔታ ታምሩ ጽጌ አነጋግሯቸዋል፡፡
ሪፖርተር፡- ወደ አዲስ አበባ የመጡት መቼ ነው?
አቶ አስመላሽ፡- በ1983 ዓ.ም. ነው የመጣሁት፡፡
ሪፖርተር፡- አዲስ አበባ ከመጡ በኋላ የተሰማሩበት የሥራ መስክ ምን ነበር?
አቶ አስመላሽ፡- አዲስ አበባ ከመጣሁ በኋላ የአስመጭና ላኪነት ፈቃድ በማውጣት በንግድ ሥራ ተሰማራሁ፡፡
ሪፖርተር፡- ምን ዓይነት የንግድ ሥራዎችን ነበር የሚያስመጡትና የሚልኩት?
አቶ አስመላሽ፡- የማስመጣው ጨርቃ ጨርቆችንና የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦችን ነበር፡፡ ይኸንን የንግድ ሥራ ስሠራ በመንግሥት በኩል የሚጠበቅብኝን ግብርም ሆነ ሌሎች የንግድ ሥራው የሚጠይቀውን ግዴታዎች እየተወጣሁ ነበር፡፡
ሪፖርተር፡- በዚህ የንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩት እስከመቼ ነበር?
አቶ አስመላሽ፡- ከ1984 ዓ.ም. እስከ 1991 ዓ.ም. ድረስ ሠርቻለሁ፡፡ ከ1991 ዓ.ም. በኋላ ወደሌላ ሥራ ተዘዋወርኩ፡፡
ሪፖርተር፡- ምን ዓይነት ሥራ ለወጡ?
አቶ አስመላሽ፡- ሥራ የመለወጥ ሳይሆን ፣ ያው የንግድ ሥራ ሆኖ ሙሉ በሙሉ በላኪነት ብቻ መሥራት ጀመርኩ፡፡ በኢትዮጵያ የሚመረቱ ሸቀጣ ሸቀጦችን ብቻ መላክ ጀመርኩ፡፡ የግብርና ውጤቶችንና ማዕድን መላክ ጀመርኩኝ፡፡
ሪፖርተር፡- የግብርና ውጤቶችን ሲሉ ምን ዓይነት የሰብል ምርቶችንና ማዕድን መላክ የጀመሩ?
አቶ አስመላሽ፡- ከማዕድን እጣን፣ ከጥራጥሬ ዘሮች ሁሉንም ዓይነትና እንጨት እልክ ነበር፡፡
ሪፖርተር፡- እንጨት እንዴት ነው የሚልኩት?
አቶ አስመላሽ፡- የባሕር ዛፍ እንጨት ነው የምንልከው፡፡ በአንድ አካባቢ ለልማት ተብሎ የሚቆረጥን ባሕር ዛፍ ወይም አልምቶ ከሚሸጥ እገዛና፣ ወደ ውጭ እልካለሁ፡፡
ሪፖርተር፡- እንጨቱ በምን ዓይነት ሁኔታ ተዘጋጅቶ ነው የሚላከው? የትኞቹስ አገሮች ናቸው የሚገዙት?
አቶ አስመላሽ፡- ዋና ገዢ አገር የመን ነች፡፡ እንጨቱን አድርቀን በቁመቱ ሳይቆራረጥ አዘጋጅተን እንልከዋለን፡፡ እነሱም የሚጠቀሙበት በአብዛኛው ለወይን እርሻ ነው፡፡ ማለትም፤ የወይን ተክላቸው በመሬት ላይ ሲተኛ በተለያዩ ነገሮች ይበላሽባቸዋል፡፡ ይኸንን ለመከላከል ከእኛ በሚገዙት እንጨት እንደ ዳስ በመጠቀም ከብዙ ነገር ይከላከሉበታል፡፡ ከእጣንና እንጨት በተጨማሪ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የዱባ ፍሬ ወደ ውጭ አገር መላክ የጀመርኩት እኔ ነኝ፡፡ የዱባ ፍሬ ለዘመናት የሚጣል እንጂ ወደ ውጭ አገር ተልኮ የውጭ ምንዛሪ የሚያመጣ አልነበረም፡፡
ሪፖርተር፡- የዱባ ፍሬ የሚልኩት የት ነበር?
አቶ አስመላሽ፡- ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ዮርዳኖስ፣ የመንና ሌሎች የዓረብ አገሮች ነበር፡፡ ይኸንን ሥራዬን በወቅቱ አብሬያቸው (በመበደርና በማበደር) የምሠራው፣ አዋሽ፣ ወጋገን፣ ንብ እና ዳሽን ባንኮች ያውቃሉ፡፡
ሪፖርተር፡- ንግድ ሲጀምሩ መነሻ ካፒታልዎ ስንት ነበር?
አቶ አስመላሽ፡- በወቅቱ የነበረው የገንዘብ ዋጋ ከፍተኛ ስለነበር እንጂ መነሻ ካፒታሌ የተጋነነ አልነበረም፡፡ በ100 ሺሕ ብር ካፒታል ነው ወደ ንግዱ ዓለም የተቀላቀልኩት፡፡ ከትንሽ ነው የተነሳሁት፡፡ ከውጭ አልባሳትና የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦችን በማስመጣት ጀምሬ፣ እያደግኩኝ ስመጣ ወደ ላኪነት ሥራ አደግኩኝ፡፡ በላኪነት ንግድ ለመሰማራት በዋናነት ያነሳሳኝ ብዙ ምክንያቶች አሉ፡፡ የመጀመሪያው የአገሬን ምርት ለውጭው ዓለም በመላኬ የውጭ ምንዛሪ ከማስገኘት በተጨማሪ፣ አገርንና ምርቷን ማስተዋወቅ ነው፡፡ ሁለተኛ እኔም ተጠቅሜ የአገሬን አርሶ አደር ተጠቃሚ ማድረግ ነው፡፡ አበዳሪዎቼ ባንኮችም ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ በተለይ ወጋገን ባንክና ንብ ባንክ ዋና አበዳሪዎቼ ስለነበሩ፣ ሥራውን አብረን እየሠራን ነበር ማለት ይቻላል፡፡ በእርግጥ ባንኮቹ ብድር ሲሰጡኝ ለምበደረው የገንዘብ መጠን ኮላተራል ይዘው ቢሆንም፤ በቀናነትና በተባባሪነት መንፈስ ተግባብተን ስንሠራ ቆይተናል፡፡
ሪፖርተር፡- ከጥራጥሬ እህሎች በዋናነት የምትልኳቸው የትኞቹን ዓይነት ነው? የምትልኩላቸው አገሮች የትኞቹ ናቸው?
አቶ አስመላሽ፡- የምልከው አውሮፓ፣ ዓረብ አገሮች በሙሉ፣ ወደ አፍሪካና አሜሪካ ነው፡፡ ጥራጥሬዎች፣ የቅባት እህሎችና ቅመማ ቅመሞችን ነበር የምልከው፡፡
ሪፖርተር፡- በላኪነት የንግድ ሥራ ላይ ምን ያህል ጊዜ ሠርተዋል?
አቶ አስመላሽ፡- ለስድስት ዓመታት ሠርቻለሁ፡፡ እኔ ወደ ላኪነት ሥራ ስገባ ዝም ብዬ በድፍረት አልገባሁም፡፡ የላኪነት ሥራ እንዴት እንደሚሠራ፣ ውጤታማ ለመሆን ምን መደረግ አለበት? ከነማንና በምን ሁኔታ ይሠራል? እኔ ለራሴና ለሀገሬ ማድረግ ያለብኝ ምንድን ነው? የሚለውን ጭምር ለማወቅ በአገሬና በውጭ አገር ሥልጠና ወስጄ ነው ወደ ዘርፉ የተቀላቀልኩት፤ ከሥልጠና በኋላም፣ የላኪነት ሥራ ላይ ከተሰማሩ ነጋዴዎች ጋር በመሆን ሥራውን ተለማምጄ ነው በራሴ መሥራት የጀመርኩት፡፡ በአሁኑ ጊዜ በጣም ብዙ በላኪነት ሥራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች አሉ፡፡ ኢትዮጵያም ከዚህ የንግድ ዘርፍ ጥሩ የውጭ ምንዛሪ እያገናኘ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ ነገር ግን እኔ በዚህ የሥራ ዘርፍ በተሰማራሁበት ጊዜ በላኪነት የንግድ ዘርፍ ተሰማርተው የነበሩት በጣት የሚቆጠሩ ነበሩ፡፡
ሪፖርተር፡- የግብርና ውጤቶችን ወደ ውጭ የምትልኩት በምን ዓይነት ሁኔታ ነበር?
አቶ አስመላሽ፡- እኔ መላክ የጀመርኩት መጀመርያ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አማኑኤል አካባቢ የማበጠሪያና ማሸጊያ ማሽን በማዘጋጀት ሁሉንም የምልካቸውን ምርቶች በልዩ ሁኔታ በማሸግና የሚፈለገውን የአላላክ ሁኔታ በማሟላት ነበር፡፡ የሚላከው ዝም ብሎ አበጥሮና አሽጐ ሳይሆን፣ ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀና በአገራችንም የደረጃዎች መዳቢ ባለሥልጣን ባስቀመጣቸው መስፈርቶች አማካይነት ነው፡፡ በመሆኑም ያንን ሁሉ ነገር አሟልቼ ነበር የምልከው፡፡ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው የኤክስፖርት ንግድ አሠራር መመሪያ መሠረት፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር (በወቅቱ) በሰጠው ፈቃድ መሠረትና ኢትዮጵያ የንግድ ሕግን በሚመለከት ያስቀመጠችውን ሕጋዊ አካሄድ ሁሉ በማሟላት እሠራ ነበር፡፡ በመንግሥት ደረጃ ጥሩ ተቀባይነትም ነበረኝ፡፡ የመላክ ሥራ በአዲስ አበባ አማኑኤል አካባቢ በደቂቃ አንድ ኩንታል የሚያዘጋጅ ሁለት ማበጠሪያና ማሸጊያ ማሽን በመታገዝ ጀምሬ፣ ሥራው እየተስፋፋና የውጭ አገር ደንበኞች እየበዙ ሲሄዱ ቡራዩ፣ ናዝሬት፣ ጐንደርና ሁመራ ላይ በድምሩ ዘጠኝ የማበጠሪያና ማሸጊያ ማሽኖችን በመትከል ሥራውን በሰፊው መሥራት ጀመርኩ፡፡ የማበጠሪያና ማሸጊያ ማሽኖችን በተለያዩ ቦታዎች ለመትከል ያስገደደኝ፣ ምርቱን የሚያቀርቡ ነጋዴዎችና አርሶ አደሮች ባሉበት አካባቢ በቀላሉ መገበያየት እንድንችል ነው፡፡ ሌላው በየአካባቢው የሚሰበሰቡ ምርቶች ባሉበት አካባቢ ተዘጋጅተው በዚያው ለመላክ አመች በመሆኑና የትራንስፖርት ወጪን ለሁላችንም ለመቀነስም ጭምር ነው፡፡ ሥራው በየክልሉ እየተስፋፋ ሲሄድ ዜጐችም ሥራ የማግኘት ዕድል ይኖራቸዋል፡፡ ብዙም ሠራተኞች ነበሩኝ፡፡  
ሪፖርተር፡- የድርጅትዎ ስያሜ ምንድነው?
አቶ አስመላሽ፡- አንደኛው ኤቨር ግሪን ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፡፡ ሁለተኛው ሥረዋት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበርና ሦስተኛው ድርጅቴ ኦል ግሪን ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት የሚባሉ ሲሆኑ የላኪነት ሥራው ይሠራ የነበረው በእነዚህ ድርጅቶች ነበር፡፡ የላኪነት ሥራው ጥሩ እየሆነ በመሄዱ ተጨማሪ የላኪነት ሥራውን የሚያግዙ ሌሎች ኩባንያዎችን እንዳቋቁም ሥራው እራሱ አስገደደኝ፡፡ በመሆኑም በደቡብ ክልል አርባ ምንጭ አካባቢ የእርሻ መሬት በመውሰድ ከባልደረቦቼ ጋር በመሆን ኦል ግሪን አግሮ ኢንዱስትሪ የሚባል ድርጅት አቋቋምን፡፡ ከአርሶ አደሮች ከምንገዛው የሚላኩ ምርቶች በተጨማሪ ራሳችንም አምርተን ለመላክ በማሰብ ነው ወደ እርሻው ኢንቨስትመንት የገባነው፡፡ ቃሊቲ አካባቢም የምግብ ማደራጃ አቋቋምኩ፡፡ ይኸንን ደግሞ ለማቋቋም ያስገደደኝ ነገር፣ ወደ ውጭ አገር የምንልካቸው የግብርና ውጤቶች በውጭ አገር ወደ ሌላ የምግብ ዓይነት ተቀይረው ወደ አገራችን ሲገቡ በማየቴ ነው፡፡ ስለዚህ ‹‹ለምን እዚሁ አገራችን ላይ አናመርታቸውም?›› በማለት የምግብ ማደራጃ ፋብሪካ ለማቋቋም ወሰንኩ፡፡ በውጭ ምንዛሪ የላክናቸውን ሸቀጣ ሸቀጦች ዓይነትና መልካቸውን ቀይረው ሲላኩልን፣ በውጭ ምንዛሪ መግዛታችን ያለማወቅ ስለነበር፣ ያንን በማጥናት አስፈላጊነቱ ጐልቶ ስለታየን ፋብሪካ ለማቋቋም ችዬ ነበር፡፡ በሥራ አማካይነት ከማውቃቸው አንድ የየመን ዜጋ ጋር በመሆን በሽርክና የሲሚንቶ ፋብሪካ ለመሥራት ተስማምተን በአማራ ክልል ደጀን ከተማ አካባቢ ቦታ ወስደን ነበር፡፡ ቦታውን ከተረከብን በኋላ፣ የማምረቻ ማሽን ለማስገባት አዘዝን፡፡ ይኸንን ሁሉ የምናደርገው ከሚመለከታቸው መንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች ተገቢውን ሕጋዊ ፈቃድ በመውሰድ ነው፡፡ ለአገር መጠቀሚያና ወደ ውጭ ለመላክ ከፍተኛ ዕቅድ ይዘን ነበር የተነሳነው፡፡ የውጭ ብድር ከአውሮፓ አግኝቼ የማሽኑን መግቢያ ቀን እየተጠባበቅሁ ነበር፡፡ የሁሉም ኩባንያዎች ዋና ሥራ አስኪያጅ እኔ ብሆንም፣ ለቅርንጫፍ ድርጅቶቼ ግን፣ የማምናቸውና ሙሉ በሙሉ ኩባንያዎቹን በኃላፊነት ተቆጣጥረው ይሠራሉ ያልኳቸው በተለይ ሁለት ምክትል ሥራ አስኪያጆች ነበሩኝ፡፡ በወቅቱም ጥሩ ሠራተኞቼ ነበሩ፡፡ ታማኞችና ለአገር ለወገን ተቆርቋሪ፣ ዕድገት ፈላጊና ብሩህ ተስፋ የነበራቸው መልካም ዜጐች ነበሩ፡፡ ጥሩ ደመወዝተኞችና ከሥራቸው ያሉ ሠራተኞችን በጥሩ ሁኔታ እየተቀጣጠሩ ይሠሩ ነበር፡፡ በነገራችን ላይ መጀመሪያ የላኪነትም ሆነ ሌሎች የንግድ ድርጅቶቼን የመሠረትኩት ከእህቶቼ ጋር እንደነበር ለመጥቀስ እወዳለሁ፡፡ ሌሎች ሸሪኮች የመጡት በኋላ ላይ ነው፡፡  
ሪፖርተር፡- ምን ያህል ሠራተኞች ነበሩዎት? በቋሚነትና በጊዜያዊነት የሚሠሩ?
አቶ አስመላሽ፡- በወቅቱ ቋሚ ሆነው የሚሠሩት ከ50 በላይ ሠራተኞች ነበሩ፤ በጊዜያዊ ወይም በቀን ሠራተኛነት እስከ አሥር ሺሕ ይደርሱ ነበር፡፡
ሪፖርተር፡- የጊዜያዊ ሠራተኞቹ ቁጥር አልተጋነነም?
አቶ አስመላሽ፡- አልተጋነነም፡፡ ቦሎቄ፣ ጥቁር አዝሙድ ጤፍና፣ ሌሎቹም የእህል ዘሮች በማሽን ከተበጠሩ በኋላ፣ አንዳንድ ከማሽኑ የሚያልፉ አሉ፡፡ እነዚህ ከማሽንና ከወንፊት ያለፉት የሚለቀሙት በእጅ ነው፡፡ በተለይ ቦሎቄ በእጅ የተለቀመ ቢሆን በገዥም ስለሚፈለግ፣ የሚሠራው በሰው ኃይል ነው፡፡ በዚህ ምክንያት የቀን ሠራተኛ ቁጥር ተጋኖ ሳይሆን የሥራው ባሕሪ የፈጠረው ነው፡፡
ሪፖርተር፡- ከውጭ ነጋዴዎች ጋር የምትገናኙት ወይም ገበያ የምታፈላልጉት እንዴት ነው?
አቶ አስመላሽ፡- አገር ውስጥ ያለውን ሥራ የሚከታተሉና የሚቆጣጠሩ በጥሩ ደመወዝ የቀጠርኳቸው ምክትል ሥራ አስኪያጆች አሉ፡፡ እነሱ ልክ እንደኔ ሆነው ይሠራሉ፡፡ በተለይ ሰብሎች በሚሰበስቡበት ወቅት እኔ አለሁ፡፡ ግዢ ካጠናቀቅን በኋላ፣ ምክትሎቼ የማስበጠርና የማሳሸግ ቁጥጥር ሥራውን እንዲሠሩ መመሪያ ሰጥቼ ወደ ውጭ እሄዳለሁ፡፡ ምርቶቹን በምልክባቸው አገሮችም ወኪሎች አሉኝ፡፡ እነሱ ገዥዎችን አመቻችተው ይጠብቁኛል፡፡ ካለወኪልም በቀጥታ ግዥ የሚፈጽሙ ደንበኞች አሉን፡፡ በአጠቃላይ የእኔ ምክትል የሆኑ ሦስት ሰዎች በኃላፊነት እየሠሩ ነበር፡፡ በነገራችን ላይ የቁም ከብትና ሥጋም እንልክ ነበር፡፡
ሪፖርተር፡- በአማራ ክልል ደጀን ከተማ አካባቢ ሲሚንቶ ፋብሪካ ለመትከል ፈቃድ ወስዳችሁና መሬት ተረክባችሁ ማሽን አዛችሁ እንደነበር ገልጸውልኛል፡፡ ፋብሪካውም አልተተከለም፤ ማሽኑም አልመጣም፡፡ ለምን?
አቶ አስመላሽ፡- ማሽንና ፋብሪካ ብቻ አይደለም ተግባራዊ ሳይሆን የቀረው፣ ሌሎችም ብዙ ጅምሮች ነበሩ፡፡ ሆለታ ላይ የአበባ እርሻ ከአንድ የመናዊና ጣሊያናዊ ጋር መሬት ወስደን በጅምር የቀረ አለ፡፡ ሞጆ ላይ ደግሞ የማድለቢያና የቄራ መሬት ወስደን ሥራው በጅምር ቀርቷል፡፡ ሌሎችም ብዙ ዕቅዶችና ጥናቶች ነበሩኝ፡፡
ሪፖርተር፡- ተግባራዊ ያልሆነበት ምክንያት ምንድነው?
አቶ አስመላሽ፡- ምክንያቱ እኔ በ1997 ዓ.ም. ለሥራ ወደ የመን ሄጀ ነበር፡፡ ነገር ግን የመን ውስጥ ከአንድ የንግድ ድርጅት ጋር ስለሥራ ሁኔታ ተነጋግሬ ተፈራርሜ ከምሽቱ 4 ሰዓት ስወጣ በታጣቂዎች ታፈንኩኝ፡፡ ሰነዐ ከተማ ላይ፡፡
ሪፖርተር፡- እርስዎ ታዋቂ ነጋዴና በሕጋዊ መንገድ የሚሠሩ መሆኑን ነግረውኛል፡፡ በቀን መፈራረም ሲቻል በምሽት መፈራረሙ ለምን አስፈለገ?
አቶ አስመላሽ፡- ዓረብ አገሮች በተለምዶ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ይሠራሉ፡፡ ዋና የድርጅት ኃላፊዎች የሚገኙት ከሰዓት በኋላና ግማሽ ሌሊት ድረስ ነው፡፡
ሪፖርተር፡- እነማን እንዳፈንዎትና ወዴት እንደወሰድዎት ታውቋል? ያደረሱብዎት ጉዳትስ?
አቶ አስመላሽ፡-  አፍነው ወዴት እንደወሰዱኝ አላወቅኩኝም፡፡ እነሱ ጋ ከሁለት ወራት በላይ አቆይተውኛል፡፡ በወቅቱ የጠየቁኝ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ነበር፡፡ ነገር ግን ምንም ያገኙት ነገር የለም፡፡
ሪፖርተር፡- ወራቱን የቆዩት በእስር ቤት ነው ወይስ በግለሰብ ቤት ውስጥ?
አቶ አስመላሽ፡- በግለሰብ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ዶላር እንድሰጣቸው ደጋግመው ጠየቁኝ፣ ወደ ቤተሰብና የመን አገር ደንበኞች ጋ ቢደውሉም ቢያስደውሉም ግን ምንም ያገኙት ነገር አልነበረም፡፡ መታፈኔንና በማላውቀው ቦታ መታሰሬን እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ በምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅነት ለቀጠርኩትና በወቅቱ ፍፁም ታማኝ ለነበረው ግለሰብ (ለጊዜው ስሙን መጥቀስ አልፈልግም) አሳውቄዋለሁ፡፡ አፋኞቼም የሚፈልጉት ዶላር መሆኑን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲያውቅልኝና በኢትዮጵያ የየመን ኤምባሲ በኩል ክትትል እንዲያደርጉልኝ እንዲነግርልኝም ነግሬው ነበር፡፡ ነገር ግን፣ ግለሰቡ ‹‹አይለቀቅም አብቅቶለታል›› ብሎ አስቦ ይሁን ወይም በወቅቱ ምን እንዳሰበ ባላውቅም፣ ለኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ ለሚመለከታቸው ወገኖች አላሳወቀልኝም፡፡ በመሆኑም ማንም ያስታወሰኝ የለም፡፡ ከተወሰነ በኋላ ‹‹አመሲያንሴ›› የሚሉት የፖለቲከኞች እስር ቤት አስረከቡኝ፡፡ ‹‹ይኸ ማንነቱ ያልታወቀ እስረኛ ነው›› በማለት አስረከቡኝ፡፡ አፋኞቼ ከዛቻና ማስፈራራት ያለፈ ምንም ዓይነት ድብደባም ሆነ መንገላታት አላደረሱብኝም፡፡ እንዲያውም ያበሉኝ ያጠጡኝ ነበር፡፡ ፖለቲከኞች እስር ቤት ግን ‹‹ማነህ? እንዴት ልትገባ ቻልክ? ከየት ነህ›› በማለት ድብደባ ደርሶብኛል፡፡ አንድ ወር አካባቢ እንደቆየሁ ‹‹በእኛ በኩል አጣርተናል፣ አንፈልግህም፡፡ ነገር ግን ከኢትዮጵያ በማጭበርበር ወንጀል እንደምትፈለግ ተገልፆልናል፡፡ እንድንመረምርህና እንድናጣራ ነግረውናል በማለት የአካል መጉደል እስከሚደርስብኝ ማለትም በመታፈኔ እንደልብ እንዳልተነፍስ የሚያደርግ ሕመምተኛ ሆኛለሁ፡፡ ከፖለቲከኞች እስር ቤት ሰነዐ ወደሚገኘው ወህኒ ቤት ‹‹ኢንተርፓል ነን›› በሚሉ ፖሊሶች ተወሰድኩ፡፡ በተደጋጋሚ ‹‹ወደ አገርህ ብንልክህ የፖለቲካ ችግር ይገጥምሀል?›› በማለት ስጠየቅ፣ ምንም ችግር እንደሌለብኝ በመግለጽ እንዲልኩኝ ተማፀንኳቸው፡፡ ሰላማዊ፣ ነጋዴና አገሬን ጠቅሜ እራሴን የምጠቅም ሰው መሆኔን ስነግራቸው፤ ‹‹በምን እንደተፈለክ እስከምናጣራ ምግብና ሕክምና ባለበት ወህኒ ቤት መቆየት አለብህ›› አሉኝ፡፡ ሁለት ወር ወህኒ ቤት ከቆየሁ በኋላ ‹‹ኢመነልጐ›› ወደሚባል እስር ቤት ወስደውኝ ከምድር በታች (Underground) አስገብተውኝ ለሁለት ሳምንታት ገረፉኝ፡፡
ከሁለት ዓመት በኋላ ‹‹ምርመራውን ጨርሰናል ተፈላጊ ሰው ነህ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ አጭበርብረሀል፡፡ የባንኮች ብር ዘርፈህ የመጣህ መሆኑን አረጋግጠናል፡፡ አሁን ልናስረክብህ ነው›› አሉኝ፡፡ በቃል፡፡ ሊያስረክቡኝ ነው ብዬ ደስ ሲለኝ ዘገዩብኝ፡፡ ለምን እንደዘገዩ ስጠይቃቸው ‹‹የአገርህ ፖሊስ ሲመጣ ነው የምናስረክብህ›› አሉኝ፡፡ ሳያስረክቡኝ ባጠቃላይ ሰባት ዓመታት ከአራት ወር እዚያው ታስሬ ከረምኩኝ፡፡ ከሰባት ዓመታት በኋላ በድንገት ከምሽቱ አራት ሰዓት ‹‹ትፈለጋለህ›› ተብዬ በፖሊስ ታጅቤ ወደ የመን ሰነዓ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወሰዱኝ፡፡ ከኢትዮጵያ ለመጡ ሁለት ፖሊሶች ሲያስረክቡኝ የነበረኝ ደስታ ወሰን አልነበረውም፡፡ አመሰገንኳቸው፡፡ የአገሬን መንግሥትም አመሰገንኩ፡፡ አለመረሳቴም ገረመኝ፡፡ ሐምሌ 2 ቀን 2005 ዓ.ም. አገሬ ገባሁ፡፡  
ሪፖርተር፡- ከየመን ያመጡዎትን ፖሊሶች ለምን ይኸንን ያህል ዓመታት እንዳቆዩዎት አልጠየቋቸውም?
አቶ አስመላሽ፡- ‹‹ይኸ የእኛ ችግር አይደለም፡፡ የየመን ችግር ነው፡፡ እነሱ ካላስረከቡን እኛ ማምጣት አንችልም፡፡ አሁንም የመጣነው ለማስረከብ ፈቃደኛ ስለሆኑ ነው›› አሉኝ፡፡
ሪፖርተር፡- ኢትዮጵያ ሲገቡ ምን ገጠመዎት?
አቶ አስመላሽ፡- ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ስደርስ መጀመሪያ በቴሌቪዥን ተቀረጽኩኝ፡፡ የፌዴራል ፖሊስ ፕሮግራም አዘጋጆች እየቀረጹኝ ‹‹የምትናገረው ካለ›› ብለው ጠየቁኝ፡፡ ‹‹ለምንድነው የምትቀርጹኝ›› በማለት እንዳይቀርጹኝ ጠይቄ ነበር፡፡ ግን የሰማኝ አልነበረም፡፡ ‹‹የምንቀርጽህ ለዶክመንት ነው›› አሉኝ፡፡ እኔ ወንጀለኛ ልባል የሚገባኝ በፖሊስ አስፈላጊው ምርመራ ተደርጐብኝ፣ በዓቃቤ ሕግ ክስ ከተመሠረተብኝና ፍርድ ቤት ወንጀለኛ መሆኔን ሲያረጋግጥ ብቻ ቢሆንም፣ የፖሊስ ፕሮግራም አዘጋጆች ወይም የሚመለከተው አካል ሐምሌ 2 ቀን 2005 ዓ.ም. አዲስ አበባ ከገባሁበትና ከቀረፁኝ ከሰዓታት ቆይታ በኋላ ሙሉ ቀን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በየሰዓቱ ‹‹ለሰባት ዓመታት ስንከታተለው የነበረው፣ ከወጋገን ባንክና ከንብ ባንክ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ተበድሮ ተሰውሮ የነበረውን ግለሰብ ከተወሰረበት ቦታ በቁጥጥር ሥር ውሎ በኢንተርፖል አማካይነት ወደ አገር ውስጥ ተይዞ ገባ›› የሚል ዘገባ ተላለፈ፡፡ የሚያሳዝነውና የሚገርመው ነገር እኔ ሰባት ዓመታት የት እንደቆየሁ ያውቃሉ፡፡ ሌላው አስገራሚና እንኳን የንግድ ወይም የባንክ ዕውቀት ላለው ቀርቶ ለሌለው ሰው ግልጽ የሆነ ነገር ቢኖር ባስተላለፉት ዜና ላይ ‹‹ከወጋገን ባንክና ንብ ባንክ ከፍተኛ ብር ተበድሮ የተሰወረው›› ማለታቸው ነው፡፡ ‹‹ለመሆኑ ባንኮቹ ብድር የሚሰጡት በእምነት ነው እንዴ? በእምነት የሚሰጥ ቢሆን አይደለም ነጋዴ ሌላው ዜጋ አይበደርም?›› ሁሉም ወገን፣ መንግሥትም፣ ዜጐችም፣ ተቋማትም ሆኑ ሌሎች አካላት ልብ ሊሉት የሚገባው ነገር፣ አንድን ዜጋ ወይም ተቋም ለማጥቃት ሲፈለግ የሚኬድበት አካሄድ ምን ያህል የተዛባና ግምት ውስጥ የሚከት መሆኑን ኢትዮጵያውያን ከእኔ ሊማሩ ይገባል፡፡ እኔ በበኩሌ፣ ስንቱ እንደኔ ያልሆነ ስም እየተሰጠው ሰለባ ሆኖ ይሆን? መልሱን ለመንግሥትና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ትቼዋለሁ፡፡ እኔ ምንም የፈጸምኩት ወንጀል ባለመኖሩ ሰው ብቻ ሳይሆን ፈጣሪም ያውቀዋል፡፡
ሪፖርተር፡- ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በፌዴራል ፖሊስ ታስረው ነበር፡፡ እዚህ የደረሰብዎ ችግር አለ?
አቶ አስመላሽ፡- አገሬ ውስጥ ምንም የደረሰብኝ ችግር የለም፡፡ የሚፈልጉትን ምርመራ በስፋት አካሄዱ፡፡ ምርመራው ከዓቃቤ ሕግ ጋር በጋራ ነበር የተደረገው፡፡ ሐምሌ 29 ቀን 2005 ዓ.ም. ምርመራውን ያደረገው ዓቃቤ ሕግ፤ ምንም የሚያስጠይቀኝ የወንጀል ድርጊት እንደሌለብኝ በመጥቀስና ነፃ መሆኔን በመግለጽ ከእስር እንድፈታ በፍትሕ ሚኒስቴር በኩል ተነገረኝ፡፡ ነገር ግን ‹‹ነፃ ነህ›› ብባልም ፖሊስ ሊለቀኝ ፈቃደኛ አልሆነም፡፡
ሪፖርተር፡- ለምን?
አቶ አስመላሽ፡- ‹‹መርማሪ ፖሊስ፣ ‹‹እኛ ገና ምርመራ ሳንጨርስ ዓቃቤ ሕግ እንዴት ይዘጋዋል?›› በማለት ‹‹አልፈታም›› በማለት ‹‹ምርመራ እንቀጥላለን›› ብሎ ቀጠለ፡፡ ፍርድ ቤት አቀረቡኝና ተጨማሪ ጊዜ ጠየቁብኝ፡፡ እኔ ደግሞ ፖሊስና ዓቃቤ ሕግ በጋራ መርምረውኝ ዓቃቤ ሕግ ክስ የሚያስመሠርት ምንም ዓይነት ወንጀል ያልተፈጸመ መሆኑን በመግለጽ የምርመራ መዝገቡን መዝጋቱን አስረዳሁ፡፡ ፍርድ ቤቱ በሁለት ሚሊዮን ብርና ከአገር እንዳልወጣ ዕግድ ጥሎ እንድፈታ አዘዘ፡፡ ነገር ግን የዋስትና ማስያዢያው ገንዘብ ከአቅሜ በላይ ስለነበረ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አልኩኝ፡፡ ፍርድ ቤቱ ጥቅምት 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ሥራ ሲጀምር የይግባኙን መዝገብ ተመልክቶ በነፃ እንድሰናበት ውሳኔ በማስተላለፉ፤ የፍትሕ ሚኒስቴር ዓቃቤ ሕግ ‹‹ግለሰቡ ወንጀል አልፈጸመም፣ ነፃ ነው ይለቀቅ›› ባለ በ37ኛ ቀኔ ከእስር ተፈታሁ፡፡ እዚህ ጋ ልብ ሊሉ የሚገባው ‹‹የበላይ አካል ማነው? የሚለውን ነው ‹‹ዓቃቤ ሕግ ወይስ ፖሊስ? በእኔ ጉዳይ የበላይ የነበረው ፖሊስ ነበር፡፡ እንዳጠቃላይ ግን መንግሥትንና ፍርድ ቤቶችን እንዲሁም ፍትሕ ሚኒስቴርን ላመሰግን እወዳለሁ፡፡ ምክንያቱም ንፁህ በሆነ መንገድ ጉዳዩን መርምረውና አጣርተው ትክክለኛውንና ተገቢውን ፍትሕ ስለሰጡኝ ነው፡፡ ቀደም ብለው ከየመን አስመጥተውኝ ቢሆን ኖሮ የወጣትነቴን ጊዜ በእስር ቤት ከማሳልፍ ብዙ እሠራበትና ራሴን፣ ወገኖቼንና አገሬን እጠቅም ነበር፡፡
ሪፖርተር፡- ከብዙ የእስር ቤት ቆይታ በኋላ ወደ አገርዎ በመመለስ ፍትሕ አግኝተዋል፡፡ ከሰባት ዓመታት በፊት የጀመሯቸውና የወጠኗቸው የንግድ እንቅስቃሴዎችን በምን ሁኔታ ላይ ሆነው አገኟቸው?
አቶ አስመላሽ፡- ከእስር እንደወጣሁ ከአንድ ሳምንት ዕረፍት በኋላ በልጅነት ዕድሜ ወደጀመርኳቸው የንግድ ሥራዎችና በውጥን ላይ ወዳሉት የተለያዩ የኢንቨስትመንት ፕሮጄክቶቼ ነበር ያመራሁት፡፡ ምንም ነገር ላገኝ አልቻልኩም፡፡ ደብዛቸው ጠፍቷል፡፡ ምክትል ሥራ አስኪያጅ በማድረግ በዋናነት የቀጠርኳቸው ሦስት ግለሰቦችን (ስማቸውን ለጊዜው መጥቀስ አልፈልግም) ላገኛቸው አልቻልኩም፡፡ በዚሀ አጋጣሚ መናገር የምፈልገው በወቅቱ በቂ ኮላተራል በማስያዝ የተበደርኳቸው ባንኮች ነበሩ፡፡ እኔን ሲያጡና ክፍያ ሲቆምባቸው በኮላተራል የያዟቸውን ንብረቶች ሸጠው እንደሚወስዱ በብድር ውሉም ላይ የተገለጸ ነገር ቢሆንም፣ የሸጡት ንብረት ሳይበቃቸው ወይም ካበደሩት ገንዘብ ጋር ያልተመጣጠነላቸው ካሉ፣ አብረውኝ ሆነውና የነበረኝን ንብረት በጋራ አስመልሰን ለመክፈል ፈቃደኛ መሆኔን ነው፡፡ ባንኮች ብቻ ሳይሆኑ፣ ምርቶቻቸውን በዱቤ ወደ መጋዘኖቼ ያስገቡና ሳይከፈላቸው የቀሩም ካሉ፣ ተባብረንና በእምነት በውክልና እንዲያስተዳድሩ የፈቀድኩላቸውን ግለሰቦች በሕግ ፊት አቁመን ንብረታችንን በማስመለስ በጋራ ለመሥራት ፈቃደኛ መሆኔን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ መንግሥት የነበሩኝን ማሽነሪዎች፣ የንግድ መጋዘኖች አጠቃላይ ንብረቶቼን የግል መኖሪያ ቤቴን ሳይቀር በግላቸውና በቤተሰቦቻቸው ስም ያዞሩት፣ በቀድሞ የእኔ ሠራተኞች (ምክትል ሥራ አስኪያጆች)፣ አሁን ደግሞ ባለሀብት የሆኑትን ግለሰቦች ተፈርዶልኝ ወደነበርኩበት ሥራ በመመለስ ራሴን፣ ቤተሰቤን፣ ወገኔንና አገሬን እየረዳሁ እንድኖር ያደርግልኝ ዘንድ እምነቴ ሙሉ ነው፡፡ የማስተምራቸው የሙት ልጆችና የራሴ ልጆች አሉኝ፡፡ ምክትል ሥራ አስኪያጆቹ እህቶቼን ‹‹ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እየፈለጓችሁ ነው›› በማለትና በማስፈራራት ብዙ ጉዳት አድርሰውብኛል፡፡ የማምነው፣ እመካበት የነበረውና ምክትል ሥራ አስኪያጅ ያደረግኩት ግለሰብ፣ የመኖሪያ ቤቴን ውክልና እህቴ እንድትሰጠው በማድረግ፣ በአክስቱ ስም አዙሮት አገኘሁት፡፡ ጐንደር ላይ የነበረው የማበጠሪያና ማሸጊያ ማሽንን አንዱ ሠራተኛዬ የነበረው ግለሰብ በቀጥታ በራሱ ስም አዙሮ ትንሽ ከቆየ በኋላ በሚስቱ ስም ማዞሩን መረጃ ደርሶኛል፡፡
ሪፖርተር፡- እርስዎ ነፃ መሆንዎ ተረጋግጧል፡፡ ንብረትዎን በሚመለከት በሕግ አልጠየቁም?
አቶ አስመላሽ፡- ጠይቄያለሁ ‹‹ማጣራት የምትችለው አዲስ አበባ ላይ ያለውን ብቻ ነው፡፡ ሌላውን ማጣራት የሚቻለው በየክልሉ ነው አለኝ›› የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፡፡ በየክልሉ ሄደህ አመልክት ተባልኩ፡፡ ነገር ግን ያለፉት ሰባት ዓመታት ያለአግባብ ታስሬ እንደነበር መንግሥት ያውቃል፡፡ ጉዳዬ በፌዴራል መንግሥት ታይቶ የነበሩኝ ንብረቶቼ የት እንደደረሱ ተጣርቶና ተሰብስቦ ‹‹ገንዘብ አለን›› ለሚሉ ባንኮችም ሆኑ ግለሰቦች ከተሰጠ በኋላ ቀሪው ደግሞ እንደ አዲስ ‹‹ሀ›› ብዬ ድሮ በጀመርኩት ሥራ እንድሰማራ ሊደረግልኝ ይገባል የሚል ጥያቄ ለሚመለከታቸው የፍትሕ አዛዦች ጥያቄ አቅርቤያለሁ፡፡ ፌዴራል ፖሊስ ‹‹የግለሰብ ጉዳይ አናይም›› ብሎኛል፡፡ ከየመን ድረስ ያመጣኝ ግን እኔን ግለሰቡን ፌዴራል ፖሊስ ነው፡፡ የግል ቤቴን በሚመለከት ለፖሊስ አመልክቼ ምርመራ ከተደረገበት በኋላ ወንጀል መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ በተጠርጣሪው ላይ ክስ ቢመሠረትም ተጠርጣሪው ለጊዜው ታስሮ ወዲያው ተፈትቷል፡፡ መለቀቁ ግን ግራ አጋብቶኛል፡፡ ተመሳሳይ ወንጀል የፈጸሙ ግን ዋስትና ተከልክለው በእስር ላይ የሚገኙ ብዙ ናቸው፡፡ የእኛ ተጠርጣሪ ግን ከእስር ወጥቶ እኛ የቆጠርናቸውን ምስክሮች ከፍርድ ቤት በራፍ ላይ አሳስሯቸው በዋስ ተለቀው ጉዳያቸውን የተገላቢጦሽ እየተከታተሉ ነው፡፡ ግለሰቡን ግን ከ15 በላይ ድርጅቶች፣ በጣም ብዙ ተሽከርካሪዎች፣ ኦርጅናል የንግድ ፈቃድ፣ ውሎችና የተለያዩ የግልና መንግሥታዊ ሰነዶች፣ መኖሪያ ቤት፣ ጥሬ ገንዘብና በሌሎች ጉዳዮች መንግሥት እንዲጠይቅልኝ እየጠየቅኩኝ ነው፡፡ ‹‹ማስረጃ ስለሌለው ሊጠይቀኝ አይችልም›› በማለት የፈጸመው ቢሆንም፣ ብዙ ሐቀኛ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞችና ሌሎች እማኞች ስላሉኝ፣ ከመንግሥት ድጋፍ ጋር እውነታው ላይ እደርሳለሁ የሚል እምነት አለኝ፡፡
ሪፖርተር፡- እርስዎ በታሰሩበት ዓመት የድርጅቶችዎ ካፒታል ምን ያህል ደርሶ ነበር?
አቶ አስመላሽ፡- 2.5 ቢሊዮን ብር ደርሶ ነበር፡፡ በ1997 ዓ.ም.፡፡
ሪፖርተር፡- አሁን ከተፈቱ በኋላ እየደረሰብዎ ያለ ችግር አለ?
አቶ አስመላሽ፡- በጣም ብዙ ችግር እየደረሰብኝ ነው፡፡ አንደኛ ካገር እንድወጣ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶኛል፡፡ ሁለተኛ ከአገር የማልወጣ ከሆነ በእውነትም ይሁን በውሸት ሴራ ተጠንስሶ ወደ እስር ቤት እንደምወረወር ተነግሮኛል፡፡ ይኸንን ማድረግ ካልተቻለ ሕይወቴን እንደሚያጠፉ ጊዜ ገደብ ወስነው ነግረውኛል፡፡ ለአንድ ወር የተሰጠኝ የጊዜ ገደብ ቢያልፍም እስካሁን አለሁ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር እየተጠነቀቅሁ የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ እንዲያውቅልኝ የምፈልገው ነገር፣ እኔ በሕይወቴ ከማንም ጋር ተጋጭቼና ፀብ ውስጥ ገብቼ አላውቅም፡፡ የቅርብ ወዳጆቼ የነበሩ የቀድሞ ሠራተኞቼና ኃላፊ ያደረግኳቸው ግን እያስፈራሩኝ ነውና ሕይወቴ ቢያልፍም ሆነ አንድ ጉዳት ቢደርስብኝ ከእነሱ ሌላ ተጠያቂ እንደማይኖር ሊታወቅልኝ ይገባል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ እያለ በጓዳ ውስጥ ተሸሽጌ አልሞትም፡፡ መጠየቅ የሚገባኝንም በሕግ ፊት የመጠየቅ ሕገ መንግሥታዊ መብት እንዳለኝም ልገልጽ እወዳለሁ፡፡ እታሰራለሁ፣ እታፈናለሁና እገደላለሁ ብዬ መንግሥትና ሕግ ባለበት አገር የከተማ ውስጥ ሽፍቶችና ትናንንሽ ‹‹መንግሥት ነን›› ባዮችን ፈርቼ የማጀት አጫዋች እንደማልሆን ሊያውቁትና ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ አንዳንዶች ማንነታቸው በግልጽ ባይታወቅም፣ ዓቃቤ ሕግ በእኔ ላይ የወንጀል ድርጊት ፈልጐ ክስ እንዲመሠርት እየገፋፉት መሆኑንም ለማወቅ ችያለሁ፡፡ ነገር ግን መንግሥትም ሆነ የፍትሕ አካሉ ማንነቴን በደንብ አብጠርጥረው ካወቁ በኋላ ነፃ መሆኔን ስላረጋገጡልኝ፣ ካሁን በኋላ ለሚመጣብኝ ‹‹በሬ ወለደ›› የክስም ሆነ የውንጀላ እንቅስቃሴ ቅንጣት ታክል የሚያስፈራኝ ነገር የሌለ መሆኑንም ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲያውቁልኝ እፈልጋለሁ፡፡

ምንጭ ሪፖርተር ጋዜጣ

ኢህአዴግና ደርግ የፈጠሯቸው አስደንጋጭ ስብዕናዎች


የደርግን ዘመነ ግዛት ከእልቂትና ከጭፍጨፋ፣ከሰቆቃና ዋይታ ነጥሎ ማየት እጅጉን ከባድ ነው፡፡የኢህአዴግን የማጠልሸት ዘመቻንም ልብ ይሏል፡፡በ20ኛው ክ/ዘመን ውስጥ እንደ ሐይማኖት ብቅ ያለው ኮምዩኒዝም በሶቭየት ዩኒየን፣በቻይና፣በኢንዶቻይና እና በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ከአንድ መቶ ሐያ ሚሊዬን ህዝብ በላይ ጨፍጭፏል፡፡ የመንግስቱ ኃ/ማርያም መንግስትም አገራችን አንድ ትውልድ እንድታጣ አድርጓል፡፡ የደርግ ዘመንን ዛሬ ላይ ሆኘ ሳስበው ከጭፍጨፋውና ከዋይታው በላይ ደርግ የፈጠረው ስብዕና ኢትዮጵያን ላትቃና ተስፋዋን ዘልሶባታል እላለሁ፡፡ደርግ በወኔው የላሸቀ፣ለውጥን ከአፈሙዝ ለይቶ የማያይ፤ ስለ ፍትህ መጮህን በነጭ ሽብር ሒሳብ አስልቶ የቀይ ሽብርን አፀፋዊ ድምር ውጤት በህሌናው የሚየሰላስል፣ወኔው የተሰለበ ትውልድ በመፍጠር ለተረኛው ባለ ቀምበር ደርግ የማነቆን ሚና ተጫውቶለታል፡፡እናም ደርግ የተሸማቀቀ፣ ፓለቲካን፣መብት መጠየቅን አብዝቶ የሚፈራ የፍርሐት ዛር በኢትዮጵያውያን ላይ ተክሎ ህዝቦቹን ለወያኔ አሳልፎ ሰጥቶ በመሸሽ የፍርሐት አብዮቱን እራሱ መንግሰቱ ኃ/ማርያም ጀመረውና ሐበሻ የአሉላ፣የበላይ፣የቴዎድሮስ የባልቻ ሳፎ የትላንት ወኔው፣ ጀግንነቱ ከድቶት በአባቶቹ ጀግንነት እራሱን እያሰላ በፍርሐት ድባብ መኖሩ እውነት ሆኗል፡፡
ሌላው ደርግ ፈጥሮት የነበረውና ዛሬም ድረስ የዘለቀው ስብዕና “አብዬት ጠባቂነት” ነው፡፡ቀደምት አባቶች እንኳንስ የአበሻ ሰው ወንዝ ያፈራላቸውን ይቅርና የውጭ አገር እንግዳቸውን እንኳን አሳልፈው አይሰጡም ነበር፡፡ድህነት የጎዳው ስነ-ልቦናቸውን ሊፈተታን የሚችል የረብጣ ብር ስጦታ እንኳን ቢሆን ለእውነታቸውና ለእምነታቸው የሚሰውም ነበሩ (ማንዴላን በገንዘብ እንዲገድሉ ተጠይቀው አሻፈረኝ ያሉትን ጀግና ያስቡ)፡፡ይህ ያማረ ማንነት ግን ደርግ በዘራው የክህደት ዘር ከምድረ ኢትዮጵያ ላይመለስ እንደጉም ተንኖ ጠፍቷል፡፡ ደርግ አበሻን እፍኝ በማትሞላ ሲሳይ፣እንደ ውሻ በአጥንት እያስሰየ አበሻ እርስ በእርሱ ይባላ ዘንድ “አብዮት ጠባቂነት” የተሰኘ ተውሳክ አውርሶታል፡፡ የቀበሌ ሙገሳን አሳቦ የጎረቢቱን ልጅ በቀይ ሽብር ሽፋን ያስደፋውን፣ ከአስራ ሰባት አመት ላልዘለለ ሹመት የእህት የወንድሙን፣የአብሮ አደግ እድርተኛውን ልጅ በደርግ አብዬት ያስበላውን፣ ከአንደበቱ በታች ላላሰረገው የሶሻሊዝም ኮምዩኒዝም ርዕዬት ፅንሰሐሳብ ሲል የአበሻን እናቶች ቅስም የሰበረውን…እዳ! ተወኝ እባክህ! ሁሉንም ቤት ይቁጠረው!! ከዚህ የባሰ ውድቀት ምን አለ? በእፍኝ ስንዴ ወገንን አፍር ከማስቃም በላይ ከቶ ዝቅጠትስ ይገኝ ይሆን? ሆዱ ከቂጣና ሽሮ ያልዘለለ ወጣትን በጥይት አሳርሮ የጥይት ዋጋ ከመጠየቅ የዘለለ ግፍስ ከቶ ከየት ይገኝ ይሆን? እንጃ!! በእርግጥ የኮሚንዩዝም ስሪቱ ከሰው ደም ይሆን? የዚህ ፅሁፍ ኣላማ ደርግ የሰራውን ግፍ መዘከር አይደለም ከዚሁ ጋር የሚገናኝ ገጠመኝን ማካፈል እንጅ!!
አቢዮት አደባባይ የሚገኘውን “የቀይሽብር ሰማዕታት” ለመጎብኘት አስበው ገና ሲገቡ ጀምሮ “ሞት ሞት” ወደ ሚሸተው አዳራሽ ገብተው የአገርዎን ቅሌት እየጎበኙ ነው እንበል፡፡መቼም እዚያ አዳራሽ ገብተው ከጎበኙ ትላንትናና ዛሬ ይደባለቅበዎታል፡፡ደርግ ይጠቀምባቸው የነበሩ የማሰቃያ መሳሪያዎች የሴቶችን ጡት ያጣብቁበት የነበረው ጉጠት፣ ወፌላላ የተባለው ገልብጦ መግረፊያ፣ የእግርና እጅ ጥፍር መንቀያ ሜንጦ… የቀረ የለም “ደርግ ግፍ ሲፈፅምባቸው የነበሩ መሳሪያዎች” ተብለው ተሰድረውልዎታል፡፡ ቅሉ በምስል ቀይ ሽብር ሰማዕታት አዳራሽ በአካል ግን ማዕከላዊ በተባለው ቦታ! አሁንም መሳሪያዎቹ ስራ ባይፈቱም!! ብቻ ትላንትን ከዛሬ ለመለየት እየሞከሩና አልሆንልዎት እያለ ብቻዎትን ለመግባት የሚፈሩበት ክፍል ከፊት ለፊትዎ በደርግ አቢዮት ጠባቂዎች ተረሽነው አፅማቸው የተጠራቀመበት ክፍል አስፈሪና ለአይን ያዝ የሚያደርግ ጨለማ ክፍል ያገኛሉ፡፡ ወደ ውስጥ ዘልቆ ለመግባት ከፍርሐተዎ ጋር መታገልዎ አልቀረም… ግዴልም ይቅርብዎት! የሆነውን እኔ ራሴ እነግርዎታለሁ፡፡ አንዲት የሥራ ባልደረባዬ ከባለቤቷ ጋር በመጎብኘት ላይ ሳለች ወደ አስፈሪው ክፍል የባለቤቷን እጅ ይዛ ስትገባ ሁለት “በህይዎት ያሉ” ወጣቶች ተመለከተች ዙርያቸውን በአፅም ተከበዋል፤ ጥርሳቸው ያገጠጠ፣ ፀጉራቸው ከነጩ የራስ ቅላቸው ላይ የጨገሰ የራስ ቅሎች ከስራቸው የተሰባበሩ የክንድ፣የጎን አጥንት፣ የጉልበት አጥንቶቻቸውን አድርገው “እንዴት የተገደልን ይመስልሻል?” ፣ “እኛ የተሰዋነው ለዚህ ነበር?” ፣ “ህዝባችን የጠማውን ፍትህ ጠጥቶ ይሆን?” ፣” በእውኑ ደመ ከልብ ሆነን ቀርን ማለት ነው?”፣ ” በአፅማችንም ትነግዱብን ጀመር?”… የመሳሰሉ አናት የሚበረቅሱ ጥያቄዎችን የሚሰነዝሩ ይመስል ፀጥ-ረጭ ብለው አፋጠው በሚታዘቡበት ክፍል ኢህአዴግ የፈጠረው ስብዕና ግን ይህን ሁሉ አጽም ረግጦ፣ ሞትን ንቆ ምናልባትም እዚያ ለቅርስ የተቀመጡት አፅሞች ብሔራቸውን ተመልክተው እንደሁ አይታወቅም የኢህአዴግ ውጤት የሁኑት ወጣቶች ግን አፍ ለአፍ ተጣብቀው እየተሳሳሙ ነበር፡፡አዎ! ይህ ልቦለድ አይደለም አውነተኛ አጋጣሚ እንጅ! ባልደረባዬ ከአፅሙ ይልቅ በወጣቶቹ መዘኗን ነግራኛለች፡፡
በግፍ የተገደሉት ሰማዕቶች ለፍትህ ትጮህ ዘንዳ ወኔ ይሰንቁልሃል! “ ግን ለምን?” ብለህ አራስህን እንድትጠይቅ ጉልበት ይሆኑሃል! እናማ ሞተው እንኳን የህዝብን አደራ ያስታውሱሃል! ደርግ እለታቸውን ቢቀማቸውም ዛሬም ስለ ፍትህ ይጮሃሉ! እነዚህኞቹ ግን የኢህአዴግ ስብዕናዎች ግን ከከንፈር ያለፈ ሳይኖሩ ይሞታሉ፡፡ስለ ከንፈር እያለመ በፍርሃትና በንቅዘት ውስጥ የሚኖር፣ ቆሞ የማይፈይድ ሞቶም ወግ ሆኖ እንጅ የማያቆጭ ስብዕና ኢህአዴግ ፈጥሯል፡፡ በእርግጥ ይህ ስብዕና አንድ ሙሉ ትውልድን ባይወክልም የዚህ ትውልድ ናሙና መሆኑ ግን አሌ አይባልም፡፡ይህ አጋጣሚ ልቦናውን ለከንፈርና፣ለሱስ፣ለጭፈራና ዳንኪራ ያተጋው፤ለእውነትና ለቁም ነገር ግን ያዳተው ትውልድ ማሳያ ነው፡፡ ከዚህ ጀርባ ደግሞ በአንድ ወገን ፓለቲካን ሞት፣መብት መጠየቅን ድንቁርናና ቂልነት አልፎም “የአደጋ ቀጠና” ነው ብሎ እንዲያስብ የፍርሃት ዘር የዘሩት የደርግ አመራሮችና የኢህአዴግ ትውልድ ገዳይ “ዳንኪረኛ!” ባለስልጣኖች የረቀቀ ስርዓት ውጤት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ “ዋልጌነትና ዳንኪራን፣ጭፈራና እልቆቢስ ሱስን” ለአዲሱ ትውልድ የሚመጥን “ስልጣኔያዊ ገፀ-በረከት” ያደረገው የኢህአዴግ “የዴሞክራሲ” ለምድን ያጠለቀ “አስተኝቶ የመጋለብ” ፓለቲካ ውጤት ነው፡፡ እሺ ነገስ? ምን ይሻላል? ወገን መተኛት ዝንብ አያስቀዋም ብላችሁ ነው? አበቃሁ፡፡
 
ልጅ ተይሚያህ አል-ሐበሽይ Miniliksalsaw.iblogspot.com

አክራሪ ... አሸባሪ ... የሰለቸን መንግስታዊ መዝሙር ... የፖለቲካ የበላይነት የፈጠረው አክራሪነት/አሸባሪነት የህዝቦች ስጋት ነምንሊክ ሳልሳዊ:-ሃገሪቱን የሚያሰጋት የሃይማኖት አክራሪነት/አሸባሪነት ሳይሆን የፖለቲካ የበላይነት የፈጠረው አሸባሪነት ጽንፈኝነት እና አክራሪነት ነው::ጥላችሁን እንዳታምኑ እየተባለ ሃይማኖት መንግሥታዊ ቅርጽ ይዞ እንዲወጣ ለማድረግ መሞከር አክራሪነት ነው፡፡

«መጾም፣ መጸለይ፣ ሥርዓተ-አምልኮን መፈጸም ለሃይማኖቱ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንጂ አክራሪነት ሊባል አይችልም፤»...የአክራሪ ክርስትና ወይንም እስልምና ቡድን መኖር የክርስትና እና እስልምና ተከታዮችን በሙሉ «አክራሪ» አስብሎ ሊያስፈርጃቸው አይችልም::አክራሪ ተብሎ የሚፈረጀው የሚራመዱ የፖለቲካ ጡዘቶች በሰዎች ላይ ሌላ እምነትን በመጫን በግዳጅ እና በሃይል ሊያስገድዱ ሲሞክሩ ይህ ማለት አህበሽን እና ተሃድሶን በጥንታውያኑ እስልምና እና ተዋህዶ ላይ በኢትዮጵያ እንደተሞከረው ማለት ነው::

አክራሪነት አሉታዊ ትርጉም ሲኖረው የራስን እምነትና አመለካከት በሌሎች ላይለመጫን መሞከር ነው፡፡ ሃይማኖት መንግሥታዊ ቅርጽ ይዞ እንዲወጣ ለማድረግ መሞከር ራሱ አክራሪነት ነው፡፡ አክራሪነት የፖሊቲካ ገጽታ ያለው ነው፡፡ ኾኖም ግን ሃይማኖትን ማጥበቅ አክራሪነት አይደለም፡፡ሃይማኖት ፍጹም እውነታን በፍጹም እምነት ስለሚቀበል ከሌሎች ግላዊ አስተሳሰቦች የተለየ ነው፡፡ የሃይማኖት መገለጫዎችን መጠቀም የዚያን ሃይማኖት ጥልቀት የሚያሳይ እንጂ እንደ ችግርም የሚወሰድ ወይም አክራሪነት ሊኾን አይችልም፡፡ «መጾም፣ መጸለይ፣ ሥርዓተአምልኮን መፈጸም ለሃይማኖቱ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንጂ አክራሪነት ሊባልአይችልም፤» ይላሉ የዘርፉ ምሁራን፡፡

የአክራሪነትና የአጥባቂነት ፅንሰ ሐሶቦች በጥሩ ኹኔታ ተለይተው ተገልጸዋል፡፡ አንዳንድ ሰነዶች ወያኔም ለይስሙላ የገለበጣቸው ሰነዶቹ አክራሪነትንና አጥባቂነትን በአግባቡ ለይተውና ተንትነው ያስቀምጣሉ፡፡ በዚሁ መሠረትአጥባቂነትን፣ ‹‹የግል ሃይማኖትን ሃይማኖቱ በሚያዘው መሠረት ሳይንጠባጠብ ሁሉንም ትእዛዛት መፈጸም ነው፤» በማለት ሲፈታው አክራሪነትን ደግሞ፣ «ከራስ እምነት ወጥቶ ሌላውን መተንኮስና የሌሎችን ሃይማኖት መኖር አለማመንና አለመፍቀድወይም ሌሎቹን አስገድዶ የራስ እምነት ተከታዮች ለማድረግ መጣር ነው፤» ይላል፡፡ በተግባር ላይ አለመዋሉ እና በጣልቃ ገብነት መተርጎሙ ጉዳት አመጣ እንጂ::

ከዚህ ብያኔ ስንነሣ ክርስቲያንም ሆነ ሙስሊም ከርሱ ውጭ የኾኑትን የሌሎቹን መኖር የማይቀበልና ከግለሰቦቹ ፈቃድ ውጭ አስገዳጅ እስከኾነ ድረስ እርሱን አክራሪ ማለት ይቻላል፡፡መብትን መጠየቅ ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት መሸሽ አክራሪነት አይደለም:: በዚህ መልኩ አክራሪው ይህንኑ ድርጊት ሊፈጽም የተነሣውን ቡድን ብቻ እንጂ «አክራሪው ቡድን» የወጣበትን/የተገኘበትን ቤተ እምነት ሊወክል አይችልም፡፡ ስለዚህ በአለማቀፍ ደረጃ የአክራሪ ክርስትና እና እስልምና ቡድን መኖር የክርስትና እና እስልምና ተከታዮችን በሙሉ «አክራሪ» አስብሎ ሊያስፈርጃቸው አይችልም፤ ለሌላው ቤተ እምነትም እንዲሁ፡፡ ሃገሪቱን የሚያሰጋት የሃይማኖት አክራሪነት ሳይሆን የፖለቲካ የበላይነት የፈጠረው አሸባሪነት ጽንፈኝነት እና አክራሪነት ነው::ምንሊክ ሳልሳዊ

ቢሮክራሲያዊ ካፒታሊዝም የግለሰቦች አሻጥር ሲጨመርበት፣ ከቁጥጥር ውጪ ወደሆነ ደረጃ ይሸጋገራል፡፡ የሃገራችን ጉዳይ ሁላችንንም ያሳስበናል::


አገር ትልቅ ለውጥ ላይ ናት፤ ከፍተኛ የትራንስፎርሜሽን ሂደት ላይ ነን እየተባለ፤ በጐን የዝርፊያ የኮንትሮባንድ እና “በአንድ ጀንበር ፎቅ ሠርቼ ልደር” ዓይነት ዘመናዊ ምዝበራ ይታያል፡፡የጥፋት ድርጊት የሚፈጽሙ ወገኖች ለሀገር እንደቆሙ፤ የህዝብ ልጆች እንደሆኑ አድርገው መጮሃቸውና ሀቀኛ መምሰላቸው፤ ሌላው እንዳይናገር በር ይዘጋል፡፡ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ እንከኖቻችን ጥቅል ውጤት ማስጨነቁና ማሳሰቡ የሀገርና የህዝብ ስሜት ላለው ሁሉ አይቀሬ ነው፡፡ በተለይም ዱሮ የእጅ - እላፊ ይባል የነበረው የምዝበራና አገርን የማራቆት ተግባር፣ (ዛሬ ሙስና የተባለውን)፤ “ባንዱ ያለማ ባንዱ ያደለማ” ሆኗል፡፡ “በአንዴ ዘጋ/ዘጋች” ዛሬ የተለመደ ቋንቋ ነው፡፡ እንደነናይጄሪያና እንደነናይሮቢ (“ናይሮበሪ” እንደተባለው) ዐይን - ያወጣ የቀን ተቀን ዘረፋ የሚመጣው ከላይ እስከታች እየተወሳሰበ ያለው ሙስና ፍፁም ወደፈጠጠ ደረጃ ሲደርስ ነው፡፡

አንድም ሙስናው በየአቅጣጫው መሆኑ፤ አንድም ደግሞ ቢሮክራሲያዊ መጠቅለያ መኖሩ እጅግ ውስብስብ ያደርገዋል፡፡ (ዱሮ “ቢሮክራሲያዊ ካፒታሊዝም ይውደም” የሚል መፈክር ነበር፤ ነብሱን ይማረው!) በዚህ ላይ የግለሰቦች አሻጥር ሲጨመርበት፣ ከቁጥጥር ውጪ ወደሆነ ደረጃ ይሸጋገራል፡፡ የመሬት አሰቃቂ አወሳሰድ፣ ከፍተኛ የኮሚሽንና የድለላ ሥራ፣ አደገኛ ወገናዊ አሠራር…በአስደንጋጭ የድህነት መቀመቅ ውስጥ ለገባች አገር ከምትሸከመው በላይ ትከሻ አጉብጥ ሸክም ይሆንባታል፡፡ የባሰ ዘግናኝ የሚሆነው ደግሞ ከዕለት ወደ ዕለት በምዝበራ ምክንያት መታሰር ራሱ እየተለመደና ቀላል እየመሰለ መምጣቱ ነው፡፡ “እገሌ ታሠረኮ” ሲባል፤ “ተወው በልቷል - የሚበቃውን ቀለብ አከማችቷል” ማለት እንደሰላምታ የሚነገር መሆኑ አሳዛኝ ነው፡፡

ዱሮ “በሥራው አጋጣሚ በእጁ የገባውን የመንግሥት ገንዘብ ለግል ጥቅሙ በማዋሉ” የሚለው ሐረግ ነበር ሬዲዮንና ቴሌቪዥን ያጣበበው፡፡ ዛሬ ዳር እስከዳር በየሰው አፍ የሚወራ ነገር ሆኗል፡፡ ዝርፊያው ዓይነት በዓይነት ሆኗል፡፡ ተወርቶም በቀላሉ ይረሳል፡፡ በተለይ ለህብረተሰብ ቀጥተኛ መጥፊያ የሚሆኑ እንደመድሃኒት ያሉ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ባመቸው መንገድ ሁሉ ተበርዘው ከተባዙ፣ ምን ያህል አሰቃቂ የሆነ ዕልቂት እንደሚያስከትሉ መገመት አያዳግትም፡፡ የሚያስገኙት ገንዘብ የትየለሌ፣ የሚፈጁት ህዝብ የትየለሌ!!

ማናቸውንም የጥፋት ድርጊት የሚፈጽሙ ወገኖች ለሀገር እንደቆሙ፤ የህዝብ ልጆች እንደሆኑ አድርገው መጮሃቸውና ሀቀኛ መምሰላቸው፤ ሌላው እንዳይናገር በር ይዘጋል፡፡ ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮህ እንደማለት ነው፡፡ ጩኸቱ በቅጡ ለገባው አገር - ወዳድ ሰው ግን፤ “ቤቱን አቃጥሎ እንዴት ብሩህ ቀን እንደሆነ ተመልከቱ” አለ እንደተባለው ነው፡፡ ልዩነቱ ያኛው ለግሉ እየተጠቀመ፤ ይሄኛው የገዛ ንብረቱን ጭምር እያወደመ የሚጃጃል መሆኑ ነው፡፡ ሁለቱንም መዋጋት ተገቢ ነው!

የብኣዴን እና የኦሕዴድ ባለስልጣናት ቅርርብ ለሕወሓት አልተመቸውም::# "...አደጋ ውስጥ ነን::" የሕወሓት የደሕንነት መሪዎች የኦህዴድ ውስጥ ውስጡን መደራጀት ሕወሓትን አሳስቦታል::ምንሊክ ሳልሳዊ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ከፍተኛ የሆኑ የብኣዴን እና የኦሕዴድ ከፍተኛ ባለስልጣናት መቀራረብ እና አብሮ መዋል የሕወሓት ሰዎችን ማሳሰቡን እና የደህንነት ክትትል እያደረጉባቸው መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል:: ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከደመቀ መኮንን እና ከሙክታር ከድር ጀምሮ እስከ በታች የፌዴራል ባለስልጣኖች ላይ ከፍተኛ ስለላ እየተካሄደ መሆኑን ታውቋል::

ሃገሪቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሳለች ከፊታችን አደጋ ተደቅኗል::የሚሉ የተቆጡ ድምጾች በስፋት በእሕኣዴግ አባላት እየተሰሙ ያለበት አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው ሕወሓት በግል እና በጋራ ባለስልጣናቱ ላይ ከፍተኛ ማስፈራራት እና ዛቻ እያደረገባቸው መሆኑን የተናገሩት ምንጮቹ ኢሓዴግን ለመናድ ብትሞክሩ ሃገሪቷ ትበታተናለች ;እንደ ሱማሊያ መንግስት አልባ ሆና ትበጠበጣለች እያሉ ከማስፈራራትም አልፎ በግል የተነከራችሁበት ሙስና አደባባይ እናወጣዋለን:: እኛን ማንም ሊተይቀን አይችልም ቁልፉ እኛ ጋር ነው የሚሉ በኣደገኛ መርዞች የተሞሉ ማስፈራሪያዎች በመሰንዘር ላይ ናቸው ሲሉ ምንጮቹ ተናግረዋል::

የብኣዴን እና የኦሕዴድ ባለስልጣናት የየቀን ሪፖርት እና ግንኙነት በተመለከተ ማን ከማን ጋር እንደዋለ ማን እነማን ቤት እንደሄደ በመከታተል እየቀረበ ሲሆን የሃገሪቱን የደህንነት ቢሮ በጋራ የሚመሩት አቶ ጸጋዬ አቶ ጌታቸው እና ዶ/ር ደብረጺሆን በየቀቱ ለትግሪኛ ተናጋሪ ደህንነቶች በአጫጭር ስብሰባዎች መመሪያ እያወረዱ ከመሆኦኑም በላይ አደጋ ውስጥ መሆናቸውን እየደጋገሙ እንደሚናገሩ ምንጮቹ አክለዋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚህ ቀደም በእሕዴድ ወጣቶች የተጀመረው እና የሌንጮ ለታ ወደ አገር ቤት የሚለውን ዜማ ተከትሎ የለውጥ ጥያቄ እያንሰራራ መሆኑ ታውቋል:: በዚህም ምክንያት የኢሕኣዴግ አጋር ድርጅት የሆነው ኦሕዴድ ወጣት አባላት እና ለውጥ ፈላጊዎች ራሳቸውን ውስጥ ውስጡን እያደራጁ ነው በሚል ሕወሓት የድርጅቱን መዋቅር ሊበርዘው መሆኑ ተሰምቷል:: በተለያዩ ፖለቲከኞች ዘንድ ኦሕዴዶች ድምጻቸውን አጥፍተዋል እየተባለ ባለበት በዚህ ወቅት ሕወሓት አሳሳቢ ጉዳይ ላይ ነው ሲል ይነጋገርበት ጀምሯል::

በወጣቶቹ የኦሕዴድ አባላት መሃከል በተፈጠሩ መግባባቶች እስከመቼ ድረስ የፖለቲካ አሽከር ሆነን እንቀጥላለን የሚሉ የድርጅቱ ካድሬዎች በዙሪያቸው እየተቧደኑ ሲሆን ይህ ያሰጋው ሕወሓት የእነዚህ ሰዎች ዝምታ ይህን ሰሞን በአመራሮቹ ደረጃ በቢሮ ስብሰባ እየተነጋገረበት ይገኛል::

ጥርሳቸውን ነክሰው አድፍጠው ያሉት የኦሕዴድ አባላት በስልጣን ክፍፍሉ እና ራሳችንን መምራት ያለብን ራሳችን ነን በሚል እንዲሁም በተያያዥ የፖለቲካ ጉዳዮች በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል ያሉት የህዝብ ሃብቶች ላይ የሕወሓት ባለስልጣናት የሚሰጡት ውሳኔ እንደፖለቲካ ባርነት ነው የሚሉ ሮሮዎች በመደመጥ ላይ ሲሆኑ ነጻነታችንን መረጋገጥ አለብን የሚሉ ቢሊሶማ2 የተሰኙ ወጣት ባለስልጣናት ሕወሓትን አጣብቂኝ ውስጥ ከተውታል::ምንሊክ ሳልሳዊ

የብሔር ፖለቲካ አሳፋሪ ነው፡፡አንድነታችንን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ ብናተኩር ሁላችንንም ይጠቅመናል፡፡ኢትዮጵያ ምሳሌ ልትሆንበት የምትችልበት ነገር ሃይማኖት ብቻ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ከሰማንያ በላይ ብሔር ብሔረሰቦችን በውስጧ አቅፋ የያዘች አገር ናት፡፡ አይደለም ሰማንያ ቀርቶ ሁለት ብሔረሰቦች ያሉባቸው አገሮች ግጭት ውስጥ ሲገቡ እናያለን፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቃቅን ግጭቶች የሉም ማለት ባንችልም፣ በአጠቃላይ ግን ለመኖር የሚያዳግት ግጭት ግን አስተናግዳ አታውቅም፡፡ ይህ ታሪካችን የሚያኮራን ቢሆንም፣ አሁን አሁን ግን የሚስተዋሉት ነገሮች ሃይ ሊባሉ የሚገባቸው ናቸው፡፡ ስለአብሮ መኖር ታሪካችን የማንጠነቀቅለት ከሆነ ይህ አኩሪ ታሪክ ሊበላሽና ሊጠፋ ይችላል፡፡ በተለያዩ ወቅቶች በአገሪቱ ውስጥ በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚነሱ የብሔር ግጭቶች የጉዳዩን አሳሳቢነት ሊያሳዩን ይችላሉ፡፡ በተለይም አገሪቱ ተስፋ የምታደርግባቸው እነዚህ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጠባብ በሆነ የብሔር ፖለቲካ ውስጥ ገብተው ሲጋጩና ሲበጣበጡ ማየት አሳፋሪ ነው፡፡

ኢትዮጵያ የአማራ ብቻ አይደለችም፤ ኢትዮጵያ የኦሮሞ ብቻም አይደለችም፤ ኢትዮጵያ የደቡብ ብቻም አይደለችም፤ ኢትዮጵያ የትግራይ ብቻም አይደለችም፤ ኢትዮጵያ የሁሉም ናት፡፡ ስለዚህ አንዱ ብሔር ከአንዱ ብሔር አይበልጥም፡፡ አንዱ ብሔር ከአንዱ ብሔርም አያንስም፡፡ ሁሉም እኩል ነው፡፡ አንዱ ከአንዱ ይሻላል በሚል ጽንፈኛ የብሔር ፖለቲካ አንድነታችንን ማፍረስ አይገባንም፡፡ የሁሉም ብሔሮች መገኛ የሆነችውን ኢትዮጵያን መመልከት ይገባል፡፡ በዚህም ረገድ ራሳችንን መሳል ተገቢ ነው፡፡ ያለበለዚያ ግን በየጊዜው እየዶለዶምን ሄደን አንድነታችንን ልናጣው እንችላለን፡፡

ሃይማኖቶች በመርህ ደረጃ አይጋጩም፡፡ ሁሉም ፍቅርን፣ መተሳሰብንና ሰላምን የሚሰብኩ ናቸው፡፡ ስለዚህ ሁሉም የመረጠውን ሃይማኖት የመከተል መብት አለው፡፡ ነገር ግን የአንድ ሃይማኖት ጠበቃ ነኝ በሚል የሌላ ሃይማኖት ተከታዮች ላይ ምንም ዓይነት ተፅዕኖ ማድረግ ተቀባይነት የሌለው ድርጊት ነው፡፡ ሰዎች በሚከተሉት ሃይማኖትና በማንነታቸው ፈጽሞ ሊፈረጁ አይገባም፡፡ ምክንያቱም ከሁሉም በላይ ሰውነታቸው ይበልጣልና፡፡ ስለዚህ ሰዎች ሐሳባቸውን በማንፀባረቃቸው ምክንያት በጠላትነት ሊፈረጁ አይገባም፡፡ ምክንያቱም ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ሕገ መንግሥታዊ ብቻ ሳይሆን ተፈጥሯዊም ነውና፡፡ ጽንፈኛ የሆነ አመለካከት በመያዝ የእኔ መንገድ ብቻ ነው ትክክል ማለት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኋላቀር የሆነ ብቻ ሳይሆን የማያስኬድ ነው፡፡ ስለዚህ ራስን በአንድ ሳጥን ውስጥ ጨምሮ እኔ ብቻ ያልኩት ይሁን ማለት አንድነታችንን ሸርሽሮ በኋላ ባዶ ሊያስቀረን ይችላል፡፡ በመሆኑም በሃይማኖቱም ሆነ በፖለቲካው እንዲሁም በሌላውም ጉዳይ የእኔ ሐሳብ ብቻ ይንገሥ ማለት ማንንም የትም አያደርስም፡፡ ስለዚህ በየትኛውም ጉዳይ ላይ ጽንፈኝነትን በማስወገድ አንድነታችንን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ ብናተኩር ሁላችንንም ይጠቅመናል ፡፡ #ምንሊክሳልሳዊ

የወያኔ የውሸት ዘገባዎች ሲጋለጡ

“ኦክስፋም” በመልካም ሥራቸው ከታወቁ ትላልቅ ዓለም ዓቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አንዱ ነው። በቅርቡ አንድ መቶ ሀያ አምስት አገሮችን ያካተተ ከምግብ አቅርቦትና አጠቃቀም ጋር የተያያዘ ጥናት ውጤት ይፋ አድርጓል። ጥናቱ አራት ዝርዝርና አንድ አጠቃላይ አመላካቾች አሉት።

1. አመላካች አንድ: የምግብ እጥረት

ይህ አመላካች “በየአገሮቹ ምን ያህል ለበላተኛው የሚበቃ ምግብ አለ?” የሚለውን ይለካል። በጥናቱ ውጤት መሠረት በምግብ እጥረት እጅግ የተጎዱ የመጨረሻዎቹ አስር አገሮች የሚከተሉት ናቸው: – ቡሩንዲ፣ የመን፣ ቻድ፣ ኢትዮጵያ፣ ማዳጋስካር፣ ናይጄሪያ፣ ላኦስ፣ ባንግላዴሽ፣ መካከለኛዉ አፍሪካ ሪፑብሊክ እና ህንድ። ኢትዮጵያ አገራችን ከመጨረሻ አራተኛ ናት።

2. አመላካች ሁለት: ለምግብ የመክፈል አቅም (Affordability)

ይህ አመላካች “የአገሩ ሕዝብ በአገሩ ዋጋ ምግብ ገዝቶ ለመብላት ምን ያህል አቅሙ ይፈቅድለታል?” የሚለውን የሚመልስ ነው። አሁንም ከመጨረሻ እንጀምር። አንጎላ፣ ዚምባቡዌ፣ ቻድ፣ ጉያና፣ ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ፣ ኮንጎ፣ ኬንያ፣ ጋምቢያ እና ኢራን የየአገሩ ሕዝብ ምግብ መሸመት የሚቸገሩባቸው አገሮች ናቸው። አገራችን ኢትዮጵያ ከመጨረሻ አምስተኛ ናት።

3. አመላካች ሶስት: የምግብ ጥራት

ይህ የምግብ ይዘትንና የአያያዝ ንጽህናን የሚመለከት ሲሆን ኢትዮጵያ፣ ማዳጋስካር፣ሞዛምቢክ፣ ቻድ፣ ቶጎ፣ ዛምቢያ፣ ማሊ፣ ናይጄሪያ፣ ባንግላዴሽ፣ ሌሶቶ ከመጨረሻው እስከ አስረኛ ደረጃ ይዘዋል። ኢትዮጵያ በምግብ ጥራት የመጨረሻዋ አገር ናት።

4. አመላካች አራት፡ የሰውነት ውፍረት እና የስኳር በሽታ

ይህ አመላካች ከልክ ያለፈ ውፍረት ዓለም ዓቀፍ የጤና ችግር እየሆነ በመምጣቱ የገባ አመልካች ነው። ኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥሩ ውጤት ያመጣችሁ በዚህ አመላካች ብቻ ነው። ኢትዮጵያ አብዛኛው ሕዝቧ ቀጫጫ ነው፤ የስኳር በሽታም እንደሌላው አገር የተስፋፋባት አገር አይደለችም።

5. አማካይ ውጤት

የእነዚህ አራት አመላካቾች ድምር ውጤት አጠቃላይ ውጤትን ይሰጣል። በአጠቃላይ ውጤት: ቻድ፣ ኢትዮጵያ፣ አንጎላ፣ ማዳካስካር፣ የመን፣ ቡሩንዲ ናይጄሪያ፣ ሞዛምቢክ፣ ዚምባቡዌ፣ ሴራሊዮን ከመጨረሻ እስከ አስረኛ ወጥተዋል። ኢትዮጵያ ከመጨረሻ ሁለተኛ ነች።

ይህ ምንን ያመለክታል?

ወያኔ ባለፉት አስር ዓመታት በተከታታይ ከ11% በላይ ኢኮኖሚውን አሳድጌዋለሁ ሲለን ነበር። እድገቱ ያተኮረው ገጠር፤ ምንጩም ግብርና ነው ብሎን ነበር። ሐቁ ግን ከላይ የተመለከተው ነው።

እርግጥ ነው የወያኔ ሹማምንት በከተሞች ሕንፃዎችን ይገነባሉ፤ በገጠሮች በመቶዎች ሄክታር የሚለካ ለም መሬት ይዘው ፈጣን ገንዘብ በሚያስገኙ የአበባ፣ የጫትና የቃጫ ምርት ላይ ተሰማርተዋል። ከራሳቸውም አልፈው ሀብታም የውጭ አገራት ሸሪኮቻቸውን በአገራችን ለም መሬት ይበልጥ ያበለፅጓቸዋል። የእነሱ የግላቸው፣ የቤተሰቦቻቸው፣ የዘመዶቻቸው እና የሸሪኮቻቸው ኢኮኖሚ እየተመነደገ መሆኑን እናውቃለን። ይህን በገዛ ዓይኖቻችን የምናየው ሀቅ ነው።

ሆኖም ግን የእነሱ ኢኮኖሚ ማደግ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማደግ አለመሆኑ እናውቃለን። አገራችን ከጓረቤት አገሮች ጋር ስትነፃፀር ወደ ኋላ እየቀረች መሆኑ ያንገበግበናል። በቅርቡ አክስፋም በጥናት ያረጋገጠዉ የኢትዮጵያ ገበሬዎች በየቤታቸው ከወዳጆቻቸው ጋር በምስጢር የሚያወሩትን እውነት ነው።

ከሳምንት በፊት ደግሞ “ኢኮኖሚክ ኢንተለጀንስ ዩኒት” የተሰኘው ታዋቂ የምርምር ተቋም አንድ የጥናት ውጤት ይፋ አድርጎ ነበር። በዚህ የጥናት ውጤት መሠረት በዓለም በከፍተኛ ፍጥነት እያደጉ ያሉ አስር አገሮች በቅደም ተከተል ሞንጎሊያ፣ ሴራሊዮን፣ ቱርክሜንስታን፣ ቡታን፣ ሊቢያ፣ ኢራቅ፣ ላኦስ፣ ቲሞር-ሊስቲ፣ ኤርትራ እና ዛምቢያ ናቸው። በዝርዝሩ ውስጥ ኢትዮጵያ አገራችን የለችበትም።

በዓለም አቀፍ መድረኮችም የወያኔ መረጃዎች ውሸትነት እየተጋለጡ መሆናቸው በጎ ምልክት ነው። የሚያሳዝነው ግን ይህንን ሀቅ የሚያዉቁ ምዕራባዉያን ለጋሽ አገሮች አሁንም ወያኔን እየረዱና እየደገፉ ሥቃያችን የሚያራዝሙብን መሆኑ ነው።

ለዚህም ነው ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዘላቂ መፍትሔ ሊመጣ የሚችለው በአገራችን መሠረዊ የሆነ የአስተዳደር ለውጥ ሲኖር ነው ብሎ የሚያምነው። የወያኔ አገዛዝ በዲሞክራሲያዊ አስተዳደር እስካልተተካ ድረስ የኢትዮጵያ አብዛኛው ሕዝብ መደህየቱ፤ ጥቂት ሀብታሞች ደግሞ በብዙሀኑ ድህነት መበልፀጋቸው አይቀርም። የወያኔ ውሸቶች ለኢትዮጵያ ድሀ ምግብና መጠለያ አይሆኑለትም። ለኢትዮጵያ ዘላቂ ጥቅም ማምጣት የምንችለው ወያኔን አስወግደን በምትኩ ለሕዝብ ሁለተናዊ እድገት የሚጨነቅ መንግሥት መምረጥ ስንችል ብቻ ነው።

ስለሆነም ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በውሸት እድገት እያደናቆረን፤ በተግባር ግን እያደኸየን ያለውን ዘራፊውን ወያኔን አስወግደን በሕዝብ ነፃ ምርጫ የተመረጠ መንግሥት እንዲኖረን ትግላችን እናጠንክር ይላል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

ለስርኣቱ ቅርበት አላቸው ያሉ ምንጮች ወያኔ ወገቡ እንደተሰበረ እየተናገሩ ነው::

ወያኔ እየመራው የሚገኘው ኢኮኖሚ ተሽመድምዶ ሃገርን ረመጥ ላይ እየከተታት ሲሆን የወያኔ ሳቦታጅ ጥቂት ሰዎች በሃገር ሀብት በህዝብ ላይ እንዲፈነጩ አድርጓቸዋል::በሃገሪቱ ማንኛውም አይነት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ከበፊቱ በተለየ እና በባሰ ሁኔታ ተንኮታኩተው አፈር መልበሳቸው በይፋ ታውቋል::ለስርኣቱ ቅርበት አላቸው ያሉ ምንጮች ወያኔ ወገቡ እንደተሰበረ እየተናገሩ ነው::በፖለቲካው ረገድ የስርኣቱ ገዢ ፓርቲዎች እርስ በርስ አለመተማመን ደረጃ ላይ ከመድረሳቸውም በላይ አመራሮቹ አድፍጠው አንዱን አንዱን እየጠበቀ በፍራቻ አለም ውስጥ እየዋተቱ ይገኛሉ::አቤት የሚባልበት እየጠፋ ነው፡፡ የውሳኔ ሰጪ ያለህ ቢባል መልስ አይገኝም፡፡ ፋይሎች የሚያያቸውና የሚያነባቸው አጥተዋል፡፡ መልካም አስተዳደር ገደል ገብቷል::በአላማ ሳይሆን በጊዜያዊ የመኖር ሂደት ላይ የተመሰረተው የካድሬዎቹ ሩጫ ድካምን በመፍጠሩ ሁሉም በያለበት ቆም ብሎ እያሰበ ሲሆን አሳቡም የገፈፍኩትን ገፍፌ ሃገርን ድባቅ መትቼ ልሽሽ ሆኗል::

ገበናን ገበና ይገፈዋል እንደሚባለው የወያኔ ጁንታ በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ የገነባው ኢኮኖሚያዊ ገበና በገበና ተጋልጧል:: የማይሰማ ነገር የለም እና እኛም ሰማን አነበብን አየንም እነሆ ታዝበን ዝም አላልንም ገበናዎቹ ገበናውን ሲገልቡት አብረን አልሳቅንም ሀገር ነውና ገበናዎቹን ተመርኩዘን የምንለውን ልንል ይኸው ተከሰትን::

የስርኣቱ ቅርብ ምንጮች የሃገሪቱ ኢኮኖሚ በመሽመድመዱ ወያኔ ወገቡ መቆረጡን እና መምራት አለመቻሉን በለሆሳስ በመተንፈስ ኢኮኖሚው መንኮታኮቱን ሲናገሩ የንግድ ስራዎች ከፓርቲ ድርጅቶች ውሽ በታም ተዳክመው እና ሞተው ያሉ ሲሆን የገንዘብ እንቅስቃሴዎች ጭራሽ ገደል መግባታቸውን እና ደንበኞች በባንኮች ላይ ያላቸው አመነታ በመጥፋቱ ግንኙነቶች መልፈስፈሳቸው በይበልጥ ለግል ባንኮች መዳከም ምክንያት ሆነዋል ሲሉ ይህ ደሞ አሉ የገንዝብ እንቅስቃሴውን ገድሎታል:: ምንሊክ ሳልሳዊ በጣም ድብን ያለ እውነት ነው::በውጭ ምንዛሪ ችግርና እጥረት ምክንያት በጣም የሚያስፈልጉ ዕቃዎች እንደተለመደው ከውጭ እየገቡ አይደለም፡፡ በጥቂቱ የመጡ ካሉም ዋጋቸው የማይቻል እየሆነ ነው፡፡ ብለውም አክለው አስቀምጠዋል::

ወያኔ አስፈላጊውን ገንዘብ ባለማግኘቱ ፕሮጀክቶች የቆሙ የተጓተቱ ሲሆን የሚሰበከው እድገት ለፕሮፓጋንዳዊ የሚዲያ ፍጆታ ብቻ መሆኑ ተረጋግጧል::ወያኔ የፋይናንስ ጥያቄውን ሊጨብጠው አይደለም ሊዳስሰው አልቻለም::በኢንቨስትመንት እንሰማራለን ብለው የመጡ የውጭው አለም ሰዎች በቢሮክራሲው መንተክተክ የተነሳ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ ትብብር ማግኘት አለመቻላቸውን ከመናገራቸውም በላይ የጀመሩት ኢንቨስትመት እንደሚቋረጥ የወያነ ባለስልጣናት እንደሚያስቆሟቸው እና ለምን ሲሉ መልስ የሚሰጣቸው አከል እንደሌለ እና ጨረታ ካሸነፉ በኋላ እንደሚሰረዝ ለማን እንደሚሰጥ እንደማያውቁ አማረው እየተናገሩ ነው::

ሌላው የሃገር ውስጥ ታዋቂ ነጋዴዎችን ጨምሮ የወያኔ ባላባቶች ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እያሸሹ መሆኑ ነው::የተረፈ ካለ ደሞ ወደ ባንክ ከመውሰድ ይልቅ ቤጅ መያዝ እየተመረጠ መቷል::አገር ውስጥ ደሞ ከማስቀመጥ ይልቅ ውጪ አገር መላክ እየተለመደ መቷል::ምንሊክ ሳልሳዊ አገር ውስጥ ባለው የውጭ ምንዛሪ ክምችት ላይ ተጨማሪ ጉልበት ሊፈጥር የሚገባው የውጭ ምንዛሪ ግኝትም ውጭ እንዲቀር እየተደረገ ነው፡፡ የገባ ካለም በጥቁር ገበያ እንደገና እንዲወጣ እየተደረገ በመሆኑ አገሪቱ ተጠቃሚ መሆን አልቻለችም፡፡ብለዋል የስርኣቱ ታማኞች:; ይህ የሚያመለክተው ዜጎች በፖለቲካው ጉዞ ላይ እምነት እንዳሌላቸው ሲሆን እየተሽመደመደ እና እየደቀቀ ያለው የፖለቲካ ስራቲ ምንም ለውጥ ሊያመጣ አለመቻሉ ሰዎች በወንጀለኝነት ሳይሆን በአስተሳሰባቸው ወህኒ መውረዳቸው የፈጠረው ስጋት ነው:: ምንሊክ ሳልሳዊ

ዜጎች በህግ ላይ እና በንጽህናቸው ላይ ከመተማመን ይልቅ የህግ የበላይነት ከመጥፋቱ አንሳር እጅግ ፍርሃት ውስጥ በመግባታቸው የተማሩ እና በንግዱ አለም የተሰማሩ ሁሉ አፍርሃት ከመርበድበዳቸው እና ከመሰደዳቸው በላይ አሉ የተባሉትም ወያኔ በሙስና ባልደረቦቹ ላይ ፖለቲካዉ ገጀራ ሲያሳርፍ እየተመለከቱ ስራ በማቆም ከመደናበራቸውም ሌላ በራሳቸው አለመተማመን ያለባቸውን ጨምሮ በሙስናው ከባለስልጣናት ጋር የተነከሩ ሲሆን ሌሎች ደሞ እስከሚጣራ ለምን ልታሽ በሚል ባለው የፖለቲካ አመራሩ ላይ እምነት በማጣት የንግዱን ስራ ገለውት ከሃገር በመሸሽ ላይ ናቸው::

የተጭበረበረ አፋኝ ፖለቲካ ያስከተለው የኢኮኖሚ መንኮታኮት የአገሪቱን የፖለቲካ አናቶች ለውጥ እንዳያመጡ በመተብተብ ቀውስ ውስጥ የከተታቸው መሆኑን ከስብሰባዎች እና ከጭብጨባዎች ብዛት እየታዘብን ነው::በሌላ በኩል ሚዲያዎች ህዝብን መዋሸታቸው እና ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ መዋላቸው አገሪቷ እንድትንኮታኮት በር የከፈተ ሲሆን የዚህ መፍትሄ ስልጣን መልቀቅ ወይንም ሁሉን ህዝብ ያሳተፈ አዲስ ለውጥ እና ፖሊሲ ማጽደቅ ነው::ምንጭ በአደባባይ ወያኔን ይህን መርፌ የወጋቹህልንን (ያድነው/አያድነው) ባይታወቅም ውስጥ አዋቂዎች እናመሰግናለን::
ምንሊክ ሳልሳዊ