ፕሮፌሰር መስፍን እና አቶ ስብሃት ነጋ “እብድና ዘበናይ እንደልቡ ይናገራል”

ፕሮፌሰር መስፍን እና አቶ ስብሃት ነጋ “እብድና ዘበናይ እንደልቡ ይናገራል”
Postby MINILIK SALSAWI » Thu Feb 06, 2014 1:44 am
Image

ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያም “አይ ስብሃት ነጋ!” በሚል ርዕስ ባለፈው ሰሞን በኢንተርኔት ያሰራጩት ጽሑፍ ነው። ጽሁፉ በጋዜጦችም ላይ ታትሞ ይሆናል። ፕሮፌሰር መስፍን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከአንድ ገጽ ባልበለጡ ማስታወሻዎች የሚወረውሯቸው ሃሳቦች ከመጠናቸው በላይ እንደሚናገሩ ማስተዋል ይቻላል።

“አይ ሀበሻ! ሀበሻና ሆድ” በሚል ርእስ እንደ የጻፉት ዓይነቶቹ በብዙዎች ዘንድ ባለመወደዳቸው ጫጫታን መፍጠራቸውም ታይቷል። በበኩሌ (በውስጣቸው መረን የለቀቁ ስድቦችን ባይጨምሩ ኖሮ) የአንዳንዶቹ ማስታሻዎች ሃሳቦች የምጠላቸው አይደሉም። እንዲያውም በነካ እጃቸው “ሀበሻና ስንፍና፣ ሀበሻና ፈሪነት፣ ሀበሻና አቋራጭ መንገድ ፈላጊነት፣ ሀበሻና አሉባልታ፣…” በሚሉ ርእሶች ተጨማሪ ማህበራዊ ሂስ ቢያቀርቡ ጥሩ ነበር የሚል ምኞት አለኝ።

ይሄ እንደተጠበቀ ሆኖ ለዚህ ጽሁፍ መነሻ ወደሆነኝ የፕሮፌሰር መስፍን ጽሑፍ እናምራ። ለነገሩ “አይ ስብሃት ነጋ!” የሚለው ጽሁፍ ለዚህ መጣጥፍ መነሻ ሆነኝ እንጂ፤ በአጠቃላይ በፕ/ር መስፍን ጽሁፎች ላይ ለዘመናት ሳስተውለው የኖርኩትና ሊታረም የሚገባው ጉዳይ አለ። “አይ ስብሃት ነጋ!” በሚለው ጽሁፍም ላይ የሚስተዋለው ይኸው ነው።

ፕሮፌሰር መስፍን “አይ ስብሃት ነጋ!” በሚል ርእስ ያዘጋጁትን ጽሁፍ “የሚቀድሱት” በስድብ ነው። እንዲህ ይላሉ፤ “በኢትዮጵያ ስልጣን ሳይኖረው ባለሙሉ ስልጣን፣ እውቀት ሳይኖረው ባለሙሉ እውቀት የሆነ ሰው ስብሃት ነጋ ብቻ ነው። እንዲያውም ከዚያም አልፎ ራሱን የቻለ ሉዓላዊነት ያለው ግለሰብ ነው…” ይላሉ። ይህንን አባባላቸውን ግን እንደ ምሁር በምሣሌ አስደግፈው፣ በማስረጃ አንተርሰው በማቅረብ እንድናምናቸው አያደርጉንም። ማሳመኑም ይቅር! ግን እርሳቸው ራሳቸው ከአቶ ስብሃት የተሻሉ ናቸው ወይ? አይመስለኝም!

ፕሮፌሰር መስፍንን ከ1992 ዓ.ም ጀምሮ በቅርበት፣ ከዚያ በፊት ደግሞ በዝና አውቃቸዋለሁ። አቶ ስብሃትስ የፓርቲም የመንግስትም ስልጣን አያጡም። የመንግስትም፣ የፓርቲም፣ የእድርም፣ ስልጣን ሳይዝ፤ ባለስልጣናትን፣ ፖለቲከኞችን፣ ጋዜጠኞችን፣ ተማሪዎችን፣ እንደ እኔ ያለውን ተራ ዜጋ እና አልፎ ተርፎ ፈጣሪን ጭምር የሚሳደብ፣ የሚያንጓጥጥ፣ የሚያሽሟጥጥ፣ የሚዘልፍ፣… ከፕሮፌሰር መስፍን የሚበልጥ ሰው በሀገሪቱ ይገኛል? በኔ እምነት ሪከርዱ በእጃቸው ነው!

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ማስረጃ ለማቅረብ ብዙ ርቀት መኳተን አያስፈልግም። ይቺን ጽሁፍ ከማዘጋጀቴ በፊት በቅርብ ጊዜያት የተሰናዱ የፕሮፌሰሩን አስር መጣጥፎች አይቼ ነበር። በሚገርም ሁኔታ በአስሩም ላይ በተደጋጋሚ ያየሁት “ደደብ፣ ደንቆሮ፣ እውቀት ሳይኖረው፣ መሃይም፣…” የሚሉትን የስድብ ቃላት ነው። አቶ ስብሃትንም “እውቀት ሳይኖረው አዋቂ የሆነ” ይሏቸዋል። ለመሆኑ ፕሮፌሰር መስፍንን እውቀት ያለውንና የሌለውን ሰው አረጋጋጭ ተቋም ያደረጋቸው ማን ነው? ከአቶ ስብሃትና ከእርሳቸው “ስልጣን ሳይኖረው ባለሙሉ ስልጣን” የሆነውስ ማን ነው? ፍርዱን ለአንባቢ ልተወው!!!

በነገራችን ላይ አቶ ስብሃት በምጣኔ ሀብት (ኢኮኖሚክስ) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መመረቃቸውን ሰምቻለሁ። የፕፌሰር መስፍን ሊቅነትም ቢሆን በመልክዓ-ምድር (ጂኦግራፊ) እንጂ በዓለም ላይ ባሉ የእውቀት መስኮች ሁሉ ባለመሆኑ የሌሎችን እውቀት በአግባቡ ለመመዘን “ብቃት አላቸው” ብሎ ለመቀበል አስቸጋሪ ነው። ስለሆነም፣ ክቡር ፕሮፌሰር! በአቶ ስብሃት ዓይን ውስጥ “አለ” የሚሉትን ጉድፍ ሲጠቁሙ በራስዎ ዓይን ውስጥ የሚስተዋለውን ግንድ ዘንግተውታልና ልብ ቢሉት መልካም ነው እላለሁ።

እንዲያው የእውቀት ነገር ከተነሳ አይቀር አንድ ነገር ማለት ወደድሁ። እኔ እንደሚገባኝ እውቀት ማለት የአንድን ማህበረሰብ ችግር ለመቅረፍ የቻለ እንደሆነ እንጂ ሦስት አራት ዲግሪ ተሸክመው ራስን “በሊቅነት” ተራራ ቢያሳክሉት ትርጉም ያለው አይመስለኝም። በዚህ ረገድ አቶ ስብሃትንና ፕ/ር መስፍንን በማነጻጸር ውጤቱን ማየት እንችላለን። አቶ ስብሃት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመረቁ፣ በተለያዩ ት/ቤቶች አስተማሩ፣ በቢሮክራሲውም ውስጥ (በገንዘብ ሚኒስቴር) ጥቂት ሰሩና የመጡበትን ማህበረሰብ ‘ከጭቆና አወጣለሁ’ ብለው ጫካ ገቡ። የፖለቲካ ድርጅት መሰረቱ። መሪም፣ ተራ ተዋጊም፣ ሰላይም፣ ካድሬም፣ ዘበኛም፣ ሽማግሌም፣… ሆነው አገለገሉ። ምንም ይሁን ምን የተነሱለትን ዓላማ ለድል አበቁ። ስልጣንም፣ ሹመትም አገኙ። ፕሮፌሰር መስፍንስ?

ፕሮፌሰር መስፍንም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመረቁ። እዚያው አስተማሩ፣ እዚያው ተመራመሩ፣ እዚያው ሊቅ (ፕሮፌሰር) ሆኑ።… ደርግ ሊወድቅ አካባቢ “የሽማግሌ መንግስት” ለማቋቋም ሞከሩ - አልተሳካም ከሸፈ! የሰብአዊ መብት ድርጅት አቋቁመው ጥሩ ስራ በመስራት ላይ ሳሉ ለውጤት ሳያበቁት በጅምር ተውት - አሁንም ክሽፈት! የፖለቲካ ፓርቲዎችን አስታርቃለሁ ብለው ተነሱ። ይሄም አልተሳካም - ክሽፈት! ቀስተ ደመና የተሰኘ ፓርቲ አቋቋሙ። ፓርቲውን ለውጤት ማብቃት ሲገባቸው ይሄ እንደማይሳካላቸው ገና ከጅምሩ ሲገባቸው “አሻሮ ይዞ ወደ ቆሎ” እንደተጠጋው ብልጥ አንድ ወር ያልሞላው ፓርቲ ይዘው እንደ መኢአድ ካሉ ፓርቲዎች ጋር ተቀናጅቼ እሰራለሁ አሉ። በመሀል ላይ ይሄም እንደማይሳካ ሲረዱ “ቅንጅቱ የቅቤ ገበያ ሁኗል” በማለት ከአመራርነት ራሳቸውን አገለሉ። ምርጫው ተቃርቦ ነገሩ ሲጋጋልና ፖለቲካው ሲደምቅ ወደ ፖለቲካው እንደገና ተመለሱ። … ታሰሩ… በይቅርታ ተፈቱ… ታመሙ… ዳኑ… እንደገና ፓርቲ አቋቋሙ… ተጣሉ… መርህ ይከበር አሉ… እያለ ይቀጥላል ታሪካቸው። ውጤቱስ - ምንም! - ሌላ ክሽፈት!!! የአንድ ሰው አዋቂነት የሚለካው ባስመዘገበው ውጤት ነው የምንል ከሆነ ከአቶ ስብሃትና ከፕሮፌሰር መስፍን ባለሙሉ እውቀት ሊባል የሚችለው ማን ነው ታዲያ? ፍርዱን አሁንም ለአንባቢ እተወዋለሁ።

ወደ ሌላ ጉዳይ እናምራ። ፕሮፌሰር መስፍን “አይ ስብሃት ነጋ!” በሚል ርእስ በጻፉት ጽሁፍ ውስጥ “በኢትዮጵያ ስልጣን ሳይኖረው ባለሙሉ ስልጣን፣ እውቀት ሳይኖረው ባለሙሉ እውቀት የሆነ ሰው ስብሃት ነጋ ብቻ ነው” ከሚለው ቀጥሎ ያሰፈሩት ሃሳብ “…[ስብሃት ነጋ] እንዲያውም ከዚያም አልፎ ራሱን የቻለ ሉዓላዊነት ያለው ግለሰብ ነው” የሚል ነው። በዚህም ረገድ ቢሆን፤ በአፄ ኃ/ስላሴም፣ በደርግም ይሁን በኢህአዴግ የአስተዳደር ዘመን “ራሱን የቻለ ሉዓላዊነት ያለው ግለሰብ” ከፕሮፌሰር መስፍን ውጪ ፈልጎ ማግኘት የሚቻል አይመስለኝም። ፕሮፌሰሩ በሦስቱም መንግስታት “ሉዓላዊነታቸውን” አረጋግጠው የኖሩ ሰው ናቸው።

ፕሮፌሰር መስፍን ለየትኛውም ስርዓት እጅ ሳይሰጡ ሃሳባቸውን እንደልባቸው እየተናገሩ መኖራቸውንና መብትና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ያደረጉትን ጥረት አደንቃለሁ። ነገር ግን እንደ እርሳቸው ሁሉ ሌሎች ሰዎችም “የእኔ” የሚሉት ፍላጎት፣ እምነትም ሆነ አመለካከት ያላቸው መሆኑን ዘንግተው ወይም ሆነ ብለው በጉልበታቸው የተቀዳጁትን “ሉዓላዊነት” በመጠቀም የሌሎችን መብት ለመጨፍለቅ ሲፍጨረጨሩም ለዘመናት ተመልክቻለሁ። ለዚህ አባባሌ ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ ሁለት ምሣሌዎችን ላቅርብ።

የመጀመሪያው ማስረጃ ከአቶ ስብሃት ጋር የተያያዘ ነው። ፕሮፌሰር በፈለጉት ሰዓት፣ በፈለጉት መድረክ ላይ ብቅ ብለው መንግስትንም፣ ኢህአዴግንም፣ አቶ ስብሃትንም ወይም ሌላ ግለሰብን ወይም ፓርቲ ይተቻሉ። ከትችትም አልፈው ደስ በሚላቸው (ከእሳቸው በማይጠበቅ) ቋንቋ ጭምር ይሳደባሉ፣ ያንቋሽሻሉ፣ ይዘረጥጣሉ፣ ያጣጥላሉ፣…። እርሳቸው እንደዚያ በማለታቸው “ለምን እንዲህ ብለህ ጻፍክ ወይም ተናገርክ” ያላቸው የመንግስት አካል ስለመኖሩ በእርግጠኛነት ለመናገር እቸገራለሁ። ምክንያቱም ፕሮፌሰር መስፍን በጻፉት ጽሁፍ ተከሰሱ ሲባል አልሰማሁም። እርሳቸውስ?

አቶ ስብሃት አንድ መድረክ ላይ ተገኝተው “እንዲህ አሉ” መባልን ሲሰሙ ፕሮፌሰር ፀጉራቸውን ይነጫሉ። “ደፋሩ፣ ደንቆሮው፣ እውቀት የለሹ፣… ስብሃት እንዴት እንዲህ ይላል? እሱ እንደልቡ ተናጋሪ ነው! ማን ከልካይ አለው!...እንዴት?... እንዴት?...” የሚል መንፈስ ያለው ሃሳብ ሲሰነዝሩ ይታያሉ። “እኔ የምናገረው ሁሉ ለሀገር ይበጃል፣ አንድም ስህተት የለውም። እናም እንደፈለግኩ መናገር እችላለሁ። ስብሃት ግን በሃገሩ ምንም ዓይነት ጉዳይ ላይ መናገር አይችልም” መሆኑ ነው ነገሩ!!!

‘የተሳሳተ ነው’ የሚሉትን የማንንም ሰው ሃሳብ መተቸት፣ አቃቂር ማውጣት አንድ ነገር ነው። እርስዎ በፈለጉት ጉዳይ ላይ እንዳሻዎት እየተናገሩ ሌሎች አይናገሩ ማለት ግን ተገቢ አይመስለኝም። እንዲያው ለነገሩ እርስዎ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር አብሮ መሄድ ያለበትንና የሌለበትን ሰው እንዲመርጡና ቀጭን ትእዛዝ እንዲያስተላልፉ ስልጣን የሰጠዎት ማን ነው? እርስዎ ከመሬት እየተነሱ እከሌ ደደብ ነው፣ እውቀት የለውም፣… የማለት ስልጣን ያቀዳጀዎትስ እኮ ማን ነው?

ፕሮፌሰር መስፍን ራሳቸውን በራሳቸው የሾሙበትን ሁለተኛውን ምሣሌ ላቅርብ። ከምርጫ 97 በኋላ በቅንጅት ውስጥ የነበረው የሃሳብ ክፍፍል አለቅጥ በጦዘበት ወቅት አንዱን ጓደኛዬን ፕሮፌሰር መስፍን ቤታቸው ድረስ እንዲመጣ ካደረጉ በኋላ “ስማ! ይሄ እከሌ የሚባለው ጓደኛህ በ24 ሰዓታት ውስጥ ሃሳቡን ካልቀየረ በጋዜጦች ላይ በመጻፍ በሕዝብ እንዲጠላና እንዲወገዝ አደርገዋለሁ” እንዳሉት ያኔውኑ እየበረረ መጥቶ ነበር ያጫወተኝ። ታዲያ ከዚህ በላይ ራስን የሉዓላዊ ስልጣን ባለቤት አድርጎ መሾም አለ? ታዲያ ከዚህ በላይ ራስን በመንግስት ውስጥ ያለ መንግስት (A state within a state) አድርጎ መሾም አለ? ፕሮፌሰር መስፍን የኢትዮጵያን ሕዝብ በጋዜጣ ላይ ወጥተው ተነስ ሲሉት የሚነሳ፣ ተቀመጥ ሲሉት የሚቀመጥ፣ ፀጥ ለጥ ብሎ፣ እርሳቸው እንዳሉት ሆኖ የሚገዛ ሳይመስላቸው አይቀርም። ያ ባይሆን ኖሮ ከላይ እንደተጠቀሰው ‘ሕዝቡ አንቅሮ እንዲተፋው አደርጋለሁ’ የሚል ደፋር ሃሳብ አይሰነዝሩም ነበር።

ስለፕሮፌሰር መስፍን ሳስብ በርካታ ነገሮች ግርም ይሉኛል። በአንድ በኩል የሰዎች ሰብአዊ መብት እንዲከበር፣ ሰዎች ሃሳባቸውን በነፃነት እንዲገልጹ እታገላለሁ ይላሉ። ይሄ ጥሩ ነው -የተቀደሰ ሃሳብ! በሌላ በኩል፤ አንዳንድ ሰዎች እርሳቸው የማይወዱትን ወይም የማይደግፉትን ሃሳብ ሲናገሩና ሲጽፉ ደግሞ “የተሳሳተ ነው” የሚሉትን ሃሳብ አንጥረው በማውጣት እንደ ምሁር መተቸት ሲገባቸው የሃሳቡን ባለቤት ቁምስቅሉን ያሳዩታል። እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ አድርገው ያዋርዱታል። ለምን ተናገርክ፣ ለምን ጻፍክ ብለው ይዘልፉታል፣ ያብጠለጥሉታል። እንዲህ ያለው ሁኔታ አንድ ጊዜ፣ ሁለት ጊዜ ቢሆን ምንም አልነበረም። እድሜ ልካቸውን እንዲህ ያለ (Double Standard የሆነ) አቋም ማራመድ ትዝብት ላይ የሚጥል ነው። ከአንድ ምሁርም የሚጠበቅ አይመስለኝም።

የ“Double Standard”ን ነገር ካነሳሁ አይቀር ሌላ ምሣሌ ልጨመር። ፕሮፌሰር መስፍን የቀድሞው ቅንጅት አመራር አባል በነበሩበት ወቅት በ“ቅንጅት” ዙሪያ የተሰባሰበው ኃይል በርካታ ጊዜውን የሚያጠፋው በንትርክና በጭቅጭቅ መሆኑን ሲያዩና ይህ ኃይል አንድ ሆኖ በመስራት ውጤት ላይ እንደማይደርስ ሲገባቸው ከምርጫው በፊት ከ”ቅንጅት አመራርነት” ለመውጣት በጻፉት ማመልከቻ ያቀረቡት ምክንያት “ቅንጅት የቅቤ ገበያ ሆኗል። እኔ በዚህ አካል ውስጥ ሆኜ የታሪክ ተጠያቂ መሆን አልሻም” የሚል እንደነበር አስታውሳለሁ። አቶ ልደቱ መጽሐፍም ላይ ይኸው ተጠቅሷል።

የሚገርመው ነገር እርሳቸው ሊኖሩበት ያልፈለጉትን “ቅንጅት” እነ አቶ ልደቱ የራሳቸውን ምክንያት አቅርበው “በቅቤ ገበያው ውስጥ መሆን አንፈልግም” ሲሉ ደግሞ የጊዜ ገደብ (Ultimatum) በማስቀመጥ በጋዜጣ እጽፍባችኋለሁ አሉ። ነገሩ እኔ የፈለግኩትን፣ ደስ ያለኝን፣ ያሻኝን፣… አደርጋለሁ፣ ሉዓላዊ ነኝ…። እናንተ ግን ይህንን የማድረግ መብት የላችሁም፣ እኔ በምላችሁ መንገድ ሂዱ ነው። ታዲያ ይሄ ከ“Double Standard”ነት አልፎ አምባገነንነት አደለም?

ፕሮፌሰር መስፍን በአቶ ስብሃት ነጋ ላይ ወዳነሱት ሌላ ጉዳይ እናምራ። “[አቶ ስብሃት] በሉዓላዊነቱ የተጎናጸፈውን ስልጣን ሙሉ በሙሉ ይጠቀምበታል። ይቆጣኛል ወይም ይቀጣኛል ብሎ የሚፈራው የለም። ስብሃት ነጋ የሚፈራው ምንም ነገር የለም…” ይላሉ። ይህንን የፕሮፌሰር መስፍንን ሃሳብ ሳነብ ከት ብዬ ነው የሳቅኩት። እንዲህ ብሎ የሚጽፍ ወይም የሚናገር ሰው “ፈሪሐ እግዚአብሔር ያለው፣ ለነፍሱም ለስጋውም ያደረ፣ ለታላላቆቹ፣ ለእኩዮቹና ለታናናሾቹ ተገቢውን ሰብአዊ አክብሮት የሚሰጥ ሰው መሆን እንዳለበት አምናለሁ። ፕሮፌሰር መስፍን ግን እንዲህ ያለውን ኢትዮጵያዊ ሥነ-ምግባርና ግብረ-ገብነት ይናገሩት እንደሆነ እንጂ በተግባር ሲገልጡት ታይቶም ተሰምቶም አያውቅም።

የእኒህን ሰው ተግባራት ልብ ብዬ ሳስተውል በርግጥ እኒህ ሰው በወላጆቻቸው ተቆንጥጠውና ተገስፀው፣ በኢትዮጵያዊ ባህልና ወግ ታንጸው ነው ያደጉት? የሚል ጥያቄ ድቅን ይልብኛል። በበኩሌ፣ ፕሮፌሰር መስፍን ከአቶ ስብሃት በባሰ መጠን “ይቆጣኛል ወይም ይቀጣኛል ብለው የሚፈሩት” ምድራዊ ኃይል እንደሌለ በጥሩ ሁኔታ አስተውያለሁ። እናም አቶ ስብሃት ላይ ‘አየሁ’ የሚሉትን ግድፈት መጀመሪያ ከራስዎ ላይ እንደ አሮጌ ቁና አሽቀንጥረው ይጣሉ ፕሮፌሶሬ!

አሁንም ወደ ሌላ የፕሮፌሰር መስፍን እና የአቶ ስብሃት ጉዳይ እናምራ። “ስብሃት ነጋ የተናገረው ነገር ትክክል ይሁን አይሁን ጉዳዩ አደለም። ዋናው ነገር መናገሩ ነው” ይላሉ። እርስዎስ ፕሮፌሰር? እውነት ከአቶ ስብሃት የተሻሉ ነዎት? ለመሆኑ እርስዎ አስቦ መናገሩ ይቅርና የተናገሩት ትክክል ስለመሆኑ ነገሩ ካለፈ በኋላ አስበውት ያውቃሉ? እርስዎ በምንም ጉዳይ ላይ የሚሰነዝሩት ሃሳብ ሁሉ ትክክል፣ ሌሎች የሚናገሩት ግን ምንም ይሁን ምን ስህተት ተደርጎ የሚወሰደው በየትኛው መመዘኛ ነው?

አቶ ስብሃት ሰው ናቸው። እናም አቶ ስብሃት የሚናገሩት ሁሉ ትክክል ሊሆን እንደማይችል አስባለሁ። ያም ቢሆን የተሳሳተውን ሃሳብ ነቅሶ በማውጣት ‘ይሄ ይሄ ስህተት ነው’ ይባላል እንጂ አቶ ስብሃት የተናገረው ሁሉ ስህተት ነው ብሎ መደምደም ትክክል የሚሆንበት ሥነ-አመክንዮ (Logic) የለም። በኔ እይታ ከፕሮፌሰር መስፍን ይልቅ የሚናገሩትን የሚያውቁት አቶ ስብሃት ናቸው። አቶ ስብሃት ምንን መቼ መናገር እንዳለባቸው ጭምር አስበው እንደሚናገሩ አስተውያለሁ። እንዳመጣላቸው የመዘርገፉ ሁኔታ የሚታየው በፕሮፌሰር መስፍን ዘንድ ነው ባይ ነኝ። ፕሮፌሰር መስፍን ጥንቆላ ጀምረው ካልሆነ በስተቀር “ስብሃት ነጋ የተናገረው ነገር ትክክል ይሁን አይሁን ጉዳዩ አይደለም” የሚል ሃሳብ ባልሰነዘሩም ነበር።

ፕሮፌሰር መስፍን “…[ዮ]ናስ አበበ እንደሚነግረን ‘አቶ ስብሃት ነጋ የውጭ ሰው እንዳይገባ ከተማሪዎቹ ጋር ተደራድረው ነበር’….” ካሉ በኋላ “ስብሃት ይህንን ያደረገው ‘ብቻውን ተናግሮ በጭብጨባ የሚሸኝበት መድረክ በመፈለጉ [እና] በከባድ ጥያቄ… የሚያጣድፉት ሰዎች እንዳይኖሩ’…” መሆኑን ይነግሩናል። እንዲህ ዓይነት የ‘ሳይሆን አይቀርም’ መላምት የሚያነሳ ሰው እንዲህ ያለ ተግባር የመፈጸም ልምድ እንዳለው መጠርጠር ፕሮፌሰሩ በሄዱበት መንገድ መንጎድ ስለሚሆን መተውን መረጥኩ።

እንዲያው ለነገሩ አንድ ሰው የሚከራከርበትን ወይም ሀሳብ የሚያቀርብበትን መድረክ “እንዲህ ያለ ገጽታ ይኑረው” ቢል ሀጢያቱ ምኑ ላይ ነው? ይህንን የማለት መብት የለውም ሊሉን ነው ፕሮፌሰር?! በሰለጠኑት ሀገሮችም እኮ “ድምጼም ምስሌም እንዳይቀረጽ፣ ፎቶም እንዳልነሳ” የሚል ቅድመ ሁኔታ የሚያስቀምጡበት አሰራር አለ። አንዳንዶቹ እንዲያውም ንግግር እንዲያደርጉ ሲጋበዙ ይህንን ፍላጎታቸውን የሚገልጹበት ፎርም እንዲሞሉ ይደረጋል። ታዲያ አቶ ስብሃት መከራከርም መነጋገርም የምፈልገው (ብለው ከሆነ) ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር ብቻ ነው የማለት መብት የላቸውም ነው የሚሉን ፕሮፌሰር መስፍን? እንዲህ ያለ የመብት ጥያቄ ማንሳት በየትኛው ሎጂክ ነው ከጥያቄ መፍራትና ከጭብጨባ መፈለግ ጋር ሊገናኝ የሚችለው? በበኩሌ “ሌባ እናት ልጇን አታምንም” የሚለውን ብሒል ከማስታወስ የዘለለ ትርጉም ያለው ሆኖ አልታየኝም። ይህንን ‘ቅድመ ሁኔታ’ ያቀረበው ፕሮፌሰር መስፍን የሚያውቁት ሰው ቢሆን ኖሮ፤ ይኸኔ እርሳቸው ሲያሞግሱትና ሲያወድሱት ይገኙ ነበር።

“ስብሃት ነጋ ዋና ዓላማው በሙሉ ነፃነት የመጣለትን እንደመጣለት መናገር ነው” ይሉና ምሣሌዎችን ይደረድራሉ ፕሮፌሰር መስፍን። እንደመጣለት በመናገር ረገድ እውን ፕሮፌሰር መስፍን ከደሙ ንፁህ ነኝ ብለው ጣታቸውን በሌሎች ላይ ለመቀሰር ይችላሉ? በበኩሌ አይመስለኝም። ይህንን አባባሌን ለማስረገጥ እስቲ የሚከሉትን አብነቶች እንይ።

ኢህአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ፣ “አማራ የሚባል ብሔር/ሕዝብ የለም” አሉ ፕሮፌሰር መስፍን። ነገሩ የአንድ ሰሞን ወሬ ሆኖ አለፈ። ከጥቂት ዓመታት በኋላ አሁንስ አማራ የለም ወይ? የሚል ጥያቄ ሲቀርብላቸው ደግሞ “አሁን እንኳ አማራ የሚባል ሕዝብ/ብሔር እየተፈጠረ ነው” አሉ። “የለም” የተባለው አማራ በአጭር ጊዜ እንዴት ሊፈጠር እንደቻለ ባይገባንም ይህንንም ሰምተን አለፍነው። በምርጫ 97 ለቅስቀሳ ወደ ትግራይ ሄዱና “የትግራይ ሕዝብ በፋብሪካ እንደወጣ ሣሙና…” ነው የሚል ሃሳብ መናገራቸውን ሰማን። … ሌሎችንም ምሣሌዎች መጥቀስ ይቻላል። ታዲያ በአቶ ስብሃትና በፕሮፌሰር መስፍን መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?

ሁለቱም የሚያምኑበትን ይናገራሉ። በዚህ ረገድ ፕሮፌሰር መስፍን አቶ ስብሃትን “እንደመጣልህ ተናጋሪ ነህ” ብለው ለመክሰስም፣ ለመውቀስም ሆነ ለመተቸት የሚያስችል የሞራል ብቃት ያላቸው ሆኖ አይታየኝም። ‘እኔ እንደመጣልኝ ብናገርም እችላለሁ፣ ስብሃት ነጋ ግን አይችልም’ እያሉን ከሆነ ፕሮፌሰር ጤናቸው መመርመር አለበት ባይ ነኝ። ፕሮፌሰር ስለኤርትራውያን ሰብአዊ መብት ቋሚ ጠበቃ ሆነው ሲከራከሩ ትክክል፣ አቶ ስብሃት ስለኤርትራውያን ኢትዮጵያዊነት ሲናገሩ ስህተት የሚደረግበትም አግባብ ትክክል አይመስለኝም።

ፕሮፌሰር መስፍን አቶ ስብሃት ነጋን “እንደመጣለት የሚናገር፣ ዘባራቂ፣ ሳይማር የተማርኩ ነኝ የሚል፣… ወዘተረፈ” ማለታቸውንም ከዚሁ ጽሁፋቸው አንብቤአለሁ። የፕሮፌሰር መስፍን የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪነት አልፋና ኦሜጋ እንግዲህ ይሄ ነው! አቶ ስብሃት “ወያኔ” ስለሆኑ ሰብአዊ ክብር አያስፈልጋቸውም እያሉን እንዳይሆን ፕሮፌሰሩ! ድንቄም የሰብአዊ መብት ተሟጋች! ከመሬት ተነስተው በአደባባይ፣ በጋዜጣ፣ በመጽሔት፣ በኢንተርኔት ላይ የሰውን ሰብእና እያጎደፉ፣ ሰድበው ለሰዳቢ አሳልፈው እየሰጡና እያዋረዱ የሰዎች መብት ተቆርቋሪ መሆን የሚቻል አይመስለኝም። እንዲያ የሚሉ ከሆነ ፌዝ ነው!

አቶ ስብሃት ስለሰሚያዊ ፓርቲ ሰልፍ መከልከል ተጠይቀው “አላውቅም” ማለታቸውንም ፕሮፌሰር መስፍን “አላውቅም ማለት ለመዘላበድ ይጠቅማል” በማለት አቶ ስብሃትን ይዘልፋሉ። ወይ ፕሮፌሰር መስፍን! አላውቅም ማለት መዘላበድ የሚሆነው በየት ሀገር ነው ፕሮፌሰር?! ሲናገሩ “እንዳመጣለት የሚናገር” ማለት፤ “አላውቅም” ሲሉ “መዘላበድ ነው” ማለት ምን የሚሉት አማርኛ ነው? ለፕሮፌሰር መስፍን “መዘላበድ” የሚለው ቃል በትክክል ገብቷቸው ይሆን? ሽቅብ ወደ ላይ መናገር በወሎ አማርኛ “ያርማጃ ልጅ!” ያሰኘኛል ብዬ ሰጋሁ እንጂ መዘላበድ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማስረዳት ጥሩ ምሣሌ ነበረኝ። ‘ወይ ነዶ የሐመር ጌታ’ አለ ሰውየው!

ስለ ፕሮፌሰር መስፍን እና ስለ አቶ ስብሃት ጉዳይ ከዚህ በላይ ባልቀጥል ጥሩ ነው። ይሁን እንጂ፣ ጽሁፌን ከመቋጨቴ በፊት አንዳንድ የማጠቃለያ ነጥቦችን ላንሳ። ፖለቲከኛ በነበርኩባቸው ዓመታት አንድም ቀን አግኝቻቸው ከማላውቃቸው የኢህአዴግ ባለስልጣናት አንዱ አቶ ስብሃት ነጋ አንዱ ናቸው። ከአቶ ስብሃት ይልቅ ከፕሮፌሰር መስፍን ጋር የቅርብ ግንኙነት ነበረኝ።

ይህንን ጽሁፍ ያዘጋጀሁት ለአቶ ስብሃት ጥብቅና ለመቆም ወይም ልዩ ፍቅርና መቆርቆር ስላደረብኝ አይደለም። ይህንን ጽሁፍ ያዘጋጀሁት በፕሮፌሰር መስፍን ላይ የተለየ ጥላቻ ስላደረብኝም አይደለም። ፕሮፌሰሩ የዛሬ ዘጠኝ ዓመት ገደማ “አብዱራህማንና ጓደኞቹ” እያሉ፣ ከደርግ አባላትና ከመንግስቱ ኃ/ማሪያም ጋር እያነጻጸሩ፣ በ“ሳይሆን አይቀርም” ጥርጣሬ የሌለብኝን ነውር እየደረደሩ በሰባት ጋዜጦች ላይ (እርግጠኛ ነኝ ዛሬ የሚያፍሩበትን) ጽሑፍ ጽፈውብኝ እንኳ አቅሙም ጉልበቱም እያለኝ መልስ አልሰጠኋቸውም ነበር። በሳቅ በፈገግታ ነበር ያለፍኳቸው።

ለአቶ ስብሃትም ለፕሮፌሰር መስፍንም ልዩ አክብሮት አለኝ። ሁለቱም ለኢትዮጵያ ያስፈልጓታል ባይ ነኝ። ሁለቱም በሚያቀርቧቸው አንዳንድ ሃሳቦች እስማማለሁ። ሁለቱም በሚሰነዝሯቸው አንዳንድ አስተያየቶች ደግሞ አልስማማም። ጠቤም፣ ፍቅሬም፣ ጥላቻዬም ሆነ ቅያሜዬ ከሚያፈልቋቸው ሃሳቦች ጋር እንጂ ከእነርሱነታቸው (ከሰብእናቸው) ጋር አይደለም። ሁለቱም በአባትነት መንፈስ፣ በታላቅነት አግባብ የማያቸው ወንድሞቼ ናቸው።

ሁለቱም በሃሳብ መሻኮታቸውን፣ መፋጨታቸውን፣ መጋጨታቸውንም ሆነ መቆራቆሳቸውን እፈልገዋለሁ። ምክንያቱም ከሁለቱ ሰዎች የሃሳብ ፍጭት ሀገርና ሕዝብ የሚጠቅም አንዳች ነገር ሊፈልቅ ይችላል የሚል ግምት አለኝና ነው። ይሁን እንጂ፣ የሃሳብ ፍጭቱም ሆነ ግጭቱ ፍፁም ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን በተላበሰ መንፈስ፣ የሁለቱንም ሰብእናና ክብር ሳይነካ፣ ያላቸውን ኃላፊነት፣ ዕድሜ፣ ክብርና ሞገስ በጠበቀ መልኩ፣ ታናናሾቻቸውንና አዲሱን ትውልድ በሚያስተምር አግባብ፣ ከመናናቅና ከጥላቻ በራቀ ሁኔታ፣… ሊቀርብ ይገባዋል የሚል እምነት አለኝ።

ለወደፊቱም ቢሆን ፕሮፌሰር መስፍን የሰውን ሃሳብ ከመተቸት አልፈው ሰብእናን በሚነካ ሁኔታ “ደንቆሮ፣ አላዋቂ፣ ቂል፣ እውቀት የለሽ፣ ዘላባጅ፣…ወዘተ.” ብሎ መሳደብ፣ መዝለፍም ሆነ ማንጓጠጥ የእርሳቸውን “ሊቅነት” አያረጋግጥም። ለክብራቸውም አይመጥንም። ሳይሳደቡ ማስተማር እኮ ይቻላል።

‘ተማሪ የሚገባው ሰድበው ሲነግሩት ነው’ ከሚል ለዘመናት የገነገነ የፊውዳል አስተሳሰብ መውጣት ይኖርባቸዋል ባይ ነኝ። በዚህ መጣጥፍ ላይ ባነሳሁዋቸው ሃሳቦች ተበሳጭተው ፀጉራቸውን ከመንጨት ይልቅ፤ ሰው በመሆናቸው አንዳች ጉድለት ሊኖራቸው እንደሚችል (የእድሜአቸው ማምሻም ላይ ቢሆን) ቆም ብለው በማሰብ ራሳቸውንና የመጡበትን መንገድ በመመርመር በቀጣይ ጊዜያት ጨዋ ጨዋ ሃሳቦችን በጨዋ ቋንቋ በማቅረብ የእስከዛሬውን ጉድለት እንዲያካክሱ አመለክታለሁ።

ክቡር አቶ ስብሃትም ቢሆኑ አንዳንዱ መድረክ ላይ ብቅ እያሉ ሌሎች ክርክር ሊያደርጉበት በማይችሉበት ሁኔታ ሃሳባቸውን “እንደወረደ” መዘርገፉን ለአፍታ ቢያስተውሉት መልካም ነው። መቼም ሁሉም ሰው እርሳቸው ባሉበት ደረጃና መጠን ሊያስብ እንደማይችል የሚጠፋቸው አይመስለኝም። እናም እርሳቸው ባላቸው ግንዛቤ ልክ ሊያስብ ያልቻለን ሁሉ ‘በንቀት’ ከመመልከት ይልቅ፤ በረጋ ሁኔታ በመናገር እንዲያውቀው፣ እንዲያየውና እንዲገነዘበው ቢያደርጉ እነ ፕሮፌሰር መስፍንንም ፀጉር ከመንጨት ያድኗቸዋል ባይ ነኝ።

አበው “እብድና ዘበናይ እንደልቡ ይናገራል” ቢሉም በበኩሌ ሁለቱንም በእብድነት አልጠረጥራችሁም። የመጠን ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ሁለታችሁም እንደልባችሁ የምትናገሩ ዘበናዮች ለመሆናችሁ ግን ጥርጥር የለውም። ለሁለታችሁም እድሜና ጤና ይስጥልኝ!!!
Image
MINILIK SALSAWI

ህግ እና ስርኣት ለባለስልጣናት የሚገዛበት አገር ..

በሃገሪቱ የተፈጠሩ ስብርባሪ ህወሓት መራሽ መንግስታት የህዝቦችን የመኖር መብት ደፍጥጠዋል::

ምንሊክ ሳልሳዊ : ባለስልጣናት ለህግ እና ለስርኣት ተገዢ አለመሆናቸው ህግና ስርኣት ለእነሱ ተገዢ እንዲሆን ማድረጋቸው ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ነው;: የህግን የበላይነት ማረጋገጥ የተሳነው ስርኣት የወለዳቸው ስብርባሪ ህወሓት መራሽ መንግስታት የህዝቦችን የመኖር መብት ደፍጥጠዋል::በሃገራችን ውስጥ ላለፉት 22 አመታት ተንሰራፍቶ ያለው የአንድ ፓርቲ ህገወጥ አገዛዝ ለህዝቦች ነጻነት የሚከፈለውን መስእዋትነት እንደ መንግስት ሳይከፍል ህዝብን በማሸበር እና በማወናበድ የህግ የበላይነትን ደፍጥጦ ለስልጣኑ ብቻ እየተራወጠ ይገኛል::በሃገሪቱ የህግ የበላይነት የተከበረ ጊዜ ስልታንህ ያበቃል የተባለ ይመስል ከበላይ ባለስልጣናት ጀምሮ እስከ በታች ካድሬዎች ድረስ የህግን የበላይነት ክደዋል:: ማንም ማንንም ማዘዝ በማይችልበት እና የተሰባበሩ ትንንሽ በንግስታት በራሳቸው ሂደት የተፈጠሩባት ኢትዮጵያ ባለስልጣናቱ መናበብ አለመቻላቸው ህዝቡ በፍትህ ላይ ተስፋ ከቆረጠ ውሎ አደረ አድሮም ኖረ::

የአንድ ሃገር ህግ የህዝብን ትኩሳት እና ጥያቄዎች ይዞ መጓዝ ሲኖርበት በሃገራችን ግን የህግ የበላይነትን የፖለቲካ ትኩሳቶች እያሽመደመዱት እንዳይከበር እና እንዲደፈጠጥ እያደረጉት ይገኛሉ:; አንድ ህዝብ ባላረቀቀው እና ባላጸደቀው ህግ ሲገዛ የህግን ትርጉም እንደማያውቅ ታሳቢ አድርጎ በህዝብ ነጻነት ላይ የሚደረጉ የፖለቲካ ጨዋታዎች እንኳን በበሰለው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ይቅር እና በሌላውም ባልሰለጠነ ህዝብ ላይ ሊተገበር መድፈር ራስን እንደመናቅ ይቆጠራል:: ወያኔ ራሱ አርቅቆ እና አጽድቆ ህጎችን በማውጣት ከፈለገም በመሻር በመቀየር በመገለባበጥ በመተርጎም ህዝቦች የራሳቸውን መብት እና ነጻነት እንዳያገኙ በከፍተኛ ደረጃ መሸራረፎችን እየፈጠረ ነው::ምንሊክ ሳልሳዊ

ባለስልጣናት የወንበር ግዝፈታቸውን ተጠቅመው የተለያዩ ውሳኔዎችን ትእዛዞችን ተግባራትን በስልክ በደብዳቤ በቀላጤ ወዘተ የህግን ስርኣት ባልተከተለ መልኩ እያሽከረከሩት ከህግ የበላይነት ላይ በድንፋታና በትእቢት በመጓዝ ላይ ሲሆኑ ይህንን ያየ የበታች ካድሬ እንዲሁ ህግን እና ስራትን ባልትየከተለ መንግድ የህዝቦችን ህልውና ገደል ከቶታል:: ከበላይ ባለስልጣናት ባልተናነሰ እንዲሁም በበለጠ ማለት ይቻላል የወያኔ ካድሬዎች እና ተባባሪዎቻቸው በአገሪቱ ላይ ስርኣት አልበኝነት እና ህገወጥነት እንዲሰፍን እየሰሩ ነው::ይህ ደግሞ ህዝብ በስርኣቱ ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ አድርጎታል::

በከፍተኛ ደረጃ ህግን እየበረዙ አድርገው በሙስና የተዘፈቁ የወያኔ ባለስልጣናት እና ደጋፊ ታዛዥ ካድሬዎቻቸው በሃገሪቱ ራሳቸው ያወጡትን ህግ ራሳቸው እየጣሱ የሚገኙ ሲሆን በራሳቸው ህግ ራሳቸው እንደሚጠየቁበት እየዘነጉ መሆኑን አለማወቃቸው ለህዝብ ያላቸውን ንቀት ያመለክታል::የምናነበው ሕጉና የምንመለከተው ተግባሩ የተለያየ ነው፡፡በሙስና ከተዘፈቁበት አንዱ የመሬት እደላ እና አሰጣጥ ነው መሬትን በተመለከተ ህጉ የሚለውን የሚከተል ባለስልጣን ማግኘት አስቸጋሪ ነው ህጉን የሚያስፈጽም ካድሬ ሹመኛም ማግኘት አይታሰብም::ይህ ማለት ደሞ ሁሉም ከመሬት እደላ ጋር በተያያዘ ህጉን ተከትለው የሚሰሩት ሳይሆን የግለሰቡ ብሄር እና የፋይናንስ አቅም ተመልክተው ይፈጽሙለታል:; ለእውነት እና ለሃገር የሚሰራ ኢንቨስተር ከአከባቢው ይነቀላል ሌባው እና ሙሰኛው ኢንቨስተር በአደባባይ በመንግስት ባለስልጣናት እንክብካቤ ይደረግለታል አፋሽ አጎንባሽ ካድሬዎችን ይበዙለታል::

የህግ የበላይነት በሃገሪቱ አለመስፈኑ ኢኮኖሚውን ከማንኮታኮቱም በላይ ባለስልታናት በዝርፊያ እና በሽሽት ላይ እንዲያተኩሩ አድርጓቸዋል::ህዝቡም ይህን ተከትሎ እንዲሁም በፖሊሶች በደህንነት አባላት በቅጥረኛ የመንግስት አሸባሪዎች በጥቂት የከተማ ወታደራዊ ኮማንዶዎች ህግ ሲጣስ እየተመለከተ ስለሆነ አንድም መንፈሱ ሲጎዳ ሌላም አለው ስርኣት ላይ አመኔታ በማጣቱ ድምጹን እንዲቋጥር አስገድዶታል::በሃገሪቱ የፍትህ አካላት ላይ የመንግስት ባለስልጣናት ጣልቃ ገብነት የፖለቲካ የበላይነት መከሰቱ ህዝቦች አንገታቸውን በፍትህ አካላት ፊት እንዲሰብሩ እንዲሸማቀቁ አድርጎታል::

በየመንግስት ተቋማት፣ ከሚኒስቴር ጀምሮ እስከ ተራ የቀበሌ ካድሬ ቢሮ ጠረጴዛ፣ በፍርድ ቤቶች እና በፍትህ አካላት ፍትሕ የተነፈጉ፣ ሕገ መንግሥትና ሥርዓት እንዲከበር የሚጠይቁና አቤት የሚሉ በርካታ መዝገቦች ሰሚ ጆሮ አጥተዋል፡፡ ለሕግና ለሥርዓት ቅድሚያ የሚሰጥ አዕምሮ፣ ጆሮና ዓይን ተነፍገዋል፡፡ ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ምንሊክ ሳልሳዊ ሕገ መንግሥቱና ሕግ ያስገድዳሉ፡፡ቢሆንም ምንም አይነት መልስ ሲሰጣቸው ይሁን ሲገመገሙ ታይቶ አይታወቅም በተዋረድ የመንግስት አሰራር አለመኖር በስልክ እና በቀላጤ ህግ እየተጣሰ ከህዝብ በሚሰበሰብ ግብር የሚተዳደሩት ፖሊስ እና የፍትህ አካላት በግለሰቦች ትእዛዝ ህዝባዊ ሂደቶችን ሲያመክኑ ህግን ሲጥሱ ህገወጥ እርምጃዎች ሲፈጸሙ ከህግ ውጭ የህዝቦችን መብት ሲደፍሩ እየታየ መንግስት ነኝ የሚለው አካል ዝምታን መርጧል::ይህ ደግሞ የሚያመለክተው በሃገሪቱ ውስጥ ስብርባሪ ትንንሽ መንግስታት መፈጠራቸውን ነው::ባለስልጣናት ለህግ እና ለስርኣት ተገዢ አለመሆናቸው ህግና ስርኣት ለእነሱ ተገዢ እንዲሆን ማድረጋቸው ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ነው;: እነዚህ ስርኣቱ የወለዳቸውን ባለስልጣናት እና ካድሬዎች ከኢትዮጵያ ምድር ወደ ከርሰ መቃብራቸው ከቶ ህዝብን ለነጻነት ለማብቃት በጋራ መታገል ግዴታችን መሆኑን አውቀን በአንድነት ስርኣቱን ማስወገድ ማንኛውም ሃገሬን እወዳለሁ የሚል ዜጋ ሊነሳለት እና ሊተገብረው የሚገባ መሆኑን ለማስገንዘብ እወዳለሁ::ምንሊክ ሳልሳዊ

ወገን ሳይኖር፣ አጋር ሳይኖር፣ በዙሪያ ደግ - አሳቢ ሳይኖር፤ ሹመት የዛፍ ላይ እንቅልፍ ነው! ጣጣው የማያልቅ ችግር ለትውልድ ይተርፋል፡፡

Horror: Rwandans view bodies during the country's horrific genocide in 1994
ጣጣው የማያልቅ ችግር ለትውልድ ይተርፋል፡፡ በትምህርት ከሀ እስከ ፐ መጓዝ የማይናቅ መሆኑ ባይካድም፤ ውጣ - ውረዱ፣ መከራው ሰቆቃው አይጣል ነው፡፡ ችግርን ከምንጩ መንቀል ብልህነት ነው። ከፊደልም ከህይወትም መማር ሙሉ ያደርገናል፡፡ ለለውጥ ዝግጁ የምንሆነው አንድም ዕውቀታችን ወደ ጥበብ ሲበስል፤ አንድም ለአዲስ ነገር አዕምሮአችን ክፍት ሲሆን፤እንዲሁም ከስህተታችን ለመማር እንችል ዘንድ ግትርነትን ስናስወግድ ነው፡፡
በሀገራችን የታሪክ ሂደት፤ ትግል፣ ድርድር፣ ዕርቅና ስምምነት፣ ጠቅልሎ ገብቶ ከመንግሥት ጋር መሥራት፣ መጣላትና መክዳት አዘውትረው የታዩ ክስተቶች ናቸው፡፡

በተለይ መከዳዳት እጅግ ተደጋግሞ የታየ ነው፡፡
“ወዳጅን አንዴ መክዳት ይቻላል ሁለት ጊዜ ግን አይቻልም” ትግል ሲከር፣ ዘመን ሲከዳ፣ አቋም ሲሟሽሽ፣ ተስፋ ሲጠፋ፣ በተለይም ወኔ ሲከዳ፤ አሊያም አቋም ሲለወጥ፤ እናት - ክፍልን ትቶ ወደሌላ ሠፈር ይገባል፡፡ መደራደር፣ ዕርቅና መስማማት ከጦርነት እኩል ሜዳ ላይ ናቸው ይባላል፡፡ ጂኬ ቴስተርተን እንደሚለን “መደራደርና መስማማት ማለት ግማሽ ዳቦ ማግኘት ከምንም ይሻላል ነበር፡፡ አሁን ግን በዘመናዊ መንግሥታት ዘንድ ግማሽ ዳቦ ከሙሉ ዳቦ ይሻላል በሚል ተለውጧል”፡፡ ተደራድሮ አንድ ነገር ማግኘት ታላቅ ነገር ነው፡፡ ሆኖም መደራደርን እጅ ከመስጠትና ከክዳት ለይቶ ማየት ያሻል፡፡ ከማጐብደድ መለየት የስፈልጋል፡፡

ደራሲና ፀሐፌ - ተውኔት ፀጋዬ ገ/መድህን “በምኒልክ” ተውኔቱ ያለውን አለመርሳት ደግ ነው። “ሸዋም ያው ያባት ልምዱን፣ የባህል ግብሩን፣ በጐበና ሹመት ላይ አጉተመተመ፡፡ አጉረመረመ፡፡ ያኑ የሆድ ክፋት ቅርሱን፣ ምሱን፣ የምቀኛ ተውሳኩን፣ ውስጥ ውስጡን አቀረሸ፡፡ “ማናቸውን ንጉሥ እንበል?!” እያለ፤ ይሄ አዲሱ ጐበና፣ የልቼው ሳይሆን፣ ራሱን እንደንጉሥ ላስጠራ ባይ ተቆናኝ ሆኗል፤ መሾሙንስ ምኒልክ ሾመው፣ መሻሩንስ ማን ይሽርለት ይሆን? እያለ…”

ወገን ሳይኖር፣ አጋር ሳይኖር፣ በዙሪያ ደግ - አሳቢ ሳይኖር፤ ሹመት የዛፍ ላይ እንቅልፍ ነው! በእርግጥ አያሌ ከእናት ፓርቲያቸው የተለያዩ የጥንት የጧት ሰዎች እናውቃለን፡፡ ምናልባትም እነሱም የራሳቸው ምክንያት ይኖራቸው ይሆናል፡፡ ለአንድ የእንግሊዝ ፓርላማ ቀዳማዊት ኤልሣቤጥ አደረጉት የሚባል ንግግር ላይ “እንደኔ ከሆነ፤ ለምን መኖርን መውደድ እንዳለብኝ ወይም ለምን መሞትን መፍራት እንዳለብኝ አንዳችም ምክንያት የለኝም፡፡ የዚህችን ዐለም በቂ ልምድ አግኝቻለሁ፡፡ ዜጋ መሆንም፤ መሪ መሆንም ምን ማለት እንደሆነ አውቄያለሁ፡፡ መጥፎም ጥሩም ጐረቤት ኖሮኝ ያውቃል፡፡ ስለዚህ በራሴ ዕምነት መክዳት ጥሩ እንደሆን ተገንዝቤአለሁ፤ ብለዋል፡፡ ደግና ክፉ መለየት ያለበት ራሱ ባለቤቱ ነው።

የዱሮም ይሁን የአሁን ወዳጅ፣ ከጊዜ በኋላ፤ አቋም ለውጠው ሲገናኙ እንዴት እንደሚገናኙ፣  እንዴት እንደሚወያዩ፤ ግራ ሊገባቸው ይችላል፡፡ ሆድ ለሆድ ተግባብተው? ተቂያቂመው? ወይስ ይቅር ለእግዚሃር ተባብለው፤ ስለአገር ጉዳይ ተስማምተን እንሥራ ተባብለው?

በየትኛውም የሹመት ደረጃ ብንሆን፤ አገርን የሚጐዳ ከሆነ ሥልጣን በቃኝ ማለት መክዳት አይደለም የእንግሊዝ ተወላጁ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዴ ሀይለኛ ግምገማ ተደርጐ አይምሬ የሆነ ግልጽ ሂስ ሲካሄድባቸው፤ “እኔምኮ ዶሮ እስኪጮህ ነበር የምጠብቀው ሥልጣኔን ለመልቀቅ” አሉ፤ አሉ፡፡ የፖለቲካ ሥልጣንን፤ ተዋግተንም እናምጣው፣ በሰላማዊ ድርድር፤ አሊያም ደጅ ጠንተን፤ ዳገት ቁልቁለት የሌለበት፣ በወርቅ አልጋ፣ በእርግብ ላባ ላይ መተኛት ነው ብሎ ማሰብ፤ ቢያንስ የዋኅነት ነው። ምንሊክ ሳልሳዊ

የኢትዮጵያችን ችግር የሃገር ችግር ሳይሆን የህዝቦች የጋራ የሆነ እና ገዢዎች የሚፈጥሩት የፖለቲካ ካንሰር ነው:: የፖለቲካ ካንሰራችንን ተጋግዘን ከማዳን በሽሙጥና ... እስከመቼ??


ምንሊክ ሳልሳዊ :-በሃገሪቱ የተከሰተውን ደዌ ከማዳመጥ ይልቅ በሽሙጥ አንዱ አንዱን እየወገረው በመብረር ላይ እንገኛለን :; እርስ በእርስ ከመወጋገር ያድነን እንዳንል እየተወጋገርን ጸሎት ለቅጽበት ነው::ማን ከማን ይማር ሎሌ ከንጉሱ ሆኖብን ሆነና የራሳችንንም ሆነ የሃገራችንን ህመም ተጋግዘን እንዳናድን ራሳችን በሽታ ሆነናል::ምን እንደተባልን እንኳን ማዳመጥ አለመቻላችን አንዱ ደንቃራችን ሲሆን የምንናገረውንም ከማንነገርው መራርጠን መተንፈስ እስኪያቅተን ድረስ እያቃተትን በሽታችንን እያባስን ብዙሃዊ ተላላፊ ህመም አድርገነዋል ከዚህ ይሰውረን እንዳንል ራሳችን አሁንም ደንቃራ ሆነናል::

የኢትዮጵያችን ችግር የኢትዮጵያ የሃገር ችግር ሳይሆን የህዝቦች የጋራ የሆነ እና ገዢዎች የሚፈጥሩት የፖለቲካ ካንሰር ነው::ልዩነት እንዳለ ሆኖ በጋራ ሃገራዊ መርህ ላይ ያልተመሰረተ ፖለቲካ እንዴት ህዝባዊ መተሳሰብ ሊፈጥር እንደሚችል በሃገራችን የሚገኙ ፖለቲከኝኣ ነን የሚሉ አልተረዱትም ወይንም አውቀው እየተባሉ እያባሉን እያነካከሱን ነው:: በጋራ መተሳሰብ ላይ ያልተመሰረተው ፖለቲካችን እና በመጭበርበር የሚያጭበረብሩን ገዢዎቻችን ለነገ ሃገር ተረካቢ ትውልድ አደገኛ የሆነ የፖለቲካ በሽታ እያወረኡ ይገኛሉ የፖለቲካ በሽታ ብቻ ሳይሆን በአንድ ወጥ መርህ ላይ የተመሰረተ እና የደቀቀ ኢኮኖሚ ጭምር:: ይህ በተጭበረበር ፖለቲካ ላይ የተገነባ ኢኮኖሚ የህዝቦችን የጋራ መደጋገፍ ቢተይቅም ገዢው መደብ በፍጹም ከኔ ውጪ የሚነካ ካለ እሳት እንደነካ ነው በማለት በፍራቻ ላይ የተመሰረተ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ዜጎች በሃገራቸው ብሄራዊ አጀንዳ ጉዳይ እንዳይሳተፉ እንዳይተሳሰቡ እንዳይደጋገፉ እንቅፋት ሆኖ ይገኛል::ከማህበረሰቡ ተገልሎ እየተሰራ ያለውን ውጤት እያየነው ነው:: የገዢው ፓርቲ አይን እንዲገለጽልን ሱባዬ እየገባን ልናሳስበው የምንወደው ነገር ቢኖር ሃገር በምታድግበት ጊዜ መቀመቅ እየከተታት እንደሚገኝ ነው::

በሃገራችን በመጀመሪያ ደረጃ ሁሌ ለገዢዎቹ የሚኒነግራቸው ቢኖር የህግ የበላይነት እንዲከበር ነው:: የስልጥኣን እድሜ ለማስረዘም ሲባል በሃገሪቱ ገንዘብ የተገዙ የፓርቲ ካድሬዎች በህዝቡ ላይ ከህግ በላይ በመሆን አሳር እና አበሳ እያሳዩን ሲሆን ይህንንም ከተራ ዜጋ ጀምሮ እስከ ሃይማኖት መሪዎች ድረስ አበቱታ እያሰሙ የህግ ያለህ የመንግስት ያለህ እያሉ ነው::ሲታይ ግን ምንም መፍትሄ ያለው አይመስልም ይህ ደግሞ መንግስት ነኝ የሚለው አካል የስርኣት ለውጥ ማምታት እንዳለበት ሲያመለክት ለውጡን ተከትሎ ህግና ደንብ ሊከበር እንደሚችል የሚታወቅ እና የተጠና ነው::በዚሁ ከቀጠለ ግን አገር ከገባችበት አደጋ ወደ ሌአል አደገኛ አደጋ እንደምትሸጋገር ልመናገር እወዳለሁ:: ሌላው የተንሰራፋው ሙስና የሃገር ሃብትን በተገቢው ቦታ ላይ እንዳናውል እንቅፋት ሆኗል:: ሁልኡም በተደጋጋሚ የምንነገረው ታግለው ስልታን እንደያዙ የሚደነፉት የወያኔ ጁንታ አባላት በሙስና ውስጥ ተዘፍቀው አገሪቷን እርቃኗን አስቀርተዋታል:: ይህ አደገኛ የሙስና ሂደት ህዝብን ወደ ኑር ውድነት እና ድህነት እስር ውስጥ ከቶታል:: ደጋግመን እንናገራለን እጅግ ሊለወጥ የሚገባው ጉዳይ መሆኑን ለማሳወቅ እንፈልጋልን::በተጨማሪ በፖለቲካ ታማኝነት ያልተማሩ እና ከካድሬ ትምህርት ቤት ተመርቀው የወጡ በፖለቲካ ጥላቻ የተሞሉ ሰዎች የአገርን አመራር እና የህዝብን አንድነት ሊጠብቁ ስለማይችሉ በሃገሪቱ የፖለቲካ መስክ ትልቅ በሽታ ሆነዋል::

የፖለቲካ ካንሰራችንን ተነጋግረን እና በጋራ ሆነን ከማዳን በጉልበት በሽሙጥ እና እኔ አውቅልሃለሁ በሚል አባዜ እስከመቼ ድረስ እንደምንቀጥል አልታወቀም::ሁኔታዎች ገዢው ፓርቲ ብቻ በሚፈልገው መንገድ የሚቀጥል ከሆነ ደጋግመን ልንነገር የምንፈልገው ለሃገርም ለህዝብም ከባድ እና አደገና አደጋ እንዳለው ነው::ሁላችንም ዜጋ እስከሆንን ድረስ ለሃገራችን እኩል አስታውጾ ማበርከት አለብን እየተገፋን እስከመቼ???

እቅድ - ትራንስፎርሜችን - ራእይ = ኢሕአዴጋዊ መንጠራራት


አቅዶ የሚያብድ ሥውር አደገኛ ሕሊና፣ ቁምነገር አልባ ነው!

የሰላም ትልቁ ጠላት ከአቅም በላይ መመኘት ነው፡፡
የሥራ መንፈስ ከብዙሃኑ የልብ ፍቅርና የአገር መውደድ ስሜት ጋር በፅኑ መቆራኘት አለበት፡፡ ላገር አሳቢ እየመሰለ ውስጥ ውስጡን እንደሚቦጠቡጥ ሹም ባለበት ቦታ ዕቅድ ሲታቀድ ቢውል ፍሬ-ቢስ ነው የሚሆነው። ነባር ነባር በላተኛ አባርረን ትኩስ ትኩስ፣ ልጅ-እግር በላተኛ ካመጣን፤ የበላተኞች መተካካት እንጂ የአዲስ ደም - ቅያሪ አይሆንልንም፡፡ እጃችንን ዘርግተን የማንደርስበትን ነገር ለመጨበጥ መሞከር፤ በር ከፍተን ለዘራፊ እንደመተው ነው፡፡ የሰላም ትልቁ ጠላት ከአቅም በላይ መመኘት ነው፡፡ አሊያም የክቡር እምክቡራን ዕብደት ነው። “ከአቅም በላይ መኖር የዕድገት ፀር ነው” ይሉ ነበር ያለፈው ሥርዓት ነገረ-ሠሪዎች! ኮከብ እነካለሁ ብሎ ሠምበሌጥ ላይ መወድቅ ይከተላል፡፡ ለራስ ጥቅም ሲሉ የአገር ዕቅድ አወጣሁ ማለት መዘዙ ብዙ ነው፡፡ ድህነት ባጠጠበት፣ ችጋር በተንሠራፋበት አገር እንደ ህንድ እጉልላቱ አናት ላይ ጥቂት ባለ ፀጋ ሰዎች ብቻ ተቀምጠው፣ የበለፀገች ኢትዮጵያን መመኘት ከንቱ መገበዝ ነው፡፡
ምንሊክ ሳልሳዊ 
 
በአየር ላይ ህንጻ መገባት እንደማይቻለው ሁሉ ማቀድና በባዶ ሜዳ መመኘት እጅግ የተራራቁ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ማቀድ፤ በዝርዝር ያቀድኩትን ለመፈፀም ምን ምን አደርጋለሁ ማለትን፣ ያንንም ማስፈፀሚያ ፋይዳ ያለው ቁሳቁስንና አጋዥ የሰው ኃይልን፤ እንዴት እቀዳጀዋለሁ ማለትን፤ በመጨረሻም ቀን በቀን ሥራ ላይ ማዋልን ይጠይቃል፡፡ በዚህ ማህል ባይሳካስ ብሎ ማውጠንጠንን፣ ሁለተኛ ዘዴ መዘየድን እቅድ 2 እንዲሉ የግድ ማሰብን ይሻል፡፡ ካልሆነና አማራጭ ሁሉ ከተሟጠጠም በጊዜ ሀሳብን ለውጦ ወደ ሌላ ዕቅድ መሸጋገር ነው፡፡ ከዚህ ቀላልና ግልፅ መንገድ ውጪ በጉልበት ልሥራህ ቢሉት ሀብትንም ማባከን፣ የሰው ኃይልንም በአጓጉል መንገድ ሜዳ ማፍሰስ ነው፡፡ እግርህን በአልጋህ ልክ ዘርጋ፤ እንደማለት ነው፡፡ ይህን በአገር ደረጃ መንዝሮ ማየት ነው እንግዲህ አገርን ለማሳደግ መጣጣር፡፡ ከምንጨብጠው በላይ መጀመሪያ እጃችን ረዥም መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል;;

“ይህንንማ ማን ያጣዋል ይሄንን ማንም ያውቀዋል፡፡ ዝቅተኝነት’ኮ፣ የለጋ ምኞት መሰላል ነው ጠዋቱን ሥልጣን የጠማው:- ደረጃውን ሲያያዘው፣ ሽቅብ ሽቅብ ያንጋጥጣል ጫፉ ላይ ሲደርስ ግና፣ ጀርባውን ለመስጠት ይሻል ጧት የበላበትን ወጪት፣ ማታ ሰባሪ ይሆናል ቀና ብሎ ወደ ሰማይ፣ ደመናውን ብቻ ያያል እላይ ያወጣውን ታች ሰው፣ ቁልቁል ረግጦ ይሳደባል” ይላል የሺክስፒሩ ብሩተስ፡፡ ዞሮ ዞሮ ዕቅድ እንደ አቃጁ፣ ዕቅዱ እንደ ከዋኙ ነው፡፡ የሸር ዕቅድም፣ የአውቆ-አበድ ዕቅድም አለና ጠንቅቆ ማየት ይገባል፡፡ ታዋቂው ፀሀፌ-ተውኔት ፀጋዬ ገብረ መድህን በሚኒልክ ተውኔት፣ በኢልግ አፍ፣ እንዲህ ይላል፡- “ኮንቲ ኦሊኒ ግን ጭምት፣ ቀዝቃዛ፣ ነገር ለማሻከር ሆን ብሎ በዕቅድ የሚቆጣ፣ ሆን ብሎ በዕቅድ እንዳስፈላጊው ሁኔታ የሚያብድ፣ አንድ ነፃ መንግሥት ያለኔ ፈቃድ ለምን ሰንደቅ ዓላማ ተከለ ብሎ በነገረ-ቀደም አቅዶ እሚጮህ፤ … አቅዶ የሚያብድ ሥውር አደገኛ ሕሊና፣ ቁም - ነገር - አልባ ሰው ነው!” ከዚህ ይሰውረን፡፡ ዕቅዶች ይከወናሉ፡፡ ፓርቲዎች ይለመልማሉ፡፡ አገር ታድጋለች፡፡ የዕለት ጉርሥ የዓመት ልብስ ይኖረናል ማለት ያባት ነው፡፡ ሆኖም ያ እስኪሳካ ድህነት አንድያውን እንዳያደቀን ሁሉን በወግና በቅጡ ማስተካከል፣ መቆጣጠር፣ መተግበር ያስፈልጋል፡፡
ምንሊክ ሳልሳዊ:-