Geneva : Andargachew Tsige's Supporters Burned TPLF Logo / Flag


መንግስታዊ ወንጀል በነጻነት የሚራመድባት ሃገር ኢትዮጵያከመሃል አዲስ አበባ የተቃዋሚ አመራሮች መያዝ የሚያሳስብ ጉዳይ ነው።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
በዚህ ወር ብቻ እጅግ ከባድ የሆኑ ለጆሮ የሚቅፉ እና ለሰው ልጆች የሚያሰቅቁ የሰብአዊ መብት ገፈፋዎች እና የዜጎች ወደ እስር ቤት ምወርወር የበለከተበት ከሃገር ቤትም አልፎ እስከ ጎረቤት አገር ድረስ ተዘልቆ በጉቦ የዜጎች የመዘዋወር መብት በስውር እጆች የተደፈሩበት እሱንም ተከትሎ የተቃዋሚ ድርጅቶች አመራሮች ከየመንገዱ እና ከቤታቸው እየተያዙ ወደ እስር የተወረወሩበት ሁኒታ እያየን እየሰማን ነው።

የግንቦት ሰባት አመራር የሆነው አንዳርጋቸው ጽጌን ከመንገድ ያውም ከሰው አገር በጉቦ፡ተልፈው አምጥተወት ለአስራ አምስት ቀን የሚጠጋ በደህንነት ድብቅ የስቃይ ማእበል ሲንጡት ከርመው ጫና ቢበዛባቸው አክመው ባያስተካክሉትም አቅረቡት ። ወገናችን አንዳርጋቸው የተመለከትንበት በድብቅ የተቀረጸው ቪዲዮ ከኦዲዮው ጋር በፍጹም የማይሄድ ከመሆኑም በላይ ልብ ብሎ ለተመለከተው የአንዳርጋቸውን የአፍ እንቅስቃሴ እንዳናየው ከታች በጹሁፍ መልክ በማስቀመጥ የተደጋገመ እና ለማደናበር ሞክረዋል።

እንደ አንዳርጋቸው እምነት እን ዶክተር ብርሃኑ ነጋ እንደነገረን ከሆነ የሁለቱም አባባል አንድ ነገር ላይ ያርፋል ፡ " አንዳርጋቸውን የያዙት ስራውን ጨርሶ ልተተኪዎች አስረክቦ እረፍት ላይ በሆነ ሰአት ነው፤" የፖለቲካ ቋንቛ ለሚገባው ሰው አንዳርጋቸው የተናገረው ነገር ቢኖር ለሃገሩ ድርሽውን እንደተወጣ እና እረፍት ላይ በሆነበት ወቅት እንደተያዘ ነው።

አንዳርጋቸውን በሚዲያቸው ከማቅረባቸው በፊት የወያኔ የዲሞክራሲ መገለጫ የሆነው የመቀሌውን የአረና አመራር ጨምሮ ዳንኤል ፡ የሺዋስ እና ህብታሙ የተቃዋሚ አመራሮች ተይዘው ቤታቸው እስከመበርበር ደርሶ ወደ ሰቆቃው ማእከል ማእከላዊ ተወርውረዋል። የተቃዋም አመራሮችን ከግንቦት ሰባት እና ከአንዳርጋቸው ጋር አቆራኝቶ ለመወንጀል እየሮጠ ያለው ወያኔ ጉልበቱን እና የሃገር አንጡረ ሃብትን በመጠቀም ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል በዜጎች ላይ እየፈጸመ ይገኛል፡

በተቃዋሚዎች ዘንድ አንድ እርምጃ የትግል እርከን እንደተጀመረ እየተነገረ ባለበት በዚህ ወቅት በጋራ በመሆን ይህንን የትግል ጥሪ በመተግበር ለሕዝቦች ነጻነት ራሳችንን መስእዋት በማድረግ ብአሸናፊነት ወያኔን ደምሠን በመቃብሩ ላይ የዲሞክራሲን እና የነጻነት ችቦ መለኮስ እንዳለብን ለመናገር እወዳለሁ #ምንሊክሳልሳዊ

ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን !!! አንዳርጋቸው ጽጌ የጊዜ ጀግና ሳይሆን የሰው ጀግና ነው !!!!ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ለሰው ልጆች ሕልውና ስኬት ... ለነጻነት ለዲሞክራሲ ለፍትህ እና ለኢትዮጵያዋይት ታላቅ ትንሳኤ ደፋ ቀና ሲል በጅቦች እጅ የገባው ታላቅ ሰው አንዳርጋቸው ጽጌ ዘላለም በትውልድ ሃረግ ውስጥ ሲታውስ የሚኖር የጊዜ ጀግና ያልሆነ የሰው ጀግና የሆነ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ነው።

አንዳርጋቸው ጽጌ ወያኔዎችን ከውስጣቸው ጀምሮ የታገለ ተነጥሎም በቅንጅት እና በግንቦት ሰባት ድርጅቶች ውስጥ እስከ ወታደራዊ አዛዥነት የሰራ ወንድ ታሪክ የማይሽረው በፍጹም ሊረሳ የማይችል የ21ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያዊ ጀግና ነው። አንዳርጋቸው ብዙ ያልተጻፉለት እና ያልተነገሩለት የትግል ስኬቶቹን የያዝ ታላቅ ታጋይ ነው። አንዳርጋቸው ለማንም ያልተበገረ ለግል ጥቅሙ ያላጎበደደ ለስልጣን ጥማት ያልተገዛ ቁምጣውን ለብሶ ቤተሰቡን ትቶ በኤርትራ በረሃዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ታላላቅ ወጣት ታጋዮችን ያፈራ የትግል ሰው ነው።

አንዳርጋችው ቆራጥ ለምንም የማይበገር ሲሆን ወያኔዎች ቢይዙትም አንዳርጋቸው አንድ ጊዜ እጃቸው እንደገባ እና ተመልሰው እንደማይለቁት ስለሚያውቅ እንዲሁም አንድ ታጋይ መዘጋጀት ያለበትን ዝግጅት ያደረገ ታላቅ ሰው ስለሆነ በፍጹም አያሸንፉትም በተቃራኒው በከባድ የቃላት ቀውስ ውስጥ ሊከታቸው እንደሚችል እንጂ በፍጹም ከአንዳርጋቸው አንደበት የግንቦት ሰባትን ገበና አገኛለሁ ማለት ዘበት ነው። ይህም ያልተሳካለት ወያኔ አንዳርጋቸው ራሱን እስኪስት ቶርች ቢያደርገዉም ሃቅን ማግኘት አልቻለም ። አይችልምም።

አንዳርጋቸው ጽጌ ራሱን ዝቅ አድርጎ እንደ ሌሎች የተቃዋሚ መሪዎች ሳይኮፈስ የአውሮፓን ምርጥ ከተሞች በመተው የግል ዝና እና ስም ሳያስጨንቀው የኤርትራን ተራሮች ክላይ ታች በመውረድ እሾህ ወጋኝ ጸሃይ አቃጠለኝ ሳይል ለሃገሩ ነጻነት ዝንተ አለም የማይረሳ ታላቅ አስታውጾ ያበረከተ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው። #ምንሊክሳልሳዊ