"ማለት የሚገባዉን ብለን ጨርሰን ማድረግ የሚገባዉን የምናደርግበት ዓመት ነው።" የግንቦት 7 ንቅናቄ ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋየግንቦት ሰባት ለፍትህ እና ለዲሞክራሲ ንቅናቂ ዋና ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የአዲስ አመት መልእክት

Ginbot 7 movement chairman Dr Berhanu Nega Ethiopian New Year Message (2007)

 https://www.youtube.com/watch?v=XdOIFewzuOE&feature=youtu.be


ሕዝብ አከባቢ ያለውን አቤቱታ ተቃዋሚዎች ሆነ የለውጥ ሃይሎች በጥሞና ሊረዱት ይገባል።( 2007 ለለውጥ !!! )በመጪው አመት 2007 ወያኔን ለመቅበር ልዩነትን በማቻቻል በጋራ መታገል ችላ የማይባል ጉዳይ ነው።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) 2007 ለለውጥ !!!

ላለፉት 23 አመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተቀምጠውን ዘራፊውን እና ጨቋኙን የወያኔ ጁንታ በመጪው አመት ለመቅበር የአንድነት እና የለውጥ ሃይሎች ልዩነቶችን በማቻቻል በጋራ ልንታገል የሚገባና ለውጥ ልናመጣ የሚገባ ችላ የማይባል ጉዳይ ነው።ባሳለፍነው የትግል አመታት ውስጥ የተቃዋሚዎች እርስ በ እርስ መፈራረጅ መወነጃጀል ለስልጣን ጥመኝነት መሮጥ እንዲሁም ለስም እና ለዝና መትጋት ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተረፈው ነገር ቢኖር ከጭቆን ወደ ጭቆና ማቅ ውስጥ ከመዘፈቅ ውጪ ምንም የናፈቀውን የነጻነት አየር እንዲተነፍስ አላደረግነውም። የተቃዋሚ ሃይሎች ጥንካሬ እንዲጎለብት በየድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እንከኖች በማጥራት በጋራ እና በተመቻቸ የሃሳብ መግባባት ተቻችሉ እና ተግባብቶ የትግል ስትራቴጂን ግብ ለማድረስ ተግቶ መስራት ይጠበቅብናል።

ሕዝብ አከባቢ ያለውን አቤቱታ ተቃዋሚዎች ሆነ የለውጥ ሃይሎች በጥሞና ሊረዱት ይገባል።ሕዝቡ በተቃዋሚዎች መካከል ያለውን መናቆር እና አለመግባባት ሲመለከት ራሳቸውን በችግር የተበተቡ ሃሎች ነገ እናን እንዴት ሊመሩን ይሽላሉ ከማለት ጀምሮ ወያኔም በአቅሙ ለፖለቲካ ፍጆታው በመጠቀም ተቃዋሚዎችን በማሳጣት ላይ ነው። ተቃዋሚዎች ሆኑ ለውጥ ፈላጊ ሃይሎች በውስጣቸው ያለውን ገበና በሰለጠነ መንገድ በመፍታት አደባባይ ላይ መዘላለፍን ማቆም ግድ ይላቸዋል። ዲሞክራሲያዊ አሰራር ማለት የትግልን ስልት ባዶ ማስቀረት ማለት አይደለም። የትግል ስልት ማለት አንዱ አንዱን እያረመው መጓዝ እና ለስኬት እና ለድል ማብቃት ሲሆን በመፈረጅ አሊያም በመወንጀል ሲባልም የፖለቲካ ጥላቻ በመርጨት ጥንካሬ ማበጀት እንደማይቻል ልንረዳው ግድ ይለናል።

ወያኔ የትቃዋሚዎችን እና የለውጥ ሃይሎችን እርስ በ እርስ መፈነካከት በማየት እንዲሁም የውስጥ አሰራራቸውን በመሰለል በትግሉ ውስጥ ያላቸውን ሚና እንዲኮላሽ በመስራት የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመጠቀም እርስ በርስ እንዲፋጁ እና ተቃዋሚዎች እንዲከስሙ ጥንካሪያቸውን እንዳያገኙ ሲሰራ ይህንን እንዴት አድርገን በማሻሻል የወያኔን ሴራ ማክሸፍ አለብን የሚል አመኔታ የሚያስገኝ ሕዝባዊ ስራዎችን በመስራት ጥንካሬን ማግነት እንዲሁም ሕዝባዊ ድጋፎችን ማግኘት ግድ የሚልበት አመት መሆን አለበት።መጪው አመት ተቃዋሚዎች ካለፈው ድክመቶቻችን ተምረን ከዘለፋ እና ከስድብ እንዲሁም ከመፈራረጅ የሴራ ፖለቲካ በምውታት ጥንካሬዎቻችንን የምናሳይበት ለውጥ የምናመጣበት አመት እንዲሆን በጋራ ጠንክረን መስራት አለብን።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል። ይህ ሳይታለም የተፈታ እና የሁሉም የነጻነት ፈላጊ ሃይሎች ጥያቄ ነው። በሃገር ውስጥ ያሉትን ፓርቲዎች መዋቅሮቻቸውን በማጠናከር የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመቅረፍ እንዲጠነክሩ የማድረግ ግዴታ ከለውጥ ፈላጊ ሃይሎች ይጠበቃል። መመካከር መተራረም ግድ ይላል። በውጪው አለም የሚገኙ የነጻነት እና የለውጥ ሃይሎች እንዲጠናከሩ እና ከጥልፍልፎሽ ፖለቲካ ወተው ጠንካራ ሃይል እንዲሆኑ የዲያስፖራው ሃይል ከበፊቱ በበለጠ መልኩ ሊሰራ ግድ ይለዋል። የወያኔ የጎን ውጋት እና የራስ ምታት የሆነው ዲያስፖራው የጀመረውን የትግል ስልት እና ትጋት በማስፋት ሚዲያዎችን በማጠናከር እና የነጻ አውጪ ፓርቲዎችን በመርዳት በማግባባት ጠንካራ ሰንሰለት ከሃገር ቤት ጋር በመፍጠር ሕዝብን ከጨቋኞች ነጻ ማውጣት አለበት።

የሚዲያ ተቋማት እና የድህረገጽ ውጤቶች ሕዝብን በማስተማር ሕዝብን መብቱን እና ነጻነቱን አውቆ ለሌላው እንዲያስተምር በማድረግ ረገድ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል። ያለፉ እና የከሰሙ ወሬዎችን እና አሉባልታዎችን ከመርጨት ሕዝቡን ስለመብቱ እና ነጻነቱን በማስተማር ረገድ መትጋት ከተያዘ ለውጥ የማይመጣበት ምንም ምክንያት የለም። ትችን እና ሂስን ላለመዋጥ እውነትን ላለመቀበል የሚደረጉ ሩጫዎች ታጥቦ ጭቃ እንጂ የትም እንደማያደርሱ እንዲሁም ሰዎችን መፈረጅ እና መወንጀል ምንም ለውጥ እንደማያመጣ ካለፈው ተምረናል ። ስለማያዋጣ ጥንካሬን እና ለውጥን የምናመጣበትን የትግል ስልት በመመካከር እና በመወያየት ሃሳብን በማቻቻል መረጃ በመለዋወጥ ልንቀትል ይገባል እላለሁ።

በተረፈ ለመላው ኢትዮጵያውያን 2007 የነጻነት እና የድል ቀንዲል የሚበራበት እንዲሆን ምኞቴን እገልጻለሁ።
#ምንሊክሳልሳዊ