ኢትዮጵያ - ምእራባውያን - አንዳርጋቸው - የወደፊት እጣ - ለትግል መነሳት

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
በአሸባሪው መንግስታዊ ዘራፊ እና አፋኝ ቡድን የታፈነው አቶ አንዳርጋቸው ጸጌ ወያኔ ለመፍታትም ሆነ ለመግደል ዝግጁ አይደለም ። ግደሉት አሊያም ስቀሉት ቢባሉ እንኳን በፍጹም አያደርጉትም። ምእራባውያኑ ከአፍ ወሬ ውጪ ምንም የሚተገብሩት ነገር የለም ፡ እስክንድር ነጋ በቂ ምሳሌ ሊሆን ይችላል ከሰብአዊ መብት ድርጅቶች ጀምሮ እስከ አሜሪካው የውጪ ጉዳይ አናት ኬሪ ድረስ ድምጻቸውን ቢያሰሙም ለይስሙላ እና ለብሄራዊ ጥቅማቸው እንዲሁም ነገ ሌላ መንግስት ቢተካ እንዲህ ብለው ነበር እንዲባልላቸው እና እዳ ማውረጃ ንግግራቸው ለትግሉ ምንም የሚያበረክተው አሊያም ለአንዳርጋቸው የሚፈይደው ነገር የለም ።

ለአንዳርጋቸው ይሁን በእስር ለሚማቅቁት ወገኖቻችን የሚፈይደው ዋናውና አንዱ ጉዳይ የኛ ጠንክረን መታገል እና አንድ እርምጃ መጓዝ ሲሆን የዛን ሰአት የኛን መጠናከር እና መታገል የተመለከቱ ም እራባውያን ምን እንርዳችሁ ከምን ደረሳችሁ ምናምን ማለታቸው እና መጠየቃቸው ግድ የሚልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ፡፤ አሁን የሚፈለገው የኛ መታገል እና መታገል ብቻ ነው። የነጮቹ የከንፈር ልብላቤ ከብሄራዊ ጥቅም ሚዛን ሂደት ምስረታ ላይ ስለተመረኮዘ ከንግግር ውጪ ምንም አይፈይድም:

ልብ ማድረግ ያለብን ከማ እከላዊ አፍሪካ እስከ አፍጋኒስታ ከሊብያ እስከ ኢራቅ በተለያዩ የአፍሪካ እና የመካከለኛው እንዲሁም የኢስያ ሃገራት ም እራባውያኑ የሚያካሂዱት የፕሮክሲ ጦርነት የተነሳ ሌላ ዙር ቀውስ በምስራቅ አፍሪካ እና ውጥረት እንዲከሰት ስለማይፈልጉ ከወያኔ ጋር እጅና ጓንት ሆነው ለመስራት አለመቦዘናቸው የሚያመለክተው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሃገራት ላይ በአሁኑ ሰአት ሊፈጠር የሚችለውን አመጽ እና ችግር መቆጣጠር ይዞ የሚመጣውን ውጤት እርግጠኛ ሆነው ለማወቅ አለመቻላቸው ከወያኔ ጋር እንዲተሳሰሩ አድርጓቸዋል።ምንሊክሳልሳዊ

እንዲሁም ደቡብ ሶማሊያ ላይ ነዳጅ መኖሩን ስካን አድርገው ስላረጋገጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ25 አመት በኋላ እንግሊዝ ኤምባሲዋን ሞቃዲሾ የከፈተች ሲሆን ይህን ተከትሎ ከ100 በላይ የብሪታንያ ካምፓኒዎች ካልተረጋጋችው ሶማሊያ ፍቃድ እንደተሰጣቸው ለማረጋገጥ ተችሏል። ይህንን ከሶማሊያ ሊያገኙትን ብሄራዊ ጥቅም ሊያስጠብቅ የሚችለው አገር ቢኖር ወታደሮቹን ለሞት እየገበረ የሚተባበራቸው የወያኔው መንግስት ብቻ ስለሆነ ያላቸውን ሃይል ሁሉ በመጠቀም ሕዝብን በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ በመደለል የአምባገነኖች እድሜ እንዲረዝም ሚናቸውን ይጫወታሉ።

እንዲሁም ስለግንቦት ሰባትም ይሁን ታጥቀናል እንዋጋለን ስለሚሉ ድርጅቶች እንቅስቃሴ በቂ መረጃ ስለሌላቸው እንዲሁም እነሱ የማይደግፉት እና የማይቆጣጠሩት አመጽ ላይ ሪስክ/ሃላፊነት ስለማይወስዱ የሚያደርጉል አስታውጾ አነስተኛ ሲሆን እኛ ታግለን አንድደርምጃ ወደፊት እስካልሄድን ድረስ እና ትግላችንን አሳይደን የድጋፍ እና የቁጥጥር ሰንሰሎችን ከም እራባውያን ጋር እስካልፈጠርን ድረስ በመግለጫ እና ድህረገጽ ወሬ ጋጋታ ምንም የምናመጣው ነገር እንዳሌለ ለመናገር እወዳለሁ፡፤ የአንዳርጋቸውን ጉዳይ ግንቦት ሰባት በሎንዶን ፍርድ ቤቶች ቀርቦ የቻለውን ያህል መጋፈጡ የማይቀር ቢሆንም የሚወስደው ጊዜና ጉልበት ቀላል ስለማይሆን እንግሊዛውያኑ ጊዜ ይገዙበታል። ዋናው ቁም ነገሩ ግን ጠንክረን የዲፕሎማሲውን እና የሃገር ቤቱን ትግል ከያዝነው አንድ ነገር መፈንዳቱ አይቀርም ።

ብቸኛው እና ዋናው ጉዳይ ትግሉ/ጦርነቱ በመሃል እና በዳር አገር ከተፋፋመ ፣ ሕወሓት እና አመራሩ አደጋ ውስጥ መግባት ሲጀምሩ የዛን ወቅት ም እራባውያኑ በሌላው አለም እንደለመዱት ይመጡና አንዳርጋቸውን እንደ ጆከር ካርድ ለመጠቅም ይሞክራሉ። በቃ ወያኔ አንዳርጋቸውን እንዲፈታ እና የተኩስ አቁም ተደርጎ ድርድር እንዲጀመር ያደርጋሉ ከዚህ ውጭ ግን የሃይል ሚዛኑ በወያኔ እጅ ባለበት የመንግስትን ወንበር ተቃዋሚዎች ባላዩበት ሁኔታ ምእራባውያኑ የሚያሰሉት ከወያኔ ጋር ያላቸውን ቁርኝት ነው። ይህንን ለመበጠስ ደሞ የግዴታ የተኩስ ትግል መጀመር አለበት ። ወያኔም ቢሆን የትጥቅ ትግሉ በመሃል አገር እና በዳር አገር ሲስፋፋበት ጭንቀት ውስጥ ስለሚገባ ከአጣብቂኙ ለመውጣት ሲል ያለውን አማራጭ ለመጠቀም ይሞክራል። ወያኔ ደጋፊዎቹን እና ካድሬዎቹን ብእጥቅም ስለገዛቸው ጦርነት ከተስፋፋበት ያለውን ሃይል ሁሉ ወደ ዛው ስለሚያጋድለው ለካድሪዎቹ ጥቅሞች ጊዜ ስለማይኖረው አብዮታዊ መበላላት በፓርቲው ውስት ስለሚፈጠር እድሜውን ማቀጨጭ ከዛም መጣል ይቻላል። መታገል ካልቻልን ባሁኑ አካሄዳችን ወያኔን እንድማንጥለው ማወቅ አለብን።

አንዳርጋቸው የት እንዳለ ባልታወቀበት ሁኔታ ቶርቸሩ ባልቆመበት ሁኔታ ላይ 500 ሚሊዮን እነ ብሪታንያ እየሰጡ ባለበት ሁኔታ ወያኔ እና የየመን መንግስት የሚፈልጉትን ነገር እንዲያደርጉ ቀድመው ላይሰንስ አድርገዋቸውል ለማለት መገመት ብቻ ሳይሆን ያስደፍራል።አስር ጊዜ ወያኔዎችን የሚያጥላላ ነገር ከመጻፍ በየመንገዱ ሰልፍ ከመውታት በጋራ ተሰባስበን ሳንናናቅ እና ከኛ በላይ አዋቂ የለም ብለን ሳናስብ አንዱ ለ አንዱ ዝቅ ብሎ የወያኔን ስልጣን አደጋ ውስጥ የሚከት ከባባድ እንቅስቃሴ ማድረግ ከቻልን በትግላችን ስኬት ምእራብያውያኑን ማሳመን እንደምንችል ማወቅ አለብን። ህዝባችንንም ነጻ ማውጣት እንደምንችል መረዳት ግድ ይላል።‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

በሐሰት መንግስታዊ ማጭበርበሮች ሳንታለል በጋራ በመታገል ቀጣይ ድሎችን እናረጋግጥ !!!

የጀመርነው ትግል ፍሬ በማፍራቱ በቀጣይነት በጋራ በመታገል ተከታታይ ድሎቻችንን እናረጋግጣለን!!
Minilik Salsawi
በሃገሪቱ ያለውን ሁኔታ በትክክለኛው መንገድ የማያስቀምጡ የወያኔ ፕሮፓጋንዲስቶች እርስ በእርሳቸው የሚጋጩ ዘገባዎችን በመስራት እና እውነትን ለመሸፋፈን በመትጋት የሕዝቦችን የማወቅ መብት ያለርሕራሄ እየተጋፉ ይገኛል። ይህ በወያኔ የፕሮፓጋንዳ አካላት የሚፈጸም ማጭበርበር እና ማደናገር የገዢውን ፓርቲ ውስጣዊ ዝርክርክነት በይፋ ያሳብቃል።ያለለውን እንዳለ ድሮ ተግንብቶ የታደሰውን እንደ አዲስ እንደተገነባ ፤ ያልተሰራውን እንደተሰራ ሕዝቡ የማያገኘውን አገልግሎት እንደሚያገኝ ወዘተ በማድረግ በሁለት እና ሶስት እጥፍ በማባዛት በመቶኛ በማስላት በመደመር በማባዛት ያሌለውን ምስል በመፍጠር ሕዝቡን እያደናበሩ ይገኛሉ።ህዝብ መንቃቱን መረዳት እስኪያቅተው ድረስ ወያኔ ማላዘኑን ተያይዞታል።
በአለም ላይ ካሉ መንግስታት በተለየ ሁኔታ ዜጎቹን እያጭበረበረ ወደ ድህነት አዘቅት እየከተተ ያለ መንግስታዊ አስተዳደር ነኝ የሚል ቢኖር ወያኔ እና ወያኔ ብቻ ነው። የወያኔ የማይሳኩ እና የሚያደሐዩ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ፖሊሲዎች መነሻቸው የተሳሳቱ ፕሮፓጋንዳዎች ናቸው። ማንኛውንም ፖሊሲ ይሁን አዋጅ መመሪያ ይሁን ደንብ ወያኔ ሲያወጣ በተቆጣጠራቸው ሚዲያዎቹ እያጋነነ የሕዝብን ልብ ለመስቀል በመሞከር እደርስበታለው ያለው ግብ ምንግዜም እየተኮላሸ ተጨባጩን ሁኔታ ባለማገናዘብ እየካደ ስለሚጓዝ የሃገር ኢኮኖሚ የጨው ክምር በመሆኑ እየተናደበት ይገኛል።
ሕዝቡ ትክክለኛ አስተዳዳሪ ባለማግኘቱ ምክንያት እየተንገላታ በየቦታው ምሬት በበዛበት በአሁኑ ሰአት ተገቢውን አገልግሎት እንዳገኘ በማድረግ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ በመርጨት ለማሳሳት እየተሞከር ሲኦን በቀረቡ መዝገቦች ላይ ውሳኔ መስጠት አቅቶት ወይም በቸልተኝነት አልወስንም ብሎ የሚኮፈስ ቢሮክራሲ ዜጎችን ሲያስለቅስ በአደባባይ እየታየ መፍትሔ እየተገኘ ነው የሚል ማደናገሪያ ሲቀርብ ያሳዝናል፡፡ ያሳፍራል፡፡በፍትሕ ሥርዓቱ አካባቢም ሲታይ እየወጡ ያሉ መግለጫዎችና ሪፖርቶች የሚያስገርሙ ናቸው፡፡ ፍትሕ ዘገየብን፣ ፍትሕ ተነፈግን የሚሉ በርካታ ዜጎች ባሉበት አገር ውስጥ የፍትሕ ሥርዓቱ ተደራሽነት ወደር የለውም ዓይነት ሪፖርቶች ይቀርባሉ፡፡ ሕዝቡ በየፍርድ ቤቱ በተጓደለ ወይም በተነፈገ ፍትሕ ምክንያት ከላይ ታች ሲቅበዘበዝ እየታየ የማይመስል ነገር ይነገራል፡፡ በዚህ መስክ ያለው ማደናገር ራስ ያሳምማል፡፡
በኑሮ ውድነት በትራንስፖርት በውኃ በኤሌክትሪክና በስልክ አገልግሎቶች አለመሟላት እና መቆራረጥ ምክንያት ሥራውና ኑሮው አሳር እያየበት ያለው ሕዝብ የአገልግሎቱ ተደራሽነት በዚህን ያህል በመቶ አደገ ወይም ደረሰ ሲባል ቀልድ የተያዘ ይመስለዋል፡፡ ለሳምንታት ውኃ አጥቶ የሚንከራተት ሕዝብ የውኃ ተደራሽነት ከዘጠና በመቶ በላይ ሆኗል ተብሎ ሲለፈፍበት እንዴት ይቀበላል? በኤሌክትሪክ ኃይል እጦት ምክንያት ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ማምረት እያቃተውና ሕዝቡ በጨለማ ሲሰቃይ ተደራሽነቱ ይህን ያህል ደርሷል ሲባል ማን ያምናል? በሌሎች ዘርፎችም ተመሳሳይ ማደናገሪያዎች ሞልተዋል፡፡ከመሃል አገር እና ከተለያዩ ክፍለሃገሮች ገበያዎች የተገኙ ተብለው የሚቀርቡ የእህል ዋጋዎች መጋጨት የሚያስገርሙ ናቸው፡፡ ጤፍ፣ በርበሬ፣ ጥራጥሬና የተለያዩ የግብርና ምርቶች ዋጋ በወያኔ መገናኛ ብዙኃኑ ሲተነተን፣ በፍፁም ገበያ ውስጥ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ አያሳይም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ማደናገሪያ ማንን እንደሚጠቅም አይገባንም፡፡ ህዝብ መንቃቱን መረዳት እስኪያቅተው ድረስ ወያኔ ማላዘኑን ተያይዞታል።
ስለዚህ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አንዱ ለሌላው መረጃዎችን በማስተላለፍ ወያኔ እና ሚዲያዎቹ የሚጠቀሙበትን የማደናበሪያ ስልት በማጋለጥ እና ሊደናበር የሚችለውን የዋሁን ኢትዮጵያዊ በማስረዳት የዜግነት ግዲታችንን እየተወጣን በጋራ በመታገል ይህንን ውሸታም እና አጭበርባሪ አደናባሪ ስርአት ልናስወግደው እና ለመጪው ትውልድ እውነትን የተሞላች አገር የማስረከብ ሃላፊነት እንዳለብን ለማሳሰብ እወዳለሁ። በጋራ በመታገል ቀጣይ ድሎቻችንን እናረጋግጣለን!! ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬