ማኅበረ ቅዱሳን እንዴት ወዳጆች አፈራ? ጠላቶችስ ለምን ተነሡበት? Photo: 'ቤተክርስቲያንን ማገልገል አክራሪነት አይደለም'! #እኔም_ለእምነቴ ! 
ኦርቶዶክስ ክርስቲያን አከረረ ከተባለ መጨረሻው ምንኩስና ነው፡፡
ማኀበረ ቅዱሳንን የሚቃወሙ የሀገርና የቤ/ክ ጠላቶች ብቻ ናቸው፡፡

"ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ...በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል ትን.ዕንባ.3፡17-19"

በእግዚአብሔር ፈቃድ በቅዱስ ሲኖዶስ ይሁንታ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለመደገፍና ለማጠናከር የተመሠረተው ማኅበረ ቅዱሳን ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ አያሌ ፈተናዎችን እያሳለፈ 22 ዓመታት ተጉዟል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን በዓመታት ጉዞው ባከናወናቸው መልካም ተግባራት ታላላቅ የቤተክርስቲያን አባቶችን ጨምሮ እጅግ በርካታ ወዳጆችን እንዳፈራ ሁሉ ጥቂት በተቃራኒው የቆሙ ስሙን በየጊዜው በክፉ የሚያነሱ ቡድኖችም ተነሥተውበታል፡፡
ወዳጆቹ የቤተ ክርስቲያን ወዳጆች ናቸውና በአገልግሎቱ ተማርከው በሚሠራቸው መልካም ሥራዎች ተስበው ቤተ ክርስቲያን ያለባትን የአገልግሎት ክፍተት ለመሙላት በጋራ ከማኅበሩ ጋር በመሥራት ሲተባበሩ፤ በአንጻሩ ጠላቶቹ ደግሞ የተለያዩ አጋጣሚዎችን እያስታከኩ ማኅበሩን ለመወንጀል እየተጣጣሩ ይገኛሉ፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን እንዴት ወዳጆች አፈራ? ጠላቶችስ ለምን ተነሡበት?
ማኅበረ ቅዱሳን እግዚአብሔር ፈቅዶ ከተመሠረተበት ጊዜ አንሥቶ ወጣቶችን በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከመደበኛው ትምህርታቸው ጎን ለጎን በየአካባቢው ወደሚገኙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሔደው መሠረታዊውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት እንዲማሩ በማድረግ ሃይማኖታቸውን ጠንቅቀው እንዲያውቁና ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲጠብቁ እንዲሁም በዕውቀታቸው፣ በገንዘባቸውና በጉልበታቸው እንዲያገለግሉ በማድረግ፤ በተጨማሪም ወጣቱ ሀገሩንና ሕዝቦቿን አክባሪ፣ በሥነ ምግባር የታነጸ እንዲሆን በማስቻሉ ብዙ ወዳጆችን አግኝቷል፡፡

ከዚህም ሌላ የመናፍቃኑንና ቤተ ክርስቲያኒቱን እናድሳለን ብለው የተነሡትን የመናፍቃኑ ተላላኪ ቡድኖችን ሴራና የአክራሪ እስልምናውን እንቅስቃሴ በመረጃ አስደግፎ በማጋለጡ፣ ከክፉ ትምህርታቸው መመለስ ያልፈለጉ የተሐድሶ ቡድን አባላት ከቤተ ክርስቲያን እንዲወጡ ስለተወሰነባቸው እና ሌሎችንም የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግሮች እየተከታተለ ለዕድገቷና ለብልጽግናዋ በመሥራቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የቤተ ክርስቲያን ወዳጆችን አፍርቷል፡፡

ከዚህ በተቃራኒው የተሰለፉት ወገኖች ደግሞ ወጣቱን እንደጠፍ ከብት ወደ ማያውቀው የመናፍቃን አዳራሽ የመንዳት ልምዳቸው በመቋረጡና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመግባት የሚያደርጉት ሥርዓቷን የማፋለስ እንቅስቃሴ፤ እንዲሁም አገልጋዮቿንና ምእመናኖቿን የማስኮብለሉ አካሔድ ማኅበሩ በክትትል በተለያዩ መረጃዎች ስለገለጠባቸው ማኅበረ ቅዱሳንን በጠላትነት በማየት ማኅበሩ እንዲፈርስ የማይቧጥጡት ዳገት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡

እነዚህ የቤተ ክርስቲያን የውስጥ ጠላቶች ለጥቂት ጊዜ ጋብ ብለው የነበሩ ቢሆንም አሁን ባገኙት አጋጣሚ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንጀራዋን እየበሉ የሚኖሩ ወዳጆቻቸውን በማጠናከርና በማስፋፋት በሚሊዮን የሚቆጠር በጀት ከወዳጆቻቸው ተመድቦላቸው የቤተ ክርስቲያኒቱን ሥርዓት ለማዛባትና በጎቿን ለመበታተን ሌት ከቀን እየሠሩ ነው፡፡

ይኼ ዕቅዳቸው የሚሳካው እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ያሉ ለቤተ ክርስቲያኒቱ እምነትና ሥርዓት መጠበቅ የሚቆረቆሩ ማኅበራትን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ አጀንዳ በማድረግና እንዲበተኑ ክፉ ሥራ በመሥራት ነው፡፡ እነዚህ የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ይሔንን ከንቱ ቅዠታቸውን እውን ለማድረግም በቤተ ክርቲያኒቱ የተለያየ ሓላፊነት ላይ የሚገኙትን የዓላማቸው አስፈጻሚዎች ሁሉ እየተጠቀሙ እንደሚገኙም ይታወቃል፡፡

ከዚህም ሌላ ድብቅ ዓላማቸው እንዲሳካ ተላላኪዎቻቸው በቤተ ክርስቲያኒቱ ሥር የሚሆን ነገር ግን ስውር ዓላማ ያለው ማኅበር እንዲመሠርቱና ከዚህ በፊት ከንቱ ተግባራቸው ታውቆ በቤተ ክርስቲያኒቱ ታግደው የነበሩ ማኅበራት ሁሉ ከሞቱበት እንዲቀሰቀሱ እየሠሩም እያደረጉም ይገኛሉ፡፡

በቤተ ክርስቲያን ስም ድብቅ ዓላማቸውን ለማስፈጸም ያቋቋሟቸውና የሚያቋቁሟቸው፣ ማኅበራትንም ሕጋዊ ዕውቅና ለማሰጠት እንዲያመቻቸው ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ከኔ ሌላ ሌሎች አያስፈልጉም የሚል አቋም ያለው ማኅበር እንደሆነ ያስወራሉ፡፡

በእርግጥ ማኅበረ ቅዱሳን በትክክል የቤተ ክርስቲያኒቱን ሥርዓትና ደንብ ተከትለው በሚቋቋሙት ማኅበራት ላይ የማኅበሩ ጠላቶች ከሚያወሩትና ከሚያስወሩት አሉባልታ የተለየ አቋም አለው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርቲያን የሁለት ሺሕ ዓመታት ታሪክ ያላት ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ትሁን እንጂ መንበሯ ከሊቀ ጵጵስና ደረጃ ወደ ፕትርክና ለማሳደግ አንድ ሺሕ ስድስት መቶ መራራ ዓመታትን አሳልፋለች፡፡ በዚህ ማለፏ ደግሞ ሌሎች አኀት አብያተ ክርስቲያናት የደረሱበት ዘመናዊ የአደረጃጀት ደረጃ ላይ ለመድረስ አልቻለችም፡፡ ልጆቿንም ጊዜው በሚጠይቀው መንገድ ለመምራት ሳትችል ስለቆየች እነዚህን ክፍተቶች የሚሞሉ አንድ አይደለም በርካታ ማኅበራት እንደሚያስፈልጓት ማኅበረ ቅዱሳን ያምናል፡፡ ነገር ግን እኩያኑ እንደሚሉት ሳይሆን እነዚህ ማኅበራት ሲቋቋሙ ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን ዕድገትና የአገልግሎት ሥምረት የሚንቀሳቀሱ ተልእኮአቸውና ዓላማቸው ተለይቶ የሚታወቅ፣ መንፈሳዊ ተግባርን ብቻ የሚፈጽሙ፣ የሚናበቡና በስልት ለአንድ ውጤት የሚተጉ ሊሆኑ ይገባቸዋል የሚል ጽኑ አቋም አለው፡፡

ይሔንን አቋሙን ደግሞ በርካቶች የሚደግፉት እንደሆነ ማኅበረ ቅዱሳን ያምናል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ የመናፍቃኑ ተላላኪዎች በቤተ ክርስቲያን ስም ያቋቋሟቸው ማኅበራት ከዚህ በፊት በቤተ ክርስቲያን ላይ ጥለውት የሔዱት ጠባሳ የሚታወቅ ስለሆነ ማኅበረ ቅዱሳን በማኅበራት ላይ ግልጽ አቋም አለው፡፡ ከዚህም ሌላ እነዚህ የውስጥ ዐርበኞች ይኽ ስውር ዓላማቸው ያልታወቀባቸው ይመስል ማኅበሩን ለመወንጀል የማይለጥፉለት ታፔላ፣ የማይለፍፉት ወሬ የለም፡፡ ነገር ግን እነዚህ የቤተክርስቲያን ጠላቶች ስለማኅበሩ የሚያወሩት ሁሉ ከእውነት የራቀ እና ሁሉም የሚገነዘበው ግልጽ እውነታ መሆኑን ባለማወቃቸው እናዝናለን፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ምንም ስውር ዓላማ የለውም፤ ከማንኛውም የፖለቲካ አስተሳሰብ የጸዳና በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በተሰጠው መተዳደሪያ ደንብና መመሪያን ሳያዛንፍ እየሠራ ያለ፤ በተሰጠውም መተዳደሪያ ደንብና ሓላፊነት መሠረት ከአባላቱ የሰበሰበውን የገንዘብ መዋጮ ገቢና ወጪ እያሰላ በውስጥ ኦዲተሮችም እያስመረመረ በመሥራት ተጨባጭ ለውጥ ያመጣ ማኅበር እንጂ በወሬ የሚኖር አይደለም፡፡ ይሔንን አሠራሩንም ቀርቦ ማየት ይቻላል፡፡ አባላቱም በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸው በጉልበታቸውና በመላ ሕይወታቸው ቤተ ክርስቲያንን የሚያገለግሉ እንጂ እንደ መናፍቃኑ ተላላኪዎች ለሆዳቸው ያደሩ፣ ሆዳቸው አምላካቸው የሆነባቸው እዚህም እዚያም ደሞዝ የሚቀበሉ አይደሉም፡፡

ማንኛውም አካል እንዲያውቅልን የምንፈልገው ሐቅ ማኅበረ ቅዱሳን ቅዱስ ሲኖዶስ ለሰጠው ሓላፊነትና አባላቱም ለገቡለት ቃል ኪዳን ሃይማኖታቸው የሚፈቅደውን መስዋዕትነት ለቤተ ክርስቲያን ልዕልናና ክብር ለመክፈል የተዘጋጁ እንጂ በተዛባ አመለካከት ወደ ኋላ የሚያፈገፍጉ አለመሆናቸውን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎቱ የሚታይ አሠራሩም ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህም የመናፍቃኑ ተላላኪዎች መሠረተ ቢስ ውንጀላ ከአገልግሎታችን አንዲት ጋት ወደ ኋላ እንደማይመልሰን እንዲታወቅልን እንፈልጋለን፡፡ ርእይና ተልእኮአችንን ለማሳካት ዛሬም ነገም እንሠራለን፤ ትናንትን ያሻገረን እግዚአብሔር ዛሬንም ያሳልፈናልና፡፡

ማህበረቅዱሳንን ለማፍረስ ከመነሳት በፊት የራሳቸውን ካድሬያዊ ጵጵስና ያፍርሱ !!!ጳጳሳት ከመንግስታት ጋር ተዋህደው ህዝብን ከማስጨቆን ውጪ እንደማህበረ ቅዱሳን በጎ የሆነ ስራ አልሰሩም።

ከአሁን ቀደም ለዜጎች የማይበጁ የሃይማኖት መሪዎች ለሼጎች የማይበጁ ከሆነ ቆባቸውን እንዲያወልቁ ተናግሬ ነበር። ( http://minilik-salsawi.blogspot.com/2014/06/blog-post_18.html ) ወደደም ጠላም ቄስም ሆነ ጳጳስ እያንዳንዱ በመንፈሳዊም ይሁን በስጋዊ ሕይወቱ እመራዋለው የሚለውን ምእመን ሁሉ የማገልገል ግዴታ አለበት። ይህ ካልሆነ የማይገባ አንቱታ የስድብ ያህል ይቆጠራል ነውና የሚሰራቸውን እኩይ ተግባራት እንዲያቆም ይነገርዋል።

ባለፈው እንደ መግቢያ የተተቀምኩትን ለመጥቀስ ያህል ቤተክርስቲያን እና መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ እጅና ጓንት ሆነው በኢትዮጵያውያን ላይ የማያባራ ጭቆና ማካሄድ ከጀመሩ ረዥም ዘመናት ተቆጥረዋል። ይብልጡኑ የመንግስቶች ጎህ ከቀደደ ጀምሮ በተለይ የተዋህዶ ሃይማኖት መሪዎች  አስፈሪ እና አስደንጋጭ እንዲሁም አሳዛኝ ደግሞም አሳፋሪ ቃላቶችን በመጠቀም ስጋዊ እና ምድራዊ ስልጣኖችን ለገዢዎች ለማደላደል ይህ ነው የማይባል ግፍ በምእመናኖቻቸው እን በሌሎች አማኞች ላይ ፈጽመዋል አስፈጽመዋል፤ እየፈጸሙ ነው፤ እያስፈጸሙ ነው። ይህ የማይዋጥለት አሊያም የሚክድ ካለ እውነት የማይደላው ብቻ ነው።

በዚህ ሰሞን ከበፊት ጀምሮ እየተቀጣጠለ የመጣ እና የተጋጋለ የማህበረ ቅዱሳን ጉዳይ ቤተክህነትን ሲያምስ ሰንብቷል። እያመሰም ነው። በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የማይደሉትን እና የተማሩ ሰዎች ስብስብ የሆኑትን ቡድኖች ባገኘበት ሁሉ እየፈረጀ መበተን ከተያያዘ 20 አመታት አስቆጠረ፤ በአሸባሪነት እና በአክራሪነት ማስፋፋት ስም ከዘመተባቸው ማህበራት አንዱ እና ንብረቱን ወርሶ ለመቅበር ካሰፈሰበት ማህበር ዋነኛው እና በመንፈሳዊ አገልግሎት ታላቅ አስታውጾ ያበረከተው ማህበረቅዱሳን ተጠቃሽ እና የዚህ ሳምንት በስፋት ተዘምቶበት ይገኛል።

ማህበረ ቅዱሳን ባለፉት አመታቶቹ በሃገሪቱ ውስጥ በተለያዩ ክፍለ ሃገራት በመዘዋወር በተለያየ መስኩ ዘር ቀለም እና ሃይማኖት ሳይለይ በስፋት ኢትዮጵያውያንን በመርዳት የልማት አስታውጾ በማበርከት መንፈሳዊነትን በማስረጽ እና በማስተማር ወዘተ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በታሪክ ውስጥ በጉልህ ሊጠቀስ የሚችል ከፍተኛ የሆነ አስታውጾ አበርክቷል። ማህበረ ቅዱሳን ነዳያንን ከመርዳት አንስቶ እስከ ማቋቛም አስተምሮ ለወግ ማእረግ እስከማብቃት ድረስ ለውገን እና ለሃገር ተቃሚ ተግባራትን አበርክቷል። (ድህረገጹን http://eotcmk.org/site/ መጎብኘት ይቻላል)

የኢሕአዴግ መንግስት እና ጥቂት ለሆዳቸው ያደሩ ጳጳሳት ሲኖዶሱን በመጠምዘዝ ማህበረ ቅዱሳንን በአሸባሪነት እና በአክራሪነት ለማገድ ያደረጉት ሙከራ ይሁንታ በማጣቱ እስከዛሬ ሳይሳካ ቀርቷል።በእግዚአብሔር ፈቃድ በቅዱስ ሲኖዶስ ይሁንታ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለመደገፍና ለማጠናከር የተመሠረተው ማኅበረ ቅዱሳን ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ አያሌ ፈተናዎችን እያሳለፈ 22 ዓመታት ተጉዟል፡፡ማኅበረ ቅዱሳን በዓመታት ጉዞው ባከናወናቸው መልካም ተግባራት ታላላቅ የቤተክርስቲያን አባቶችን ጨምሮ እጅግ በርካታ ወዳጆችን እንዳፈራ ሁሉ ጥቂት በተቃራኒው የቆሙ ስሙን በየጊዜው በክፉ የሚያነሱ ቡድኖችም ተነሥተውበታል፡፡ወዳጆቹ የቤተ ክርስቲያን ወዳጆች ናቸውና በአገልግሎቱ ተማርከው በሚሠራቸው መልካም ሥራዎች ተስበው ቤተ ክርስቲያን ያለባትን የአገልግሎት ክፍተት ለመሙላት በጋራ ከማኅበሩ ጋር በመሥራት ሲተባበሩ፤ በአንጻሩ ጠላቶቹ ደግሞ የተለያዩ አጋጣሚዎችን እያስታከኩ ማኅበሩን ለመወንጀል እየተጣጣሩ ይገኛሉ፡፡

ማንኛውም አካል እንዲያውቅ የሚፈለገው ሐቅ ማኅበረ ቅዱሳን ቅዱስ ሲኖዶስ ለሰጠው ሓላፊነትና አባላቱም ለገቡለት ቃል ኪዳን ሃይማኖታቸው የሚፈቅደውን መስዋዕትነት ለቤተ ክርስቲያን ልዕልናና ክብር ለመክፈል የተዘጋጁ እንጂ በተዛባ አመለካከት ወደ ኋላ የሚያፈገፍጉ አለመሆናቸውን ማሳወቅ ግድ ይላል፡፡ማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎቱ የሚታይ አሠራሩም ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህም የመናፍቃኑ ተላላኪዎች መሠረተ ቢስ ውንጀላ ከአገልግሎታቸው አንዲት ጋት ወደ ኋላ እንደማይመልሳቸው ሊታወቅ ይገባል፡፡

የወያኔ ካድሬዎች- በምላሱ የሚተዳደር ሰው በዕውቀት ያልተደገፈ ድፍረት፣ የህሊና ማጣት ምርኩዝ ነው፡፡

ማህታማ ጋንዲ እንግሊዝን “በመጨረሻ ባዶህን ትወጣታለህ!” ማለቱን አንርሳ፡፡  

Minilik Salsawi

ለሀገራችን ጐታቿም አጥፊዋም፣ “አሾክሿኪው” ነው፡፡ ከታሪክ መማር ዕርም በሆነባት አገር ቀለሙን እየለዋወጠ አድር - ባይ ሁሉ እየመጣ፤ “እንቅፋት በመታው ቁጥር ቲዎሪ ድረሽ” (ያውም ዕውነተኛ ቲዎሪ ካለው) እያለ፤ “መንገድ ባስቸገረው ቁጥር” መመሪያ ማሪኝ” እያለ ህሊናውን እየሸጠ ይኖራል፡፡ ልባም አይደለምና አፍ ያወጣል፡፡ ምላሱ እየረዘመ፣ አንጐሉ እየጨለመ ይሄዳል፡፡ አበው “ከመሃይም ምላስ ይሰውረን” የሚሉት ለዚህ ነው፡፡
የጌቶች አስተሳሰብ ምን እንደሚመስል ተገዢ ወዳጆች ማወቅ አለባቸው፡፡ ሎሌነቱንም በቅጥ በቅጥ አለመያዝ፣
የመጨረሻውን ቀን ከማፋጠን አያልፍም፡፡ “የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ የሚለውን ተረት፤ በአፉ የሚንጣጣ
ሁሉ በጊዜ ሊገነዘብ ይገባል፡፡ መጨረሻው፤ “ያመኑት ፈረስ፣ ይጥል በደንደስ” ነውና፡፡ “እናቴን ያገባ ሁሉም
አባቴ ነው” ለሚሉ የዋሀን ሁልጊዜ ፋሲካ ሊመስላቸው ቢችልም፤ ለሁሉም ጊዜ አለውና “ምነው ምላሴን
በቆረጠው” የሚያሰኝ የፍርድ ቀን እንደሚኖር አሌ አይባልም፡፡
“እንብላም ካላችሁ እንብላ፤ አንብላም ካላችሁ እንብላ” በሚል ጅባማ ፍልስፍና ውስጥ መበላላት መሪ መርሀ -
ግብር መሆኑን ለአፍታም መዘንጋት የለበትም፡፡
“ለጋማማ አህያም ጋማ አላት
አያስጥልም እንጂ ጅብ ሲዘነጥላት” ሲባል የከረመው ያለ ነገር አይደለም፡፡
“እነሆ ብዙ ዘመን አለፍን፡፡ ከሁሉም የተረፈን ብዙ ምላሶችና እጅግ ጥቂት ልቦች ናቸው” ይላል ሲ ጆርጅ
የተባለ ፀሐፊ፡፡ በሀገራችን በቅንነት ሃሳብ የሚሰጡና በሎሌነት ሃሳብ የሚሰጡ መለየት አለባቸው፡፡ “ውሸት
አለምን ዞሮ ሊጨርስ ሲቃረብ ዕውነት ገና ቦት ጫማውን እያጠለቀ ነው” መባሉ በምክን እንጂ በአቦ - ሰጡኝ
አይደለም፡፡
በየአገሩ፤ የንጉሥ አጫዋቾች የተለያዩ ናቸው፡፡ አንድ የጋራ ባህሪ ግን አላቸው - ንጉሱ ሲያስነጥሱ
ማስነጠስ፡፡ አድር ባይነት፡፡ በመካያው ራሱ አድርባዩ ማንነቱ ይጠፋበትና “የዘሬን ብለቅ ያንዘርዝረኝ” ማለት
እንኳን ይሳነዋል፡፡ “ነገር አንጓች፤ እንኳን ለጌታው ለራሱም አይመች” ነውና ፍፃሜው አጓጉል መሆኑ ዕሙን
ነው፡፡የትዕዛዝ ሁሉ ጉልላት ለህሊና መታዘዝ ነው፡፡ ማንም ቢሆን ማን፤ ህሊናውን ሲክድ አታላይ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ ብልጥ ለማኝ፤ “ጌታዬ ጌታዬ አምና የሰጡኝን ልብስ አምስት ዓመት ለበስኩት”እያለ ይኖራል፡፡
በዕውቀት ያልተደገፈ ድፍረት፣ የህሊና ማጣት ምርኩዝ ነው፡፡” ወትሮም፤ “መራዡ ተኳሹ” ሲል
የኖረ፣ “በራዡ ከላሹ” ማለት ከጀመረ ሁለተዜ ጥፋት ነው፡፡ ሀገራችን አያሌ አድር - ባይ አይታለች፡፡
ማህታማ ጋንዲ እንግሊዝን “በመጨረሻ ባዶህን ትወጣታለህ!” ማለቱን አንርሳ፡፡ “ቅዳሴው ሲያልቅበት ቀረርቶ አከለበት” እንዲሉ በምላሱ የሚተዳደር ሰው ውሸት ማብዛቱ ግዱ ነው፡፡ ዕውቀተ-ቢስ መሠረቱ ለዕውነት ረሃብ ያጋልጠዋልና! addisadmassnews.com አዲስ አድማስ።

በገዛ ሃገራችን በአሸባሪነት የሚፈርጀንን የወንበዴ አገዛዝ ታግለን ለማስወገድ ተባብረን እንነሳ።

ወያኔ የሕዝብን ጥያቄ ከማድመጥ ይልቅ ንቆ በመተው ለማዳፈን በመሞከር በሕዝብ ተቀባይነትንና አመኔታን ወዳገኙ ግለሰቦችና ፓርቲዎች ላይ ለማመካኘት እየሞከረ ነው፡፡ 
 
Minilik Salsawi


ወገኖቻችን ለኢኮኖሚና ማሕበራዊ ችግሮች ከመጋለጥ አልፈው ከባድ አደገኛ አጣብቂኝ ውስጥ ናቸው ፡፡ ለሕዝቡና ለሀገሪቱ ጥቅም የሚቆም ብቃት ያለው አስተዳደር የለም፡፡ ህግ አለ ህገ መንግስት አለ ቢባልም ተገቢ ያልሆኑና ከሕገ መንግሥቱ ጋር የሚጣረሱ አፋኝ አስደንጋጭ እና ኢሰብአዊ ሕጐችና ደንቦች በተከታታይ ይወጣሉ፡፡ እነኚህም ሕዝቡን በተደራራቢነት እያስጨነቁት ይገኛሉ፡፡ ህጐችና ደንቦች ሲወጡ ሕዝብ መወያየትና መምከር ሲገባው ውይይት ሳይደረግባቸው በዘፈቀደ እና ባልሰለጠኑ አስፈጻሚዎች ተግባራዊ ሲሆኑ ይታያል፡፡ የወጡና የፀደቁ ሕጐች ላይም ሆነ በአፈፃፀም ላይ ችግሮች ሲፈጠሩ ማየት የሚኖርበት ፍርድ ቤት ነበር፤ነገር ግን በሚወጡ ሕጐች የፍ/ቤት ሥልጣን ተነጥቆ ለኤጀንሲዎችና ለባለስልጣናት እንዲሁም ለሌሎች ባልበሰሉ ካድሬዎች ለተሞሉ መስሪያ ቤቶች እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡ ከዚህ አኳያ ስናይ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት በሀገራችን አለ ወይ? የሚል ጥያቄን አስነስቶ አስነስቶ ከመሰላቸታችን የተነሳ በኢትዮጵያ ሕግና መንግስት እንደሌለ ደምድመናል።
የፖለቲካው ሁኔታ ደግሞ እጅግ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው ያለው፡፡ዜጐች ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ፣ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸው በመገፈፉ አቤቱታ ሲያቀርቡ የሚሰማ አስተዳደር ባለመኖሩ፤የሕዝቡ ብሶት እንዲሰማና ጥያቄያቸው መልስ እንዲያገኝ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ “ሀገሪቱ ላይ ሁከትና ሽብር ልትፈጥሩ ነው” እየተባለ በተለይ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት፣ጋዜጠኞችና ወጣቶች እየታሰሩ ናቸው፡፡ ላለፉት 7 አመታት ብቻ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን በነጻ ሃሳባቸውን በማስተላለፋቸው ብቻ በ “ፀረ ሽብርተኝነት” ስም እየታሰሩ ይገኛሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ወቅታዊው የሀገራችን የፖለቲካ ሁኔታ ምህዳሩ ጠቦ ጠቦ አሁን ካለበት እና ግመልን ከማያሾልክ የመርፌ ቀዳዳ ላይ መድረሱ ምስክር አያስፈልገውም።
ኢህአዴግ የሕዝብን ጥያቄ መመለስ ስላልቻለ፣ በዕቅዱ መሠረት ቢያንስ ለ50 ዓመት ሀገሪቱን የመምራት ዓላማ ስለነበረው እንደማይሳካለት ሲያውቅና ከሕዝቡ አመኔታና ተቀባይነትን ስላጣ ፈርቶ የራሱን ስህተት ለመሸፈን ዳግም ስህተት እየፈፀመ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የሕዝብን ጥያቄ ከማድመጥ ይልቅ ንቆ በመተው ለማዳፈን በመሞከር በሕዝብ ተቀባይነትንና አመኔታን ወዳገኙ ግለሰቦችና ፓርቲዎች ላይ ለማመካኘት እየሞከረ ነው፡፡ በተለይ የተቃዋሚ አመራሮች እና ጋዜጠኞች ከሽብር ወንጀል ጋር ማያያዙ ከፍርሃት የመነጨ የከሰረ ፕሮፖጋንዳ ነው፡፡ከላይ በግርድፉ የተጠቀሱትን ጉዳዮች ለመፍታት የሚያስፈልገው ነገር ቢኖር አንድ እና አንድ ነው ። መፍትሄው ወያኔን ከስልጣን አስወግዶ ሕዝባዊ መንግስት መመስረት አማራጭ የማይገኝለት ጉዳይ መሆኑ እሙን ስለሆነ ኢትዮጵያውያን በአጠቃላይ በአንድነት በመተባበር ይህንን የበሰበሰ አስከፊ ስርአት መንግሎ ለመጣል በሚደረገው ትግል ውስጥ በመሳተፍ የዜግነት ድርሻችንን መወጣት ይጠበቅብናል። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

የፍትህ እና የመልካም አስተዳደር እጦት ወያኔ የያዘውን ስልጣን ላለመነጠቅ የሚሰራው ፖለቲካዊ ደባ

Minilik Salsawi

ለዘላቂ ልማት እንሰራለን በሚል ስርኣት ውስጥ የመሰረታዊ የዲሞክራሲ መብቶች በጊዜያዊነት መኖር እና እንደመነገጃ መጠቀም ህዝብን አገለግላለሁ ሳይሆን አጭበረብራለሁ እንደማለት ይቆጠራል:: የወያኔ ስርኣት ባለስልጣናት በፍርሃት ተውጠው በጠበንጃ ሃይል በሚኖሩባት በዚች ኢትዮጵያችን የፍትህ እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ አሁንም እጅግ መልስ የሚያሻቸው ጉዳዮች ናቸው::ዜጎች በሃገራቸው እንዳይኮሩ በመኖር ደህንነታቸው ላይ ጥርጣሬ እንዲያሳድሩ እየተደረገ ስለሆነ ይህ ደሞ ወያኔ የያዘውን ስልጣን ላለመነጠቅ የሚሰራው ፖለቲካዊ ደባ ውጤት መሆኑ እሙን ነው::
ፍትህን እና መልካም አስተዳደርን ወደ እውነት ያመጡ ህጎች በኢትዮጵያ አሉ የሚለው ወያኔ ህዝቦች ግን በተግባር ተጠቃሚ ሲሆኑ አላየንም::ህጎቹ በተግባር ይዋሉ ይህንን ህጎች በመመሪያ በደብዳቤ እና በስልክ የሚቀይሩ የሚደፈጥጡ በጥቅም የሚሸጡ የሚረጋግጡ የሚለውጡ ከየወንበራቸው ተሽቀንጥረው ይጣሉ:: የቀን ተቀን የፍትህ እና የመልካም አስተዳደር ሂደት ውስጥ እጃቸውን እያጠለቁ ፍትህን የሚያዛቡ አስተዳደራዊ በደሎችን የሚፈጽሙ ባለስልጣናት የህዝብን ማህበራዊ ህይወቶች ከማፋለሳቸውም በላይ ከቀድሞው በባሰ መልኩ ፖለቲካው እንዲጭበረበር ኢኮኖሚው እንዲደቅ ሃገር በብድር እንድትዘፈቅ ህዝብ እንዲደኽይ ከባዱን ሚና እየተጫወቱ ነው::
ህዝቦች ህግ እየጸደ ህግ እየተሽሞነሞነ እና እየተብለጨለጨ ቢቀመጥ ምንም የሚጠቅማቸው ነገር እንደሌለ መታወቅ ያለበት ሲሆ አንድ ህዝብ ባላረቀቀ ባልተወያየበት እና ባላጸደቀው ህግ እየተገዛ ፍትህን እና መልካም አስተዳደርን እንዴት ማስፈን ይቻላል??? መተማመን እና የዜግነት ኩራቱን በሚሰብሩ ባለስልጣናት እየተሰበረበት ያለ ህዝብ ፍትህን እና አስተዳደራዊ እንዲሁም አገልግሎቶችን በተግባል ለማየት እና ለመጨበጥ አልቻለም:: ለተበደለና ፍትሕ ላጣ ዜጋ፣ መልካም አስተዳደር አጥቶ ለሚንገላታ ዜጋ ፍትሕና መልካም አስተዳደር እንዲኖር በአንቀጽ ተደንግጓል እያልን ብናወራ ዋጋ የለውም::
ህዝብ ባለው ስርኣት ላይ እምነት የለውም:; ይህ ደግሞ ራሱ ስርኣቱ ያረጋገጠው ነገር ነው የስርኣቱ ታጣቂ ሃይሎች በሌሎች ወገኖቻቸው ላይ የሚያደርሱትን የሰብኣዊ መብት ጥሰት እያዩ በሃገሪቱ ህግ የለም እኔም ነገ እደበደባለሁ እታሰራለሁ ንብረቴን እነጠቃለሁ መብቴን እነፍርጋለሁ እጠቃልሁ እገደዳለሁ እሰደዳለሁ እገደላለሁ በሚል በስርኣቱ ላይ ያላቸው እምነት የተሟጠጠ ከመሆኑም በላይ ከትንሽ እስከ ትልቅ ከሃገር የመውጣት ንብረትን እና ሃብትን የማሸሽ ተግባር ላይ በመሰማራት በዜግነት አለመተማመን እንዲፈጠር በሩን በርግዶ ከፍቷል ይህ ደሞ ህጎች በተግባር ህዝብን አለማገልገላቸው እና በባለስልጣናት የመደፍጠጣቸው ውጤት ነው::
በተግባር ፍትህን እና መልካም አስተዳደርን እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት የተነሳ ማንም የለም::ስርኣቱም በጥቅመኞች የሚመራ ህዝቡም ላላወጣው ህግ በዝምታ ደንታቢስነቱን እየገለጸ ነው; ፍትህን እና መልካም አስተዳደርን የሚጥስና የሚያደናቅፍ የስርኣቱ ባለሥልጣን፣ ዜጋም ሆነ ግለሰብ፣ በማስረጃ ሲታይና ሲረጋገጥ ዕርምጃ ለመውሰድ ሕግ ፊት ለማቅረብ ምንም አይነት የተሰራ ስራ ካለመኖሩም በላይ በባሰ መልኩ በይፋ ህጎች ሲደፈጠጡ እያየን ነው:: ባለሥልጣንም ሆነ ባለ ሀብት፣ ታዋቂም ይሁን ተራ ዜጋ፣ ከፈለገው ብሔር ብሔረሰብ ይምጣ፣ የፈለገውን ሃይማኖት የሚከተል ይሁን፣ የጾታና የዕድሜ ልዩነት ሳይኖር ተቃዋሚም ይሁን ደጋፊ ሁሉም ሕግ ፊት፣ ፍትሕ ፊት፣ መልካም አስተዳደር ፊት እኩል መሆኑን አምነን በተግባር ለማዋል ቁርጠኝነት በፍጹም የለም:: ፍትህ እና መልካም አስተዳደር እንዴት ሊረጋገጡ ይችላሉ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እየተጓዝን ነው ጥያቄያችን ;ስለዚህ ህዝብ ለውጥ ይፈልጋል::የወደደ ይውደድ የጠላ ይጥላ እትዮጵያ ውስጥ ወያኔን ጨምሮ ሁሉም የፖለቲካ ጎራ ጥያቄው የስልጣን እና የአገዛዝ ሩጫ ነው::የእኛ የዜጎች ጥያቄ ግን ፍትህ መልካም አስተዳደር የአገልግሎት አቅርቦት እና ሰላም ነው::ይህንን ለማግኘት በጃችን ያለውን ነጻነት ለመቀዳጀት ከትግሉ ያልተቀላቀላችሁ እንድትቀላቀሉ ያስፈልጋል።