የወያኔ/ኢሕአዴግ የውስጥ መተራመስ ቀጥሏል:: በአዲስ አበባ ከወትሮው በተለየ መልኩ ውጥረት ነግሷል::- የተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ በዚህ ከቀጠለ ወያኔ እድሜ አይኖረውም::
- የያዝነው መስመር አያዋጣም:እስከመቼስ እንዲህ ይቀጥላል?" የሚሉ አመራሮች ተነስተዋል::
- ካድሬዎች ሕዝቡን እየዞሩ በመቀስቀስ ዳግም እንዲያደራጁ እየተደረገ ነው::  


 
Minilik Salsawi
ከምርጫው መምጣት ጋር በተያያዘ የወያኔው ጁንታ በህዝብ እና በተቃዋሚ ሃይሎች ላይ እየወሰደ የሚገኘውን እርምጃ ተከትሎ በወያኔ/ኢሕአዴግ ፓርቲ ውስጥ በአመራሮች ደረጃ የውስጥ መተራመሱ መቀጠሉ ታውቋል::ሕዝቡን ማዋከብ እና ተቃዋሚውን ማሰር እንዲሁም በየጊዜው የሚከሰተው የውጪ ሃይሎች ጫና አደጋ ውስጥ ይከተናል ልንጠነቀቅ ይገባል የያዝነው መስመር አያዋጣም በሚሉ እና በሕወሓት አመራሮች መካከል ከፍተኛ የሆነ ውዝግብ መከሰቱን ለፓርቲው ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል::
የተወሰነን ከመተግበርና ከማስፈጸም ውጪ ምንም አስተያየት መስጠት አትችሉም የሚል የቁጣ ቃላቶች ከአቶ ደብረጽዮን የሚወርድባቸው የአቶ ሃይለማርያም የደቡብ ኢትዮጵያ ፓርቲ አመራሮች በማንኛውም የፓርቲ ስብሰባ ላይ የተባለውን ከመደገፍ ውጪ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ታዘዋል::በኢሕአዲግ ውስጥ እየተከሰተ ያለው የአካሄድ ልዩነት አመራሮቹን ከማተራመሱም በላይ በአሁን ወቅት እየተወሰዱ ያሉት እርምጃዎች ከምርጫ በኋላ ቢሆኑ ይሻላል የሚሉ አስተያየቶችና የምንከተለው መስመር አዋጪነቱ ምን ያህል ነው የሚሉ ጥያቄዎች በከፍተኛ አመራሩ መካከል ልዩነት መፍጠሩ ታውቋል::የተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ መስመሩን ለማሳት አዳዲስ የተሳሳቱ መረጃዎች እና የቤት ስራዎች (በተለይ ለዲያስፖራው) እየተዘጋጁ መሆኑን የውስጥ ምንጮቹ ገልጸዋል::
ከአዲስ አበባ የሚደርሱ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ከተማዋ በውጥረት ውስጥ መሆኗ በገሃድ እየታይ ነው የሃገሪቱ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሕዝቡን ካለማስደሰቱም ውጪ ክፍተኛ የሆኑ የቢዝነስ ስራዎች ከቀድሞው በባሰ መልኩ ቀዝቅዘዋል::የገዢው ፓርቲ ተላላኪዎች በተለያዩ ቦታዎች በመዘዋወር ስለላ እያካሄዱ ሲሆን ሕዝቡም ያለውን ሁኔታ በንቃት እየተከታተለ መሆኑ ታውቋል:: የተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ እንደጅምሩ ከቀጠለ ለውጥ እንደሚመጣ እና ወያኗም እድሜ እንደማይኖረው በሚነገርበት በአሁን ሰአት የወያኗ ጁንታ በምርጫው ለሚሳተፉ ተቃዋሚዎች ከፓርላማ 15% ወንበር እንዲመቻችላቸው ከምርጫ ቦርድ ጋር እየሰራ ሲሆን ፓርላማ መግባት ያለባቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦችን በመለየት እና በማዘጋጀት ላይ መሆኑ ታውቋል::
በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች የተከሰተውን ውጥረት ተከትሎ ካድሬ የመንግስት ሰራተኞች ውጡና ቀስቅሱ አደራጁ በማለት ፓርቲያቸው መከራ አብዝቶብናል ሲሉ ማማረራቸው ተሰምቷል::ዳግም በየመንደሩ እየዞሩ በማደራጀት እና በመቀስቀስ ላይ የተሰማሩት ካድሬዎች ወጣቶችን በመቀስቀስ በማደራጅት በመመልመል ዙሪያ አዳዲስ ውይይቶች በኢሕአዴግ አመራሮች ትእዛዝ እየተሰጠ መሆኑ ታውቋል::በዚህም መሰረት አዲስ አበባ ውስጥ በየቀጠናው ካድሬዎቹ የመንግስት ሰራተኞች ስራቸውን እየተዉ ቢሯቸውን ዘግተው ለዚሁ የአደረጃጀት የምልመላ እና ቅስቀሳ ጉዳይ መሰማራታቸው ሲታወቅ መረጃውን ያደረሱኝ ተቃዋሚዎች ወያኔ ያደራጀውን ሃይል
ተጠቅመው የጀመሩትን የለውጥ ትግል ገፍተው መቀጠል አለባቸው ሲሉ አስገንዝበዋል::

ህዝብን በማይሽር ቁስል አየጎዱ በፕሮፓጋንዳ ማከም አይቻልም:


 eth     

የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ጥያቄና የኮሚቴው መፈታት ጥያቄ በአስቸኳይ ሊመለስ ይገባል:: ሙስሊም ወገኖቻችን ለሃገራቸው እና ለነጻነታቸው ምን ያህል ቀናኢ መሆናቸውን በተግባር አስመስክረዋል::


By Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ).
ወቅሰን ወቅሰን ወንጅለን ወንጅለን የሰለቸን ለመስማትም የታከተን ነገር ቢኖር ያለፉት ስርአቶች ላይ እና ሌላው ላይ ማሳበብን አንዱን ከአንዱ ለማፋጀት ማፈራረጅን መጠቋቆምን የመሳሰሉት ኢሕአዴጋዊ ባህርያት ናቸው::ወያኔ ኢሕኣዴግ የጭንቅ ነገር ውስጥ ሲገባ አጣብቂኙ መላወሻ ሲያሳጣው ያቆሰለውን የረገጠውን ህዝብ በማደናበሪያ ፕሮፓጋንዳ መሸንገል እና ማከም መልሶም መዋጥ አንደኛው አምባገነን ባህርይው ነው::ከዚህ በፊት እንደገለጽኩት ታሪክ ይቅር የማይለው ከባድ መንግስታዊ ወንጀል በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ ተፈጽሟል::http://minilik-salsawi.blogspot.com/2014/…/blog-post_23.html በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ የደረሰው ግርፍት እና መከራ ቁስሉ የኔም ነው።

በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ ሽብር ግድያ እስር ድብደባ እንግልት በጅምላ አፈሳ ዘረፋ ንጥቂያ እና ከፍተኛ የሆነ ኢሰብአዊነት እና ጭፍጨፋ በመንግስት ነኝ ባይ ሃይሎች በይፋ በአደባባይ ተፈጽሟል::ይህንን መንግስታዊ ሽብር የማይሽር ጠባሳ በመላው ኢትዮጵያውያን ላይ ጥቁር ነጥብ አስቀምጧል::ይህንን ጠባሳ በሃሰት ፕሮፓጋንዳ እና በሽንገላ አሊያም በማደናበሪያ ቃላት ማከም አይቻልም::የመንግስታዊውን ሽብርተኝነት ችግር በሌላ እምነት ላይ እንደ ሰበብ በማላከክ አሊያም የተቃዋሚ ፖለቲከኞችን አጀንዳ በመለጠጥ በፍረጃ ሌላውን ከመወንጀል ይልቅ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ጥያቄዎች እና የኮሚቴውን መፈታት ጥያቄ በአስቸኳይ መመለስ ሊዘነጋ የማይገባ ጉዳይ ሲሆን የሃይማኖት ነጻነትን ማረጋገጥ እና በሃይማኖቶች ላይ የሚፈጸም መንግስታዊ ውንብድናን ማስቆም የእያዳንዱ ዜጋ ሃገራዊ ግዴታ መሆኑንም ማውቅ ያስፈልጋል::

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለሃገራቸው እና ለነጻነታቸው ከጥንት ጀምሮ ምን ያህል ቀናኢ እና መስዋትነት የከፈሉ በመክፈልም ላይ ያሉ እንቁ ዜጎች መሆናቸውን መንግስታዊው አሸባሪም ይሁን አዋቅጭ አማሳኝ ነን የሚሉ ሁሉ ሳይወዱ በግዳቸው ሊውጡት የሚገባ ታሪካዊ እና ታላቅ እወነት ነው::የወያኔው መንግስት የሙስሊሙን የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄ ላለመመለስ አንዴ በሙስሊም መንግስት ምስረታ ሲወነጂል አልሆን ሲለው በተቃዋሚ ፓርቲዎች አጀንዳነት ሲቆላልፍ እምቢ ሲለው በሌሎች ሃይማኖት የውስጥ መርመስመስ ሽብራዊ አደጋ ሲፈርጀው እምቢ ሲለው የችግሩ መንስኤ ጥቂቶች ናቸው አሊያ የኦርቶዶክሶች እጅ በሚሉ የተለያዩ ማሳበቢያዎች ቢፈጥርም ይህ ንቃተ ህሊናው ከአሸባሪው መንግስት በልጦ በ እጥፍ ያደገው ሕዝብ ራስህ መንግስት አሸባሪ ነህ ሙስሊም ህዝቦቼን እያሸበርክ ነው እያለ እየነገረው ያለበት ሁኔታ በስፋት በመላው አገሪቱ አይተናል እያየንም ነው::

እውነትን ለመዋጥ ሁል ግዜ የሚከብደው አሸባሪው የወያኔ ስርአት አሁንም ማጭበርበሪያ መንገዶችን በመጠቀም በፖለቲከኞች መካከል የሚፈጥረውን መከፋፈል አይነት ስራዎች ለመስራት ቆርጦ የተነሳው ወያኔ ህዝብ ከሱ ቀድሞ መንቃቱን እንኳን መረዳት አለመቻሉ ጭፍንነቱን ያሳያል::አይኑን ገልጦ ሩቅ ለመመልከት ያዳገተው ወያኔ በተለያየ መልኩ የሙስሊም ወገኖችን ጥያቄ ለመፈረጅ ያማሰነው ስትራቴጅ ስላልተሳካለት እንዲሁም የምርጫው መድረስ አጣብቂኝ ውስጥ ስለከተተው በፕሮፓጋንዳ እና የራሱን መንግስታዊ ሃጢያት በሌላው ላይ ለመለጠፍ እየዳዳው ይገኛል::በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ሰቆቃ የማእከላዊ ቶርች እና ስቃይ እያንዳንዳችን እንዳንተኛ እና ነገ በኛ በማሰብ ለኮሚቴዎቹ ፍትህ በንቃት እንድንሰራ ብርታት ሰቶናል።

ስለዚህ አንድ አምባገነን ስርአት ታግለን ለመጣል የግዴታ እያንዳንዱ ዜጋ እስር ቤት ገብቶ መታሰርን እና መገረፍን መመልከት ሳይሆን ወንድሞቻችን በ እስር ቤት ያሳለፉት መከራ እንደመከራችን አይተን ሲነጋ ደሞ ወደ እኛ ቤት እንደሚመጣ አስበን ለታሰሩት ሃቀኛ ፍትህን ለኛም የማይሸራርፍ መብቶቻችንን ለማግኘት መታገል ግዴታችን መሆኑን ማወቅ ያስፈልገናል።ለዘመናት ተሳስሮ እና ተከባብሮ የኖረን ህዝብ ለማፋጀት ዘመን በወለዳቸው የአይሁዶች ቋንቋ አሸባሪ አክራሪ እየተባሉ ዜጎች የሚደርስባቸው መከራ እንዲቆም እያንዳንዳችን መስእዋት መሆን አለብን። የአብሮነታችን ተምሳሌት ለአለም ያስተማረውን የአያቶቻችንን የአንድነት ፍቅር ደግመን በዚህ ትውልድም ማሳየት አለብን ። አምባገነኖች ጠንክረን ከታገልናቸው ቀዳዳው ሁሉ ስለሚጠብባቸው ተፍረክርከው ይጠፋሉ። መላው ኢትዮጵያውያን ለዚህ አሸባሪ እና አጭበርባሪ አደናጋሪ መንግስታዊ አክራሪ ሳንዘናጋ በጋራ ተያይዘን በአንድ ሃገራዊ አጀንዳ አምባገነኖችን በመቅበር በ እጃችን ያለውን ነጻነት በማረጋገጥ ለነገው ትውልድ አዲሲቷን
 የጋራ ኢትዮጵያን በማስረከብ ታላቅ የሆነውን የዜግነት ድርሻችንን እና ሃላፊነታችንን እንድንወጣ ለማሳሰብ እወዳለሁ:: Minilik Salsawi