Benjamin Netanyahu and Ethiopian Jewish protests in Jerusalem and Tel Aviv against Racism

Minilik Salsawi's photo.የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታናሁ ከኢትዮጵያውያን እስራኤላውያን ማህበረሰብ መሪዎች ጋር ተወያዩ:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EthiopianIsraelis‬ ‪#‎Racism‬ ‪#‎Israel‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬
ጠ/ሚኒስተር ኔታናሁ በፖሊሶች የተደበደበውን የእስራኤል ወታደር የሆነውን ኢትዮጵያዊእስራኤላዊ ደማስን ተቀብለው በይፋ ይቅርታ ከጠየቁ በኋላ በሃገሪቱ የሚኖሩትን የኢትዮጵያውያን እስራኤላውያን ማህበረሰብ ወኪሎች ተቀብለው አነጋግረዋል::ውይይቱን በተመለከተ Benjamin Netanyahu - בנימין נתניהו የሚከተለውን ጽፈዋል::
This afternoon I had an extensive discussion on the plight of Ethiopian Jewry in Israel, as were also reflected in recent protests in Jerusalem and Tel Aviv. In a discussion that lasted three hours, the representatives of the Ethiopian in Israel who participated in the discussion, including those who took part in protests in recent days, the main claims and requests.
In summarizing the discussion, it was decided that in the coming weeks will be brought to the Cabinet a proposal for a comprehensive plan formulated over the past year and the Government is supposed to address some of the problems.
The Prime Minister will focus on the implementation of the plan and monitoring I personally stand in the Committee of Ministers which follow the program execution and advanced solutions to other issues. The Ministerial Committee would stand in her advanced plans for solving the problems raised at the meetings in the areas of education, housing, employment, religion, culture etc.
Minilik Salsawi's photo. In the discussion that the police will examine allegations of Ethiopian Jewry in Israel for discriminatory treatment and work to eradicate these phenomena.
We have to stand up as one against the phenomenon of racism, to denounce it and to biaura.
Photo: Kobe Gideon.

ወቅቱ የለውጥ ስለሆነ እንዳንተኛ አናንኮራፋ ! ለውጥ አይቀሬ ነው ። ዘለዓለም ውሻ ሆኖ ከመኖር አንድ ቀን አንበሳ ሆኖ መሞት !!!

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)i ራስን ችሎ፤ በራስ ተማምኖ ለመኖር ራስን ሆኖ መፈጠርን ይጠይቃል፡፡ለለውጥ በአንድነት መነሳት !!! ከሁሉም በላይ ግን ለመለመን እንኳ ጥቂት የራስ መንቀሳቀስ እንደሚያሻን መገንዘቢያ የሚሆነን ልብ ይስጠን!!በሀገራችን ከድህነት እኩል የሚፈታተነን ችግር፤ ቢያንስ ግማሽ መንገድ እንኳ ሄዶ ለመደራደር ዕውቀቱን፣ ጥበቡን አሊያም ቀና ልቡናውን ማጣታችን ነው፡፡ ግማሽ መንገድና የመቻቻል፣ ልዩነትን የማስተናገድ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን የመልመድ ትልቅ ፀጋ ነው፡፡ ይህንን ሰላማዊ መንገድ ለመቀበል ያልተዘጋጀውን ደግሞ ልክ ማስገባት የህዝቦች ግዴታ ነው። በጋራ ትግል ድባቅ መቶ ወደ መቃብሩ መክተት ግድ ይላል።
ወያኔን የምንነግረው በድርቅናው አገር በኔ ብቻ ተመርታ አገር አትሆንም ብሎ፤ ኃይለኛውና አሸናፊው ከወጣበት መሠላል ዝቅ ብሎ፤ ግማሽ መንገድ ወርዶ እንነጋገር፣ እንወያይ የማለት ባህል፤ ተሸናፊውም ከቁጭቱ፣ ከቂሙ፣ ለመጣል እንጂ አብሮ ለመቀመጥ አልፈልግም የሚልበትን ግትር አቋም ትቶ፤ እኔም የሀገር ጉዳይ ያገባኛል፣ “እንድትሰፉ እንጂ እንደትጠፉ አልፈልግም” ብሎ፤ መንገድ መሻት ያሻዋል፡፡የኋላ ታሪክ የሌለው የሚያውቀው ዛሬን ብቻ ነው፡፡ የአንድ ቀን ታሪክ የሌለው የሚያውቀው ዛሬን ብቻ ነው፡፡ አንድ ቀን ባዶነት መሰማቱ አይቀርም፡፡ ከሌላ አካል ተከፍሎ መፈጠር ዕድሜ ልክ ሙሉነት ሳይሰማን እንድንኖር ማድረጉ አሌ አይባልም፡፡ ራስን ችሎ፤ በራስ ተማምኖ ለመኖር ራስን ሆኖ መፈጠርን ይጠይቃል፡፡
በሀገራችን በፖለቲካ መከፋፈል እንጂ ተስማምቶ መጓዝ አይሆንልንም፡፡ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ እንደባህል የተያዘ ፈሊጥ ነው፡፡የማይለወጥ ነገር የለም - ከለውጥ ህግ በስተቀር ታሪካችንን ወደኋላ ብንመረምር ምን ያህል እንደተለወጥን ወይም እንደተለዋወጥን መገንዘብ ቀላል ነው፡፡ ስለተሰሩ መንገዶች፣ ስለፈረሱ ቤቶችና ስለተሠሩ ህንፃዎች፣ ስለታሰሩ ሰዎችና ስለተፈቱ ሰዎች፤ ስለተፃፉ ደንቦችና ስለተጣሱ ህጐች፤ ስለማይሸጡ መሬቶችና በሊዝ ስለተወሰዱ መሬቶች፤ ስለማይነኩ ሰዎችና ኋላ ስለተወረወሩ ሰዎች፡፡ ለውጥ አይቀሬ ነው፡፡ ህገመንግስቱን እንኳን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አይደለም ሰው ነው የፈጠረው ሰው ይለውጠዋል፡፡ከፋፋይ የሆነው የብሔር ብሔረሰብ አካሄድ ወደ ህዝባዊ አንድነት ተቀይሮ ለኢንዱስትሪ ልማት የሚሸጋገርበት ቀን ደርሷል፡፡
ዕድሜ ሙሉ ከመሞት ለአንድ ደቂቃ ፈሪ መሆን ይሻላል፡፡ ዘለዓለም ውሻ ሆኖ ከመኖር አንድ ቀን አንበሳ ሆኖ መሞት የሚለውን መዘንጋትም ተገቢ አይሆንም፡፡ ሁሉም ወቅት ወቅት አለውና! ሁኔታዎችን እንደየአመጣጣቸው መመዘን፣ እንደየልኬታቸው በቁርተኛ ትግል ዓይነተኛ መፍትሔ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ የሚያዘናጉንን ሁኔታዎች አትኩሮት ሳይሰጡ ለለውጡ ወቅቱን መጠቀም ወሳኝ ነው! ይሄ በፖለቲካም፣ በኢኮኖሚም፣ በባህልም፣ በሥነ አዕምሮአዊ ሂደትም፤ ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡ ፓርቲም፣ ግለሰብም ተሁኖ ቢታሰብ፤ ዋናው ነገር ይሄው ነው፡፡ ለለውጥ በአንድነት መነሳት !!!