አትኩሮታችን ከፖለቲካ ጥላቻ ወጥቶ ሕወሓትን በመደምሰስ ላይ መሆን አለበት(እውነትን የመዋጥ ግዴታ)

Minilik Salsawi በለውጥ ሃይሎች መካከል ልዩነቶች አሉ ይኖራሉ ይህ አዲስ ነገር አይደለም::ልዩነት ለዘላለም ይኑር::የለውጥ ሃይሉ በርካታው የፖለቲካ ብስለት ስላለው ይህን ያህል የትግሉ ችግር ባይሆንም አልፎ አልፎ በሚከሰቱ ክስተቶች ቀጥታ የፖለቲካ ጠጁን አይበጠብጥብ ባልበሰሉ እና እዚህ ግቡ በማይባሉ የገደል ማሚቱዎች ተጠቅሞ የፖለቲካ ጥላቻ ማራገብም ሌላው የትግሉ ጎታች አካል ነው::እያየን ያለነውም ይህንን ነው::እንዲህ ብላችሁ ጻፉ ከሚባሉ ጀምረው እንዲህ ብላችሁ ጻፉልን ብለው እስከሚታዘዙ የፖለቲካ አሽከሮች ተከበን ከፖለቲካ ጥላቻ መውጣት አልቻልንም::የፖለቲካ ባህል ለውጥ እና የጋራ ትብብር የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ መሆናችንን አንዘንጋ::በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ወሳኝ ወቅቶች ሳንጠቀምበት አምልጠውናል::

መታወቅ ያለበት ግዴታ ቢኖር በአሁኑ ወቅት ትግሉ ያለው በሕወሓት ዘረኛ ጉጅሌ መንግስት እና ነጻነትና ለውጥ በሚፈልገው የኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል መሆኑ የማይካድ ነው::ሕወሓት በተባለው የማፊያ ድርጅት ውስጥ ያለው የስልጣን ሽኩቻ ለለውጥ ሃይሉ የሚጠቅመው አሊያም ለወገን የሚፈይደው አንዳችም ነገር የለም::ለሁላችን የሚጠቅመን አሊያም የሚፈይድልን በፖለቲካ ጫና እና በኑሮ ውድነት እያንገላታን ያለውን የሕወሓት አገዛዝ መደምሰስ ብቻ ነው::ታዲያ አትኩሮታችን የት ላይ እንዳለ ራሳችንን መጠየቅ ግድ ይለናል::ሕወሓት የተባለው ድርጅት ተሰብስቦ አውርቶ ተመራርጦ ወደ ኢሕኣዴግ ስብሰባ መቶ ያንኑ ደግሞ ተደላድሎ እያለ እያለ ይቀጥላል::እኛ ደሞ ከዚህ ሂደት ውስጥ ተለቅመው የሚወጡ ሆኖም የጡዘት ወሬ የሆኑ ጉዳዮችን ይዘን እናላዝናለን::ሃገር ትዘረፋለች ህዝብ ይታሰራል ይገደላል እንሰድዳለን ይህ ሁሉ ሲሆን የፖለቲካ አሽከሮቻችንን ይዘን በፖለቲካ ጥላቻ ታጅበን በያለንበት ሆነን እናላዝናለን::አትኩሮቶቻችንን አለማወቃችን የምንህድበትን መንገድ እየተንፏቀቅን እንድንሄዽ አድርጎናል::እውነትን የመዋጥ ግዴታ አለብን::

የሕወሓትን የማዘናጊያ አጀንዳ ከማራገብ አንድ ሃገር አንድ ትግል በአንድ ሕዝብ የሚለውን የጋራ ትስሥር ይዘን ታሪክ ልንሰራ ይጠበቅብናል::በሕወሓት ውስጥ ያልተከሰቱ እና ያሌሉ የፖለቲካ ጡዘቶችን በምናባችን እና በጭረቶች እየፈጠን እያጋነንን ብናወራው ለትግሉ ምንም ፋይዳ የለውም::ትግሉን ሁሉ ለድርጅቶች መተው የለብንም እኛም እንደዜጋ ማድረግ ያለብን ሁሉ ማድረግ አለብን::ለውጥ እስከፈለግን ድረስ በየምናምኑ እየተወሸቅን ከምናወራ በተግባራዊ ስራዎች ላይ መሳተፍ እና ለነገው ትውልድ ታላቅ ስራ የመስራት ግዴታ እና ሃገራዊ ሃላፊነት እንዳለብን ልናውቅ ይገባል::ትግሉ በስራ ላይ ውሎ የተለያዩ የለውጥ ሃይሎች ካለው አገዛዝ ጋር በተለያዩ መንገዶች እየታገሉ ይገኛሉ:አትኩሮታችን መሆን ያለበት ሕወሓትን በመደምሰስ እና ለትግሉ የሚሆኑ መረጃዎችን በመለዋወጥ ላይ መሆን አለበት:ከኔ በላይ አዋቂ የለም በሚል ባልበሰለ የፖለቲካ ባዶነት ውስጥ እየዋኙ የሚደፈቁትን መመልከት የለብንም ::በሕዝቡ ላይ ጫና ከሚያሳድሩ እና የፖለቲካ ሃይል ሚዛን ከሚሰቅሉ መረጃዎች ራሳችንን ልንጠብቅ ይገባል::ትግሉን አስፍተው ሕዝቡን የሚያነሳሱ የሚያደራጁ የሚያታግሉ ስራዎችን መስራት ይጠበቅብናል::እንንቃ::አትኩሮታችን በሕወሓት የስልጣን ሽኩቻ ላይ ሳይሆን ሕወሓትን በመደምሰስ ላይ መሆን አለበት::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

አቶ በረከት ስምኦን በማሌዢያ ፒናንግ ደሴት የንግድ እና መኖሪያ ሕንጻ ቤት እያስገነቡ ነው::

Minilik Salsawi's photo.Minilik Salsawi - የለውጥ ሃይሉ እርስ በእርሱ በፖለቲካ ጥላቻ ሲጠዛጠዝ በሃገር እና ሕዝብ ላይ ዘረፋው ቀጥሏል:-ከጸረ - ሙስና ኮሚሽን ከመዝገብ ቁጥር /203/2007 ከተገኘው መረጃ መሰረት አቶ በረከት ስምኦን በማሌዥያ ፒናንግ ደሴት ጃላን ባሩው 62 በተባለ ቦታ ላይ በሚሊዮኖች ዶላር በወጣ ወጪ ኢትዮጵያ ውስጥ በብረታብረት ስራዎች ላይ ከሚገንኝ አንድ ማሌዢያዊ ጋር በመቀናጀት እጅግ ዘመናዊ የንግድ እና መኖሪያ ሕንጻ በኢንቨስትመት ስም እያስገነቡ መሆኑን ጥቆማ ለኮሚሽኑ ደርሶ በመመዝገብ እያጣራ መሆኑ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል::

ከሼህ መሃመድ አላሙዲ የሃገሪቱን ሃብት እያሳለፉ እየሰጡ ከፍተኛ ገንዘብ የሚረከቡት ኤርትራዊው አቶ በረከት ስምኦን በግልጽ ከሚታወቀው ከአገር ቤቱ በካፒቴኑ ስም ካስመዘገቡት ሆቴል እና ማደያዎች እንዲሁም የሪያል ስቴቶች በተጨማሪ በዱባይ እና አቡዳቢ መኖሪያቤቶች እና አክሲዮኖች ሲኖሯቸው እንዲሁም በሚላን ጣሊያን መኖሪያ ቤት በሕንድ የሚስማር ፋብሪካ ባለድርሻ ናቸው የሚል ከዚህ ቀደም በጸረ ሙስና ኮሚሽን የተመዘገበ ፋይል አላቸው:: 

የጸረ ሙስና ኮሚሽን በሕወሓት ባለስልጣናት በተለይ በአቶ ደብረጽዮን እና በጄኔራል? ሳሞራ ልዩ ትእዛዝ የሚመራ ሲሆን በከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ የሚመጡ መዝገቦች ከቦታቸው እንዳይንቅሳቀሱ እና ተጣርተው ማረጋገጫ እንደተገኘ ከነማስረጃቸው ታሽገው ቀጥታ ወደ ደህንነት ቢሮ እደሚላኩ ይታወቃል::የአቶ በረከት የመኖሪያ ቤት ግንባታም ጠቅላላ መዝገቡ እንዳለቀ በጥብቅ ምስጢር በሚል ለደህንነት ቢሮ እንደሚላክ ምጮቹ የጠቆሙ ሲሆን የከፍተኛ ባለስልጣናትን ጉዳይ በሚመረምሩ መርማሪያን ላይ ክፍተኛ የሆነ የደህንነት ክትትል እንደሚደረግ ምንጮቹ አክለው ጠቁምዋል::

የደህንነት ቢሮው በቅርቡ ያወጣቸው መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ባለስልጣኖች በተለያዩ ሃገራት የሰሯቸው መኖሪያ ሕንጻዎች መታገዳቸው ይታወቃል::የወያኔ ከፍተኛ ባለስልጣናት ኬንያ እና ሱዳንን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት መኖሪያ ቤቶች የሰሩ ሲሆን በታንጋኒካ ውስጥ ሃይቅ ዳርቻ ላይ የግል የመዝናኛ ቦታ ለመገንባት ያመለከቱ የሕወሓት ባለስልጣናት ከታንጋኒካ ባለስልጣናት ጋር በቦታ መረጣ እና በጉቦ ገንዘብ አለመግባባት እስካሁን እንዳልተፈቀደላቸው ታውቋል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

ከአቤቱታ ሮሮ እና ብሶት ተላቆ ተጨባጭ ስራ መስራት ያለበት ጊዜ ላይ መሆናችንን እንወቅ::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ገባንም አልገባንም መጻፋችንን መመካከራችንን አናቋርጥም::ዋናው ጉዳያችን ወያኔን ገንድሶ መጣል ላይ መሆኑ መዘንጋት የለብንም::ካሁን በፊት የተሰሩ ስራዎችን መከለስ እና እንዳላዋጡ ማመንም ግድ ይላል::ተጨባጭ ስራ መስራት ሲገባ በስድብ አሉባልታ አቤቱታ ሮሮ እና ብሶት ላይ ስንዘፍን ኖረን አሁንም ባለንበት እየረገጥን ነው::በተደጋጋሚ እንደሚነገረው የራሳችን ጠላቶች ራሳችን ነን::ወያኔማ አጀንዳም ፈጥሮ ይሁን ሃይል ተጠቅሞ ስራውን እየሰራ ነው::እኛ ደሞ ወያኔ በሚሰጠን አጀንዳ እየተለባለብን በሚጠቀመው ሃይል የሚፈጠረውን አቤቱታ እና ብሶት እያወራን ተጨባጭ ስራ ሳይሰራ በወሬ ናዳ ተከበን በሌሎች ትከሻ ነጻ ለመውጣት እንውተረተራለን::

በመሐል አገር እና በዳር አገር ለሃገር እና ሕዝብ ነጻነት የሚታገሉ የለውጥ ሃይሎችን ስራዎች ከፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ውጥተው ተጨባጭ ስራዎች ላይ እንዲተከሉ እያንዳንዳችን እንደ ዜጋ የመተባበር አብሮ የመንቀሳቀስ ግዴታ አለብን::ነጻነት ያለው በያንዳንዳችን እጅ ላይ መሆኑን መዘንጋት የለብንም::ወያኔ በለውጥ ሃይሎች መካከል መተማመን እንዳይኖር ጠንክሮ እየሰራ ሲሆን ፖለቲካ ያልገባቸው የመኖሪያ ፈቃድ ፈላጊዎችም በአውሮፓ ተቀምጠው ሳያውቁ በስሜት እና በደመነብስ በሚረጩት መርዝ በለውጥ ሃይሎች መካከል ጠንካራ የሆነ የትብብር ስራ እንዳይሰራ ጋሬጣ ከመሆን አልፈው ለወያኔ የስልጣን እድሜ ሚናቸውን ያበረክታሉ:: ነጻነት በማህበራዊ ድህረገጽ የሚገኝ የሚመስላቸው በጻፉ ቁጥር ሁሉ ወያኔ የወደቀ የሚመስላቸው እና እፎይ ብለው የሚተኙ ሁሉ የትግል ስራዎችን በተጨባጭ እንዲሰሩ ራሳቸውን መከለስ ያለባቸው ደረጃ ላይ መድረሳችንን ሊያውቁት ይገባል::ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል::ለውጡ ግን በሁሉም የለውጥ ሃይሎች ጎን ለጎን በመቆም እና ተግባራዊ ስራዎች በመስራት እንጂ ሮሮ እና ብሶት ካለተጨባጭ ስራ እና መፍትሄ በመተንፈስ አይደለም::

ወያኔ በፖለቲካ ስራዎች በልጦናል::ይህንን ማመን ግድ ይላል::ካለፈው ስህተት ያልተማረ ካለፈው ስህተት የማያገግም እና ስህተቱን ሸፍኖ የሚሄድ ሌላ ትልቅ ስህተት እንደሚሰራ በጊዜ ሊያውቅ ይገባል::በለውጥ ሃይሎች መካክል - ጠንካራ የሆነ ግንኙነት አለመኖሩ + በጥርጣሬ መተያየቱ + በሃሜት ስድብ እና አሉባልታ መወጠሩ + ለግል ጥቅም ጉዳይ እና ለመኖሪያ ፈቃድ ፖለቲካን መያዙ + የአንድ ሰሞን የሆይሆይታ እና ወረት ፖለቲካ + ራስን በባዶ ማግዘፍ ፕሮፓጋንዳ + ግትርነት + ከኔ በላይ አዋቂ ላሳር + የአጀንዳ ክንብንቦሹ የመሳሰሉት ጉዳዮች ተጨባጭ ስራዎች እንዳይሰሩ በዘር እና በቋንቋ እንድንከፋፈል እንዲሁም በውስጥ መደብ እና ባልበሰሉ ፖለቲከኛ ነን ባዮች የጎንዮችሽ ሽሙጥ እንድንተያይ አድርጎናል:: አናምንም ብለን እንኮፈሳለን እንጂ እስካሁን በታዩ ሂደቶች ከፕሮፓጋንዳ ውጪ በተግባር የታየ አንድም ነገር የለም:: በጋራ እንቁም::በአንድነት እየተሰሩ ባሉት የትግል ጅማሮዎች ላይ እንረባረብ::ነጻነታችንን የምናገኘው በሌላው መስእዋትነት ሳይሆን በራሳችን መስእዋትነት እንደሆነ አንዘንጋ::ከአቤቱታ ሮሮ እና ብሶት ተላቆ ተጨባጭ ስራ መስራት ያለበት ጊዜ ላይ መሆናችንን እንወቅ:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

የሃይል ሚዛን በፕሮፓጋንዳ ጡዘት ውስጥ የሚኖረውን የፖለቲካ ሚና ልናውቅ እንገደድ !!!

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) : በማይጠቅም የጠላትን ሃይል የማጋነን ስራ ላይ ከመጠመድ የራሳችንን የትግል ስራ በመስራት ሕዝብን በማስተባበር በመቀስቀስ እና በማደራጀት ላይ ያተኮሩ አመርቂ ስራዎች ብንሰራ ማንን ገደለ?ስለ ሕወሓት መተካካት እና ስለ ብአዴን መሰነባበት ከምንደሰኩር ትግላችንን አጠናክረን በጋራ በአንድነት ሆነን ለሚፈናቀለው ለሚታሰረው እና ለሚገደለው ሕዝባችን እንድረስለት::የጠላቶቻችንን ስብሰባ እያጋነንን እያሞካሸን ሲለን እያሰፋን እያንጠራራን እና እየሰቀለን የምናወራበት ጊዜ ላይ አይደለንም::ደግሜ እናገራለሁ ጠላቶቻችንን የምናንበረክክበት እና በሚገባቸው ቋንቋ የምናናግርበት ጊዜ ላይ ነን::የሚገባን ካለን::ሰሞን ሰሞን እየጠበቁ በተገኘው አጀንዳ ላይ ማጨብጨብ ይቁም!!!

አርከበ ተመለሰ ተተካ አዲሱ ተሰናበተ ለለውጥ ሃይሎች ምንም የሚጠቅም አጀንዳ አይደለም::የመከላከያ ባለስልጣኖች የደህንነት ባለስልጣኖች የአንድ ፓርቲ አባል እና የስብሰባ አካል ሆነው በአይናችን እያየን ባለንበት በዚህ ሰአት ላይ ሕዝባዊ መንግስት ሕዝባዊ የመከላከያ ሰራዊት ብሄራዊ የደህንነት ተቋም እንዲኖረን ማድረግ የምንችለው በኛው በራሳችን ትግል እንጂ የሕወሓትን ፕሮፓጋንዳ በማጦዝ አይደለም::የሃይል ሚዛን በፕሮፓጋንዳ ጡዘት ውስጥ የሚኖረውን የፖለቲካ ሚና ልናገናዝብ ግድ ይለናል::ስለ ሕወሓት መተካካት ስለ ሽማግሌዎቹ እና ዘራፊዎቹ ብኣዴን አመራሮች መሰናበት ባወራ አዲስ ትኩስ የፖለቲካ እድል በፕሮፓጋንዳው መስክ ፈጥረን የሃይል ሚዛኑ እንደተጠናከረ የሚያገጥ ስራ እየሰራን እንደሆነ አንዘንጋ::ስለ ሕወሓት ስብሰባና ጉዳይ በምናወራበት ጊዜ ሁሉ ሕዝብ ላይ ሊፈጥር የሚችለውን ተጽእኖ ከግንዛቤ ልናስገባ ይገባል::ሕዝቦች በስቃይ ወላፈን እየተመቱ ባለበት በዚህ ወቅት ትግሉን አጠናክሮ ወያኔን መደምሰስ ሲገባን የቅጥረኞቹን የሪፖርተር እና መሰሎቹን ስራ ማራገብ ለትግሉ የሚፈይደው አንድም ነገር የለም::

የሕወሓት ማፊያ ቡድን ወራዳ ነው::የሕወሓት ማፊያ ቡድን ከምድረገጽ መጥፋት አለበት::ኢትዮጵያ የምትባል አገር እንዳትኖር የሚመኝ ይህ አሸባሪ ድርጅት ለማንም አይበጅብ::ብናወራለት ተተካኩ ተባሉ ተፋቀሩ ብንልለት ምም አይበጅም::የሚበጀን ነገር ቢኖር ትግሉን በአራቱም አቅጣኛ በማጠናከር ሕዝቦችን በማስተባበር በመቀስቀስ እና በማደራጀት ይህንን ከይሲ የማፊያ ቡድን ማስወገድ ብቻ ነው:: እስኪ ራሳችን እንጠይቅ? ስንቶቻችን ነን ለራሳችን አላማ እና ግብ ጠላቶች የሆንን?በወሬ ናዳ እያሽካለልን ትግሉን የጎተትን?እርስ በራሳችን በተራ የመንደር ወሬ ተቧድነን የምንወነጃጀል? ከትግል ይልቅ በሃሜት እና በፍረጃ ላይ በፕሮፓጋንዳ ላይ የተተከልን ስንቶቻችን ነን? ከዚህ አይነቱ ጋሬጣ ራሳችንን አላቀን ሕዝብን አስተባብረን የሕወሓትን ጉጅሌ አገዛዝ በተገኘው መንገድ ሁሉ በጋራ እና በአንድነት ሆነን መደምሰስ አለብን ? ከፕሮፓጋንዳ ጡዘት እንላቀቅ!!!የሃይል ሚዛን በፕሮፓጋንዳ ጡዘት ውስጥ የሚኖረውን የፖለቲካ ሚና ልናውቅ እንገደድ !!! ( ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬ )

በተገኘበት አብሮ መውቀጥ ለምን ? በነፈሰበት መንፈስ እስከመቼ ? በሚገባቸው ቋንቋ እናናግራቸው!!!

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) እስክመቼ ድረስ እያወራን እንደምንኖር አላውቅም::ይህን ሰሞን የሕወሓትን ስብሰባ ተከትሎ አስር ጊዜ የባለስልጣኖቹን ስም በመጥራት ወሬ እያጣፈጡ የሚነግሩን ተቃዋሚ ነን ባዮች በተገኘበት አብሮ መውቀጥ በነፈሰበት አብሮ መንፈስ ለምን? እስከመቼ? ልላቸው ወደድኩ::አሁን ጊዜው የአርከበ ምንቸውት ገባ የአዜብ ምንቸት ወጣ እያልን የሕወሓትን ጉዞ የምንደሰኩርበት ሳይሆን በሚገባቸው ቋንቋ የምንነግርበት ጊዜ ላይ መሆናችንን አንዘንጋው:;እረ እስከመቼ ? እንንቃ !!!

የሃገሪቱን የማፊያ መንግስት በበላይነት የሚመራው ሕወሓት መሆኑ እሙን ነው:: ሕወሓት ከስሙ ጀምሮ እንደሚያሳየን ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያውያን የማይተኛ ድርጅት ነው:: ከሕወሓት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን አሊያም የሕዝብ ስልጣን መጠበቅ ከእባብ የእርግብ እንቁላል እንደመጠበቅ ነው::ይህ ድርጅት ከበረሃ ጀምሮ ይዞ የመጣውን ጸረ እትዮጵያ አቋሙን ለመተግበር ሃገርን እና ሕዝብን አደጋ ውስጥ ጥሎ ከፍተኛ የሆነ ወንጀል በመስራት ላይ ነው:: አመራሮቹም ቢሆኑ የሚሰሩት ግፍ ዘረፋ እና ይቅር የማይባል ተንኮል ሕዝቡን ለድህነት ሃገርን ለውርደት ዳርጓል::

የሕውሓት አመራሮች ተናከሱ አልተናከሱ ተተካኩ አልተተካኩ የሕወሓት አመራሮች ተፋቀሩ አልተፋቀሩ ዋሹ አልዋሹ ለሃገራችን እና ለሕዝባችን የማይተኙ እባቦች መሆናቸውን ልናውቅ ይገባል::ማወቅ ያለብን እነዚህን ተኩላዎች ማስወገድ ብቻ ነው በሚገባቸው ቋንቋ ልንነግራቸው ይገባል ለአለም የሚሰሩትን ግፍ በሎቢ ልናዳርስ ይገባል::ስለ ሕወሓት የፓርቲ ስራዎች ከምናፏጭ ይልቅ ለትግሉ መሆን ያለበት ተግባር በመፈጸም ሕወሓቶችን በምናስወግድበት ላይ ሁሉ ልንረባረብ ይገባል::

የኢሕአዴግ/ሃይለማርያም ደሳለኝ አሳፋሪ 11% እድገት ሲጋለጥ

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በሃገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የስራ አጦች ቁጥር ተከባለች:: የኑሮ ውድነት ንሯል::ሕዝብ በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እየተመታ ነው፡፡ መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች በየቀኑ ዋጋቸው እየጨመረ ኑሮን መቋቋም ተስኖታል፡፡ የልጆች ትምህርት ቤት ክፍያ ከአቅም በላይ እየሆነበት ነው፡፡ የቤት ኪራይ ክፍያ ከሚቋቋመው በላይ ነው፡፡ በትራንስፖርት እጦት በፀሐይና በዝናብ ይንገላታል፡፡ ፈረቃ በይፋ ያልታወጀላቸው ኤሌክትሪክና ውኃ ለቀናት እየጠፉበት ይሰቃያል፡፡ በስሙ በድጎማ የሚመጡትን ዘይትና ስንዴ በጥቅም የተሳሰሩ ሌቦችና ደላሎች አየር በአየር ይሸጡበታል፡፡ የግብይት ሥርዓቱ እጅግ በጣም ኋላቀርና ተቆጣጣሪ የሌለው ከመሆኑ የተነሳ ሕዝቡን በቁሙ እየገደለው ነው፡፡ያለው ስርአት በፍጹም አገሪቷን ሊያስተዳደር ስላልቻለ መውደቅ አለበት::አገራቸውንና ሕዝባቸውን በቅንነት የሚያገለግሉ እየተገፉና ዕድገት እየተከለከሉ ወረበሎች አገር እየበደሉ ነው፡፡በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ ከነአጋሮቹ ያገኘው መቶ በመቶ የፓርላማ መቀመጫዎችን እንጂ፣ መቶ በመቶ የሕዝቡን ይሁንታ አይደለም፡፡

ተጨማሪ ሕዝብ የረሃብ አደጋ ስለተጋረጠበት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል::

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ቢሮ (UNOCHA)ባወጣው አዲስ ሪፖርት እንዳመለከተው በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ከተራበው በድርቅ ከተጎዳው ሕዝብ በተጨማሪ በዚህ ወር ውስጥ ብቻ 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ የረሃብ አደጋ ተጋርጦበት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው አትቷል::በግማሽ አመት የሚያስፈልጉ የሰብአዊ እርዳታዎችን በተመለከተ የኢትዮጵያን መንግስት እና ለጋሾች በተገኙበት ይህ ሪፖርት ይፋ ሆኗል::

ሪፖርቱ እንዳለው ለምግብ እርዳታዎች እና ምግብ ነክ ላልሆኑ እርዳታዎች እስከ 386 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ እና እስካሁን 158 ሚሊዮን ዶላር በግማሽ አመት እንደተገኘ አሳውቋል::ለመጪው ስድስት ወራት ብቻ የሰብአዊ እርዳታ ፈላጊው እጅግ ከሚፈለገው በላይ እንደሚጨምር እና በመጀመሪያው 6 ወራት እንደተደረገው ሁሉ የዝናብ እጥረት በተከሰተባቸው ቦታዎች ሁሉ የምግብ እርዳታዎችን ለማድረግ የታለመ እንደሆነ ጠቅሶ የተረጂዎች ቁጥር እንደሚጨምር በሪፖርቱ ገልጿል::Minilik Salsawi

ያለንበት ጊዜ በተገኘው አጀንዳ ላይ የሚነፈስበት ሳይሆን ብስለት የሚጠየቅበት ጊዜ ነው::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ስሜታውያን በርክተዋል::ተናግረው እፎይ ብለው የሚተኙ በርካቶች ሆነዋል::ልክ ልኩን ነገርጉት ብለው ሌላውን ደሞ ለማሸማቀቅ (የሚሸማቀቅ ካገኙ) አስበው በየምናምኑ የሚንጎዳጎዱ ጊዜው ይቁጠራቸው::በነፈሰበት የሚነፍሱ ሳያገናዝቡ የሚያራግቡ የፈጠራ እሳት የሚያርገበግቡ በተገኘበት ተደናብረው እና ደንብረው ደንግጠው ለማስደንገጥ የሚርበተበቱ እንዳሉ ሁሉ ሙድ ለመያዝ የሕዝብን ጭንቀት የሚጠቀሙበት ተደምረው ሆዳም በጥቅም የሚደለሉ በጠለዟቸው ሄደው የሚቾመሱ አጀንዳ እና አቋም አልባ ሮቦት ካድሬዎችም በርካቶች ሆነዋል::ይህ ሁላ የግንዛቤ እጥረት ነው::ያለንበትን ጊዜ እና የሚካሄዱ ትግሎችን አለመመዘን ለትግሉ አስታውጾ ለማድረግ ደፋ ቀና ከማለት ይልቅ ተደራሽነት ያሌላቸውን የክፋት ብእር አጀንዳዎችን ይዞ መክለፍለፍ ምም ውጤት የለውም::ለመድገም ያህል ካለፈው ለመማር ያልቻልን የራሳችን ጠላቶች መሆናችንን እንደቀጠልን ነው::
ወያኔ ስራዋን ትሰራለች::ጓዳ ጎድጓዳ ገበናውን ስላወቀች በተላላኪዎቿ የሚሰጠውን የቤት ስራ ለለውጥ ሃይሎች አሸክማ እሷ የውስጥ ጉዳይውን እያስተካከለች የለውጥ ሃይሎች እያሰረች እየሳደደች እየገደለች ስልጣኗን ታጠናክራለች::እና ከሚዘመሩ የሃሰት መዝሙሮች ተነስተን ወያኔ አብቅቶላታል በሚል የፕሮፓጋንዳ መደምደሚያ ላይ ትተን የሰጠችንን የቤት ስራ እየመነዘርን እዛው ላይ እንደፋደፋለን::ራሳችን ማረም የምንጀምረው መች ይሆን ?አጀንዳ የማታጣው የቤት ስራ ለለውጥ ሃይሎች ማዘጋጀት ስራዋ የሆነው ወያኔ የምታመጣው አጀንዳ እና የቤት ስራ አትኩሮት ባንሰእጠው ያላትን የፕሮፓጋንዳ ሂደት ማኮላሸት እንችላለን::በዚህ ሰሞን ብቻ የራያ ቢራ ባለኦክሲዮን የተባለው በአቡዳቢ የሕወሓት ንብረቶች የበላይ ጠባቂ አቶ ዳዊት ቃለ መጠይቅ - በቤንሻጉል የሰው ስጋ በሚጥሚጣ ተበላይ የሚል ወጣ ያለ ምስል - የኦሮሞ ጋላ ተብሎ መጠራት አለበት የሚል ፍትፈታ .. ኧረ በስንቱ ልበጥበጥ አለች? በሶ:: ይህንን የሚያራግቡ እና አገር ወዳዱን ርሁሩሁን ዲያስፖራ ሆዱን የሚያንቦጫብጩ አጀንዳዎች ላይ እንዲሽከረከር ማድረግ ምን ያህል የወያኔን አደገኝነት የሚያሳይ ነው::
አደባባይ ላይ አተካራ ገጥሞ የለውጥ ሃይሎን በ ነው/አይደለም አተካሮ ለማናከስ ክርክሮችን ፈጥሮ አለመግባባቶች ለማስፋት የሚደረጉ ያልተጣሩ መረጃዎች እና የፈጠራ ማዘናጊያ ጽሁፎች ምን ያህል የትግሉን ወንዝ እንደሚያሻግሩን አላውቅም:; መንገድ ዳር ሰጥሞ ለመቅረት ካልሆነ በስተቀር ሚዲያዎች ባልተናገሩት እና ምንጩ ባልታወቀ ወያኔያዊ የፈጠራ አጀንዳ እና መረጃ ላይ ፊት ለፊት እየነጠሩ መጠዛጠዝ የብስለት ስርቆት መካሄዱን ፍንትው አድርጎ ያሳያል::ወያኔን ለመጣል አንድ እና አንድ ነገር ያስፈልጋል ህዝብ ተስፋ የሚያስቆርጡ መረጃዎች የለውጥ ሃይሎች የእርስ በእርስ መናከስ በተገኘ አጀንዳ እንደተፈለገ ንፍስፍስ ማለት የመሳሰሉት ጉዳዮች ሊታሰብባቸው እና ሊወገዱ ይገባል::የሚመጡ መረጃዎች ሃላፊነት የሚወስድ ሰው አሊያም ሚዲያ እስካልተገኘ ድረስ አሊያም ወያኔን ወያኔ አዋረደ በሚል የዋህነት ፈሊጥ መነሳት እንዲሁም ባልበሰለ የዘረኝነት እና የመንደርተኝነት ጽሁፎች ከመቃጠል ራሳችን ማዳን እና ልብ መግዛት ይገባናል::ሁላችንም በጋራ በሚደረጉ ትግሎች ላይ ልንረባረብ ይገባል::ትግሎችን በማስፋፋት በማስተማር እና በመቀስቀስ በመርዳት ላይ ልንሰማራ ይገባል:ብስለት ማለት ለትግል የሚደረጉ አስታውጾዎችን በማበርከት እና በተረጋገጡ አጀንዳዎች ላይ ስራ መስራት ሲቻል ብቻ ነው::እና እኔም እላለሁ ያለንበት ጊዜ በተገኘው አጀንዳ ላይ የሚነፈስበት ሳይሆን ብስለት የሚጠየቅበት ጊዜ ነው:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

የደብል ዲጅቱ የኢኮኖሚ እድገት ፕሮፓጋንዳ እርቃኑን እየወጣ ነው::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - 11% የተባለ የኢኮኖሚ እድገት ሕዝቡን ከድህነት ሊያወጣ ቀርቶ ጭራሽ የደሃ ደሃ የሚል አዲስ የቋንቋ ስያሜ ወልዷል::የኑሮ ውድነቱ እያሻቀበና ህዝቡን እያስደነገጠ ነው፡፡አጠቃላይ የምግብ ፍጆታዎች ዋጋቸው እጅግ አሻቅቧል፡፡በሚቀጥሉት ስድስት ወራት የኢትዮጵያ ሕዝብ በከፍተኛ ድህነት እንደሚመታ የሚጠቁሙ መረጃዎችን ተከትሎ የወያኔ ባለስልጣናት የደብል ዲጂት የኢኮኖሚ እድገቱ እንዳልተሳካ በመናገር ላይ ናቸው:: የኑሮ ውድነቱ ችጋር/ድህነት ችጋሩ ደግሞ ጐጠኛ አስተሳሰብና አሠራርን ልቅ ሙስናን የፍትህ እጦትን በተግባር ፈጥረዋል::የፖለቲካ ሥርአቱም አደጋ ላይ መውደቁን በተግባር እያየን ነው::ከዚህ የኑሮ ውድነት መገላገል የምንችለው ከድህነት አለንጋ ራሳችንን ማዳን የምንችለው በአንድነት ሆነን የበሰበሰውን የወያኔን ስር አት መደምሰስ ስንችል ብቻ ነው::ንግዱን በሞኖፖል ተቆጣጥሮት በመንግስት የገበያ ተቋማት ውስጥ የሚንቀሳቀሰው ወያኔ ራሱ የገንዘብ አቅርቦት እና የዋጋ ትንበያዎችን በማስፋፋት በሃገሪቱ ላይ የኑሮ ውድነት እንዲስፋፋ በጭፍን እየሰራ ይገኛል::ስለሃገር እና ስለ ህዝብ ደንታ የሌለው ይህ ስርአት ከልክ በላይ ገንዘቦችን በማተም እና በማሰራጨት መንግስት ከባንኮች በመበደር የውጭ ምንዛሬን በማከማቸት ወዘተ የሃገር ኢኮኖሚ ከሚችለው በላይ የኢኮኖሚ ውዥንብሮችን በመፍጠር በልማታዊ መንግስትነት ስም የኑሮ ውድነት እንዲንሰራፋ በማድረግ ከፍተኛ ችግርን ለህዝብ አሸክሞ በህዝብ ትከሻ ላይ በመቀመጥ እኩይ ብዝበዛውን እያደረገ ይገኛል::
የወያኔ የኢኮኖሚ ፖሊሲ በሃስት ፕሮፓጋንዳ ላይ ብቻ የተገነባ በመሆኑ ባለስልጣናቱን በፊት ለፊት እያጋፈጠ ይገኛል::የሃገሪቱን ኢኮኖሚ በምክር ይዘውራሉ የሚባሉት የወያኔ ኢኮኖሚስቶች ተብየዎች በሃገሪቱ የውጭ ምንዛሬ እንዳሌለ በመናገር ላይ ናቸው::ይህ ደሞ የፈጠረው ራሳቸው በሚያራምዱት የሙስና እና የዘረፋ ተግባራት ነው::የሃገሪቱ ጂዲፒ እያሽቆለቆለ ከመህዱም በላይ የማኑፋክቸሪው ዘርፍ አውላላ በረሃ ላይ ካለደጋፊ ተንጋሎ ቀርቷል::ላኪዎች ሆነው በተለያዩ የሃገር ውስጥ ምርቶችን በመላክ ላይ የተሰማሩት ወያኔዎች ከነዘመድ አዝማዶቻቸው ከሚልኩት እቃዎች የሚገኙትን የውጪ ምንዛሬዎች በዛው ሃገር ቤት ሳያስገቡ በውጪ ባንኮች መጨመራቸው እንዲሁም በተለያዩ ሻንጣዎች የተሞሉ የውጪ ምንዛሬዎችን ማሸሻቸው በሃገሪት ላለው የውጪ ምንዛሬ ካዝና ባዶነት ራሳቸው ተጠያቂ ናቸው::የኤክስፖርት ስራም ይሁን የውጪ ምንዛሬ ባዶነት መንስኤዎች ራሳቸው ባለስልጣናቱ ናቸው::የውጪ ንግድ ስራዎችን አቀላጥፎ በማካሄድ ሊገኙ የሚችሉ የውጪ ምንዛሬዎችን መመንተፍ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የአገዛዙ ሰዎች ያልሆኑ ነጋዴዎች እንዳይሰሩ ጋሬጣ መፍጠር ሌላኛው የወያኔ ሌቦች ትልቅ ችግር ነው::
በሃገሪቱ የተከሰተው ድርቅ የዝናብ እጥረት ቢሆንም ችግሩ በሰው ሰራሽ መንገድ መከላከል እየተቻለ በውሸት እናእውነታን ልመሸፋፈን በመሞከር ወገንን ለከፋ አደጋ እያዳረጉ ያሉት እነዚሁ ባለስልጣናት ናቸው::በምግብ እሕል ራሳችን ችለናል በሚል የውሸት ፕሮፓጋንዳ ለተራቡ ለተጎዱ ወገኖች የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት አለ በማለት ያሌለውን እንዳለ ያልተሰራውን እንደተሰራ በማድረግ በባዶ ሜዳ የሃሰት ንግግሮችን በመደስኮር ከሕዝብ ለመደበቅ ቢሞክሩም ተጋልጠዋል:: ተጠባባቂ የምግብ ዝግጅት እንኳን ሊኖር ይቅርና ከአመት በፊት እንደሚመጣ በጥናት የታወቀውን ድርቅ እንኳን ሊያስተካክል እና ሊቋቋም የሚንል ሃይል አልተዘጋጀም::በምግብ እህል ራሳችን ችለናል እየተባለ ከ15 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ሲራብ የአለም ሚዲያዎች ሲቀባበሉት ወያኔ ግን ክዶታል ይህ የሚያሳየው የአገዛዙ ፖሊሲዎች ብልሹ እና የተጭበረበሩ መሆናቸውን ነው::ሃይለማርያም ደሳለኝ በምግብ እህል ራሳችንን አልቻልንም የሚሉት ይህ ነው እንግዲህ በግብርና ላይ የተመሰረተው ደብል ዲጂት እድገት እና የአንድ አመት ድርቅ ሊቋቋም ያልቻለው ኢኮኖሚ::
ይህ ሁሉ እና ተመሳሳይ ያልተጠቀሱ ጉዳዮች ተደማምረው በገሃድ ይወያኔን ማንነት እያሳዩን ነው::የደብል ዲጂት እድገት እያለ ወያኔ የሚያላዝንለት የ11% የኢኮኖሚ እድገት ሕዝብን ለድህነት ከመዳረጉም በላይ የደሃ ደሃ የሚባል አዲስ የቋንቋ ስያሜ ወልዷል::የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ሕዝብ ከማገልገል ይልቅ አገልግሎታቸውን አቋርጠው በሕዝብ ላይ ሲያሾፉ ነው የሚውሉት::ለዚህ ሁላ መፍትሄው ያለው የወያኔ አገዛዝ አስወግዶ በአዲስ ሕዝባዊ መንግስት መተካት ብቻ ነው:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬