የአገር አድን ንቅናቄው ም/ሊቀመንበሩ ሞላ አስግዶምን አጣ፣ ከዚህ በኋላስ ? (ሳተናው)10455662_1636650653272798_5289973650861035070_n
(ሳተናው) – አራት በትጥቅ ትግል የሚያምኑ ድርጅቶች፣ የአፋር ድርጅቶች ንቅናቄ፣ የአማራ ሕዝብ ንቅናቄ፣ የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደሚት) እና የግንቦት ሰባት አርበኞች ንቅናቄ ፣ በዚህ ሳምንት ዉስጥ አገር አድን ንቅናቄ በሚል ስያሜ መቀናጀታቸው በስፋት መዘገቡ ይታወሳል። ዶር ብርሃኑ ነጋ የቅንጁት ሊቀመንበር፣ አቶ ሞላ አስግዶም ደግሞ ም/ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።
የአራቱ ድርጅቶች መቀናጀት ይፋ በሆነ በጥቂት ቀናት ዉስጥ ጳጙሜን 5 ቀን፣ አቶ ሞላ አስግዶም፣ ወደ ኢትዮጵያ እንደተመለሱ ኢሳት በሰበር ዜና ለአድማጮቹ ዘግቧል። የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ደሚት ሊቀመንበር ከንቅናቄው ከድተው ወደ ኢትዮጵያ ማምለጣቸውን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። አቶ ሞላ አስግዶም ንቅናቄው ተለይተው ከጥቂት ጓዶችቸው ጋር ወደ ኢትዮጵያ ያመለጡበት ምክንያት ያልታወቀ ቢሆንም በቅርቡ ከተፈጠረው ጥምረት ጋር የተያይዘ ሳይሆን እንደማይቀር የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ በሥራ አስፈጻሚ ደረጃ የጥምረቱን መመስረት በአብላጫ ድምጽ ሲወስን አቶ ሞላ አስግዶም ልዩነት እንደነበራቸው እነዚሁ የኢሳት ምንጮች አስረድተዋል።የሚል ነበር የኢሳት ዜና።
አቶ ሞላ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ለማረጋገጥ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። ነገር ግን አቶ ሞላ አስግዶም፣ ኢሳት እንደዘገበው ወደ ኢትዮጵያ ሳይሆን ወደ ሱዳን እንደሄዱ የደረሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ደሚት ጥምረቱን ከመሰረቱት ድርጅቶች መካከል ጠንካራው ድርጅት እንደሆነ ይታወቃል። ወደ ሰላሳ ሺህ ሰራዊት እንዳለው የሚገመት ሲሆን፣ በአንጻሩ ግንቦት ሰባት አርበኞችን ጨምሮ ሌሎች የጥምረቱ ድርጅቶች ከአንድ ሺህ የሚበልጥ ሰራዊት እንደሌላቸው ይነገራል። የኃይል ሚዛኑ ደሚት ጋር እንደመሆኑ፣ አቶ ሞላ አስግዶም ቅንጁትን መምራት ያለበት በደሚት አመራር መሆን አለበትየሚል አቋም እንደያዙ የገለጹት ምንጮቻችን ፣ ዶር ብርሃኑ ሊቀመንበር እንዲሆኑ የተደረገው በደሚቶች ስምምነት ሳይሆን በሻእቢያ ትእዛዝ እንደሆነ ይናገራሉ።
ወደዚህ የመጣነው ሕወሃትን ለመወጋት ነው። ለምንድን ነው ኤርትራ ዉስጥ ፣ ታስረን፣ እንድንቀመጥ የምታደረጉን ? ለምንድን ነው መረብንና ተከዜን ተሻግረን እንድንዋጋ የምታከላክሉን ? “ በሚል ከሻእቢያ ጋር ቀደም ሲል፣ የደሚት አመራሮች ቅሬታ እንደነበራቸው የገለጹት ምንጮቻችን፣ የአገር አድን ንቅናቄ በሚመሰረትበት ወቅት ቀጥተኛ ተጽኖ በደሚት ላይ ሻእቢያ ማድረጉ እንዳስከፋቸው ከምንጮቻችን የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።
ሰላሳ ከሚሆኑ አመራር አባላት፣ ከሃያ በላይ የሚሆኑት ከሊቀመንበራቸው አቶ ሞላ አስግዶም ጋር ወደ ሱዳን እንደገቡ የገለጹት ምንጮቻችን አብዛኛው የደሚት ሰራዊት ግን አሁንም በኤርትራ እንደሆኑ ይናገራሉ።
አቶ ሞላ አስገዶም፣ ኢትዮጵያ ገቡ፣ ወያኔ ነበሩ ..” የሚለዉን ወሬ ሆን ብሎ ሻእቢያ እያስወራ እንደሆነ የገለጹት ምንጮቻችን ፣ እነ ሞላ አስግዶም ወያኔ ቢሆኑ ኖሮ እዚያው ሆነው ለወያኔ ይሰልሉ ነበር እንጂ ጥለው አይሄዱም ነበር ይላሉ።
በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት የሰጡን የመለስ ትሩፋት መጽሀፍ ደራሲ አቶ ኤርሚያ ለገሰም፣ አቶ ሞላ አስገዶም፣ ከወያኔ ጋር የሚሰራ ነው የሚለውን አባባል እንደማይጋሩት ይገልጻሉ። በትግራይ ከፍተኛ በደልና ግፍ እየተፈጸመ እንደሆነ ያስረዱት አቶ ኤርሚያስ፣ አቶ ሞላ አስገዶምም ሆነ በሺሆች የሚቆጠሩ የደሚት ሰራዊት አባላት፣ በረሃ የወረዱት ክፉኛ የሕወሃት ተቃዋሚ ስለሆኑ እንደሆነ ይናገራሉ። አቶ ሞላ ወደ ኢትዮጵያ ሳይሆን ወደ ሱዳን እንደሄዱም የገለጹት አቶ ኤርሚያስ፣ ሱዳን እና ወያኔዎች ስምምነት ስላላቸው ፣ የመን አቶ አንዳርጋቸውን አሳልፋ እንደሰጠች፣ ሱዳኖች የሕወሃት ደመኛ ተቃዋሚ የሆነውን አቶ ሞላ አስግዶምን አሳልፈው ሊሰጡ የሚችሉበት ሁኔታ እንዳለ ያስረዳሉ።
አቶ ሞላ የተንቤን ሰው ሲሆኑ በባድመ ጦርነት ወቅት የኢትዮጵያን ወታደር እየመሩ ባሬንቱ የገቡ ወታደር ነበሩ። የራስ አሉላ አባ ነጋ አገር ፣ ተንቤን ፣ ሕወሃትን ከሚቃወሙ የትግራይ ቦታዎች በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው። ጥቂት የአድዋ ሰዎች የሚቆጣጠሩት ሕወሃት፣ በተለይም ከባድመ ጦርነት በኋላ በተንቤኖች ላይ ከፍተኛ በደልና ግፍ እየፈጸመ እንደሆነም ለአካባቢው ቅርብ የሆኑ ይናገራሉ።

በተያያዘ ዜና እውቁ ብሎገር ሚኒሊክ ሳልሳዊ አስመራ ያሉ ምንጮቹን በመግለጽ ፣ አቶ ሞላ አስግዶም ወደ ኢትዮጵያ ሳይሆን ወደ ሱዳን መሄዳቸውን ዘግቧል። አቶ ሞላ አስገዶም ላለፉት ረዥም አመታት ምንም ሳይሰራ ውጤት ስላላመጣን አሁን የመሰረትነው የአገር አድን ንቅናቄ በተግባራዊ ስራ ላይ በመሰማራት በቂ የሆነ ዝግጅት እና የሰው ሃይል ስላለን ወያኔን በአፋጣኝ መውረር አለብን የሚል አቋም በመያዝ በንቅናቄው መስራች ስብሰባ ላይ መናገራቸው የሻእቢያን ሰዎች እንዳላስደሰተ የአስመራ ምንጮች ገልጸዋልሲል የጦመረው ሚሊኪክ ሳልሳዊ፣ አቶ ሞላ በቂ ዝግጅት ስላለን ጦርነት እንክፈት የሚል አቋም መያዛቸው ሻእቢያን ስላላስደሰተው እንጂ ፣ አቶ ሞላ ከወያኔ ጋር ስለሚሰሩ እንዳለሆነ ይገልጻል።

በዚህ ጉዳይ ከአርበኞች ግንቦት ሰባት የዉጭ አመራር ሆነ ከአዲሱ የአገር አድን ንቅናቄ አመራር አባላት የተሰጠ ምንም አይነት መግለጫና ማብራሪያ እስከአሁን የለም።
አዲስ የተቋቋመው የአገር አድን ንቅናቄው እድል ፈንታ ምል ሊሆን እንደሚችል የጠየቅናቸው አንድ የፖለቲካ ተንታኝ፣ ተመርጠው ይሁን ሻእቢያ ሾሟቸው፣ ዶር ብርሃኑ ነጋ ፣ እነ አቶ ሞላ አስግዶም ወደ ሱዳን ቢገቡም፣ አብዛኛው የደሚት ጦር አሁን በርሳቸው ስር እንደመሆኑ፣ ደሚቶችን ከሌሎች ጋር ሰራዊቱን አስተባብረው የመቀጠል አቅምና ብቃት እንዳላቸው ያስረዳሉ።
ሰራዊቱ ወደ ኢትዪጵያ ምድር ሄዶ መዋጋት ይፈልጋልያሉት እኝሁ ተንታኝ፣ በዶር ብርሃኑ የሚመራው የአገር አድን ንቅናቄ፣ በቃል አቀባዩ በኩል፣ ወልቃይት ጠገዴ ፣ አርማጭሆ ..ዉጊያ አድርገን ይሄን ያህል ወያኔን ደመሰስን ..” የሚል ሊረጋገጥ የማይችል ዜና ማሰማት ሳይሆን፣ በተጨባጭ የትጥቅ ትግል መክፈት እንዳለባቸው ይናገራሉ። ወያኔዎች ጥቂት ሽፍታ ሆነው ነው ከአስመራ አዲስ አበባ ያለውን መንገድ ዘግተው የነበረው። የአገር አድን ንቅናቄ በሺሆች የሚቁጠሩ ሰራዊት ያለው እንደመሆኑ፣ ቢያንስ ድንበር ላይ ያሉትን የሁመራና የመተማ ከተሞችን በመዝጋት ትልቅ መልእክት ለአገዛዙ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብና ከአለም አቀፍ ማህበረሰቡ ማሰማት ይችላሉያሉት እኝሁ ተንታኝ፣ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ያንን ማድረግ ካልተቻለ ግን፣ የአገር አድን ንቅናቄ የወደፊት አቅጣጫ ምን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት በጣም የሚያስቸግር እንደሚሆን ያስረዳሉ።

የለውጥ ሃይሎች ካለፉት የትግል ተሞክሮዎች መማር ያስፈልገናል::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - 2007 ለለውጥ ብሎ የተነሳው የለውጥ ሃይል ከትግሉ ተሞክሮዎችን እንደቀሰመ ይታወቃል::ባለፈው አመት ወያኔ ሃይል ተጠቅሞ ከፍተኛ የሆነ ችግር በለውጥ ሃይሉ ላይ ከመፍጠሩም በላይ የጠበበውን የፖለቲካ ምሕዳር ጭራሽ ደፍኖታል::ለውጥ ፈላጊ ሃይሉ ከግድያ ጀምሮ እስር እና ስደትን በሰፊው አስተናግዷል::ወያኔ በስልጣን ላይ ለመቆየት ያል የሌለ ሃይሉን ተጠሟል:: በፖለቲካ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚ ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ የሚገኘው ወያኔ ትንፋሹን መሰብሰብ እስኪያቅተው ድረስ ተወራጭቷል::ምርጫውን በ100% የፓርላማ ወንበር በሃሰት እና በጉልበት አሸነፍኩ ቢልም 100% የሕዝብን ድጋፍ እንዳሌለው አረጋግጧል::ሕዝብን በጅምላ የመጨቆን አባዜውን ቀጥሎበታል::

በቂም በቀል የተሞላው ወያኔ የሕዝብ ድጋፍ እንዳሌለው ስላወቀ ብቻ ሕዝብን እየተበቀለ መኖርን መርጧል::ይህን ግፍና በለደል ለማስቆም ይሚታገሉ የለውጥ ሃይሎችን በማፈን በማሰር በመግደል በማሳደድ እርስ በእርስ በማባላት ስራውን አጧጡፎታል::ፓርቲዎችን እስከማፍረስ ጠንካራ አመራሮችን እስከማሰቃየት ዘልቆበታል::በሃገሪቱ ለውጥ እንዲመጣ የሚታገሉ ጠንካራ ታጋዮች እስር ቤት ሲታጎሮ በርካቶች ተሰደዋል::የነጻው ፕሬስ ለለውጥ ባደረገው አስታውጾ ጋዜጠኞች ተሰደዋል ታስረዋል::የሃይማኖት ነጻነት የጠየቁ ኢትዮጵያውያን መፍትሄ ከማግኘት ይልቅ ለከፍትኛ ሰቆቃ ተዳርገዋል::የተቃዋሚ ፓርቲዎች በድህረ ምርጫ እና ከምርጫ በኋላ በተደረገባቸው ጫና ከፍተኛ መስዋትነት ከፍለዋል::በተቃዋሚ ሽፋን ተመሳስለው የገቡ ሰርጎ ገቦች ከፍተኛ ጉዳት በለውጥ ሂደቱ ላይ ፈጥረዋል::ሕዝቦች በፖለቲካ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊው መስክ የበደል በደል እየተፈጸመባቸው ይጌኛል::ይህን ሁሉ ለማስቆም የለውጥ ሃይሉ በሃገር ውስጥ እና ከሃገር ውጪ ትግሉን አስፍቶ ቀጥሏል::ካጋጠሙን ችግሮች እና በውስጣችን ካሉ ቅራኔዎች እና ጥንካሬዎች በተሻለ መንገድ ለመታገል እና ያለምነውን ለውጥ ለማምጣት ካለፉት ሂደቶች ተሞክሮዎችን በመውሰድ ትግሉን በአዲስ መስመር እና በነቃ ሕሊና በመቀጠል አዲስ የትግል ድሎችን ለማስመዝገም በጋራ የምንቆምበት ጊዜ ላይ መሆናችንን እና ከተናጠል ጉዞ ሁሉን ያሳተፈ አዲስ የለውጥ ሂደት ለመቀየስ ካለፈው መማር ግድ ይለናል::

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለጥ ይፈልጋል ይህ በተደጋጋሚ የምናውቀው ጉዳይ ነው::ካለፈው መማር ብቻ ሳይሆን ልዩነትን አቻችሎ በጋራ ጎን ለጎን መጓዝ በጋራ መቆም ያስገድደናል::እንደ ባለፍት አመታቶች ከመጎሻሸም እና ከፖለቲካ ግልምጫ ራሳችንን ማውጣት አለብን ::እንደኔ አስብ ከማለት በዳበረ ሃሳብ በጋር ልንጓዝ ይገባል::በባዶ እና በፈጠራ ፕሮፓጋንዳ መሞላት አሊያም በውጪ ሃይሎች በኢትዮጵያ ጠላቶች በቀደዱልን መንገድ መትመም ልናቆም ይገባል::እውነተኛ መረጃ የትግል ሃይል እና መማማሪያ መሆኑን ልንዘነጋ አይገባም::ካለፈው መማር ካልቻልን የራሳችን ጠላቶች እንደሆንን መቀጠላችን ሲሆን ይህም ለጋራ ጠላታችን ለወያኔ ክፍተት ይሰጣል::የኔ ብቻ ትክክል ነው ብለን የምንጓዝ ከሆነ ለጊዜው ይመስለናል እንጂ እንደቀድሞው ሌላውን ማሸሽ እንደሚሆን ካለፈው ልምዳችን ተምረን ለመጪው ስኬትን መላበስ ያስፈልገናል::ለዚህም ነው የለውጥ ሃይሎች ካለፈው ተሞክሮዎች ተምረን በጋራ እና በአንድነት በመቆም የጋራ ጠላታችንን ወያኔን ወደ ከርሰ መቃብሩ ማውረድ ግዴታችን ነው::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ ሊቀመንበር መክዳት በትጥቅ ትግሉ ላይ ጥርጣሬዎች በድርጅቱ ውስጥ ድንጋጤን ፈጥሯል:‪

Minilik Salsawi's photo.Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - የትጥቅ ትግሉን ሂደት ከፍተኛ የሰነድ ምስጢሮችን በመያዝ እና አስቸኳይ ወረራ በወያኔ ላይ መጀመር አለበት የሚለው አቋማቸው ሻእቢያ ጥርስ ወስጥ እንደከተታቸው በደረሳቸው መረጃ መሰረት የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ (ደምሕት)ሊቀመንበር አቶ(ታጋይ) ሞላ አስገዶም 600 ወታደሮቻቸውን ይዘው የሻእቢያን የድንበር ጠባቂዎች በመግደል ድንበር በሱዳን በኩል አድርገው ማምለጣቸው በድርጅቱ አባላት ዘንድ ከባድ ድንጋጤን ከመፍጠሩም በላይ በትጥቅ ትግሉ ላይ ያሉ ጥርጣሬዎች እንዲሰፉ እንዲሁም ጥያቄዎች እንዲያስከትሉ ማድረጉ ታውቋል::በቅርቡ ተመሰረተ የተባለውን እና በአስመራ ለ9 ጊዜ የተቋቋመው የተቃዋሚ አንጃዎች ሕብረት የሆነው የአገር አድን ንቅናቄ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ሞላ አስገዶም ወታደሮቻቸውን ይዘው ከኤርትራ ወደ ሱዳን ሲወጡ እጅግ በርካታ የሆኑ የሻእቢያ ወታደሮችን በመግደል በከባድ ፈተና እንደነበር ታውቋል::
Minilik Salsawi's photo.
የቀድሞ የሕወሓት አባል እና በሻእቢያ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን እንዲፈቱ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርጉ ነበር ተብሎ የሚነገርላቸው አቶ ሞላ አስገዶም በተለያየ ጊዜ ሻእቢያ የስም ማጥፋት ቢያደርግባቸውም ተቋቁመው በአስመራ መቆየታቸው የድርጅቱ ታማኝ ምንጮች ይናገራሉ::አቶ ሞላ አስገዶም የአገር አደን ንቅናቄ ተብሎ ለዘጠኛ ጊዜ በሕብረት የተመሰረተ ድርጅት ምክትል ሊቀመንበር እና መስራች መሆናቸውን ተከትሎ የፈረሙት ፊርማ ሳይደርቅ ኤርትራን ጥለው ወታደሮቻቸውን አስከትለው መውጣታቸው ጥያቄ ቢያስነሳም የአስመራ ምንጮች እንደሚሉት የንቅናቄው ስራ በተግባር እንዲተረጎም ሃሳብ ማቅረባቸው በሻእቢያ በኩል ጥርስ እንደተነከሰባቸው እና የሻእቢያ የደህንነት ሰዎች ያደረሷቸውን መረጃ ተከትለው መውጣታቸው ተገልጿል::
Minilik Salsawi's photo. አቶ ሞላ አስገዶም ላለፉት ረዥም አመታት ምንም ሳይሰራ ውጧት ስላላመጣን አሁን የመሰረትነው የአገር አድን ንቅናቄ በተግባራዊ ስራ ላይ በመሰማራት በቂ የሆነ ዝግጅት እና የሰው ሃይል ስላለን ወያኔን በአፋጣኝ መውረር አለብን የሚል አቋም በመያዝ በንቅናቄው መስራች ስብሰባ ላይ መናገራቸው የቻእቢያን ሰዎች እንዳላስደሰተ የአስመራ ምንጮች ገልጸዋል::እውነት እና ንጋት እያደር ይጠራል ብለው ድንገት ሳይታሰብ የሻእቢያን ድንበር ጠባቂዎች በመግደል ከነወታደሮቻቸው ፀረ ኢትዮጵያ አቋም ያራምዳል ያሉትን ሻእቢያን ጥለው ወጥተዋል::በከፍተኛ አመራር ደረጃ አስመራን ጥለው ከወጡ ከአማራ ሃይል ሊቀመንበር ኮሎኔል አለበል ቀጥሎ አቶ ሞላ አስገዶም ሁለተኛው ናቸው:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬ሕወሓት እና አለቅላቂዎቹ ስለኢትዮጵያዊነት ሲነሳ ያቅለሸልሻቸዋል:ኢትዮጵያዊነት በህዝብ ልብ ውስጥ ላይወርድ የነገሰ ነው::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - ባለፉት 20 አመታት ሁላችን አንድ የታዘብነው ጉዳይ አለ::ስለኢትዮጵያዊነት ጠንካራ አቋም ያላቸው ስለሃገር የፖለቲካ ይሁን የኢኮኖሚ አንድነት የማህበረሰብ ትሥሥር ታላቅ አመኔታ ያላቸው ሰዎች ሲሰደዱ ሲወገዱ ሲሸበቡ አይተናል በአጠቃላይ አይፈለጉም:: የመንግስታዊ ፖለቲካ ጡዘት ውስጥ ሳይገቡ ስልጣን ሳይፈልጉ አሊያም የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሳይደግፉ በነጻ አእምሮ ኢትዮጵያዊነትን ብቻ ስላቀነቀኑ ስለዘመሩ ካለምንም ድርድር ለካልቾ አሊያም ለእስር ሲልም ለስደት ከፍ ሲልም ለጥይት ተዳርገዋል:: ሕወሓት እንደዚህ አይነት ሰዎችን ሲያይ ያቅለሸልሸዋል:: ከብአዴን እና ኦሕዴዽ ውስጥ ደግሞ የሕወሓት አለቅላቂ ቅጥረኞች በፍጹም ድድብና ውስጥ ሆነው የታዘዙበትን ብቻ ሲያኩ አስተውለናል ይብልጡኑ ግን ከአንድ ፓርቲ ሕወሓት ብቻ የሆኑ ሰዎች በጸረ ኢትዮጵያዊነት ሲንጫጩ በስፋት እያስተዋልን ነው::

በኢሕአዴግ ድርጅቶች ውስጥ ዘለቅ ብሎ ተገብቶ ሲታይ ሙሉ በሙሉ ሕወሓት እና በከፊል የግንባሩ አባል ድርጅት ቅጥረኞች የሚያራምዱት የዘረኝነት (ጸረ-ኢትይኦጵያዊነት)አላማ ዝም ብሎ የመጣ አይደለም አንድም በባንዳዎች መጠመቅ ከቤተሰብ የተወረሰ ሌላም በፖለቲካ ጥላቻ እና ቅናት ላይ የተመረኮዘ ሲከተልም የበታችነት ስሜትና የግል ጥቅም(ሆዳምነት) ነው::በብዛት ይህ ነገር የሚታይባቸው በበታችነት ስሜት ተጠፍንገው በራስ መተማመን ስለሚያጡ ነገን የሚፈሩ ሰዎች የወለዱት የዘረኝነት አባዜ ነው:: የሕወሓት አባላት ቤተሰቦች አብዛኛዎቹ በባንዳነት ለቅኝ ገዢዎች አድረው የነበረ በበታችነት ሕይወት ተጠፍንገው ያደጉ በቅናት እና መርዘኛ ጥላቻ የተመረዙ መሆናቸው እሙን ነው::በኢትዮጵያዊነት አሊያም በሃይማኖታዊ ትውፊት ትኮትኩቶ ያደገ ሰው ሕወሓት ውስጥ የለም ::ቢኖርም ተበልቷል አሊያም ተባሯል ሲልም ስለሰብኣዊነት እና ማንነት በመናገሩ የተለየ ሃሳብ በማምጣቱ ተወግዷል::ምንጫቸውን የረሱ የጥቅም ተገዢ የሆኑ ጥቂቶች ደግሞ ለጊዜው ስለሚጠቀሙ ብቻ ትፋታቸው እየላሱ ጸረ ኢትዮጵያዊ አቋም ይዘው ተደባልቀዋል::

ሕወሓት ከተለያዩ ሕዳጣን ሰብስቦ ያሰለጠናቸው እና በአውሮፓ እና አሜሪካ ተቀምጥው ጸረ ኢትዮጵያ አቋም የሚያራምዱ ጥቂቶች የትም ላይደርሱ ቢፈራገጡ ምንም እንደማያመጡ ላረጋግጥላቸው እወዳለሁ::የኢትዮጵያን መበጣጠስ የሚያልሙ ጥቂቶች የድህረገጽ ሹምባሾች ዲስኩራሞች ኢትዮጵያዊነትን በወሬ ሊንዱት አይችሉም::ኢትዮጵያዊነት እንኳን በየድህረገጹ ከሕወሓት እየተከፈላቸው ቡራ ከረዩ የሚሉ አይደለም ምእራባውያን እንኳን መናድ እንደማይችሉ የታወቀ ሲሆን ሞክረምው አልተሳካላቸውም:: ሕወሓት እንደአመጣጡ ቢሆን እስካሁን ያለማትን አገር ለመመስረት ቢያልምም እንደማይሳካ ስላወቀው ነው ስልጣኑን የሙጥኝ ብሎ የሚውተረተረው::አሁንም ኢትዮጵያዊነት ያሸንፋል::ስለ ኢትዮጵያ የሚያዜሙ ስለኢትዮጵያ የሚናገሩ ሁሉ ታላቅ ናቸው:: በሕዝብ ልብ ውስጥ ይነግሳሉ::ሕወሓት እና አለቅላቂዎቹ ስለኢትዮጵያዊነት ሲነሳ ያቅለሸልሻቸዋል::... እንዳቅለሸለሻቸው ወደ መቃብር ይወርዳሉ:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

የፖለቲካ አስተዳደሩ ካልተወገደ ድህነትን እና የኑሮ ውድነትን መቅረፍ አይቻልም::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - የኑሮ ውድነትና የፖለቲካ አስተዳደር እጦት ተወራራሽ ናቸው:: በሃገሪቱ የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ ከ2008 መግቢያ ጀምሮ በተለያዩ ምግብ ነክ በሆኑ እና ምንብ ነክ ባልሆኑ ሸቀጦች ላይ በነሃሴ ወር ከጀመረው ጭማሪ በላይ የሆነ ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ ከ7 በመቶ በላይ እንደሚከሰት ጥናቶች ጠቁመዋል:: እንደኔ እንደኔ አዲስ አመት ከመናፈቅ አዲስ ስርአት መናፈቅ ከአዲስ ማእረጋችን የደሃ ደሃ ክሚለው ወደ ላይ አንድ እርከን ከፍ ብለን የተሻልን እንሆናለን ለምን ከተባለ አዲስ ስርአት አዲስ ነገር ይዞ መምጣቱ ስለማይቀር ቢያንስ ስለ ነጻነታችን እና መብታችን ለየት ያለ ግንዛቤ ስለሚኖረን አዲስ ሕይወት ለመፍጠር ብዙም አያስቸግርም::እርግጥ ሕዝቡ ታማኝነቱን የሚጥልበት የፖለቲካ አመራር ባለመኖሩ ዝምታን መምረጡ እሙን ነው::ያለው አምባገነን የወያኔ ጉጅሌ ቢያንገፈግፈውም የሕዝቡ ትእግስት ግን እየተሟጠጠ የባለስልጣናቱም መፍረክረክ እየሰፋ እየተስፋፋ መጥቷል::በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ የተገነባው የወያኔ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ሕዝቡን ለድህነት አቀባብሎ በመስጠት የድሃ ደሃ የተባሉ በርካታ ባዶ እጅ ዜጎች እንዲፈጠሩ ጥቂት ቱጃሮች በሃገሪቱ እንዲሰራፉ አድርጓል::
Minilik Salsawi's photo.
በሃገራችን የተከሰተው ድርቅ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ የሆነ የምግብ ዋጋ መናር ከመከሰቱም በላይ አውዳመቱን አስታኮ ከጀርባቸው የወያኔ ባለስልጣናትን ያዘሉ ነጋዴዎች በምግብ ዋጋዎች ላይ ከነሃሴ መግቢያ ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ በማድረግ ሕዝቡን ለስቃይ ዳርገውታል::ብነሃሴ ወር ምጀመሪያ ጀምሮ በአፋር እና አማራ በኦሮሚያ እና አዲስ አበባ እንዲሁም ብደቡብ አንዳንድ አከባቢዎች ከፍተኛ የሆነ የምግብ ዋጋ ጭማሪዎች ታይተዋል::11.6 በመቶ ጭማሪ ያሳየው የምግብ ዋጋ እና በ8.9 በመቶ ጭማሪ ያሳየዩት ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎች ሕዝቡን በኑሮ ውድነት መሃል አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው የወያኔው አስተዳደር አሁንም ስህተቱን ለመቀበል ፈቃደኛ አይደለም::አውዳመቱን አስታከው የሚሸጡ ሸቀጦች ከፍተኛ ጭማሪ ሲያሳዩ ለአውደአመቱ የማይፈለጉ እቃዎች ደግሞ ወርደው ታይተዋል::

የኑሮ ውድነት የአንድ ሃገር የፖለቲካ አስተዳደር መበላሸት አካል መሆኑ ይታወቃል፡፡ የወያኔው ስርአት የሚያራምደው ቅጥ ያጣ የንግድ አተገባበር ባለስልጣኖች እና ወገኖቻቸው ከፈጠሯቸው ጥገኞች ጋር በማበር ከፍተኛውን የዘረፋ እና የንግድ ሂደቱን የመቆጣተር ስራዎችን እየሰሩ ነው:: አምባገነኖች ቡድን ፈጥረው የገነቡት የቡድን ዝርፊያዎች እና ጐጠኝነት ሙስና/ጉቦ እና የፍትህ እጦት በኢትዮጵያ እየተንሰራፋ ለመጣው የኑሮ ውድነት በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ የኑሮ ውድነትና የፖለቲካ አስተዳደር እጦት ተወራራሽ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡የፖለቲካ አስተዳደሩ ካልተወገደ ድረስ የኑሮ ውድነትንም መቅረፍ የማይቻለው ከዚህ ተወራራሽነት መነሾ መሆኑ አይካድም::የፖለቲካ አስተዳደሩ መወገዱ በሂደት ስራዎች የኑሮ ውድነትን ሊቀርፍ ይችላል::የወያኔው አገዛዝ የሚያራግበው የ11 በመቶ አመታዊ የኢኮኖሚ እድገት በገሃዱ እውነታ በሚታየው ድህነትና ጉስቁልና እርቃኑን የወጣ ስለሆነ የአገሪቱ ፈታኝ እና ዋነኛው ችግር የኑሮ ውድነት መሆኑን ሁላችንንም ሊያሳስበን የሚገባ ጉዳይ ነው::የወያኔው ስርአት በሚፈጥረው ውዥንብር ነጋዴውን እና ሸማቹን ለማናከስ በሚፈጥረው ሃሰተኛ ፕሮፓጋንዳ በሌላ በኩል በአለም የምጣኔ ሃብት መዋዠቅ ነው ቢል የራሱን ስህተቶች በመደበቅ የተንኮል መርዞችን ቢረጭም የሚቀበለው እና የሚያምነው አይገኝም:: የኑሮ ውድነት ከመስፋፋቱም በላይ የምግብ ዋጋዎች ንረት እና የአላቂ እቃዎች ከአቅም በላይ ዋጋ መጨመር ዝቅተኛውን የህብረተሰብ ክፍል ከመጉዳቱም በላይ በመካከለኛ ኑሮ ላይ ያለውን ህብረተሰብ ወደ ዝቅተኛው በመቀላቀል ለድህነት ዳርጎታል::ስለዚህ የወያኔን የፖለቲካ አስተዳደር ማስወገድን ከቻልን የኑሮ ውድነቱ ለመቅረፍ ጊዜ የማይወስድብን መሆኑ እሙን ነው::ሁላችንም ወያኔን ለማስወገድ እንረባረብ::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬