ሕወሓት የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጪ ግንባር አመራሮችን በአልሸባብ ቅጥረኞች እያስገደለ ነው::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - የወያኔው ጁንታ በምስራቅ ኢትዮጵያ ባለበት ከፍተኛ ጦርነት ምክንያት ሊቋቋመው ያልቻለውን የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጪ ግንባርን አመራሮች በገንዘብ በመግዛት በሶማሊያ እና በምስራቅ ኢትዮጵያ አሉ የሚባሉ አመራሮችን እያስገደለ መሆኑ ከግንባሩ ተሰምቷል::ሕወሓት ከአልሸባብ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላት ተደጋግሞ የሚነገር ሲሆን አልሸባብን ብገንዘብ እንደምትገዛ እና በተለያዩ የሽብር ስራ ላይ እንደምታሰማራ መረጃዎች መለቅቅ ከጀመሩ ቆይተዋል::

ከግንባሩ ለምንሊክ ሳልሳዊ በኢሜይል የተላከው መግለጫ እንደሚያመለክተው ታፍነው የተወሰዱት የግንባሩ አመራሮች አቶ አብዱላዚዝ መሃመድ ዳሂር እና አቶ መኪ ኡመር አብዲ በአልሸባብ ታጣቂዎች ከተወሰዱ በኋላ ግንባሩ ጉዳዩን ሲከታተለው ቆይቶ አልሸባብ አመራሮቹን ከባይደዋ ሶማሊያ አፍኖ ወስዶ የት እንዳደረሳቸው አይታወቅም::ኦብነግ የሶማሊያ ውስጥ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ አይደለም ያለው ግንባሩ በሶማሊያ ግጭት እጄ የለበትም ሲል ተናግሯል::አንዳን የሶማሊያ ባለስልጣናት እና የሶማሊያ ውስጥ ያሉ ታጣቂዎች የግንባሩን አባላት አፍነው በመውሰድ ለወያኔ መንግስት ያስረክባሉ ያሰቃያሉ ይገላሉ ሲል አምርሮ ገልጿል::

የግንባሩ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ አብዱላዚዝ መ.ዳሂር እና ቤተሰቦቻቸውን በጦርነት አጥተው ከኦጋዴን በመሰደድ በባይድዋ ያሉ ወላጅ አልባ ሕጻናትን የሚሰበስበው አቶ መኪ ኡመር አብዲ ሕጻናቱ በማጓጓዝ ላይ እንዳሉ ታፍነውበአልሸባብ ሚሊሻዎች ከባይደዋ ከተወሰዱ በኋላ የአልሸባብ ባለስልጣን ኢሳቅ ድሁሁሎ በሰጠው ትእዛዝ መሰረት አንገታቸውን ታርደው መገደላቸውን ግንባሩ አረጋግጧል::ይህ አልሸባብ የፈጸመው ግድያ የመጀመሪያ ባይሆንም ካሁን ቀደም የግንባሩን ወታደራዊ መሪ ኤሊያስ ሼ አሊ ን ጨምሮ ስምንት አመራሩን እንደገደለበት አትቷል::

የአልሸባብን ድርጊት ያወገዘው ግንባሩ የህ ሁሉ ግድያ እና ግፍ የሚፈጸመው አልሸባብ ከሕወሓት በሚቀበለው ትእዛዝ በገንዘብ ተገዝቶ መሆኑን እና የሕወሓት የጸጥታ እና ደህንነት ሃይሎች ከአልሸባብ ጋር በጋራ እደሚሰሩ አጋልጧል::ሕወሓት በፓርላማው ኦብነግን አሸባሪ ድርጅት ብሎ የፈረጀው ቢሆንም በተለያየ ጊዜ በእንደራደር ሲያጭበረብረው እንደነበር ሲታወቅ ከዚህ ቀደም ለድርድር ናይሮቢ ቀጠሮ ተይዞ ለድርድሩ የመጡትን አመራሮች ከናይሮቢ ያረፉበት ሆቴል አፍኖ ወደ አዲስ አበባ ማእከላዊ ወስዶ አስሮ እንደነበር ይታወሳል::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.

የተደበላለቀበትና የማይናበበው የወያኔው አገዛዝና የሞተ የኢኮኖሚ ፕሮፓጋንዳቸው (ምንሊክ ሳልሳዊ)

".... አስረአንድ በመቶ እድገት አስመስግበናል::"የወያኔ የማያረጀው ሪፖርት

- "በየአመቱ 9.7 ከመቶ እድገት ከምታስመዘግበው ቻይና ልምድ ልመቅሰም እንፈልጋለን"ጠ/ሚ.ሐ/ማ

---"በጣም በጣም አሳሳቢ ነው::...ምንም እድገት ሳይታይበት በነበረበት እየረገጠ ነው።" አርከበ እቁባይ

---"አገሪቱ በውጭ ምንዛሪ እጥረት፣ ጉድ ከመሆን የተረፈችው፣ በሁለት ምክንያቶች ነው ማለት ይቻላል ‘ዳያስፖራዎች’ ለቤተሰብ የሚልኩት ገንዘብ በመጨመሩና በአለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ በመቀነሱ። " አንድ ጸሓፊ/ በአዲስ አድማስ
 

- "ባለፉት 3 ዓመታት አቶ ኃ/ማርያም...ከአቶ መለስ የተሻሉ አፈጻጸሞችን በኢኮኖሚው ዘርፍ አስመዝግበዋል፡፡" ሪፖርተር ጋዜጣ
 

- "መንግስት የኤሌክትሪክ ሃይል ሸጦ በ9 ወር 35 ሚሊዮን ዶላር ሲያገኝ በሃገር ቤት መብራት አጥፍቶ ኢንዱስትሪውን በ6 ወር 40 ሚሊዮን ዶላር አክስሯል::" የኢኮኖሚ ባለሙያዎች
 

- "ኪራይ ሰብሳቢነት ለአደጋ አጋልጦናል::" የኢሕኣዴግ ሰዎችMinilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
ለበርካታ አመታት የምንሰማው ኢትዮጵያ ሃገራችን አስረአንድ በመቶ አደገን በኢኮኖሚ ተመነደገች የሚለውን የወያኔ ሪፖርት ሲሆን ምእራባውያን የብሄራዊ ጥቅም ጥያቄ ሲኖራቸው እንዲሁ ወያኔን ሲያቆለጻጽሱት በጎን ራሳቸው በሚደጉሟቸው አጥኚ ኢኮኖሚስቶች እና ድርጅቶች በኩል ደግሞ ኢትዮጵያ ሙልጭ ያለች ደሃ አገዛዙ በሙስና የተዘፈቀ በባዶ ካዝና የምትመራ አገር በማለት በቻርት በሰነድ እና በፎቶ አስደግፈው ሃቁን ይነግሩናል::ይህች አስረአንድ በመቶ የኢኮኖሚ እድገት የምትባል ፋሽን በሕዝብ አእምሮ ውስጥ ለመቅረጽ ከፍተኛ ፕሮፓጋንዳ ተሰርቶባታል::


የደሃ ደሃ የሚል ቃል የፈጠረው የአስረ አንድ በመቶ እድገት በኢኮኖሚ ዘረኝነት ላይ የተመሰረተው አገዛዝ ከነአሽከሮቹ በተደበላለቀ ፕሮፓጋንዳ እና በማይናበብ መሃይምነት ትላንት የተናገሩትን ዛሬ በማይደግሙት ባለስልጣናቱ ተከቦ ራሱን እያጋለጠ ይገኛል::ድህነትን እቀርፋለው እያለ የደሃ ደሃ መፍጠሩ በምግብ እሕል ራሳችንን ችለናል እያለ በረሃብ እና ድርቅ የሚጎዳው ሕዝብ መበራከቱ ሕዝቡ በኑሮ ውድነት መጦዙ ባለስልጣናት በሙስና ውስጥ መዘፈቃቸው ወዘተረፈ እንኳን የተማረው ሕዝብ ይቅርና ያልተማረው ህዝብ ያለውን አገዛዝ ላይ ትዝብቱን ብቻ ሳይሆን ጥላቻውን በማሳረፍ እንዲወገድለት እየጠየቀ ነው::

ትላንት አስረአንድ በመቶ አድገናል ያሉት ባለስልጣናት 9.7%ካደገችው ቻይና ልምድ መቅሰም እንፈልቃልን በማለት ቁልቁል ቤጂንግ ላይ ሂደው ሲለምኑ ተስተውለዋል::አሻንጉሊቱ ጠ/ሚ በቤጂንግ ጉብኝቱ የቻይናን ልምድ እና እርዳታ ሲለምን ሲማጽን ሰምተናል::እነዚሁ አደግን ተመነደግን የሚሉት የ11 ቁጥር አፍቃሪዎች ኢኮኖሚው ባለበት እየረገጠ ነውምንም እድገት የለም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው ሲሉ እነአርከበ በገዛ አንደበታቸው ነግረውናል::ስንቱን እንስተን ስንቱን እንደምንጥል አናውቅም::በሃገር ቤት ባሉት የግል ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ በላያቸው ላይ ነጋዴ ሆኖ የተነሳው አገዛዝ የኤሌክትሪክ ሃይል በማቋረጥ ብቻ 40 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ በ6 ወር ውስጥ አድርሶ በ9 ወር ከኤሌክትሪክ ኤክስፖርት የተገኘውን 35 ሚሊዮን ዶላር "ኪራይ ሰብሳቢነት ለአደጋ አጋልጦናል::" የሚለው ኢሕኣዴግ በሙስና ተቀራምቶታል::ይህ እድገት ብለው የሚያወሩት በሌላ መንገድ ደሞ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው ብለው ኢኮኖሚው ስጋት ላይ መሆኑን የሚነግሩን ችጋራም ባለስልጣኖች ሃገሪቷን እየገደሏት ነው::ብየት በኩል እንደመዘገመ በየት በኩል አፈጻጸሙ እንደተሳካ ባይታወቅም ባለስልጣናቱ አልተሳካልንም እያሉ ባሉበት ወቅት ሪፖርተር የተባለው የሕወሓት ልሳን ሃይለማርያም ሲክበው እያየን ነው ነገ አፍርጦ ካልጣለው::

አንድ ጸሃፊ በአገር ቤት ጋዜጣ ላይ በሰጡት አስተያየት ላጠናቅ:-የውጭ ምንዛሪ ምንጭ፣ የውጭ እርዳታና ብድር ነው። እርዳታው ባይቋረጥም፣ እንደታሰበው አልጨመረም። እርዳታ ሰጪዎቹ የአውሮፓና የአሜሪካ መንግስታት፣ ተጨማሪ እርዳታ የመስጠት አቅማቸው ተንጠፍጥፏል። እነሱ ራሳቸው፣ በኢኮኖሚ ድንዛዜና በበጀት እጥረት ተወጥረዋል። ብድርስ? ብድርስ አልጠፋም። ግን፣ ምን ዋጋ አለው? ብድር ሲደራረብ ያስፈራል። እንዴት ተደርጎ ከነወለዱ መመለስ እንደሚቻል እንጃ!ምንም፣ መልካም ወሬ የለም ማለት ግን አይደለም። “እድሜ ለዳያስፖራ” ብንል ይሻላል። ለቤተሰብ የሚልኩት ገንዘብ፣ ከአመት አመት እየጨመረ መጥቷል። በ2007 ዓ.ም የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ብቻ፣ ከዳያስፖራ የመጣው ገንዘብ፣ ከ1.7 ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው። በአመት፣ ወደ 3.5 ቢሊዮን ዶላር ይጠጋል። ከኤክፖርት ገቢ ይበልጣል ማለት ነው።በጥቅሉ ሲታይ፣ በ2007 ዓ.ም፣ አገሪቱ በውጭ ምንዛሪ እጥረት፣ ጉድ ከመሆን የተረፈችው፣ በሁለት ምክንያቶች ነው ማለት ይቻላል - ‘ዳያስፖራዎች’ ለቤተሰብ የሚልኩት ገንዘብ በመጨመሩና በአለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ በመቀነሱ። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

ባቡሩ ስራውን ጀመረ ከተባለ መስቀል አደባባይም ለተቃውሞ ሰልፍ ክፍት ነው ማለት ነው::

Minilik Salsawi - በእግረኞች እና በተሽከርካሪዎች ላይ አደጋ የጋረጠው በተደጋጋሚም የታየው ያልተጠናው የባቡር መንገድ ስራውን ጀመረ የሚል ኢሕኣዴጋዊ የልማት ጡዘት በሰንበት ተንሾኮሾከልን:: የመስቀል አደባባይ የባቡር መንገድ ልማትን አስመልክቶ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ልማቱን በቡዳ እንዳይበሉት ይመስል የተቃውሞ ሰልፍ እንዳያደርጉ የልማት አርበኞች ግን አይናቸው ልማቱን ስለሚያፋፋ ለድጋፍ ሰልፍ ሲፈቀድ ነበር::በልማት ሰበብ ወያኔ የሚሰራው የሰብኣዊ መብት ጥሰት እጅግ የተነነባት የመስቀል አደባባይ ተመልሳ አብዮት አደባባይ ትሆንብኛለች ብሎ ስጋት ስለወጠረው ተቃዋሚዎችን ለሰልፍ ሲወጡ ደንብሮ በቆምጥ ከማባረር ጀምሮ እስከ አይናቸው ተቃዋሚ መስሎ የሚታይ ሁሉ የገዢው ፓርቲ ኮተቶች ሳይቀሩ በመስቀል አደባባይ እንዳያልፉ የፌዴራል ፖሊስ ተራውጦ ሲያራውጥ አይተናል::

ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ ፍራቻ ያለው ወያኔ መስቀል አደባባይ ቋሚ የልማት ጣቢያ ሆንዋል ካላለ በስተቀር እስካሁን የሚያቀርበው ሰብብ የነበረው የባቡር መንገድ ስራ ስለተጠናቀቀ ተጠናቆ ስራም ስለጀመረ መስቀል አደባባይ ከማንኛውም የልማት ስራ ነጻ መሆኑ እየተሰማ ነው::አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ሃይል የሌለው ወያኔ ባቡሩን ስራ ጅሜረ ብሎ ሕዝቡን ችግር ውስጥ እንዳይከት::ከዚህ ቀደም ያየናቸው የወያኔ ስራዎች ሁሉ ፉርሽ ናቸው::ባቡሩ ስራውን ጀመረ ከተባለ መስቀል አደባባይም ለተቃውሞ ሰልፍ ክፍት ሆነ ማለት ነው::ልማቱ ተጠናቆ ባቡሩ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ለመድገም ያህል ከዚህ በኋላ መስቀል አደባባይ ለተቃውሞ ሰልፍ የሚከለከልበት ምክንያት አይኖርም፡፡

እርግጥ ወያኔ የአዲስ አበባን ሕዝብ ካለፈው 1997 የሚያዚያ 30 ሰልፍ በሄላ ይፈራል አያምነውም::የቡርቱካን አብዮት ያነሱብኛል ፈንቅለው ይወረውሩኛል ብሎ ስለሚፈራ ብቻ የተቃውሞ ሰልፍ ለመፍቀድ የዲሞክራሲ ቀሚስ ጠልፎ ጣለኝ ልማት አለብኝ በሚሉ ሰበቦች ይከበባል::ይህ ፍራቻ እና ስጋት ነው::ወያኔ ይፈራል ይሰጋል...ለራሱ መስቀል አደባባይን ሲጠቀም ከርሞ ለተቃዋሚዎች ልማት ላይ ነው ይላል በመስቀል አደባባይ ለመጠቀም የሚፈልግ ጸረ ልማት ብቻ ነው ይለናል::አሁን ደሞ ምን ምክንያት ሊያስታቅፈን ይሆን ? በእግረኞች እና በተሽከርካሪዎች ላይ አደጋ የጋረጠው በተደጋጋሚም የታየው ያልተጠናው ባቡሩ ስራ ጀመረ መስቀል አደባባይም ከልማት አረፈ::አሁን ስራውን መጀመር አለበት:መስቀል አደባባይ !!!!‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

በሶማሊያ ስለዘመተው ጦር ማብራሪያ እንዲሰጣቸው የሰራዊቱ አባላት ጠይቁ::በወያኔ ጁንታ እና በመከላከያ ሰራዊት መካከል አለመተማመን እና ጥርጣሬው መስፋቱ ተሰማ::

Minilik Salsawi- የሕዝብን መብት እና በልማት ስም በፕሮፓጋንዳ በመደለል በስልጣን ላይ ያለው በወያኔው ጁንታ እና በመከላከያ ሰራዊቱ መካከል አለመተማመን እና ጥርጣሬው እየሰፋ መምጣቱን ለምድር ጦር ክፍል ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል::ባለፉት አመታት በሰራዊት ውስጥ ወታደራዊ ደህነቶች መሰግሰጋቸውን ተከትሎ ከሰራዊቱ ጥያቄዎች ጋር ተደምሮ በተለይ በምስራቅ ደቡብ እዝ እና በሰሜን እዝ ከፍተኛ የሆነ የውስጥ ውጥረት እንዳለ ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::እንዲሁም በሰራዊቱ ውስጥ በየስብሰባው ሶማሊያ ስለዘመቱ ወታደሮች ማብራሪያ መጠየቁን ታውቋል::

በሰራዊት ውስጥ በወታደራዊ ደህንነት ቦታ የሚያገለግሉ ምንጮች እንዳሉት ሰራዊቱ ውስጥ የተከሰተው አለመተማመን እና ጥርጣሬ የፈነዳ ሰአት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ በሕወሓት እና በአሽከሮቿ ላይ እንደሚከሰት ገልጸው አሁንም በየእዙ የሚጠረጠሩ መኮንኖች እስር እንደቀጠለ ተናግረዋል::ለሆዳቸው ያደሩ የሰራዊት አባላት ቢኖሩም ይህን ያህል አይደሉም የሚሉት ምንጮቹ ሰራዊቱ ግን በመፈራራት እና እርስ በርስ ጥርጣሬ ውስጥ እየተጓዘ እንደሆነ ገልጸዋል::በተልያዩ ግምገማዎች ከ10 የሰራዊቱ አባላት ሰባቱ በማስጠንቀቂያ መታለፋቸው በራሱ በሰራዊት ውስጥ ያለው ችግር አንደኛው ገጽታ መሆኑ አውስተዋል::

የተቃዋሚው ሃይል የራሱን የትግል ስልት ነድፎ ሰራዊቱ ውስጥ ገብቶ ሊንቀሳቀስ ይገባዋል ያሉት ምንጮቹ ሰራዊቱ በሆነ ባልሆነው ከአለቆቹ ጋር የሚጋጭ ከተላከበት ሳይመለስ በዛው የሚጠፋ እንዲሁም በየጫካው ራሱን አጥፍቶ የሚገኝ መሆኑን አክለው የገለጹ ሲሆን በሱማሊያ የዘመቱ ወታደሮችን በተመለከተም በሰራዊቱ እስጥ ጥያቄዎች መነሳታቸውን ጠቁመዋል::በአዲስ አበባ እና ብደብረ ዘይት ባለፈው ሳምንት ብቻ በተጠሩ ስድስት የግምገማ ስብሰባዎች ላይ የሶማሊያ ዘማች ሰራዊት አባላትን በተመለከተ ጥያቄዎች መነሳታቸው እና ማብራሪያ መጠየቁም ታውቋል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

ወያኔ ፈሪ ነው:: ቦቁቧቃ .... ጀግኖችን ስለሚፈራ ያስራል .. ከሃዲዎችን ያከብራል::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - ወያኔ የሚያራግባት ፕሮፓጋንዳ አለች::ሻእቢያ ጸረ ልማት ጸረ ሰላም .. ምናምን ...ወዘተ..ታዲያ እንዲህ ከሆነ ወያኔ ምን እየጠበቀ ነው ወንድነቱ ጀግንነቱ ካለ ጦሩን ሰብቆ ለምን ጸረ ልማቶችን አይመታም::ቂቂቂ.....ወያኔ ፈሪ ቦቅቧቃ ነው:;ወያኔ የሚያስረው ምንም የሌላቸውን መብት እና ነጻነት የጠየቁ ያወጣውን ሕግ እንዲያከብር የጠየቁትን ጀግኖች እንጂ ለሌላውማ ልብ የለውም::እንደ ወያኔ ፈሪ ቦቅቧቃ ...ፕሮፓጋንዳ ብቻ...የወያኔ(የፈሪ)ጉልበት ባልታጠቀው ሕዝብ ላይ ነው:: አንዲት ጥይት ቢተኩስ ተመልሳ 1000 ጥይቶች ሆና ራሱን እንደምታጠፋው ስለሚያውቅ ወያኔ በፕሮፓጋንዳ ብቻ ይጀግንብናል::ድንቄም ጀግና !..አቤት ያ ቀን ...

የደምሕት መሪ የነበረው ሞላ አስገዶም በወር 25 ሺህ የኤርትራ ናቅፋ ኪራይ እየተከፈለለት በልዩ ቪላ ውስጥ አራት መኪናዎች ተመድቦለት ሲኖር፣ጀግናው አንዳርጋቸው ፅጌ በረሃ ላይ ሰሌን ዘርግቶ ያድር ነበር። ሞላ አስገዶም የ(ጀግና?) አቀባበል ተደርጎለት እንደ ፍንዳታ ጎረምሳ ጸጉሩን እየፈተለ እየተቁነጠነጠ ሲያገሳ፣ ጀግናው ቆራጡ ጽኑው አንዳርጋቸው ፅጌ ከሰው ተገልሎ በአንዲት ጠባብ ክፍል ጨለማ ውስጥ ተቆልፎበታል::የጀግንነት እና የባንዳነት ልዩነቱ ይህ ነው::የትግል ቁርጠኝነት/ጽናት እና ክህደት ልዩነቱ እንዲህ ነው::ወያኔ ፈሪ ነው:: ቦቁቧቃ .... ጀግኖችን ስለሚፈራ ያስራል .. ከሃዲዎችን ያከብራል::

ልዩነትን በማቻቻል እና በመከባበር በጋራ መታገል ችላ የማይባል ሃገራዊ አጀንዳ ነው።

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - በጋራ ላለመስራት ማንገራገር እና አለመፈለግ እና በስሜት መነዳት የፖለቲካ ውጤቱ እና ጠቀሜታው ለጋራ ጠላታችን ለወያኔ ነው::የተቃዋሚ ሃይሎች ጥንካሬ እንዲጎለብት በየድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እንከኖች በማጥራት በጋራ እና በተመቻቸ የሃሳብ መግባባት ተቻችሉ እና ተግባብቶ የትግል ስትራቴጂን ግብ ለማድረስ ለአንድ ወጥ ህዝባዊ እና ሃገራዊ አጀንዳ ተግቶ መስራት ይጠበቅብናል።ባሳለፍነው የትግል አመታት ውስጥ የተቃዋሚዎች እርስ በ እርስ መፈራረጅ መወነጃጀል መናናቅ ለስልጣን ጥመኝነት መሮጥ እንዲሁም ለስም እና ለዝና መትጋት ያለመደማመጥ እና ያለመከባበር ፖለቲካ ተቀራርቦ ያለመነጋገር እና ያለመመካከር ፖለቲካ ሃገራዊ ሆደሰፊነት እና መቻቻልን ያላዘለ ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተረፈው ነገር ቢኖር ከጭቆን ወደ ጭቆና ማቅ ውስጥ ከመዘፈቅ ውጪ ምንም የናፈቀውን የነጻነት አየር እንዲተነፍስ አላደረግነውም። 

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል። ይህ ሳይታለም የተፈታ እና የሁሉም የነጻነት ፈላጊ ሃይሎች ጥያቄ ነው። በሃገር ውስጥ ያሉትን ፓርቲዎች መዋቅሮቻቸውን በማጠናከር የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመቅረፍ እንዲጠነክሩ የማድረግ ግዴታ ከለውጥ ፈላጊ ሃይሎች ይጠበቃል። መመካከር መተራረም ግድ ይላል። በውጪው አለም የሚገኙ የነጻነት እና የለውጥ ሃይሎች እንዲጠናከሩ እና ከጥልፍልፎሽ ፖለቲካ ወተው ጠንካራ ሃይል እንዲሆኑ የዲያስፖራው ሃይል ከበፊቱ በበለጠ መልኩ ሊሰራ ግድ ይለዋል። የወያኔ የጎን ውጋት እና የራስ ምታት የሆነው ዲያስፖራው የጀመረውን የትግል ስልት እና ትጋት በማስፋት ሚዲያዎችን በማጠናከር እና የነጻ አውጪ ፓርቲዎችን በመርዳት በማግባባት ጠንካራ ሰንሰለት ከሃገር ቤት ጋር በመፍጠር ሕዝብን ከጨቋኞች ነጻ ማውጣት አለበት።ዲያስፖራው በየቀኑ ወያኔ የሚፈጥረውን ተራ የቤት ስራ እና የማደናገሪያ ማዘናጊያ አሉባልታ ፊት ሳይሰጠው በለውጡ ጉዳይ ላይ በማተኮር በሃገር ቤት ያለው ሃይል እንዲስማማ የፖለቲካ ጡዘቶች ክፍተት እንዳይኖር ተቀራርቦ እንዲሰራ ትልቁን ሚና መጫወት አለበት::

ወያኔ የተቃዋሚዎችን እና የለውጥ ሃይሎችን እርስ በእርስ መፈነካከት በማየት አርጩሜውን ተስፋ በሚጣልባቸው ግለሰቦች እና ፓርቲዎች ላይ እያወናጨፈ ባለበት እንዲሁም የውስጥ አሰራራቸውን በመሰለል በትግሉ ውስጥ ያላቸውን ሚና እንዲኮላሽ በመስራት የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመጠቀም እርስ በርስ እንዲፋጁ እና ተቃዋሚዎች እንዲከስሙ ጥንካሪያቸውን እንዳያገኙ ሲሰራ ይህንን እንዴት አድርገን በማሻሻል የወያኔን ሴራ ማክሸፍ አለብን የሚል አመኔታ የሚያስገኝ ሕዝባዊ ስራዎችን በመስራት ጥንካሬን ማግነት እንዲሁም ሕዝባዊ ድጋፎችን ማግኘት ግድ የሚልበት ጊዜ ላይ መሆናቸውን ተቃዋሚዎች ሊያውቁት ይገባል::ተቃዋሚዎች ካለፈው ድክመቶቻችን ተምረን ከዘለፋ እና ከስድብ እንዲሁም ከመፈራረጅ የሴራ ፖለቲካ በመውጣት ጥንካሬዎቻችንን የምናሳይበት ለውጥ የምናመጣበት አመት እንዲሆን በጋራ ጠንክረን መስራት አለብን።አንድነት ሃይል ነው የሚለው ብሂል ለሃገራዊ አጀንዳ መተግበር ትልቅ አስታውጾ አለው::ከኛ በላይ ላሳር ከኛ በላይ አዋቂ የለም የሚል አመለካከት ይዞ ከመክነፍ የህዝብን ጥያቄ መሰረት አድርጎ ተቀራርቦ በመነጋገር እና በመወያየት ሃገራዊ ማኒፌስቶ በማምጣት የጋራ ሃገራዊ አጀንዳ በመቅረጽ ለለውጥ መትጋት ግዴታ ነው::

የሚዲያ ተቋማት እና የድህረገጽ ውጤቶች ሕዝብን በማስተማር ሕዝብን መብቱን እና ነጻነቱን አውቆ ለሌላው እንዲያስተምር በማድረግ ረገድ አስፈላጊውን ወቅታዊ መረጃ እና መነሳሳትን በማስረጽ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል። ያለፉ እና የከሰሙ ወሬዎችን እና አሉባልታዎችን ከመርጨት የወያኔ የፈጠራ አደናባሪ እና አዘናጊ አጀንዳዎችን እኝኝ በማለት ከማውራት ብሄር ተኮር ክፋፋይ ሃሳቦችን ከማርከፍከፍ አዛኝ መሳይ መርዝ ሃሳቦችን ከመናገር ተቆጥበን ሕዝቡን ስለመብቱ እና ነጻነቱን በማስተማር ረገድ መትጋት ከተያዘ ለውጥ የማይመጣበት ምንም ምክንያት የለም። ትችትን እና ሂስን ላለመዋጥ እውነትን ላለመቀበል የሚደረጉ ሩጫዎች ታጥቦ ጭቃ እንጂ የትም እንደማያደርሱ እንዲሁም ፓርቲዎችን እና ሰዎችን መፈረጅ እና መወንጀል ሃሳቦችን ማጣጣል ምንም ለውጥ እንደማያመጣ ካለፈው ተምረናል ። ያሳልፍነው የትግል ሂደት ከጭብጨባ እና ስብሰባ ያለፈ ፋይዳ እንዳሌለው ተገንዝበን የወሬ እና ሆይሆይ ትግል ስለማያዋጣ ጥንካሬን እና ለውጥን የምናመጣበትን የትግል ስልት በመመካከር በመከባበር እና በመወያየት ሃሳብን በማቻቻል መረጃ በመለዋወጥ ሃገራዊ የጋራ አጀንዳ ሊኖረን ይገባል እላለሁ። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ

አደርባይ ታማኝ ተቃዋሚዎች ከሃዲዎችን ማንቆለጳጰሳቸው የተለመደ የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ነው::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - በሃገር ቤት የሚንቀሳቀስ ፓርቲዎች ናቸው የተባሉ አራቱ በሕዝብ ዘንድ የተጠሉ እና የተተፉ ታማኝ ተቃዋሚዎች የወያኔ የፕሮፓጋንዳ ማድነቂያ ሆነዋል::ይህ ሰሞ ከአዲስ አመት ይልቅ በአዲሱ የሞላ ፕሮፓጋንዳ እየጎዳደለ የሚገኘው ወያኔ ደልሎ ይሁን ገዝቶ አፍኖ ይሁን መንገድ አሳስቶ ያመጣውን ሞላን እንደ ትልቅ ድል ቆጥሮ አደርባይ ታማኝ ተቃዋሚዎች ለአላማ ጽናት የሌለውን ሞላን እና ተከታዮቹን እንዲያንቆለጳጵሱ በማድረግ እኩይ የፕሮፓጋንዳ ተግባሩን ተያይዞታል::ታማኝ ተቃዋሚዎች በዚህ በሰለጠነ ዘመን ለሆዳቸው ከመንከባለላቸው በተጨማሪ ለመረጃ እጅግ የራቁ መሆናቸውን ከወያኔ ጋር የሚጋፈፉት አንሶላ ፊትለፊት ታይቶባቸዋል::

አደርባይ ታማኝ ተቃዋሚዎች የትሕዴን ታጋዮች ወደ ሃገር ቤት በሞላ አስገዶም እየተመሩ ገብተዋል የሚለውን ጡዘት ወያኔ ጠቅልሎ ባጎረሳቸው ፕሮፓጋንዳ ተጨፍነው ሙሉ በሙሉ መቀበላቸው ምን ያህል የድፍን ፖለቲካ ባዶነት እንደሚታይባቸው ያሳብቅባቸዋል:: ከበፊት ጀምሮ እንደምናውቀው በፍላጎት እና በአፈና ጦሩን የሞላው ትሕዴን ወደ ሃያ ሺህ ጦር እንዳለው የምንሰማው የምናውቀው የተነገረ ነው ታዲያ ሞላ አስገዶም 600 ወታደሮቹን አስከትሎ መጣ ማለት ትሕዴን ካለው ሰራዊት ሶስት ፐርሰንት (3%) የሆነው ከዳ/ተሰናበተ/ተላልፎ ተሰጠ/መንገድ ተሳሳተ/ተደለለ ወዘተ.... ማለት ስለሆነ ይህ ደግሞ አደርባይ ታማኝ ተቃዋሚዎች እንዳሉት ትሕዴን ጠቅልሎ አልገባም::ታማኝ ተቃዋሚዎች ፖለቲካ ቢያውቁ ኖሮ ግን ጠንከር ያለ ንግግር ባስቀመጡ ነበር::

ለትጥቅ ትግል በረሃ ገብተናል ያሉ ሃይሎች የራሳቸውን አሳማኝ ነው የሚሉትን ምክንያት ማስቀመጣቸው ይታወቃል::የሚደግፋቸው ይደግፋል የማይደግፍ ደሞ የራሱን መስመር ይዞ ይሄዳል::ከሞላ አስገዶም ያልተለየ ስራ በአንድነት ፓርቲ ላይ የሰራው ከሃዲው ትእግስቱ አወሉ በየትኛው ሞራሉ ነው ከበረሃ ወደ ከተማ ስለሚገቡ ጭፍን ዘረኞች ሊመሰክር የሚችለው? በሕዝብ ልጆች አንድነት ተገንብቶ ከፍተኛ መስዋትነት ተከፍሎበት በሕዝብ ድምጽ የተመረጠውን ቅንጅት ለውድቀት የዳረገ የልደቱ አያሌው ኢዴፓ በየትኛው ሕዝባዊ አመኔታው ስለ ሞላ አስገዶም ይናገራል? በአንድ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሲሰጥ መረጃዎች ተመዝነው እንደሆነ እሙን ነው ፖለቲካ ጥንቃቄ ይፈልጋል በድመነብስ እና በእከክልኝ ልከክልህ በጉርሻ ድለላ ተናግረው የሚወጡት አይደለም ነገን ከተጠያቂነት አያስተርፍም::የመድረክ ፓርቲ አመራሮች ከጅምሩ ጀምሮ በፖለቲካው አለም ያሉ ቢሆንም ብስለታቸው በፍርሃት እና በጥቅም የተያዘ እስኪመስል አሊያም አረናን ላለማስቀየም ይመስል ለሞላ አስገዶም እና ለወያኔ ሲያሽካልሉ ይታያሉ::መድረክ የትጥቅ ትግል በረሃ የገቡ ኢትዮጵያውያን ለምን እንደገቡ የት እንደነበሩ ጠንቅቆ የሚያውቅ ፓርቲ ሆኖ ሳለ ጭልጥ ባለ አደርባይነት ውስጥ ተነክሮ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ውሏል::ሌላኛው ኢራፓ የምባል ነኝ ያለ ፓርቲም ከገዢው ፓርቲ አጋር ተለጣፊዎች አንዱ አብሮ ሲያንቆለጳጵስ ተስተውሏል:: ፓርቲዎቹ ምን ያህል ሞራላቸው እንደወረደ እና ለገዢያቸው ወያኔ ምን ያህል ታዛዥ እንደሆኑና ለሕዝብ ሳይሆን ለራሳቸው የኑሮ ለውጥ እንደሚታገሉ ይመሰክርባቸዋል::

ወያኔ ከራሱ እና ተለጣፊ ፓርቲዎቹ አልፎ በተፎካካሪ ፓርቲ ስም የሚደግፋቸው አጋር ታማኝ ተቃዋሚዎችንም ለሞላ አስገዶም የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ መጠቀሙ ስርኣቱ ውዥንብር ውስጥ መግባቱን ያሳያል::የወያኔ ካድሬዎች ራሳቸው ፕሮፓጋንዳውን እየተቹ ባሉበት በዚህ ወቅት ላይ በተፎካካሪ ስል አጋር ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሰጡ የተባለው መግለጫ ፖለቲካን ውስጥ ምን ያህል አደርባይ ሆዳም ሰዎች እያቦኩት እና ለለውጥ የሚደረገውን ትግል እየተጋፉት እንደሚገኙ ምስክር ነው::አስተዋይነት የጎደላቸው እንደ ትግስቱ አወል እና ኢዴፓ የመሳሰሉ ፓርቲዎች ለስላም እና ለዲሞክራሲ በሚደረጉ ትግሎች ውስጥ በሞት ያለፉ እና በእስር ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ላይ ዛሬም እየተዘባበቱ ነው::የለውጥ ሃይሎች ሕዝብን አስከትለው በሚያደርጉት ትግል በሚገኘው ድል ወያኔ ሲደመሰስ ከታሪ እና ከሕግ ተጠያቂነት እንደማያልፉ ላስገነዝባቸው እወዳለሁ::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

ኢሕአዴግ እየሰራ ያለው ፕሮፓጋንዳ ኪሳራ እንደሆነ ካድሬዎቹ እየተናገሩ ነው::

Minilik Salsawi - ከተለያዩ የኢሕአዴግ ካድሬዎች በተለያዩ የማህበራዊ ድህረገጽ የተሰበሰበ መረጃ እንደሚያመለክተው ኢሕአዴግ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እየሰራ ያለው ፕሮፓጋንዳ ኪሳራ እንደሆነ ካድሬዎቹ እየተናገሩ ነው::ካድሬዎቹ ድርጅታቸው የሚሰራው ዶክመንተሪ ፊልም አሊያም ቃለመጠይቅ እንዲሁም ሃተታና መግለጫ በሕዝቡ በተቃራኒው እንደሚተረጎም እና ተቀባይነት እንዳሌለው በደንብ እናውቃለን ሲሉ ድርጅቱ የሚሰራው ስራ ውስጥ ውስጡን እየገዘገዘው ነው ሲሉ ተናግረዋል::የድርጅታችን ፕሮፓጋንዳ ምንም ጠቀሜታ አለመኖሩን የሚያሳየን አብዛኛው ሕዝብ ሲያሾፍበት እና ቀልድ ሲፈጥርበት እንደሚውል የተናገሩት የወያኔ ካድሬዎች የውጪ ሃይሎችን በማሳመን ረገድ ግን ድርጅታችን የተሳካ የሎቢ ስራ ሰርቷል ሲሉ ፈርጠም ብለው ይናገራሉ:: ምእራባውያን ከተቃዋሚዎች ይልቅ በኢሕአዴግ ላይ አመኔታ ያላቸው መሆኑን በተለያየ መድረክ ገልጸዋል ያሉት የወያኔ ካድሬዎች ከዚህ ቀደም በአፍሪካ መሪዎች መውደቅ ላይ የምእራባውያንን ሚና በተመለከተ ለተጠየቁት ጥያቄ መልስ ሳይሰጡ አልፈዋል::
ባለፉት አስራሰባት ቀናት በተከታታይ ጥያቄዎች የቀረቡላቸው የገዢው ፓርቲ አባላት ከመለሱት መልስ የተጨመቀው መረጃ እንደሚያሳየው አሸባሪ ተሸባሪ የሚሏት ጉዳይ እንደ አደገኛ ቦዘኔ ለድርጅታቸው ሰበብ ይዛ ልትመጣ ትችላለች ሲሉ በ1997 የተደረገውን ምርጫ አጣቅሰው ይናገራሉ::የሕዝቡን ዝምታ በተመለከተ የተናገሩት ካድሬዎች ድንገት ከህዝቡ መሃል የሚፈነዳ ችግር እንዳይኖር በሚል በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ቡድኖች ተከፋፍለው መነጋገራቸውን ሲገልጹ ምርጫ 2007 በተመለክተ ድርጅታቸው 100% የፓርላማ ወንበር አሸነፈ እንጂ የሕዝቡን ድርሻ አላካተተም የሕዝቡን ልብ አላሸነፈም ሲሉ በተዘዋዋሪ ምርጫውን እንዳጭበረበሩ አመላክተዋል::
በቅርቡ የተከሰተው የሞላ ፕሮፓጋንዳ ኢሕአዴግን ጎዶሎ አድርጎታል::ያሉት አባላቱ ጉዳዩ እንዳልገባቸው እና በመንግስት ደረጃ የሚሰራው ስራ ቀፋፊ ነው ያሉ እንዳሉ ሁሉ የድርጅታቸውን የደህንነት እና የስለላ ተግባር ያዳነቁ በስፋት ተገኝተዋል::የሞላ ጉዳይ ፕሮፓጋንዳ እንደሚሰራለት ሳይሆን በድርጅቱ ውስጥ አነጋጋሪ ሆንዋል ያሉም አልጠፉም::የወያኔ ፕሮፓጋንዳ በሞላ ላይ እና በልማት ዙሪያ የፕሮፌሰር ብርሃኑን ስም ለማጥፋት መዋሉ በጎ ነው ወይ ብላቹ ታስባላቹ ወይ የተባሉት አባላቱ ከ126 ሰዎች 111 የሚሆኑት የፕሮፌሰር ብርሃኑን ስም የማጥፋቱ ዘመቻ ሃሰት እና የወረደ ፖለቲካ ሲሉ አጣጥለውታል::የማህበራዊ ድህረገጽ ተሳታፊ የሆኑ በ100/75% ከሕወሓት አባላት የሆኑ ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት መልስ እጅግ ብልግና የተሞላበት እና ያልበሰለ ከመሆኑም ውጪ ራሳቸውን እንደ ጀግና እና ሃገር ወዳ ሌላውን ከይሲ አድርገው በመልሳቸው አስቀምጠዋል::በአሁኑ ወቅት ያለው እንቅስቃሴ ሲለካ በማህበራዊ ድህረገጽ በተለያየ ስም የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ዘረኝነትን እና የከፋፋይነት ስራዎች ላይ እንዳተኮሩ ይታወቃል::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

ሊቆም የሚገባው ጥላቻ ምቀኝነት ቅናት ክፋት እና ግለኝነት የተጠናወተው ፖለቲካ

Minilik Salsawi መልካም እና ጽኑ ታጋዮች እንደተጠበቁ ሆነው በስለናል የትግል ልምድ አለን ከሚሉ ፖለቲከኞች ጀምሮ እዚህ ግቡ የማይባሉ ገደል ማሚቱዎች ድረስ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ቦርቅቀው ለማተራመስ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም::ከኛ በላይ ላሳር የሚሉ እንጭጭ ፖለቲከኛ ነን ባዮች ጥቂቶች ሰፊዉን ሜዳ በተግባር ኣልባ ፕሮፓጋንዳ ብቻ አጣበዉት ሌላው እጁን አጣጥፎ ሲያይ መመልከትም ግርምትን ይፈጥራል::የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሰከረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ይህን ያህል ተተራምሷል ለማለት ግን አያስደፍርም::የሕዝብ ማንዴት ያሌላቸው ፖለቲከኞች ራሳቸውን የሕዝብ ወኪል አሊያም በሕዝብ የተቀቡ አድርገው ሲያቀርቡም የፖለቲካ እብደቶች እየገነኑ ይመጣሉ::በሃገራችን ፖለቲካ ውስጥ የሚታዩ የፖለቲካ ጥላቻ ምቀኝነት ግለኝነት ቅናት የመሳሰሉት ለውጡ በእንብርክክ እያስኬዱ የሚገኙ ሲሆን ሂደቶን ሁሉ ባለህበት እርገጥ ሆነዋል:: እንደኔ እምነት ጥላቻ ምቀኝነት ቅናት ክፋት እና ግለኝነት የጎሳ እና ከፋፋይ ፖለቲካ የሚከተለ እንደ ሕወሓት ያሉ ድርጅቶች ያነገቡት አርማ ነው::
በየሄድንበት በጎራ ተከፍሎ ጥላቻ ሲሰበክ በያረፍንበት ለለውጥ ሰራን የሚሉ ሰዎች ግለሰቦችን አሊያም የፖለቲካ መሪዎችን በጥቅሉ የለውጥ ሃይሎችን ሲያብጠለጥሉ ማየት ያማል::ይህ በግለሰብ ደረጃ ተንከባሉ የፖለቲካ ሰዎችን አሊያም የለውጥ ሃይሎችን መዘርጠጥ ይሁን ማብጠልጠል የወረደ ፖለቲካ ነው::ያዉም ክፉ የፖለቲካ ሃሜት::ተሽሎ የተገኘ የዳበረ ሃሳብ ባልቤት የሆነ የፖለቲካ ሰው ከተገኘ የደጋፊዎቹን ያህል የፖለቲካ ምቀኞቹም ይበረክቱበታል::በፖለቲካው አለም ሃሳብን በሃሳብ ማሸነፍ እየተቻለ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ግን የፖለቲካ ሰዎችን ማብጠልጠል ከተቻለ ማስመታት ካልተቻለ በወረደ ቋንቋ ስማቸውን ማጠልሸት ስራ ሆኖ ተይዟል::አለም ከዘር ከሃይማኖት ከቀለም እና የተለያዩ ልዩነቶች ተገላግሎ በአንድነት ስር ለመጠለል በሚያደርገው የቴክኖሎጂ እድገት ሩጫ ውስጥ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ግን በጎሳ ታጥሮ በግፍ ተከቦ እርስ በእርሱ ሲጠባጠብ ይስተዋላል::

ከገዢው ፓርቲ ጀምሮ የለውጥ ሃይል ነን እስከሚሉ ድረስ ከፍተኛ የሆነ የክፋት የጥላቻ የምቀኝነት የቅናት እና ግለኝነት ፖለቲካ ሲያራምዱ በገሃድ እናያለን::ድርጅቶቻችንን ደግፈን ለሕዝብ እየሰራን ነን ከሚሉ እስከ ድርጅታቸው እስከከዱ ሰዎች ድረስ በምቀኝነት እና ቅናት ተሞልተው የፖለቲካ ሰዎችን ሲያብጠለጥሉ ሲሰድቡ የለውጥ ሃይሎችን ሲያንቋሽሹ ውለው ያድራሉ::ይህ ደግሞ አውቀናል ተምረናል ከሚሉ ጀምሮ እስከ ገደል ማሚቱዎቻቸው ድረስ እየታዘብናቸው ነው::ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ሂደት ምንም እውቀት ከሌለው የመኖሪያ ፍቃድ ለማግኘት ሲል ከድርጅቶች እንከሚታከከው ድረስ ፖለቲካውን/የለውጥ ትግሉን ሳያውቁት በተላላኪነት ብቻ ጥልአሸት ሲቀቡት ይስተዋላል::

የአንድ ድርጅት አባላት የሆኑ ወጥ ካድሬዎች ለኢትዮጵያ እነሱ ብቻ የተፈጠሩ አድርግ ሲያዩ ሌላውን እንደ እንጀራ ልጅ አድርገው ሲገፉ ማየት ያማል::ይህ ብቻ አይደለም ስህተታቸውን ስትነግራቸው የሚያብጠለጥሉ ካለስም ስም ሰጥተው ጥላሸት የሚቀቡ በገዢ መደብ በርካቶች ቢሆኑም በለውጥ ሃይሉም ውስጥ ተሰግስገው እያፏጩ ይገኛል::አሁን አሁን ደሞ የለውጥ ሃይል ነን በሚሉ ከሃዲዎች እና የገደል ማሚቱኦች እንዲሁም ስሜት እና ፕሮፓጋንዳ በተደበላለቀባቸው ሰዎች ላይ የፖለቲካ ክፋት ምቀኝነት እና ቅናት ብሶ ተገኝቷል ይህ ደግሞ ለለውጥ በሚድረገው ሂደት ላይ ችግር እና አለመተማመን ስለሚፈጥር በጊዜ ሊታረም የሚገባው ጉዳይ ነው::ጊዜው የለውጥ ነው:;ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል እስካልን ድረስ የሕወሓት የፖለቲካ ውጤቶች የሆኑት ጥላቻ ምቀኝነት ቅናት ክፋት እና ግለኝነት የተጠናወተው ፖለቲካ ሊቆም ይገባል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

የህዝብን ዝምታ ሰብሮ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የለውጥ ሃይሎች በጋራና በጽናት እንጓዝ::

Minilik Salsawi በእናት ሃገራችን ኢትዮጵያ ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘው የሕወሓት አምባገነን ቡድናዊ አገዛዝ በሕዝብ ላይ የሚፈጽመው የፖለቲካና የኢኮኖሚ በደል ገደቡት አልፎ ዜጎች በገዛ አገራቸው መኖር እንዳይችለ ሆነዋል:: በሃገራችን ተከስትው ይሚገኙ የፖለቲካ ጫናዎች የኑሮ ውድነት የድርቅ እና የተለያዩ ችግሮች አገዛዙ በሚፈጽመው በደል ላይ ተደራርበው ወገኖቻችንን እጅግ ለከፋ አደጋ አሳልፎ ሰጧቸዋል::ይህ ከፍተኛ የሆነ ብሄራዊ ውርደት እየታየ ያለው አገዛዙ ለዜጎች ያለውን ንቀት እብሪት እና መንግስታዊ ሃሰተኝነት ከሽብርተኝነቱ ጋር ተቀላቅለው ሕዝቡን አንገፍግፈውታል::የአገዛዙ ግፎች ተዘርዝረው የማያልቁ ሲሆን ለዚህ ደሞ መፍትሄው አገዛዙን አስወግዶ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት ብቻ ነው::

ይህንን ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የለውጥ ሃይሎች በአንድነት መቆም ይኖርባቸዋል::የጋራ ጠላታችን ወያኔ ነው የሚሉ የሃገር ውስጥ ይሁን በውጪው አለም ያሉ የለውጥ ሃይሎች ለሕዝብ ነጻነት እና መብት እንታገላለን እስካሉ ድረስ እርስ በእርስ መናከስ አቁመው በመደማመጥ እና በመወያየት በመመካከር እና በመቻቻል በመግባባት እና በመፋቃር ለሃገራዊ አጀንዳ በጋራ መቆም ችላ የማይባልበት ወቅት ላይ ተደርሷል::የሕዝብን ታማኝነት ለማግኘት የለውጥ ሃይሎች እርስ በርሳቸው እየተባሉ እንዴት እኛን ነጻ ያወጣሉ የሚለውን ቅብብሎሽ ለመቁረጥ እና በሕዝብ ዘንድ አመኔታን ፈጥሮ ትልቅ የለውጥ ስራ በመስራት አገዛዙን ማስወገድ ይቻላል::በሰላማዊ ትግል ይሁን በትጥቅ ትግል የተሰማሩ ሃይሎች ሕዝብን አስተባብሮ በአንድነት ለመምራት የሁሉንም የጋራ ልብ ለመግዛት የሚችሉት በአንድነት ቆመው የህዝብ ጠላት የሆነውን ወያኔን ለመደምሰስ የፖለቲካ ቆራጥነት እና የትግል ጽናት ሲኖር ነው::ተበታትኖ ትግል አንድም ለወያኔ ክፍተት መፍጠር ሲሆን በሌላውም በር የህዝብን ዝምተኝነት ማበርታት ይሆናል::መሰራት ያለባቸው የለውጥ ስራዎች ሁሉ በመደጋገፍ እና በመቻቻል መሆን ይገባዋል::


በዚህ ግፎች እየበረቱ በሄዱበት ወቅት ላይ የሕዝቡ የለውጥ ፍላጎት አብሮ እየጨመረ ይመጣል::ሕዝቡ ዝምታው ለምንድነው? እኛ ጋር ምን ችግር አለ? መቻቻል እና መተባበር የምንችለው እንዴት ነው? ለስልጣን የሚቋምጠው እና ልለውጥ የመሰራው እንዴት ይለይ?የሃሳብ ልዩነቶችን ማግባባት እና ማቻቻል የምንችለው እንዼት ነው? የሕዝቡን ዝምታ እንዴት መስበር ይቻላል?ሕዝባዊ ታማኝነትን በጋራ ሃገራዊ አጀንዳ እንዴት መፍጠር እንችላለን? የያዝነው ስትራቴጄ አዋጭነቱ ምን ያህል ነው..ተጠባባቂ ስትራቴጂ አለን ወይ? ሁሉም የለውጥ ሃይሎች በአንድነት ማቆም የሚቻለው የትኛው ግድፈት ቢቀረፍ ነው? ሰላም እና ዲሞክራሲን ለመተግበር ተነሳሽነት ምን ያህል ነው? ባለፉ 20 አመታት የተበታተነው ትግል እና የተበታተኑ ድርጅቶች ምን ፈጠሩ ? ካለፈው የትግል ተሞክሮ ምን እንማራለን ?...ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎችን መጠየቅ የለውጥ ሃይሎች ግዴታ ነው::ዋናው ነጥብ ግን በአንድነት መቆም ነው::ሃገራዊ አጀንዳ ይዞ የጋራ ጠላት የሆነውን ወያኔን በማጥፋት ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የለውጥ ሃይሎች በአንድነት መቆም ችላ የማይባል ነው:: የህዝብን ዝምታ ሰብሮ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የለውጥ ሃይሎች በጋራና በጽናት እንጓዝ:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የሲፒጂ አለማቀፍ የፕሬስ ነጻነት የ2015 ሽልማት ተሸላሚ ሊሆኑ ነው::

Minilik Salsawi - "ስለሚያገባን እንጦምራለን!" በማለት ለሕዝብ የዲሞክራሲን እና የሕግ ጽንሰ ሃሳብን በዳበረ መልኩ ለማስተማር እና በኢትዪጵያ እስጥ የይታዩትን ሕዝባዊ ጉዳዮች የማህበራዊ ፍትህ የፖለቲካ ጫና እና ሙስናን በተመለከተ የተለያዩ ጦማሮችን በማቅረብ ላይ እንዳሉ አሸባሪ ተብለው በወያኔ ጉጅሌ አገዛዝ ማስረጃ ባሌለው በሃሰት ክስ እስር ቤት የተወረወሩ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን በአለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ( CPJ ) በኩል የ2015 የአለማቀፍ የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ተሸላሚ ሊሆኑ መሆኑ ተሰምቷል::
ሲፒጄ በዚህ አመት ከኢትዮጵያ ከማሌዥያ ፓሯጓይ እና ሶሪያ ጋዜጠኞች እና ጦማርያን የ2015 የአለም አቀፍ የፕሬስ ነጻነት ሽልማቶችን ይሰጣል::
ዝርዝሩ እዚህ ላይ ያንብቡት :- http://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=104373

መንግስታዊ ውዥንብር - የአረና ሰዎች ሽርጉድ - የመንደርተኝነት አጀንዳ ድምዳሜው

Minilik Salsawi :- የደምሕት ታጋይ ሞላ አስገዶምን ተከትሎ ብዙ የኮካዎች ውሮሸባ የቀወሱ ሃሳቦች የስም ማጥፋቶች የተበሳጩ ኪሳራዎች የደቀቁ የተልፈሰፈሱ ዲያስፖራዎች የእርስ በእርስ ግልምጫዎች እና ዘለፋዎች አሳፋሪ ዘመቻዎች እና ፍረጃዎች ወዘተ ያላነበብነው ነገር የለም::እውነት ከማይዋጥላቸው ድንጉጥ ያልበሰሉ ፖለቲከኞች ጀምሮ ኪሳራ የተከናነቡ ያህል የለፈለፉ የገደል ማሚቱዎች እና በራሳቸው ኢጎ እስከሚጦዙ ሃይሎች ድረስ ሁሉንም አየን ታዘብን::ይሁን እኔን ግን የገረመኝ ካለው እውነት የወጡ በመግለጫ ስም የተለቀቁ መንግስታዊ ውዥንብሮች እና የካድሬዎቹ መደነባበር እንዲሁም የተቃዋሚ የአረና ፓርቲ አባላት በሞላ ዙሪያ እየተሽከረከሩ አሸንዳ መጨፈር እና ሽር ጉድ ማለት ብሎም የአቶ ሞላ አስገዶም የመንደርተኝነት አጀንዳ ድምዳሜ ብቻ ነው::

ክወያኔ ጉጅሌ አገዛዝ መግለጫ ብንጀምር መግልጫ ሳይሆን በኔ እይታ መንግስታዊ ውዥንብር ነው::ምንም ተጨባጭ ያሌለው መግለጫ እና ተከርብቶ እጁ የገባውን ሞላን የወያኔ ሰላይ ነበር አሊያም የስለላ ጥበባችን እንዲህ ነው የሚል የሃሰት ፕሮፕጋንዳ ለመርጨት ካልሆነ በስተቀር በድል ሽሚያ መሃል የገባው ወያኔ ከባድ ኪሳራ በመግለጫው አግኝቶታል:: ያልተገናኘውን ለማገናኘት ሲውተረተር የሚታየው ከደርግ በባሰ መልኩ በትምክህት እና በጦረኝነት ዘለፋ የተሞላው አምባገነናዊ ውዥንብር ሕዝብን ለማታለል ያደረጉት ቢሆንም ራሳቸውን እንዳታለሉ ሕወሓቶች አልተረዱትም::አጉል ራስን ከፍ አድርጎ በሕዝብ መሃል እኛ እንዲህ ነን የሚል ፍርሃት ለመልቀቅ ቢሞከርም ከነካድሬዎቻቸው መደነባበር ውስጥ መግባታቸውን አጋልጠዋል:: ወያኔ ለሞላ የስለላ ተልእኮ ከሰጠችው ከሞላ ጋር የገቡት ወታደሮቹ ለአገር ጉዳይ ሲሰሩ ነበር ካለች ታዲያ ለምን አሸባሪ እያለች የምትወነጅላቸው በደምህት ሜዳ ሲንሸራሸሩ ዶጋ አመድ አታደርጋቸውም ነበር? የመግለጫው ሃሰትነት እና ግንዛቤ የጎደለው ድክመት አንዱ ይህ ነው!!!የማይመስል ውዥንብር ነው::ምንም ግዜ ከአምባገነኖች የሚጠበቀው ይህ የዘቀጠ መግለጫ የወያኔን ሽንፈት ገሃድ አውጥቶ ምነው አማካሪ የላቸውም ወይ እስከማሰኘት መሳቂያ አድርጓቸዋል::ራስን ለኪሳራ አቀባብሎ መስጠት ማለት እንዲህ ነው::ካድሬዎችን መግለጫውን ደጋግማቹ ስሙት::

ሌላው ገራሚ ነገር የአረናዎች ሽር ጉድ ነው::አረና ፓርቲ በወንድሞቻችን በነአብርሃ ደስታ እስከ አምዶም ገብረስላሴ ድረስ የሚከበር ፓርቲ ነበር ሆኖም የአንድን ግለሰብ ያዉም (ለነጻነት እና ለመብት ?)እታገላለሁ ብሎ ረዥም አመታት በረሃ የከረመ ግልሰብ ተንሸራቶ ሲገኝ እንደ አረና ያሉ ለመብት እና ነጻነት እንታገላለን የሚሉ የድርጅት አባላት ጥያቄ ማንሳት አሊያም ነገሩን አጥንቶ ያለውን ሁኔታ በመገንዘብ መናገር ሲገባቸው ከሕወሓት ካድሬዎች በበለጠ መልኩ በሞላ መመለስ ላይ ሃይሎጋ ማለታቸው አንድም ፖለቲካ አያውቁም አሊያም የድርጅታቸውን የትግል ስልት ገና አላጣጣሙትም/አላወቁትም:: የግለሰቡ በረሃ መግባት ይሁን ተንሸራቶ ከተማ መድረስ ምናልባት ከዘር ጋር ተያይዞ ከሆነ በሕወሓት የላላውን ገመድ የባሰ ከማላላት ውጪ ምንም አይፈይድም::ፖለቲካ በስሜት በጥቅም በብሄር እና በፕሮፓጋንዳ ከታጀበ እንደሚበላሽ ማወቅ አለብን::ተላላኪነትን ባልበሰሉ ዲያስፖራዎች እና ስደተኞች ላይም እያየነው ነው::

ሶስተኛው የታጋይ ሞላ አስገዶም ኩርፊያ እና የመንደርተኝነት አጀንዳ ድምዳሜው ነው::ታጋዩ ሞላ ከጅምሩ የፖለቲካ አኩራፊ ነው ለማለት ያስችላል የመንደርተኝነት አባዜ የተጠናወተው በጅምሩ በሕወሓት መርሃግብር የታሸው ሞላ ከድሮም ከበረሃው የወያኔ ትግል ጀምሮ አኩራፊ ነበር:: በማኩረፍ ሲንከባለል እዚህ ደርሷል::ሞላ በወያኔ ላይ ጦርነት መጀመር የፈለገው ለስልጣኑ እንጂ ለኢትዮጵያ አልነበረም::ይህ ደሞ ከአመጥቱ ጀምሮ የተገራበት ፖለቲካ እና ኩርፊያው ምስክር ነው::ታጋይ ሞላ በሕወሓት ቆይታው ዘሎ ከኤርትራ በረሃ ያስገባው በሕወሓት ውስጥ የነበረው የአድዋ እና የተምቤን የመንደርተኝነት የስልጣን ትንቅንቅ እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ግፍ በዝቶበታል የሚል የነጻ አውጪ ጥያቄ አንግቦ አይደለም::የደምሕት መሪዎች ይሁኑ ወታደሮች የነጻነት ትግል ያደርጉ ከነበረ ትግላቸው በመርህ በአላማና በእምነት ላይ የተመሰረተ አልነበረም የሚታገሉት በእምነት ሳይሆን ከኋላ ለሚገፋቸው ልዩ ሃይል ነበር ወደ ሚል የዘር ልጓም መስመር ላይ ተሳስበናል::በተለያዩ ጊዜያት ከወያኔ መዋጋት አለብኝ ብሎ ይጠይቅ የነበረው ታጋይ ሞላ ከፍተኛ (የስልጣን ጥም?) እንዳለበት በዚህ ሰሞን የሚወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል::እርግጥ በቂ ሃይል ቢኖረዉም ከወያኔ የማይዋጋበት ምክንያቱ አሊያም መዋጋት አለብን የሚለው ጥያቄው ያልተመለሰበት ምክንያት ማወቅ አስፈላጊ ባይሆንም በሞላ የትግል ሂደት ዙሪያ የሚያጠነጥኑ መረጃዎች ግን እንደሚያመለክቱት ሞላ የተንቤንን አጀንዳ ይዞ አሊያም በሌላ አነጋገር የመንደርተኝነት አጀንዳ ይዞ ይዋልል እንደነበር ድምዳሜው ያስረዳል ያሳየናል:: እወነት እና ንጋት እያደር ይጠራል::ከአቋም መልፈስፈስ መንሸራተት ይሰውረን:: ለተሳዳቢዎች እና ለወመቴ እመጫት ፖለቲከኞች ልብ ይስጥልን::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬