የሃሰት ፕሮፓጋንዳ - የቁጥር ቁልል - መሬት ላይ ያለው እውነት - ራዲዮ ፋና (ምንሊክ ሳልሳዊ)

Minilik Salsawi - የወያኔው ጉጅሌ አገዛዝ የፕሮፓጋንዳ ወፍጮ የሆነው ራዲዮ ፋና የአገሪቱ አጠቃላይ ምርት 1 ነጥብ 24 ትሪሊየን ብር ደረሰ የዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ 691 የአሜሪካ ዶላር መድረሱን እየደሰኮረ ይገኛል::እኛ እስከምናውቀው ድረስ 1.24 ትሪሊዮን ብር የአገሪት አጠቃላይ ምርት ሳይሆን በአገሪቱ በፖሊሲ ድርቀት የተከሰተውን ረሃብ ለእርዳታ የተጠየቀው ገንዘብ ነው::አስልቶ መድረስ ይቻላል::የአንድ ዜጋ የነብስ ወከፍ ገቢ እንኳን 691 ዶላር ሊደርስ አይደለም በአለም ታይቶ የማይታወቅ የደሃ ደሃ ዜጋ የተፈጠረበት ብሄራዊ ውርደት ላይ ነን::የአለም ባንክ እና የአይኤምኤፍ ሪፖርቶች ያገጠጡ እውነቶችን አስቀምጠዋል:: ወያኔዎች ዘላለማቸውን አጣብቂኝ ውስጥ ሲገቡ ሕዝብን ለማደናበር እና ለማጭበርበር የቁጥር ቁልል ይጠቀማሉ::ሕዝቡ ከነሱ ቀድሞ መንቃቱን አለመገንዘባቸው የሚገርም ነው::

የዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ 691 የአሜሪካ ዶላር የሚለው ወያኔ እየመራው የሚገኘው ኢኮኖሚ ተሽመድምዶ ሃገርን ረመጥ ላይ እየከተታት ሲሆን የወያኔ ሳቦታጅ ጥቂት ሰዎች በሃገር ሀብት በህዝብ ላይ እንዲፈነጩ አድርጓቸዋል::በሃገሪቱ ማንኛውም አይነት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ከበፊቱ በተለየ እና በባሰ ሁኔታ ተንኮታኩተው አፈር መልበሳቸው በይፋ ታውቋል::ለስርኣቱ ቅርበት አላቸው ያሉ ምንጮች ወያኔ ወገቡ እንደተሰበረ እየተናገሩ ነው::በፖለቲካው ረገድ የስርኣቱ ገዢ ፓርቲዎች እርስ በርስ አለመተማመን ደረጃ ላይ ከመድረሳቸውም በላይ አመራሮቹ አድፍጠው አንዱን አንዱን እየጠበቀ በፍራቻ አለም ውስጥ እየዋተቱ ይገኛሉ::አቤት የሚባልበት እየጠፋ ነው፡፡ የውሳኔ ሰጪ ያለህ ቢባል መልስ አይገኝም፡፡ ፋይሎች የሚያያቸውና የሚያነባቸው አጥተዋል፡፡ መልካም አስተዳደር ገደል ገብቷል::በአላማ ሳይሆን በጊዜያዊ የመኖር ሂደት ላይ የተመሰረተው የካድሬዎቹ ሩጫ ድካምን በመፍጠሩ ሁሉም በያለበት ቆም ብሎ እያሰበ ሲሆን አሳቡም የገፈፍኩትን ገፍፌ ሃገርን ድባቅ መትቼ ልሽሽ ሆኗል::
በድርቅ የተመታች አገር አገዛዝ በረሃብ የሚሰቃዩ ዜጎቿን መመገብ ያልቻለች አገር አገዛዝ ቁጥር እየቆለለ መጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የ10 ነጥብ 1 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገቧን በዚህም ኢንዱስትሪው የ20 ነጥብ 2 በመቶ፣ ግብርና የ6 ነጥብ 4 በመቶ እንዲሁም የአገልግሎት ዘርፍ የ10 ነጥብ 8 በመቶ ዕድገት ተመዝግቧባቸዋል ቢባል የሚሰማ ጆሮ የለንም::ኧረ እፍረት ይኑር::መሬት ላይ ያለው እውነት ሌላ ነው::ችግር ድህነት የደሃ ደሃ ሕዝብ የሚበላው ያጣ የተራቆተ ምስኪን ዜጋ::

ካመጡት ጊዜ ጀምሮ ያልተሳካው ጭራሽ ድህነትን ያስፋፋው የትራንስፎርሜሽናቸው እቅድ አቃጥለውት ስልጣን መልቀቅ ሲገባቸው ይባስ ብለው የነፍስ ወከፍ ገቢው መጨመር አገሪቱ እያስመዘገበችው ያለው ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ከ10 ዓመት በኋላ መካከለኛ ገቢ ያላት አገር እንደምትሆን አመላካች ነው በማለት በውሸት ክምችት እውነትን ለመፍጠር እየተፍጨረጨሩ ነው::አገሪቱ እንኳን ፈጣን እድገት ልታስመዘግብ ይቅርና በብድር እና እዳ ተወጥራ በዜጎች ድህነት እና በኑሮ ውድነት ተከባ በድርቅ እና ረሃብ ተሸብባ የለጋሽ አገሮችን እርዳታ እየለመነች ሀገር ባለችበት በዚህ ወቅት ላይ ያሌለ አለ እያሉ ማውራት በሕዝብ ላይ ማሾፍ ሲሆን የተጭበረበረ አፋኝ ፖለቲካ ያስከተለው የኢኮኖሚ መንኮታኮት የአገሪቱን የፖለቲካ አናቶች ለውጥ እንዳያመጡ በመተብተብ ቀውስ ውስጥ የከተታቸው መሆኑን ከስብሰባዎች እና ከጭብጨባዎች ብዛት እየታዘብን ነው::በሌላ በኩል ሚዲያዎች ህዝብን መዋሸታቸው እና ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ መዋላቸው አገሪቷ እንድትንኮታኮት በር የከፈተ ሲሆን የዚህ መፍትሄ ስልጣን መልቀቅ ነው::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

የወያኔ ባለስልጣናት እና አማካሪዎቻቸው ውሸታቸውን አጧጡፈውታል::እውን የብድር እዳ ክምችት አያሳስብም?

- የኢትዮጵያ ጠቅላላ የብድር መጠን ከ30 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወይም ከ1.2 ትሪሊዮን ብር በላይ ነው::
- የአገሪቱ የብድር ዕዳ ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት አንፃር ሃምሳ ከመቶ ደርሷል::
- የዋጋ ግሽበት ከሚጠበቀው በላይ የእጥፍ እጥፍ አሻቅቧል::
- በፋይናንስ አቋሞች ላይ ቁጥጥር ባለመደረጉ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ቀውስ ተከስቷል::

Minilik Salsawi's photo.
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - የማይሸፈነው የኢኮኖሚ ገበና አግጥጦ ወጥቷል::ከዚህ ቀደም እንደምንለው የወያኔ የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በተደጋጋሚ ከኪሳራ ውጪ የፈየደው ነገር የለም::ይህ ደግሞ አረቀቅነው ከሚሉ ጀምሮ እያስፈጸምነው ነው ያሉት ድረስ አምነው መስክረውበታል::እቅዱ ስላልተሳካለት ስልጣኑን ለሃገር ገንቢዎች ያስረክብ ድህነትን እንቀርፋለን ብሎ የደሃ ደሃ ፈጥሯል ከዚህም በላይ መጪ ትውልድ ከፍሎ የማይጨርሰው የብድር እዳ እና ሙስና ተንሰራፍቷል;;የሃገሪቷ ኢኮኖሚ አሳሳቢ ነው በዲያስፖራው ድጋፍ እና በአለም ነዳጅ ቅነሳ ተደግፎ ያለ ነው ብለን ሁላችንም ጮኽናል::ሰሚ ባለመኖሩ ጆር ዳባ ልበስ ቢባልም የዓለም የገንዘብ ድርጅት እና የአለም ባንክ በተራው ፉጨቱን አሰምቷል::
የዓለም የገንዘብ ድርጅት እና የዓለም ባንክ ያወጡት ሪፖርት እንደሚያሳየው የኢትዮጵያ የብድር ዕዳ እያሻቀበ በመምጣቱ በብድር ዕዳ ክምችት ላይ የወያኔ አገዛዝ ከመጠንቀቅ ይልቅ በልማት ስም እየተበደረ እያመጣ ባለስልጣናቶቹ ክነአማካሪዎቻቸው በሙስና ተዘፍቀው ያለውን የብድር እዳ ክምችት በተመለከተ ሲጠየቁ አያሳስብም ማለት ጀምረዋል::የዓለም የገንዘብ ድርጅት በአሁኑ ወቅት የአገሪቱ የብድር ዕዳ ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት አንፃር ሃምሳ ከመቶ በመድረሱ ጥንቃቄ እንዲደረግ እያሻቀበ የመጣው የዋጋ ግሽበትም ትኩረት እንዲሰጠው ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡ እውን የብድር እዳ ክምችት አያሳስብም? ምናልባት ለወያኔዎች አያሳስብም ይሆናል አስፈላጊውን ገንዘብ ሰብስበው ከዘረፉ በኋላ ሾልከው ለማምለጥ ስለሆነ እቅዳቸው በልማት ስም ቴሸፍኖ ሃገር እና ሕዝብን ማሽመድመድ ስለሆነ ራእያቸው ለነሱ አያሳስብም ለለውጥ ሃይሎች ግን አሳሳቢ ጉዳይ ነው ለመጪው ትውልድ ከአሁኑ የባሰ ድህነትን ማውረስ ለማይፈልገው ለአሁኑ ትውልድ አሳሳቢ ስለሆነ ሊተኮርበት ይገባል::የወያኔ ባለስልጣናት እና አማካሪዎቻቸው አያሳስበንም በሚል ትእቢት ተወጥረው ሃገራችንን እየገደሉ ይገኛሉ::
ያለማ ያልተደረገ ያልተሰራ አጋኖ በማቅረብ በፕሮፓጋንዳ አጅቦ በሃሰት በማዜም ወደር ያልተገኘለት ወያኔ ዛሬም ላም ባልወለበት ...እንደሚባለው በምርታማ መስኮች ላይ እያዋልነው ነው ብድሩን የሚል የሃሰት ሰበብ እየፈጠረ ሕዝብን ማሳመን ይፈልጋል::የወያኔ አገዛዝ የግሉን ዘርፍ እያቀጨጨ በሙስና ተሳስሮ የፓርቲውን የንግድ ድርጅቶችን እና በዘመድ አዝማድ ልከክልህ እከክልኝ የተሰሩ ቢዝነሶችን እያጧጧፈ በፕሮፓጋንዳው መስክ የግሉን ዘርፍ ለማሳደግ እየሰራሁ ነው በማለት ሊደልል ይሞክራል::የወያኔ አገዛዝ የግሉ ዘርፍ ውስጥ እጁን ከቶ ስራዎችን በእኩይ ተግባሩ እያመሰ እንዴት የግሉ ዘርፍ ያድጋል?የግሉ ዘርፍ የወያኔ እጆች ባይገቡበት ባለሃብቱ በራሱ ሊያሳድጋቸው እና ሊያዳብራቸው ይችላል::ሆኖም በሙስና እርስ በእርስ የሚታከከው አገዛዝ የተበደረው ገንዘብ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ መሸከም ከሚችለው በላይ ስለሆነ አደጋው እየሰፋ ይገኛል::
በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ የተገነባው የወያኔ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ከውጪ ይሚመጣውን ብድር የባለስልጣናት ኪስ ለመሙላት ስለሚውል ብቻ ልማት ፕሮፓጋንዳ ከመሆኑም ባሻገር በተግባር ታዩ የሚባሉት ያልተጠኑ እና እድሜ የሌላቸው ለሃገር የማይጠቅሙ ስራዎች መሆናቸውን በአይናችን ተመልክተናል::አሁንም መፍትሄ ሊሆን የሚችለው የሃገሪቱ የፖለቲካ ምሕዳር በማስፋት ዜጎችን ማንገላታት በማቆም ዜጎች በሃገራቸው ሰርተው እንዳይኖሩ እንዲሰደዱ የሚድረገው ጫና በማስቀረት ማንኛውም የግል ባለሃብት የራሱን ስራዎች ሲሰራ እኩይ የአገዛዙ እጆች እንዲወገዱ ..ወዘተ...ይህንን ለማድረግ ደሞ ያለው የወያኔ ጉጅሌ አገዛ ፍቃደኛ ባለመሆኡ በቅድሚያ ሊወገድ ይገባል::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬