የሐይለማርያም ደሳለኝ ጅል ፖለቲካ ሕወሓት ከሚተገብረው ሐቅ የተለየ ነው::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - እንደኔ ሐይለማርያም ደሳለኝ የሚናገረው ንግግር ሁሉ ጊዜውን ያላገናዘበ ሕዝብ የሚያውቀውን ጉዳይ ያልመዘነ በእውነት ላይ ያልተመሰረተ በደመነፍስ የሚናገረው የጅል ፖለቲካ ድምር ውጤት ነው::የተመከረውን እና የተባለውን ሁሉ መልሶ የሚያስተጋባ በጥቂት ቡድናዊ ማፊያዎች የሚነዳ የአገር መሪ አለ ብሎ መናገር አንድም እርግማን ሰፋ ሲልም አንገትን የሚያስደፋ ነው::ሃይለማርያም እንደ ጠ/ሚኒስትር ብንወስደው እንኳን በፖለቲካ ያልበሰለ ገና እንጭጭ በራሱ የማይተማመን ራሱን ያላገኘ ከርታታ (ፖለቲከኛ?) ነው::

በየመድረኩ ቀርቦ የሚናገረው በጭንቀት መሆኑ ያሳብቅበታል::ለጋዜጣዊ መግለጫ ሲቀርብ የሚተነፍሳቸው ትንፋሾች ሰው ሰራሽ እንደሆኑ ራሱ በራሱ ላይ ያቃጥራል::ለሚመልሳቸው መልሶች ሁሉ ሃይል የተቀላቀለ ድምጽ በማውጣት ራሱን እንደ ባለስልጣን አድርጎ ለመሳል መሞከሩ ውሸታምነቱን ይናገርበታል::ለሚጠየቀው ጥያቄ እንኳን በፊት ለፊት ይቅርና ዙሪያ ጥምጥም ለመመለስ አለመቻሉ ልምድ አልባ እና ሰነፍ መሆኑን ያሳያል::በፖለቲካው አለም ይህን ያህል አመቶ ኖሮ ለራሱ የማይገዛ ሕዝብን ማሳመን ያልቻለ በነዱት የሚሄድ ሰው ቢኖር ሃይለማርያም ነው::በፍጹም መሻሻል አይታይበትም ያው እንደተርመጠመጠ ዛሬም አለ::

በትጥቅ ትግል መንግሥት ለመቀየር እየሠሩ ያሉ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች ውጤት እንደማያመጡ እርግጠኞች ነን በማለት መናገሩ ምን ያህል ስለ ኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች መረጃ እንዳሌለውና አስተላልፍ ይተባለውን ጥላቻ ከማሳየቱም በላይ እርግጠኛ ነው ማለት በውስጥ አለመተማመኖች እንዳሉ ግልጽ ያደርጋል::በትጥቅ ትግል ላይ የተሰማሩ ተቃዋሚዎች ውጤት ማምጣት ካልቻሉ በመንግስት መሪዎች ዘንድ አሊያም በጠ/ሚ ዘንድ ቃላቶችን እና አትኩሮቶችን ማግኘት ቻሉ?ካለምንም ምክንያት የፍራቻ ቃላቶችን ለመተንፈስ ለምን በወያኔ በኩል ተፈለገ?የሕወሓት ፖለቲካ ችግሩ ተከታይ ጥያቄዎችን የሚያስከትሉ የላሞኛችሁ ጉዳዮችን መናገር ላይ ነው::ሕወሓት በፍርሃት ስለራደ መሰሪ እና ገዳይ ቡድን ነው::በትጥቅ ትግል ላይ የተሰማሩ ተቃዋሚዎች ምን ያህል ስጋት እንደሆኑ በገሃድ የወያኔ ድርጊቶች እና ቃላቶች እያመለከቱን ነው::

በፖለቲካ ጫና የተሽመደመዱ ዜጎች ምድር በተጭበረበረ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ለድህንነት የተዳረጉ ሕዝቦች በሞሉበት አገር ዜጎች በአስተሳሰባቸው ብቻ ተይዘው ወህኒ የሚወረወሩበት ያልታጠቁ ዜጎች እንደ ጦር ወንጀለኛ አሸባሪ ተብለው እስከሞት የሚፈረድባት ፍትህ አልባ አገር ጥቂት ባለስልጣናት ባደራጁት የዘረፋ ቡድኖች የሃገር እና ሕዝብ ሃብት በሚበዘበዝባት አገር የፖለቲካ መሪዎች እና የሃይማኖት ምሁራን ካለወንጀላቸው በሚሰቃዩባት ኢትዮጵያ ውስጥ ሃገር እየበለጸገ እያደገ ነው ማለት በሕዝብ ላይ ያለውን ንቀት ያሳያል::የሃሳብ ልዩነት ያላቸው በሰላማዊ መንገድ ያቀረቡ እስር ቤት እንደሆኑ ሃይለማርያም ዘንግቶታል::በእጁ ሊገባለት ያልቻለውን እና በዳበረ መረጃ ማንነቱን ያወቀውን ዲያስፖራውን ለማታለል ሕወሓት የማይቧጥጠው ነገር የለም::ሃይለማርያም ተመክሮ የሚዘላብደው እና ሕወሓት የምታራምደው እኩይ ተግባር የተለያዩ ናቸው::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

ነውረኛ ውሸታም ኣገዛዝ ፡ ወገን በረሃብ አና በድህነት አያለቀ ተኣምር አንፈጥራለን ማለት በሕዝብ ላይ ማሾፍ ነው::‪

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - በስድስት ወራት ትምህርት ዶክተሬት ያገኘው ኣርከበ አቁባይ በኢኮኖሚ ፖሊሲው ዙሪያ ባለፉት ኣመታት ሲያጭበረብር ቆይቶ ኣልተሳካለትም። የቁጥር ቁልሎችን ከመፍጠር ውጪ ምንም የተገበረው ነገር የለም፤ በላኪዎች የሚገኘውን የውጪ ምንዛሬ በዜሮ ያንደፋደፈ ሀገሪቱ ማግኘት የሚገባትን ገንዘብ በሙስና ያዘረፈ ግለሰብ ዛሬ ላይ ሆኖ ለሚቀጥሉት ኣምስት ኣመታት ተኣምር አንሰራለን በማለት የተለመደ ሃሰቱን አየደሰኮረ ይገኛል፤ተአምር ጠብቁ የሚል ሙድ መያዝ ጀምሯል:: የሃገሪቱ የኢኮኖሚ ኣውታሮች ዲያስፖራው ለቤተሰቡ በሚልከው ዶላር አና የኣለም ነዳጅ ዋጋ በመውረዱ ተደግፎ መኖሩ አየታወቀ በየትኛው መስመር ተኣምር ሊሰራ አንደታሰበ ግራ ያጋባል፤ግራ ከማጋባትም ኣልፉ ግልጽ የሚያደርገው ነገር ቢኖር ኣገዛዙ ኣጣብቂኝ ውስጥ መሆኑን በገሃድ ያሳያል፥፥በብድር ገንዘብ ተኣምር ሊሰራ ከታሰበ አንዴት ኣበዳሪዎችስ ያበድራሉ፥ወያኔ የተበደረው ገንዘብ ከኣቅም በላይ ከመሆኑ ኣንጻር ካሁን በኋላ ልበደር ማለት ኣሳሳቢ ነው ሲሉ የኣለም ኣበዳሪ ድርጅቶች ሲያማርሩ ተስተውሏል::በባዶ ካዝና ምን አይነት ተአምር እንደሚሰራ አቶ አርከባ ካሳዩን በባዶ ካዝና ተአምር ይሰራ ኢኮኖሚስት ተብለው በአለም አስደናቂ ጉዳዮች መዝገብ ላይ ይሰፍራሉ::

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ሕንጻ ሶስተኛ ፎቅ ላይ ተዘፍዝፈው መላ ሃገሪቱ በምቾት የተንቆጠቆጠች የመሰላቸው አቶ አርከበ እንደ ዘራፊ ባልንጀሮቻቸው እርሳቸውም በአዲስ ስልት በድህነት እና በረሃብ በተጎዳው ሕዝብ ላይ እየተዘበባቱ ይገኛሉ::ሃምሳ ከመቶ የሚሆነው ገበሬ ምርጥ ነጋዴ ወቶታል የሚለው የሕወሓቱ አህያ አሻንጉሊት ሃይለማርያም ደሳለኝ ገበሬው የማዳበሪያ ኬሚካሎች በፈጠሩት የመሬት ድርቀት የተፈጥሮ ችግሮች በጋረጡበት አደጋ እንዲሁም በአገዛዙ ፖሊሲ ከባድ ችግር ውስጥ መሆኑን ሊናገሩ አልደፈሩም::ያው ተቃዋሚው ስለ ሕዝብ ከመጮህ ይልቅ እርስ በእርሱ በወያኔ አጀንዳ እየተባላ ባለበት በዚህ ወቅት አውሬዎቹ ወያኔዎች በሃገር እና ሕዝብ ሕልውና ላይ እየቀለዱ ይገኛሉ::

ይህ አሳፋሪ እና ጨካኝ አገዛዝ በፖለቲካ ጫና ሕዝቡን እያሰቃየ በብዝበዛ የሃገሪቱን ካዝና አራቁቶ በጉልበት እና በድርድር ፍትህን እየነገደ ተአምር ልሰራ ነው በሚል እጅግ አደገኛ የሃሰት ፕሮፓጋንዳውን እያራገበ ነው::በመልካም አስተዳደር እጦት ሕዝብ እያለቀሰ ቃልና ተግባር አልገናኝ ብለው ሕዝብን እየተማርረ ራሳቸውን ከሕግ በላይ ያደረጉ ሹማምንት ኢሰብዓዊ ተግባር እየፈጸሙ መብትን መጠየቅም ሆነ ቅሬታ ማቅረብ አሸባሪ እያሰኘ ሃላፊነት በጎደለው ግብረገብነት ባሌለው የሹማምንት እብሪተኝነት የነጻነት መብት እየተደፈጠጠ ዜጎች እየተሸማቀቁ ሐሳብን በነፃነት መግለጽም ሆነ መብትን መጠየቅ ወንጀለኛ አሸባሪ በሚሰኝበት አገር ምን አይነት ተአምር ከሹማምንት ይጠበቃል::ይህችን አይነት ማጭበርበር ለማንም አትበጅም ሃገሪቱ በከፍተኛ ደረጃ አደጋ ውስጥ ባለችበት በዚህ ሰአት ስልጣን ለሕዝብ ከማስረከብ ውጪ ምንም ተአምር ሊሰራ አይችልም::ባለፉት አመታት የነበሩ የኢኮኖሚ እድገቶች ከቁጥር ቁልል ውጪ ምንም አልፈየዱም::አሁንም ቢሆን በረሃብ የተጎዱ ዜጎቹን መመገብ ያልቻለ ሃሰተኛ አገዛዝ እንዴት አድርጎ ተአምር ሊሰራ ይችላል::የማይመስል ነገር ነው::የወያኔን ተአምር ከመጠበቅ ይልቅ በጋራ በአንድነት ታግሎ ይህንን ሃሰተኛ አገዛዝ ማስወገድ የለውጥ ሃይሎች ድርሻ መሆን ይገባዋል::በባዶ ካዝና ተአምር እፈጥራለሁ ብሎ መነሳት ራስን ከማጭበርበር ውጪ ምንም ውጤት የለውም::ነውረኛ ውሸታም ኣገዛዝ ፡ ወገን በረሃብ አና በድህነት አያለቀ ተኣምር አንፈጥራለን ማለት በሕዝብ ላይ ማሾፍ ነው:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬