በሕቡእ መደራጀት የወቅቱን የመብት ትግል ለድል ያበቃዋል !!!

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - lከዚህ ቀደም የወያኔን አንድ ለአምስት አድረጃጀት ራሱን ወያኔን ለማጥቃት ልንጠቀምበት ይገባል የሚል በመርህ ደረጃ የቀረበ ሃሳብ ቢኖርም አንዱ የአንዱ የበላይ ነኝ በሚል የፖለቲካ እደምታ እንዲሁም በፖለቲከኞች መካከል አንድነት እንዳይፈጠር እና መከፋፈል እንዲኖር በሚሰሩ ጸረ ሕዝብ ሴረኞች ሁኔታዎች እንደታሰቡት ከግብ ሊደርሱ አልቻሉም::ካለፈው መማር እንደተጠበቀ ሆኑ በአሁኑ ወቅት ሕዝቡ የመብት ትግሉን በማፋፋም መልስ የሚሹ ጥያቄዎቹን ይዞ አደባባይ በመውጣት ላይ ስለሆነ የተገኘውን አጋጣሚ በአንደነት ቆመን በመጠቀም በሕቡእ በመደራጀት ይህንን እኩይ የወያኔ አገዛዝ ልናስወግደው ይገባል::

ሕዝቡ ፊት ለፊት ተጋፍጦ ሕይወቱን ከሚያጣ የትግል አመራር ያሌለው ጩኽት ከመጮህ ለዘላቂነት ተደራጅቶ አገዛዙን እንዲያስወግድ የለውጥ ሃይሎች በያለንበት ያለ የሌለ ሃይላችንን አቅማችን ገንዘባችንን እና ጉልበታችን ተጠቅመን ትግሉን ለድል ልናበቃ ያስገድደናል::የወያኔ ወንጀል ተነግሮ አያልቅም የወያኔ እኩይ ክፋት ተነግሮ አያልቅም በአሁኑ ወቅት ግን ማተኮር ያለብን ሕዝቡን በሕቡእ በተገኘበት ማደራጀት እና እንዲደራጅ ማድረግ የዜግነት ግዴታ ነው::ካለፉት የትግል ስህተቶች መማር አለብን:;በተናጠል ለመስራት መሞከር እንደማያዋጣ ሁሉም ተጉዞ ያየው ሲሆን በአንድነት እጅ ለእጅ ተያይዘን ካለህበት እርገጥ ከሚሉት ትግል መውጣት እና ማንኛውንም ክፍተት ለወያኔ ሳንሰጥ በጋራ በመታገል ለድል ልንበቃ ወቅቱ በሩን ከፍቶልናል::
የፖለቲካ ለውጡ ሃገር እና ሕዝብ ተኮር እንጂ ብሄር እና ግለሰብ ተኮር መሆን እንደሌለበት ሁላችንም የምናውቀው ጉዳይ ሲሆን ለዚህም ሲባል ነው በመቻቻል መንፈስ ልዩነትን አቻችሎ አምባገነኑን ስርዓት ከስሩ መንግሎ መጣል ግድ የሚለው:;ጠባብ ኢትዮጵያዊነት እና ጠባብ ብሄርተኝነት አሊያም ግለሰብን ማምለክ ለትግሉ እንደማይፈይድ ካለፈው ሂደት ከማየታችም በላይ በጠንካራ አገራዊ አጀንዳ ላይ የተመሰረተ አደረጃጀት ግቡን እንዲመታ የለውጥ ሃይል የሆነውን ወጣት ሳንውል ሳናድር በሕቡእ ልናደራጀው እና እንዲደራጅ ልንረዳውና ልንመክረው ይገባናል::

በሕቡእ መደራጀት ከቻልን ራሳችንን ከወያኔ ጥቃቶች መከላከል እንችላለን::በሕቡእ መደራጀት ከቻልን አስፈላጊ በሆነ ሰአት አድፍጠን በወያኔ እና ጭፍሮቹ ላይ አስደንጋጭ አደጋ ልናደርስ እንችላለን::በተጨማሪ አንዱን ብሄር ከአንዱ ለማጋጨት በወያኔ የሚሸረቡ ሴራዎችን ተደራጅተን ልናከሽፍ እንችላለን:;ይብልጡኑ ደግሞ ይህንን አምባገነን ስርዓት ልንደመስሰው የምንችለው ተነጣጥለን ሳይሆን በጋራ በአንድነት ተደራጅተን መሆኑን ልናውቅ ይገባል::ስለዚህ በሕቡእ መደራጀት የወቅቱን የመብት ትግል ጥያቄ ለድል ያበቃዋል::
‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬