የሕወሓት ጥልቅ ተሓድሶ :- የአዲስ አበባና የመቀሌ ኣንጃ የሚባል ቃል የተቃዋሚን ጆሮ ለማደንቆር የተሰራ ሴራ ነው። TPLF Reform is Lie

የሕወሓት ጥልቅ ተሓድሶ :- የአዲስ አበባና የመቀሌ ኣንጃ የሚባል ቃል የተቃዋሚን ጆሮ ለማደንቆር የተሰራ ሴራ ነው።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - ሕወሓቶች ጓዳዊና ድርጅታዊ ፍቅራቸው ኣይጣል ነው። በኣደባባይ የተባሉ ይመስላሉ እንጂ ውስጥ ውስጡን ግን ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ዲሲፕሊን እና መደማመጥ ኣላቸው። በደጅ በሚነዙት ፕሮፓጋንዳ ሕወሓት እንዳበቃላት እንደፈረሰች እንደተከፋፈለች ተደሮ የሕዝብን ስሜት ለመሳብ የሚደረጉ ውሸቶች የውስጥ እውነታውን ይደብቁታል ኣደባባይ ላይ ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ኣስመሳይነት ሲታይባቸው የውስጥ ጥንካሬን ግን በተርታ ሰንሰለት እየገነቡት ይጓዛሉ።

በቅርቡ በኣማራ ክልል እና በትግራይ ክልል መካከል የሚደረገው የድንበር እና የማንኔት ጥያቄ ፍጥጫዎች ኣቶ ኣባይ ወልዱንና ኣቶ ደጉ ኣንዳርጋቸውን ሲወነጃጅሉ የከረሙት የወያኔ ፕሮፓጋንዲስቶች ስራቸውን ኣጠናቀው ኣዲስ የፕሮፓጋንዳ ኣጀንዳ ለማምጣት እየሰሩ ነው። በመቀሌ እና በባህር ዳር የተካሄደው የፓርቲዎች ግምገማ ተጠናቆ (ችግሮች ?) በሰላም እንደተፈቱ እየሰማን ሲሆን ምን ያህል በሕዝብ ትከሻ ላይ ኣምባገኖች እየዘለሉ እንደሚገኙ የመሰከረ ግምገማ ነበር። በዋናነት የሚነኩትና የሚወገዱት የብአዴን ካድሬዎች ሲሆን ሕወሓት በግምገማዋ ተማምላ እንጂ ተጣልታ ኣልተለያየችም።

በራሳችን የሰጡንን ኣጀንዳ ተከትለን በፈጠርነው የሕወሓት የኣዲስ ኣበባ ኣንጃና የመቀሌ ኣንጃ ንትርኩ በሰላም ተፈቶ ኣባይ ወልዱ ከስልጣን ኣልወርድም ብሎ ምናምን በሚል የደጅ ፕሮፓጋንዳ የውስጥ መሃላ የሕወሓት ግምገማ ተጠናቋል። ለማን ደስ ይበለው ብለን ነው ኣባይ ወልዱን የምናባርረው የሚል ውሳኔ ጸድቋል። ለዚህ ደጋፊ የሚሆን ፕሮፓጋንዳ ደሞ የፌዴራሉ ሕወሓት ኣፍሮ መመለሱ እንዲደሰኮር ተደርጓል። ሕወሓቶችን ማመን ቀብሮ ነው። በኣደባባይ በተላላኪዎቻቸው የሚያስነዙት ፕሮፓጋንዳና በጓዳ የሚሰሩት የፖለቲካ ሴራ የተለያየ ነው።ከሕወሓት ውስጥ ማንም ኣይወገድም ከስልጣን ኣይነሳም።የኣዲስ ኣበባና የመቀሌ ኣንጃ የሚባል ቃል የተቃዋሚን ጆሮ ለማደንቆር የተሰራ ሴራ ነው። #ምንሊክሳልሳዊ

ሳይቃጠል በቅጠል ሊታሰብበት የሚገባ እውነታ - የጋራ ሃገራዊ ዲሞክራቲክ ኣጅንዳ ::

ሳይቃጠል በቅጠል ሊታሰብበት የሚገባ እውነታ
ዘረኝነቱ ይራገባል! ይራገባል! ይራገባል! የጋራ ሃገራዊ ዲሞክራቲክ ኣጅንዳ የለም ሁሉም እኔ ኣውቅልሃለሁ እያለ ነው ሰዎችን ማዋረድና መሳደብ ፋሽን ተደርጎ ተይዟል። የማግለል የጥላቻና የፍረጃ ፖለቲካ ስለተስፋፋ የለውጥ ሃይሉን በኣንድነት ሰብስቦ የሚያታግል ጠፍቷል።በማይረባ ኣጀንዳ ላይ የሚልፈሰፈስ ጨምሯል።

መሬት ላይ ያሌለ ሃቅ በየማህበራዊ ድህረገጹ ሲፖተለክ ይሰማል።ትላንት ስለ ኢትዮጵያ ከኛ በላይ ማንም የላትም ሲሉ የነበሩ በጥቅም ተገዝተው ኢትዮጵያ ትፈረካከስ ዘንድ ዘምተዋል። ዜጎች በእኩልነት የሚኖሩባት ኢትዮጵያን ለመመስረት ከመድከም ይልቅ ለፍጅት ፖለቲካ ቅድሚያ ተሰጥቷል።ከሃገር ወዳዱ ይልቅ የመኖሪያ ፈቃድ ፈላጊው ያልበሰለ ፖለቲከኛ ሲያሞጠሙጥ ይውላል። የመኖሪያ ፈቃድ ፈላጊዎች ሕልማቸው ተሳክቶ ሲነሱ ሃገር ቤት ገብቶ ወያኔን ኮንዶሚኒየም እንዲሰጣቸው በመለመን የሚቀድማቸው ኣልተገኘም። ትግሉ ይህ ነው።

ሃሳብን በሃሳብ ከማሸነፍ ይልቅ ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑ ሰዎችን ታግሎ ከመደምሰስ ይልቅ ፎቢያ ስር ሰዶ ነግሶ የፖለቲካ ጥላቻን ወልዷል፤ካለፈው መማር ያልቻልን የራሳችን ጠላቶች ከመኖናችንም በላይ ትግላችን ሁሉ የሞኝ ሩጫ ኣድርገነው ፍጥነታችን ባለህበት እርገጥ ሆኗል። ሊታሰብበት የሚገባ እውነታ - የጋራ ሃገራዊ ዲሞክራቲክ ኣጅንዳ :: (#ምንሊክሳልሳዊ) Minilik Salsawi - mereja.com

ወያኔ የሰጠችንን የቤት ስራ እየመነዘርን እዛው ላይ እንደፋደፋለን፤ ካለፈው ለመማር ያልቻልን የራሳችን ጠላቶች መሆናችንን እንደቀጠልን ነው::

ወያኔ የሰጠችንን የቤት ስራ እየመነዘርን እዛው ላይ እንደፋደፋለን፤ ካለፈው ለመማር ያልቻልን የራሳችን ጠላቶች መሆናችንን እንደቀጠልን ነው:: #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi - mereja.com - ስምምነት የጎደለው ትግል ፣ መግባባት የተሳነው ፖለቲካ ፣ በጥላቻ ፖለቲካ የታጀለ ፕሮፕጋንዳ፣ ለጠላት የፖለቲካ ፍጆታ በሩን የበረገደ ጭፍን ኣስተሳሰብ፣ በድቦ የስድብ ፖለቲካ የሚያራምድ መንገኝነትን የለበሰ ባዶ ጩኸት ብዙ ማለት ይቻላል ለዲያስፖራው ፖለቲካ ። እነማን ማን እንዳደራጀቸው የነማን ግርፍ እንደሆኑ ለይተን የማናውቅ የማንነቃ ከትግል ይልቅ ኣፍ መክፈት የሚቀናን እጅግ ልንተች የምንገባ ንፋሳሞች ነን።ካለፈው ለመማር ያልቻልን የራሳችን ጠላቶች መሆናችንን እንደቀጠልን ነው፥ከወያኔ የማይለይ ኣስተሳሰብ ያነገቡ የወያኔ ግልባጮች ትላንት በእንበታትነዋለን ዛሬ ደግሞ ጥያቄው የቅኝ ግዛት ነው በሚሉ ንፋሳም ኣጀንዳዎች መላተም ሊቆም ይገባል። ብስለት በጣም ያስፈልጋል።ተዋጠልህም አልተዋጠልህም እውነቱ ይህ ነው።

በየማህበራዊ ድህረገጹና በየዌብ ሳይቱ ከማውራት መሬት ላይ ወርዶ ተገባራዊ ስራ መስራት ይጠበቃል። ኢትዮጵያን እንበታትናለን ኣሊያም ጥያቄያችን የቅኝ ግዛት ነው የሚሉ ሃይሎችን ማኮላሸት የሚቻለው ተግቶ በመስራት እንጂ በማውራት ኣይደለም። የሚገርመው ስሜታውያን በርክተዋል::ተናግረው እፎይ ብለው የሚተኙ በርካቶች ሆነዋል::ልክ ልኩን ነገርጉት ብለው ሌላውን ደሞ ለማሸማቀቅ (የሚሸማቀቅ ካገኙ) አስበው በየምናምኑ የሚንጎዳጎዱ ጊዜው ይቁጠራቸው::በነፈሰበት የሚነፍሱ ሳያገናዝቡ የሚያራግቡ የፈጠራ እሳት የሚያርገበግቡ በተገኘበት ተደናብረው እና ደንብረው ደንግጠው ለማስደንገጥ የሚርበተበቱ እንዳሉ ሁሉ ሙድ ለመያዝ የሕዝብን ጭንቀት የሚጠቀሙበት ተደምረው ሆዳም በጥቅም የሚደለሉ በጠለዟቸው ሄደው የሚቾመሱ አጀንዳ እና አቋም አልባ ሮቦት ካድሬዎችም በርካቶች ሆነዋል::

ይህ ሁላ የግንዛቤ እጥረት ነው::ያለንበትን ጊዜ እና የሚካሄዱ ትግሎችን አለመመዘን ለትግሉ አስታውጾ ለማድረግ ደፋ ቀና ከማለት ይልቅ ተደራሽነት ያሌላቸውን የክፋት ብእር አጀንዳዎችን ይዞ መክለፍለፍ ምም ውጤት የለውም::ለመድገም ያህል ካለፈው ለመማር ያልቻልን የራሳችን ጠላቶች መሆናችንን እንደቀጠልን ነው::
ወያኔ ስራዋን ትሰራለች::ጓዳ ጎድጓዳ ገበናውን ስላወቀች በተላላኪዎቿ የሚሰጠውን የቤት ስራ ለለውጥ ሃይሎች አሸክማ እሷ የውስጥ ጉዳይውን እያስተካከለች የለውጥ ሃይሎች እያሰረች እየሳደደች እየገደለች ስልጣኗን ታጠናክራለች::እና ከሚዘመሩ የሃሰት መዝሙሮች ተነስተን ወያኔ አብቅቶላታል በሚል የፕሮፓጋንዳ መደምደሚያ ላይ ትተን የሰጠችንን የቤት ስራ እየመነዘርን እዛው ላይ እንደፋደፋለን::ራሳችን ማረም የምንጀምረው መች ይሆን ?አጀንዳ የማታጣው የቤት ስራ ለለውጥ ሃይሎች ማዘጋጀት ስራዋ የሆነው ወያኔ የምታመጣው አጀንዳ እና የቤት ስራ አትኩሮት ባንሰእጠው ያላትን የፕሮፓጋንዳ ሂደት ማኮላሸት እንችላለን::

.. ኧረ በስንቱ ልበጥበጥ አለች? በሶ:: ይህንን የሚያራግቡ እና አገር ወዳዱን ርሁሩሁን ዲያስፖራ ሆዱን የሚያንቦጫብጩ አጀንዳዎች ላይ እንዲሽከረከር ማድረግ ምን ያህል የወያኔን አደገኝነት የሚያሳይ ነው::አደባባይ ላይ አተካራ ገጥሞ የለውጥ ሃይሎን በ ነው/አይደለም አተካሮ ለማናከስ ክርክሮችን ፈጥሮ አለመግባባቶች ለማስፋት የሚደረጉ ያልተጣሩ መረጃዎች እና የፈጠራ ማዘናጊያ ጽሁፎች ምን ያህል የትግሉን ወንዝ እንደሚያሻግሩን አላውቅም:;
መንገድ ዳር ሰጥሞ ለመቅረት ካልሆነ በስተቀር ወያኔያዊ የፈጠራ አጀንዳ እና መረጃ ላይ ፊት ለፊት እየነጠሩ መጠዛጠዝ የብስለት ስርቆት መካሄዱን ፍንትው አድርጎ ያሳያል::ወያኔን ለመጣል አንድ እና አንድ ነገር ያስፈልጋል ህዝብ ተስፋ የሚያስቆርጡ መረጃዎች የለውጥ ሃይሎች የእርስ በእርስ መናከስ በተገኘ አጀንዳ እንደተፈለገ ንፍስፍስ ማለት የመሳሰሉት ጉዳዮች ሊታሰብባቸው እና ሊወገዱ ይገባል::የሚመጡ መረጃዎች ሃላፊነት የሚወስድ ሰው አሊያም ሚዲያ እስካልተገኘ ድረስ አሊያም ወያኔን ወያኔ አዋረደ በሚል የዋህነት ፈሊጥ መነሳት እንዲሁም ባልበሰለ የዘረኝነት እና የመንደርተኝነት ጽሁፎች ከመቃጠል ራሳችን ማዳን እና ልብ መግዛት ይገባናል:: ሁላችንም በጋራ በሚደረጉ ትግሎች ላይ ልንረባረብ ይገባል::ትግሎችን በማስፋፋት በማስተማር እና በመቀስቀስ በመርዳት ላይ ልንሰማራ ይገባል:ብስለት ማለት ለትግል የሚደረጉ አስታውጾዎችን በማበርከት እና በተረጋገጡ አጀንዳዎች ላይ ስራ መስራት ሲቻል ብቻ ነው::እና እኔም እላለሁ ያለንበት ጊዜ በተገኘው አጀንዳ ላይ የሚነፈስበት ሳይሆን ብስለት የሚጠየቅበት ጊዜ ነው:: ‪#ምንሊክሳልሳዊ
በየማህበራዊ ድህረገጹና በየዌብ ሳይቱ ከማውራት መሬት ላይ ወርዶ ተገባራዊ ስራ መስራት ይጠበቃል። ተዋጠልህም አልተዋጠልህም እውነቱ ይህ ነው።

የምንሄድበት መንገድ ያሳፍራል ያሳዝናል!!! የሕወሓት ቅልብ ዘረኞች ለለውጥ የሚደረገውን ትግል እያመሱ ነው::(ምንሊክ ሳልሳዊ)

የምንሄድበት መንገድ ያሳፍራል ያሳዝናል!!! የሕወሓት ቅልብ ዘረኞች ለለውጥ የሚደረገውን ትግል እያመሱ ነው::(ምንሊክ ሳልሳዊ)

ሕወሓት የሚዘውረው የሚመራው አገዛዝ ይህን አደረገ ይህን አደረገ ዘረፈ ሰቀለ ገለፈ አሰረ ገደለ አሳደደ ወዘተ የሚሉ እኩይ ተግባራቱ ብንዘረዝረው አያልቅም ከዚህ ይልቅ አሁን የሚያስፈልገን ነገር ቢኖር ይህንን እኩይ አገዛዝ ለመጣል የምንሄድበት መንገድ የምንጓዝበት ስትራቴጂ አዋጪ ነው እቅዳችን አሳዛኝና አሳፋሪ ነው የምንለውን እንዴት ማስተካክል አለብን ኬዘመነ ትግል ጀምሮ ሲሰበክ የነበረው አንድ እንሁን በም አይነት መቻቻል እና ስልት ይሳካል ብሎም በዲያስፖራው ውስጥ ተቀምጠው ለሕዝብ ይተከራከሩ የሚመስሉ የሕወሓትን ራእይ የሚያሳኩ እና ተልእኮ ይዘው ለሚያናክሱ ፖለቲከኛ መሳዮች ባለመንታ ምላሶችን ከጨዋታ እጪ ማድርግ የመሳሰሉ ጉዳዮችን በተግባር የምንተረጉም ሆነ መገኘት ለጥያቄዎቻችንም መልስ ማግኘት አለብን ካልሆነ የምንሄድበት መንገድ ያሳፍራል ያሳዝናል::

ሕወሓት ኢትዮጵያን በታትኖ የራሱን አገዛዝ ለመመስረት እየተጣደፈ ይገኛል ለዚህ አላማ ስኬት ይሆነው ዘንድ በሃገር ቤትም ይሁን በውጪ ያሰማራቸው ዘረኝነትን የሚሰብኩ የሕወሓት ተቃዋሚ መስለው ኢትዮጵያን እንደ ቅኝ ገዢ ያስቀመጡ ቅልብ ዘረኞች ለለውጥ የሚደረገውን ትግል እያመሱ ነው::ሕዝቦች ለራሳቸው ነጽነት በሚታገሉበት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጫና አንገብግቧቸው አደባባይ በሚጮኹበት በዚህ ወቅት ላይ የሕዝብን ትግል ለጠባብነታቸው የሚጠቀሙበትን የእናት ጡት ነካሾች እቅተናል ብቻ ሳንል በተግባርም ልናስወግዳቸው ይገባል::ሕወሓት ከአነሳሱ ጀምሮ የመገንጠል ሱሱን ለማሳካት ደፋ ቀና እያለ ሲሆን የኢትዮጵያን ሉዋላዊነት ከመርህ እስከ ተግባር በመዳፈር ላይ ከመሆኑም ሌላ የበረሃ ስሙን እንኳን ሳይቀይር እስከዛሬ ሲዘልቅ ለዚሁ ግቡ ደግሞ አንዴ በኦሮሞ ሲለው በአማራ ስም የተፈለፈሉ ጠባብ ግለሰቦችን በማደራጀት የአገርና የሕዝብን ሕልውና በመጋፋት ላይ ይገኛል::ሕወሓት ክፋቱን ተንኮሉን እየቆፈረ ባለበት በዚህ ወት ክፍተት የሚፈጥሩ የቃላት ጦርነቶች ከማድረግ ይልቅ ሕወሓትን በቆፈረው ጉድጓድ ለመቅበር በጋራ መቆም ይጠይቃል ይህን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ የምሄድበት መንገድ ያሳዝናል ያሳፍራል::

የኦሮሞ ሕዝብን ትግል የኣማራን ሕዝብ ትግል ለማቀናጀት የተኬደበት መንገድ የኦጋዴን ሕዝብን ጥያቄ ለመተባበር የተኬደበት መንገድ የወልቃይት ጠገዴን እንዲሁም የጎንደር አከባቢን ጉዳይ ለመመለስ የተኬደበት መንገድ ሊመረመር ይገባዋል::እነማን ገብተው አደፈረሱ ከሚለው ጀምሮ በቃላት እና በወሬ እስከመቼ ይዘለቃል ብሎም የትግሉ እንቅስቃሴ እውን ዘልቆ ገብቶ የሕዝቡን የገነፈለ ቁጣ አቀናጅቶ ለግብ ይመራል ወይ ተደርጓል ወይ ካልተደረገስ.. ወዘተ የሚሉ ጉዳዮች ሊመረመሩ ይገባል::የትግሉን መንገድ ከግብ ለማድረስ የምሄድበት መንገድ በፖለቲካ ድርጅት ስር የታቀፉ አባላቶች እየታገሉበት ያለው መንገድ ሊመረመር ይገባል::አንድ ችግር በተነሳ ሰአት ወያኔ ስለ መልካም አስተዳደር እንደሚያላዝነው የለውጥ ሃይሉም ችግሩ እስኪቀዘቅዝ በአንድ እንሁን ሰበብ ከሚፋተግ ዘላጊ መፍትሄ እና በመከባበር በመቻቻል መንፈስ ላይ የተመረኮዘ መፍትሄ ሊያበጅ ይገባል::ካልሆነ አሁን የተያዘው መንገድ ያሳፍራል ያሳዝናል::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

«የሚቆርጡንን የምንነክስበት ጊዜ ላይ ደርሰናል !!! » የእርስ በእርስ የጅምላ ፍረጃ ይቁም።ኪሳራው ከባድ ነው።

Image may contain: text and food

«የሚቆርጡንን የምንነክስበት ጊዜ ላይ ደርሰናል !!! » የእርስ በእርስ የጅምላ ፍረጃ ይቁም።ኪሳራው ከባድ ነው።

ሕወሓትን ከመታገል ይልቅ የጽንፍ ፖለቲካ ይዞ መላፋት ያሳፍራል። የትግሉ እውነታዎች እንደተጠበቁ ሆነው የትግል ሻሞ ያለ ይመስል ላም ባልዋለበት ኩበት መልቀምም ያሳፍራል።ኣደርባይነት ኣስመሳይነት እጅግ ኣደገኛ ነው። የእርስ በርስ መኮራኮም የጅምላ ፍረጃ ከሕዝብ ልብ የሚፈልቀውን ተኣማኒነት ያሳጣል።

 የወያኔ ውሸት ስልችት ብሎን ባሌበት ጊዜ የቅፈላ ፖለቲካ የሚከተሉ የለውጥ ሃይሎች ጎታችነታቸውን ገትተው የመቻቻል የመከባበርና የመደማመጥ ፖለቲካ ኣካል ሊሆኑ ይገባል። ለውጥ የሚፈልጉ ሕዝቦች በተነሱ ሰዓት ሁሉ ኣበረታቹን ተበረታቹን የምንፈርጅ ከሆነ ኣደጋ ኣለው። ያውም ከባድ ኣደጋ።

ትግል ምንም ጊዜ የሚፈልገው መቻቻልና መደማመጥ ሲሆን ፍረጃ ቅፈላ እና የውሸት ፖለቲካ ያልበሰሉ ካድሬዎች ጩኸት ስኬቱን ያኮላሸዋል፤ ዛሬ ላይ እኛ ብቻ እናውቅልሃለን ብለው ለሚናገሩ ሰዎች ደጋፊ የሆኑ ነገ ላይ ጠያቂ ሆነው መታለላቸውን መረዳታቸው ኣይቀርም።እውነት ቀኗን ጠብቃ ነጻ ትወጣለች።በግራ በቀኝም በመሃልም የቆማጩ የለውጥ ሃይሎች ከመፈራረጅና ከልፊያ ፖለቲካ ወጥታቹ ኪሳራቹን በማስላት ወደ ሕዝባዊ የጋራ ትግል ተሰባሰቡ። #MinilikSalsawi

ቆራጥ ትግል ያስፈልጋል፡፡ የሕወሓት/ኢሕኣዴግ ባለሥልጣናት ምግባረ ብልሹነት የተጠናወታቸው ስለሆኑ ወንጀል ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም፡፡

By ምንሊክ  ሳልሳዊ

ይሰማል ?? #Ethiopia : ቆራጥ ትግል ያስፈልጋል፡፡ የሕወሓት/ኢሕኣዴግ ባለሥልጣናት ምግባረ ብልሹነት የተጠናወታቸው ስለሆኑ ወንጀል ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም፡፡ #Miniliksalsawi 

Minilik Salsawi – mereja.com – መንግስታዊ ሌቦች ተራ ሌቦች አይደሉም፡፡ አደገኞች በገንዘብ የታጀቡ በሥልጣንም የተደገፉ ናቸው፡፡ የሕወሓት/ኢሕኣዴግ ሌቦች ተራ ሌቦች አይደሉም፡፡ አደገኞች ናቸው፡፡ ምክንያቱም በገንዘብ የታጀቡ ናቸው፡፡ በሥልጣንም የተደገፉ ናቸው፡፡ ምግባረ ብልሹነት የተጠናወታቸው ስለሆኑ ሕገወጥ ገንዘብና ሥልጣናቸውን ላለማጣት ሕግን ከመጣስና ወንጀል ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም፡፡ ሌላውን አስወግደው እነሱ ብቻ የሚቆጣጠሩትና የእነሱን ፍላጎት ብቻ የሚያረካ መንግሥት የተቁዋቁዋመበት ነው!!!፡፡ ጉዞው ሌቦች የበላይነት የያዙበትና የሌቦች መንግሥት የተቁዋቁዋመበት ነው!!!በቆራጥ ትግል ሕወሓት ከኢትዮጵያ ምድር እንዲወገድ እንረባረብ።

የተወገዘ የነበረው የተለመደ ሆኗል፡፡ ጉቦ መውሰድ ኃጢአትና ወንጀል መባሉ ቀርቶ ጉቦ አለመቀበል ጅልነትና ሞኝነት እየተባለ ነው፡፡ፀረ ሕዝብ፣ ስስታም፣ ስግብግብና በሙስና የተጨማለቁ ለግል ጥቅምና ክብር ሲሉ አገርንና ወገንን ከመሸጥ፣ ከመለወጥ፣ ከመካድና ከመርገጥ ወደኋላ የማይሉ ባለሥልጣናት በሥልጣን ላይ መቀመጥ የሌለባቸው፣ መሾምና መከበር የማይገባቸው ባለሥልጣናት እንደዚህ ዓይነት ባለሥልጣናትና ሹሞችን ይዞ አገርን ከአደጋ ማዳን፣ ሕዝብን ከድህነት ማላቀቅና ፍትሕና ዴሞክራሲን ማስፈን አይቻልም፡፡በቆራጥ ትግል ሕወሓት ከኢትዮጵያ ምድር እንዲወገድ እንረባረብ።

ይህን ሕዝብ ከድህነት ማላቀቅና ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን የሚሆነውና በተግባር የሚታየው፣ ሀቀኖቹ በሌቦቹ ላይ የበላይነት ሲያረጋግጡ ብቻ ነው፡፡ በተግባር ሀቀኞች በሌቦች ላይ የበላይነት ሊኖራቸው የሚችለው ደግሞ ሲታገሉና በትግሉም ዋጋ መክፈል ሊኖርባቸው እንደሚገባ አምነው ሲንቀሳቀሱ ብቻ ነው፡፡
በቃል፣ በንድፈ ሐሳብ፣ በመግለጫና በቃለ መጠይቅ የመንግሥት ሌቦች እንዳሉ መናገሩና ማውገዙ ብቻ የትም አያደርስም፡፡ እንቅፋት ናቸው ብሎ መግለጹ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ የመንግሥት ሌቦች ካልተወገዱ የሌቦች መንግሥት ይመሠርታሉ ብሎ ማመን፣ ይህ የሌቦች መንግሥት እውን እንዳይሆን ለመቅጣት፣ ለማስወገድና ለመጠራረግ ቆራጥ ትግል ያስፈልጋል፡፡በቆራጥ ትግል ሕወሓት ከኢትዮጵያ ምድር እንዲወገድ እንረባረብ።

ሌቦችን ለማስወ ቆራጥ ትግል ያስፈልጋል፡፡ የሕወሓት/ኢሕኣዴግ ባለሥልጣናት ምግባረ ብልሹነት የተጠናወታቸው ስለሆኑ ወንጀል ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም፡፡ ፡፡ ሀቀኛው በተዝናና ቁጥር ሌባው እየተጠናከረ ይመጣል፡፡ በገንዘብ ተከታዩን ይገዛል፡፡ በገንዘብ ኔትወርክ ይዘረጋል፡፡ በገንዘብ ከውጭ ጠላት ጋርም ሊተሳሰር ይችላል (ሌብነት ድንበር የለሽ ነውና)፡፡ በገንዘብ ሀቀኞችን የሚያስወግዱ ኃይሎችን በማሰማራት ሊያሸንፍ ይችላል፡፡ በገንዘብ የመገናኛ ብዙኀንን ሊቆጣጠር ይችላል፡፡አቅም ያጣውን፣ ዕውቀትና ልምድ ያነሰውን በትምህርትና በሥልጠና ማጠናከር ይቻላል፡፡ ሌባና ወንጀለኛን ግን የሥልጠና፣ የሴሚናርና የውይይት ብዛትና ዓይነት አይለውጠውም፡፡ ሕጋዊ ዕርምጃ ብቻ ነው መፍትሔው፡፡የሕዝብ፣ የአገር፣የዴሞክራሲ፣ የፍትሕና የሰላም ጠላቶችን ማስወገድ ነው፡፡በቆራጥ ትግል ሕወሓት ከኢትዮጵያ ምድር እንዲወገድ እንረባረብ። #ምንሊክሳልሳዊ

በፍርሃት የሚኖር ፈሪ ኣገዛዝ – 11,607 ሰዎች ታስረዋል።

በፍርሃት የሚኖር ፈሪ ኣገዛዝ

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ኣምባገነኑ ሕወሓት ኮማንድ ፖስት ብሎ በገዳይ ወታደሮቹ ያደራጀው ቡድን 11,607 ሰዎችን ማሰሩን ስንሰማ ስርዓቱ ምን ያህል የሕዝብ ፍራቻ ውስጥ እንደሚገኝ ቁልጭ ኣድርጎ ያሳያል። በራሳቸው የማይተማመኑ ለስልጣናቸው ጥም ሲሉ ያልታጠቁ ንጹሃንን ከየቤታቸው በመውሰድ ማጎሪያ ካምፕ ውስጥ መክተታቸው የሕዝብ ተቃውሞ ስጋት ውስጥ እንደጨመራቸው ኣመላካች ሲሆን ኣገዛዙ የሕዝብን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ ኣፈናን መፍትሄ ማድረጉ ከባድ ፍራቻ ውስጥ መዘፈቁን ይመሰክራል።

ከየቤታቸው የታፈኑ ለዝብ ተቆርቋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ ሲሆን የዞን ዘጠኝ ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ ዛሬ ማለዳ 12 30 ገደማ ኮማንድ ፓስት ይፍለግሃል በሚል ሰበብ ከመኖሪያ ቤቱ በጸጥታ ሃይሎች ተይዞ እዛው መኖሪያ ቤቱ አካባቢ በሚገኝው 06 ፖሊስ ጣቢያ መታሰሩ ታውቋል። ኣሰርነው ብለው ያመኑትን በኣስር ሺዎች ቁጥር ኣሳንሰው ሲሆን ቁጥራቸው ውስጥ ያላስገቧቸው በሺዎች የሚቆጠር የታፈኑ ወጣቶችን ቤት ይቁጠራቸው።

ኣገዛዙ በፍርሃት የሚኖር ፈሪ በመሆኑ ብቻ ኢትዮጵያውያንን እያፈሰ በየማጎሪያ ካምፑ ኣስሮ ይገኛል። የሕዝብ ንቅናቄ ቀጣይነት ለስርዓቱ ኣደጋ መሆኑን ስለሚያሳይ የሕዝብ የጋራ ተቃውሞ በርትቶ ሊቀጥል ይገባዋል። የለውጥ ፈላጊ ሕዝቦችን ንቅናቄ ግድያ እስርና ኣፈና ኣይመልሰውም። ሕዝብ ኣሸናፊ ነው ሕዝብ ትክክል ነው። ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል። #Miniliksalsawi

ወያኔ ነፍሶበታል። የሕዝቡን ትግል እያለሰለሱ እንዲያጣጥሉና የወያኔን ሃያልነት እንዲሰብኩ ለሚዲያዎች በጀት ሊመደብ ነው።

Image may contain: text
 ወያኔ ነፍሶበታል። የሕዝቡን ትግል እያለሰለሱ እንዲያጣጥሉና የወያኔን ሃያልነት እንዲሰብኩ ለሚዲያዎች በጀት ሊመደብ ነው። #MinilikSalsawi

Minilik Salsawi - mereja.com - ከዚህ ቀደም ተሞክሮ ባይሳካም ለስልጣኑ ርዝማኔ ተስፋ የማይቆርጠው የሕወሓት የደህንነት ቢሮ በሃገር ውስጥ ላሉ ሚዲያዎች በተለይ በነጻ ፕሬስ ስም ለሚንቀሳቀሱ ጋዜጦች የ ኤፍ ኤም ራዲዮኖች የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በኣሉባልታ እንዲከፋፍሉ እንዲሁም የሕዝቡን ትግል እያለሰለሱ እንዲያጣጥሉ በጀት በመመደብ ስራ ለማስጀመር ማቀዱን የደህነት ቢሮ ምንጮች ተናግረዋል።

ለዚሁም ሪፖርተር፣ ካፒታል፣ ፎርቹን፣ አዲስ አድማስ ጋዜጣ የ ኤፍ ኤም ራዲዮኖች ግንባር ቀደም ተጠቃሚ እንደሚሆኑና ከሕዝቡ ትግል ጋር ተመሳስለው በመግባት እያለሰለሱ ሕዝቡን ተስፋ በማስቆረጥ የወያኔን ሃያልነት የሚያሰርጹ ጽሁፎችን በማተም እንዲሁም ኣጀንዳ የሚሆኑና ሕዝቡን ስጋት ውስጥ የሚከቱ ዬWስጥ ሽብር የሚፈጥሩ ጽሁፎች ከደህንነት ቢሮ ተጽፈው ሲላኩ በየኣምዶቻቸው በማውጣት እንዲሰሩ ለየጋዜጦቹ ከ150 ሺህ ብር እስከ 300 ሺህ ብር በጀት ሊመደብ መዘጋጀቱን ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል። ኣክለውም የግል ራዲኦ ጣቢያ የተባሉ በተለየ መልኩ ኣትኩሮት ተሰጧቸው በትጋት እንዲሰሩ ጉዳዩ የሚመለከተው ግብረ ሃይል ኣስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል የሚል ውስኔ መወሰኑ ምንጮቹ ጠቁመዋል።

እንዲሁም የኦሮሞ እና የኣማራን ተቃውሞ በተመለከተ በስሱ እንዲዘግቡና ኣንዳንድ የሕዝብ ጽሁፎችን በም ኣስገባት እንዲያትሙ ጎን ለጎንም ይህንን የሚያከሽፍ ተደጋጋሚ ጽሁፍ በማውጣት ሽፋን እንዲሰጡ ታቅዷል።ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የሙስሊሞች ትግልን ኣሳንሰው ኣጠልሽተው እንዲዘግቡ 2013 G.C. ለ አዲስ አድማስ እና ሪፖርተር ጋዜጣ ሰባ ሺህ ብር በኣንድ ዜና ብቻ ቢከፈላቸውም የታቀደው ሳይሳካ ቀርቶ መክሸፉና መጋለጣቸው ይታወሳል፥ http://minilik-salsawi.blogspot.com/2013/01/blog-post_9.html ኣሁን የራዲዮ ሚዲያዎችን ያካተተው ይህ የክሽፈት ዘመቻቸው ወደ ባሰ መቀመቅ ይዟቸው ይወርዳል ሲሉ የደህንነት ቢሮ ምንጮች ይናገራሉ።
የሕዝብን ትግል ማክሸፍ የሚቻለው ለሕዝብ ጥያቄ ትክክለኛ መልስ በመስጠጥ ካልተቻለ ስልጣን በመልቀቅ ነው የሚሉት ምንጮች ወታደራዊው ክፍል እያጉረመረመ መሆኑን ለደህንነት ቢሮ የሚመጡ ሪፖርቶችን ጠቅሰው በተጨማሪ ተናግረዋል፥ ስርዓቱ የመጨረሻው ሰኣት ላይ ስለሆነ የሚሰራቸው የሚያወያያቸው የሚፈጽማቸው የሚያስባቸው ነገሮች ሁሉ የጥፋት መሆናቸውን ምንጮቹ ኣስረግጠው ተናግረዋል። #ምንሊክሳልሳዊ

የሕወሓት እባቦች ዛሬም ለመከፋፈል ኣሰፍስፈዋል። ዘረኞች ያዩት የሰሙት ሁሉ ዘረኛ ይመስላቸዋል።

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የኣማራና የሌሎች ሕዝቦችን ጥያቄ ለማኮላሸት ከኦነግና ኣስተባባሪዎቹ ጋር መደራደር ያስፈልጋል የሚል ፉጨት የሴራ ፕሮፖዛል ሹሩባ ከሚጎነጉኑ ኣስመሳይ ከሕወሓት ካድሬዎች ተጀምሯል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የሕወሓት የበላይነት በቃ በማለት የበይ ተመልካች ሆኜ በድህነት መኖር ኣልሻም ሲል ኣደባባይ በመውጣት ብሶቱን እያሰማ ይገኛል፥ የኦሮሞ ሕዝብ የጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄ ቀጥሎ ኣማራው ክልል በመድረስ ሕዝቦች በኣንድነት በጋራ ለመታገል ወንድማማችነታቸውን ለማጠንከር እጅ ለእግ በመያያዝ የጋራ ጠላታቸው ወያኔን ለማጥፋት ቆርጠው ተነስተዋል። የኦሮሞ ሕዝብ ኣገዛዙን ሲቃወም ኣማራ ሕዝብ ስር ሲወሸቅ የኣማራው ሕዝብ ሆ ብሎ ሲወጣነት ኦሮሞው ሕዝብ ስር የሚወሸቅ የነበረው ሕወሓት በጎጥ እየከፋፈለ ለመግዛት ያለመው እቅድ ስለተነቃበት ኣደገኛ ድንጋጤና አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል።

በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ብአዴን የሚሉትን ጀሌውን ይዞ የኦሮሞን ሕዝብ ተቃውሞ ለመጨፍለቅ ያደረገው ሩጫ በሽንፈት የተጠናቀቀበት ሕወሓት ሽንፈቱን ውጦ ሳይጨርስ የኣማራው ሕዝብ ሕወሓትን ቅንድቡን ብሎት ቀልቡን ገፎታል።ይህን ተከትሎ የሕወሓት ካድሬዎችና አቀንቃኞች ኣንድ ጊዜ ፌዴሬሽኑ ፈርሶ ኮንፌዴሬሽን ይመስረት ሌላ ጊዜ ኣማራው ትጥቅ ይፍታ ደጉ ኣንዳርጋቸው ይደምሰስ ሲላቸው ደግሞ ከነኣለቆቻቸው በድርድር ስም እና በሃይማኖት እበቶች በኩል የሕዝብን ትግል ለማኮላሸት ደፋ ቀና እያሉ ይገኛሉ።

ሕወሓትን ማመን ቀብሮ ነው ሕወሓት ድርድር ስትል ስኳር የሆነ ቅድመ ሁኔታ ስታቀርብ የተንኮል ጉድጓድ እየማሰች እንደሆነ በኣንክሮ ልናውቅ ይገባል፤ የኣማራና የሌሎች ሕዝቦችን ጥያቄ ለማኮላሸት ከኦነግና ኣስተባባሪዎቹ ጋር መደራደር ያስፈልጋል የሚል ፉጨት ከሕወሓት ካድሬዎች ተጀምሯል። በኦሮሚያ ውስጥ ያለው ችግር አሁኑኑ ዘላቂና አቃፊ መፍትሔ ይፈለግለት፤ የሚሉት የሕወሓት አቀንቃኞችና ካድሬዎች የኦሮሞን ሕዝብ ዝም ኣለማሰኘታችን በዘረጋነው የጎጥ ፖለቲካ ላይ ትልቅ ችግር ስለፈጠርን ኣደጋ ሆንኦብናል የኦሮሞን ሕዝብ በድርድር እና በተለያዩ ሰበቦች ዝም ማሰኘት ከቻንል በኦሮሞ ሕዝብ ስር ተወሽቀን ሌላውን ሕዝብ ለመምታት ይቻለናል በሚል የወረደ አስተሳሰብ ይዘው ተሰይመዋል።

ድርድር የሚጠላ ሰላም የሚገኝበትን መንገድና መፍትሄ የሚቃወም ምንም ሃይል የለም። በሕወሓት ቤት ግን ድርድር ውይይት የሚሉ ብልሃቶች ጊዜ መግዣ ጠላትን ለይቶ መምቻና ተቃውሞን ማጥፊያ ተስፋ ማስቆረጫ መሆናቸው ያለፉ ተደጋጋሚ ሂደቶች በግልጽ ይመሰክራሉ። ኣሸባሪና ጸረ ሰላም ጸረ ሕዝብ ናቸው ብሎ ከፈረጃቸው ጋር ለመደራደር መዘጋጀቱ ሕወሓት በሕዝቡ የተፈጠረበትን ጫና ያሳያል።ዘላቂ መፍትሄ ሊሆን የሚችለው የኣንዱን ድምጽ ኣግልሎ የኣንዱን ድምጽ ይዞ ሳይሆን ሁሉም የሚሳተፍበት የሽግ ግር መንግስት ሲመሰረት ቢሆንም ሕወሓት እባብ እና መሰሪ ስለሆነ ሕወሓትን ማመን ቀብሮ ነው። ባለፉት ሃያ ኣምስት ኣመታት የተጫወታቹበት የከፋፋይነት ካርዳቹህ ኣሁን ላይ በሕዝብ ስለተነቃበት ተቀባይነት የለውም።‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

በአልሸባብ በጸረ ሰላም ሃይሎች እና በሻእቢያ ስም ሽፋን ፍንዳታዎችና ዘረፋዎች ሊፈጸሙ ነው ።

Image may contain: 1 person , textMinilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የኢጋድ መረጃ ነው በሚል ሽፋን ሕዝብንና ምእራባውያንን ለማታለል የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር የኢጋድ ማህተምና ኣስፈላጊ የኢጋድ መብቶች በእጁ የሚገኘው ሕወሓት እየበሰበሰ በመፍረክረክ ላይ የሚገኘው የሕወሓት ስርአት በመላው ሃገሪቱ ከፍተኛ ፍንዳታዎች እና ዘረፋዎችን ለመፈጸም ማቀዱን ከደህንነት አካላት የተገኙ ምንጮች ጠቁመዋል፥፥ይህ ፍንዳታ እና ዘረፋ አልሸባብ እያለ ራሱ የሚጠራውን ድርጅት ላይ ለማላከክ እና አልሸባብን ለመወንጀል ዝግጅቱ የተጠናቀቀ ሲሆን ከፍተኛ ፍንዳታዎች ይካሄዳሉ የተባለው በስፋት በመሃል ሃገር በገጠር መንገዶች ትራንስፖርቶች እንዲሁም በክልል ከተሞች መሆኑ ተጠቁሟል፤ያለውን የተኩስ ግለትና የፖለቲካ ጡዘት አየሮች እየተከተለ በወያኔ ቅጥረኞች እንደሚፈጸምም ታውቋል።
እንዲሁም በከፍተኛ የገንዘብ ተቋማት የመንግስት መስሪያ ቤቶች የግል ድርጅቶች እና የባለሃብቶችን ገንዘብ ለመዝረፍ መታቀዱን እነዚሁ የደህነት አካላት የተናገሩ ሲሆን ለዚሁ ጉዳይ የተደራጀ አካል ከሕወሓቶች እየተዘጋጀ መሆኑን ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል፤ የህዝብ ንቅናቄ ጥርስ ውስጥ የገባው ወያኔ በምእራባውያን ሳይቀር ስልጣኑን እንዲልቅ ቢፈለግም አንቆ የያዝው ሲሆን ስልጣን ብንለቅ መጪው መንግስት ከገባንበት ቆፍሮ ያወጣናል የሚል ፍራቻ እንዲሁም የህዝብ ንቅናቄ ከፍተኛ ውጥረት ፈጥሮበት ወያኔ አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው ሲሆን በህዝብ ሃይል እንደሚወገድ ኢትዮጵያውያ ብቻ ሳይሆኑ የውጪ ሃይሎችን ያመኑበት ጉዳይ መሆኑን ይታወቃል።
ከአልሸባብ ጋር ባለው ጉልህ ቁርኝት አገሪቷን የማመስ እቅድ እንዳለው በሚሰሙበት ወቅት ላይ የድንበር አከባቢዎች የሚሊሻዎችን ግጭት ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ ጦርነት ከኤርትራ ጋር በድንበር አከባቢዎች ማንዣበቡን በገሃድ እየታየ ነው፤ ሰራዊቱን ጨምሮ በደህንነቱ እና በተለያዩ የመዋቅር ተቋማት ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን በዘረኛው የወያኔ አገዛዝ እንደተንገሸገሹ እና የሚፈልጉት አስተማማኝ የሆነ ወያኔን ሊጥል የሚችል ሃይል ስለሆነ ካለምንም ማመንታት የህዝብን ንቅናቄ የሚያመጣውን የውድቀት ውጤት እንደሚቀበሉት ከድርጅቱ ውስጣዊ ውጥረት የተረጋገጠ ሃቅ ነው። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬ More Info - http://www.mereja.com/amharic/509458

ህወሃት ግድያ እንዲያቆም ከጌቶቹ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጠው * “ብልጡን ባለ ራዕይ መሪ” ክፉኛ ናፍቋል!

ወልቃይትን ለባለቤቱ ህዝብ ለመመለስ ህወሃት እየመከረ ነው
ህወሃት ግድያ እንዲያቆም ከጌቶቹ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጠው በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®
ethiopia police soilders
* “ብልጡን ባለ ራዕይ መሪ” ክፉኛ ናፍቋል!
የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር /ህወሃት/ አመራሮች ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ከመግደልና ከማስገደል እንዲታቀቡ ታዘዋል። ግድያው የሚቀጥል ከሆነ ከወትሮው በተለየ ርምጃ እንደሚወሰድ ተነግሯቸዋል። “ወልቃይትን ለባለቤቱ ህዝብ ብንመልስ ይሻላል” በሚሉና “አንመልስም” ሲሉ በሚቃወሙ መካከል ክርክር የጀመረው ህወሃት ስምምነት ሊደርስ አልቻለም። ሁኔታው መለስን ከመቃብር ቀስቅሷል።
አባይ ጸሃዬ፣ ሳሞራ የኑስና ሌሎች ባለስልጣናት አሜሪካ እንደነበሩ ለጎልጉል ጠቁመው የነበሩት የመረጃው ምንጮች እንዳሉት ባለስልጣናቱ ግድያ እንዲያስቆሙ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ተቀብለዋል። በአማራ ክልል የተነሳው ተቃውሞ ያሳሰበው ህወሃት በተመሳሳይ አሜሪካ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወደ ሰላማዊ ድርድር እንዲመጡ ጫና እንድታደርግ ጠይቀዋል። ለዚህም ይመስላል በአሜሪካ በኩል የተቀናቃኝ ድርጅት መሪዎችን በተናጠል ማነጋገር ተጀምሯል።
tplf military agaziህወሃት በግድያው ከገፋበት ከአሜሪካ በኩል የሚሰጠው ምላሽ እንደ ወትሮው በኤምባሲ ወይም በህዝብ ግንኙነት በኩል እንደተለመደው “ጉዳዩ አሳስቦናል” የሚል ተራ መግለጫ እንደማይሆን ማረጋገጫ መሰጠቱን ጎልጉል የሚያምናቸው የዲፕሎማት ምንጮች ከአሜሪካ ተናግረዋል። እንድ መረጃ አቅራቢዎቹ ቀጣዩ የአሜሪካ አቋም በውጭ ጉዳይ መ/ቤቱ (ስቴት ዲፓርትመንት) ዋና ኃላፊ ወይም ከፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት (ኋይት ሃውስ) በኩል የሚተላለፍ እንደሚሆን ይጠበቃል። ባለፉት ሳምንታት ግማሽ ያህል የህወሃት ባለስልጣናት አሜሪካ ደርሰው መመለሳቸውን ለስርዓቱ ቅርብ የሆኑ ሌላ ዜናን ለማስተባበል ሲሞክሩ ሳያስቡት ማረጋገጫ ሰጥተዋል።
በሌላ ዜና በህወሃት ውስጥ “ወልቃይትን መመለስ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው” በሚሉና “ሊመለስ አይገባም” በሚል የሃሳብ ልዩነት መፈጠሩ ታውቋል። የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ምንጮቹን ጠቅሶ እንዳለው በዚሁ ጉዳይ የተሰየመው የህወሃት አመራሮች ስብሰባ ለቀናት ቢወያይም ስምምነት ላይ ሊደርስ ግን አልቻለም።
“ወልቃይትን እንመልስ” ባዮቹ ወገኖች አማራ ክልል የተነሳው ተቃውሞ አስፈሪ፣ የከረረ፣ እስከወዲያኛው ለስልጣናችን የሚያሰጋ ስለሆነ ወልቃይትን መልሶ አገሪቱን ማረጋጋት የግድ ነው ይላሉ። “ወልቃይትን መመለስ የለብንም፣ እንዴት ተደርጎስ ይመለሳል? ውርደት ነው” በሚል አቋም የያዙት ደግሞ ሁለት መከራከሪያ አላቸው።
እንደ ዘጋቢያችን መረጃ ከሆነ እነዚህ ክፍሎች ሁለት ነጥቦችን በማቅረብ የተከራከሩት “አንመልስም፣ ከመለስንም መሰረተ ልማቱንና ያፈራነውን ሃብት ምን እናደርገዋለን?” በሚል ጥያቄዎች የታጀቡ ናቸው።
“ወልቃይት የኖሩት ወገኖቻቸን ሃብት አፍርተዋል። ለማን ነው ጥለውት የሚሄዱት?” የሚሉት እነዚህ ወገኖች አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ/ሃይል በመጠቀም በተጀመረው መንገድ መቀጠል እንዳለበት የሚመኙ ሲሆኑ፣ ምኞታቸው ካልተሳካ መሰረተ ልማቱን በሙሉማፈራረስ ሌላው የመጨረሻ ውሳኔያቸው ነው።
በዚህ ሁለት ሃሳብ የሚነታረከው የህወሃት አመራሮች ስብሰባ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ዕለት ድረስ ከውሳኔ ላይ አልደረሰም። ይሁንና በዚህ ውሳኔ ላይ እንደ ከዳ የሚነገርለት ብአዴን አቋሙ እንዲጠየቅ አልተደረገም።
ህወሃት ለረጅም ዓመታት በተለያዩ መንገዶች ሲያፍን የቆየው የሕዝብ ዓመጽ በአገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች መፈንዳቱ ሥርዓቱን ክፉኛ አናግቶታል፡፡ በፓርቲ ወይም በድርጅት ሳይመራ በሕዝብ እምቢተኝነት የገነፈለው ተቃውሞ በስልትና በግለት እየጠነከረ መምጣቱ ህወሃት የመግደል እርምጃ እንዲወስድና ከምዕራባዊ ጌቶቹ ጋር እንዲቃቃር እያደረገው ነው፡፡ በሥልጣን መቆየት በአንድ በኩል፤ በሌላ ደግሞ ከምዕራባውያን ጋር ስሙም መሆን የወጠረው ህወሃት ከዓቅሙ በላይ የሆነው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ከቀን ወደ ቀን እያየለበት በንጹሃን ላይ ጥይት መተኮሱን አላቆመም፡፡
samantha powerይህ አካሄድ ህወሃትን ለክፍፍል እንደሚዳርገው ከተለያየ አቅጣጫ ይነገራል፡፡ ለዘመናት ህወሃትን ስትንከባከብ የነበረችው አሜሪካ በተወሰነ መልኩ ጉዳዩን የማክረር ሁኔታ ይታይባታል፡፡ የአሜሪካንን ፖሊሲ የማስቀየር አቅም ያላቸው ጋዜጦች ኢትዮጵያ በአናሳዎች የምትመራ ከዴሞክራሲ የራቀች አገር መሆኗን እንደ አዲስ ለፖለቲከኞቻቸው እያስተዋወቁ ነው፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ነጻ አካል ምርመራ እንዲደረግ የተደረገውን ውሳኔ ህወሃት አልቀበልም ባለ ወቅት በመንግሥታቱ ማኅበር የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ሰማንታ ፓወር ህወሃት “ነጻ ምርመራውን መቀበል አለበት” በማለት በትዊተር የከረረ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
መጪው ጊዜ የከፋ እንደሚሆን የገመቱ፣ ለዘብተኛ ለመሆን የሚፈልጉና በሃብት የደለቡ የህወሃት ሰዎችና አሽከሮቻቸው “በጥገናዊ ለውጥ” ሁኔታዎች እንዲረግቡ ይፈልጋሉ፡፡ ምዕራባዊ አገራት በመቆየት ዘምነናል የሚሉና የምዕራባውያን ድጋፍ እንዳላቸው በተለያየ መልኩ የሚጠቅሱት በዚህ ውስጥ ይካተታሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ህወሃት/ኢህአዴግ ከየቦታው የሰበሰባቸውና በየአገሩ ተወካይ (አምባሳደር) አድርጎ ያስቀመጣቸው ተላላኪዎቹም ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ክፍሎች በራሱ በህወሃት ከረከሰው ሽምግልና እስከ ዕርቅ ለመሄድ የሚጥሩትንም ይጨምራል፡፡ ብንከስርም ወልቃይትን ለባለቤቱ እንመልስ ባዮቹ የዚህ ዓላማ አራማጆች ናቸው፡፡ የነዚህ ተቃራኒዎች ማሸበርና መግደል በመቀጠል “ካልገዛን እንሞታለን” ብለው ህወሃትን ከጌቶቹ ከማቃቃር እስከ “አሜሪካ ከከፋት ጉዞ ወደ ቻይና” የሚሉ የተሰባሰቡበት ነው፡፡ የበረሃ ገድላቸውን እየጠቀሱ “ደጋፊዎቻቸው” ጠብመንጃ እንዲወለውሉ የሚቀሰቅሱና “ሪፓብሊካቸውን” በአየር ኃይል ጭምር ለመከላከል የወሰኑ በዚህ ምድብ ውስጥ ተከማችተዋል፡፡
የእነዚህና ሌሎች ኃይላት ትንቅንቅ ህወሃትን አደገኛ ፈተና ውስጥ እንደጣለው ይነገራል፡፡ አራት ዓመታት በሙት መንፈስና ሌጋሲ ሲመራ የቆየው ህወሃት/ኢህአዴግ ታዛዥነት፣ መደማመጥና “ብልጠት” ጠፍቶበት “ባለ ራዕይ መሪውን” ክፉኛ ናፍቋል፡፡

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

ድርድር ፣ውይይት ፣መቅለስለስ የሕወሓት ማዘናጊያ ስልት ነው። – ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው::ቀብሮ ብቻ ሳይሆን አቃጥሎ አመድ አድርጎ ነው::

ድርድር ፣ውይይት ፣መቅለስለስ የሕወሓት ማዘናጊያ ስልት ነው። – ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው::ቀብሮ ብቻ ሳይሆን አቃጥሎ አመድ አድርጎ ነው::

Minilik Salsawi - mereja.com - ከአማራው ክልል በተለይ ከጎንደር የሚመጡ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ሕወሓት ድርድር ውይይት እርቅን ሽፋን በማድረግ ተቅለስልሶ እያዘናጋ ወጣቶችን በማፈስ ላይ ነው።ባለፈው ጊዜ የኦሮሞ ተቃውሞን ተገን በማድረግ ወሮበላ ቡድን ኣደራጅቶ በሻሸመኔ የፈጸመውን የግድያ ጥቁር ሽብር በጎንደርና በሌሎች የኣማራ ክልል ከተሞች ላይ የማይደግምበት ምክንያት እያሰላሰልን ዋስትናው ምንድነው ? ድርድር ፣ውይይት ፣መቅለስለስ የሕወሓት ማዘናጊያ ስልት ነው። – ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው::ቀብሮ ብቻ ሳይሆን አቃጥሎ አመድ አድርጎ ነው::የአማራው ሕዝብ መነሳት ለሕወሓት ትልቅ ኣደጋ ኣለው የኣማራው ሕዝብ መንቀሳቀስ ለሕወሓት መጪ እቅድ ትልቁ ጋሬጣ ሲሆን ሕወሓትን ላትመለስ እንደሚቀብራት ይታወቃል።

በተደጋጋሚ የምናገረው ጉዳይ ነው።ወያኔ በፍጹም በፍጹም በፍጹም ኣይታመንም። ኢሕአዴግ ተሃድሶ አያስፈልገውም በስብሷል መፍረስ አለበት::እኛ አይደለንም ራሳቸው አመራሮቹ ድርጅታቸው እንደበሰበሰ ከሟቹ ጀምሮ ተናግረውታል::አሁን ያለው አመራር ሰው ያልተረዳለት ነገር ቢኖር ራሱን የሚክበው በባዶ ነው:: ሕዝብን እያስገደለ የሚገኘው ያልተማሩ በፕሮፓጋንዳ የተሞሉ ያልሰለጠኑ ፖሊሶችን ከአንዱ ክልል ወደ አንዱ ክልል እየወሰድ ነው::ለመሆኑ ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን ? 25 ሺህ የልዩ ሃይል ፖሊስ ሰራዊት ከሶማሊያ ከደቡብ ሱዳን እና ኦሮሚኛ ተናጋሪ ከሆኑ ኬንያውያን ተመልምለው ሰልጥነው ከፌዴራል እና ከክልል እንዲሁም ከአግኣዚ ሰራዊት ጋር ተደባልቀው ሕዝብ እየገደሉ ይገኛሉ አሁንም ስልጣንን ከሕወሓት ሚሊሻዎች ጋር በጋራ ይጠብቃሉ የተባሉ ከየቦታው እየተመለመሉ እየሰለጠኑ ይገኛሉ::ከደህንነት ቢሮ የሚወጡ ጥቆማዎች አስደንጋጭ ናቸው::ወያኔ ጊዜ መግዣ ፋታ ማግኛ ማዘናጊያ ማደናበሪያ ያላቸውን የፕሮፓጋንዳ ስራዎች እየሰራ ነው:;የወያኔን አካሄድ ጠንቅቀን ማወቅ አለብን ዝም ብሎ ፖለቲከኛ ነኝ አያሉ ማራገብ አክቲቭስት ነኝ እያሉ መብጠልጠል/ ማጦልጦል ጥቅም የለውም::ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው::ቀብሮ ብቻ ሳይሆን አቃጥሎ አመድ አድርጎ ነው::ካልሆነ ጊዜ ገዝቶ እያዘናጋ የለውጥ ሃይሉን ወጣቶችን አመድ ለማድረግ ቆርጧል::

ሕወሓት በፖለቲካው እና በኢኮኖሚው ዘርፍ የማፊያ የወሮበላ ቡድን የሌቦች ስብስብ ነው።የራሱን ካልሆነ በቀር የሌሎች ክልሎች ይሁን የሕዝቦቻቸን የኢኮኖሚ እድገት በፍጹም ኣይፈልግም።ያኮላሻል ተስፋ ያስቆርጣል በሙስና እንዲዘፈቁ ያደርጋል ኣሰልሶ ያጠፋቸዋል። ሁሉም ነገር ስህተት ነው ብለው ራሳቸው አምነዋል ከተባለ እነዚህ ሰዎች ስልጣን የማለቁበት ምክንያት ምንድነው? የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን.. የኦሮሞና የኣማራ ሕዝብ ላይ ላይ የወሰዱት ድድብና የተሞላበት ግድያና ድብደባና እስር … የትራፊክ ሕግ … የጤና መድህን ዋስትና … ሁሉ ፖሊሲያቸው ስህተት ነው እያሉ እየተናገሩ ነው::በአገራችን ላይ አስተዳዳሪ ነን ብለው እስከተቀመጡ ድረስ ሃገርና እና ሕዝብን የሚመሩበት ፖሊሲ ስህተት እና ፉርሽ ከሆነ ምን እየጠበቅን ነው::ሕዝብ ላይ እየደነፉ ሕዝብ ላይ እያሾፉ ሕዝብን እየዋሹ ከዚህም አልፈው እየገደሉ እያሰሩ እያሳደዱ ይህ ስራችን ስህተት ነው እያሉ ደጋግመው እያደረጉት እኛ ግን ምን እየሰራን ነው?እነሱ ሰው ለመጨፍጨፍ በአንድነት ሲዘምቱ ደግመው ለለመዋሸው በአንድነት ሲደሰኩሩ እኛ ስለ ነጻነታችን ምን እየሰራን ነው?እስከመች እንዘናጋለን ? ድር ቢያብር አንበሳ ያስር አንድ እንጨት ብቻውን አይነድም:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬
Minilik Salsawi's photo.

ሕዝብን መሰረት ያደረገ የፖለቲካ ሽኩቻ እውን ኣለ ?? ሕወሓት ብአዴንን ሰጥ ለጥ ያደርገው ይሆን??

ሕዝብን መሰረት ያደረገ የፖለቲካ ሽኩቻ እውን ኣለ ?? ሕወሓት ብአዴንን ሰጥ ለጥ ያደርገው ይሆን?


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ኢሕዴን ቆየት ብሎም ብአዴን ብሎ ራሱን የሚጠራው ድርጅት የፕሮፌሰሩን በመአሕድ ስም መነሳት ተከትሎ ራሱን የአማራው ወኪል ኣድርጎ ቢሾምም ለኣማራ ሕዝብ የፈየደው ኣንዳችን ነገር የለም። ለላኛው ደግሞ ከዱቄት ተሸካሚዎች እነ ከእንጨት ፈላጮች ከነበሩ ምርኮኞች የተመሰረተው ኦሕዴድ የኦሮሞን ወጣቶች ሲያስፈጅ እንጂ ለኦሮሞ ሕዝብ የጥላቻ መዝሙር ከማስጠናት ውጪ ምንም ኣልፈየደለትም። የነዚህ ሁለቱ ፈጠሪ የሆነው ሕወሓት ከሚዲያ ሰበካ ውጪ የክልሎቹን እነ ሕዝቦቹን ኣንጡረ ሃብት በመዝረፍ የኣመራሮቹን ኪስ ሲያደርብ ትርፍራፊዉን ደሞ ነገን በሙስና ስም ሊወነጅላቸው ለሚፈልግ የብኣዴን እነ ኦሕዴድ ኣመራሮች ከነካድሬዎቻቸው ያበላል።
Minilik Salsawi's photo. የጨዋታው ሜዳ ይሁን የኣጥቂዎቹ ሚዛን ያለው እንግዲህ ሕወሓት እጅ ነው።በተነሱ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ዙሪያ ምናልባት የኣንዳንድ ኣመራሮች እና የተወሰኑ ካድሬዎች እጅ ሊኖር ይችላል ይህን ኔትወርክ ደሞ ሕወሓት ትቦውን ብሎ ሊዘጋ ኣያዳግተውም፥ሕወሓት በቅጥረኞቹ ኣማካኝነት መጀመሪያ ከሕዝብ ጎን የተሰለፉ ለማስመሰል የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናትን ስም ያስጠፋል ሮሮ በካድሬዎቹ ያስነዛባቸዋል።ይህ የሚጠቅመው ደግሞ ከታች ያሉ ትንንሾቹን እና ተከታዮቻቸውን ለማጥመድ ይረዳዋል፥፥ በተቃውሞ ውስጥ የትልልቆቹ እጅ እንዳለበት በፕሮፓጋንዳ የሚታለሉ የከፍተኛ ባለስልጣናት የክልል ካድርዎች ፊታቸውን ወደ ሕዝቡ ኣዙረው ሲያጨበጭቡ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ የተቀሰሩ አጆች ትንንሾቹን ለማጥመድ ጊዜ ኣይፈጅባቸውም፥ ይህ ደግሞ ከኦሮሞ ተቃውሞ ላይ በነሙክታር ከድር ኣባዱላ እና ሌሎች ከፍተኛ የኦሕዴድ ባለስልጣናት ላይ የተቀሰሩ እጆች በብዛት ያጠቁት የበታቹን ኣካላት ነው፥ ኣሁንም ሕወሓት ካድርዎቹን በኣማራ ክልል ባለስልጣናት ላይ የቀሰረው የበታቹቹን ለማጥመድ እንዲያመቸው ሲሆን ኣስፈላጊ በሆነ ሰዓት ሁሉ በግምገማ ስም ከፍተኛ ፓለስልጣናት ላይ የስልጣን ፕወዛ ያደርጋል፤በጉዳዩ ዙሪያ በሙስና ስም የሚታሰሩ ቢኖሩ እንኳን በሕወሓት ተመልምለው በጥቅም ተደልለው እንጂ በሕዝብ ተቃውሞ ላይ ተሳትፈው ኣይደለም።
ወደ ብአዴን መለስ ስንልም ጉዳዩ እንዲሁ ከኦሕዴድ ጋር የተቆራኘ ነው፤ባለፈው የኦሮሞ ፕሮቴስት ሕወሓት በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ለመምታት ብ አዴንን በመያዝ ሌሎችን ኣጋሮቹን እንደተጠቀመ ሁሉ ኣሁንም ኦሕዴድን እና ኣጋሮቹን በመያዝ በኣማራ ክልል የተነሳውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት ለመምታት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፥ ሕወሓት በኢሕ አደግ ውስጥ ያሉን ድርጅቶች ኣንዱን ከኣንዱ በ አይነ ቁራኛ እንዲተያዩ ኣድርጎ በደንብ ስለቀረጻቸው መተማመን እንዳይፈጠር ኣድርጓል ይህም የፖለቲካ ሽኩቻዎች እነ የሕዝብ ተቃውሞዎች በተነሱ ቁጥር ሕወሓት በየወገኑ ከጎኑ ለማሰለፍ እየተጠቀመባቸው ይገኛል።
ኣሁን እንግዲህ ከላይ በኣጭሩ የተቀመጠውን ተከትሎ በኢሕ አዴግ ውስጥ ሕዝብን መሰረት ያደረገ የፖለቲካ ሽኩቻ እውን ኣለ ሕወሓት ብአዴንን ሰጥ ለጥ ያደርገው ይሆን ለኔ የማይመስል ነገር ነው በወያኔ ውስጥ የፖለቲካ ሽኩቻ በቀላሉ ማምከን የሚቻልበት ሕወሓታዊ ኣሰራር ኣለ ይህ ኣሰራር ከፍተኛና መካከለኛ ባለስልጣናትን በጥቅም ከመደለልና ከማስፈራራት ኣንስቶ አንከ ፖለቲካ ጥፊ ይከተላል ይህም ሕወሓት በኢሕ አዴግ ውስጥ በዘረጋው የጥላቻ ድርጅትዊ ኣሰራር ከፍተኛ የፖለቲካ የበላይነት አንዲቀዳጅ ስላደረገው የሚከሰቱ ችግሮች ሁሉ ጊዜያዊ ኣጀንዳ ከመሆን ኣያልፉም፥ ሕወሓት ከኢሕ አዴግ ድርጅቶች ውስጥ የሚፈራው ቢኖር የኣማራውን ሲስተም ብቻ ነው ይህ ሲስተም የደቡብ ኣጋር የተባሉ ድርጅቶችን ሊያሳድፍብኝ ኣሊያን እንዲሸራተቱ ሊያደርግ ይችላል የሚል ፍራቻ ስላለው በኣማራው ክልል የፖለቲካ እነ የኢኮኖሚ እድገት ልንዲኖር ኣይፈልግም፤ኣማራው በደህንነት እነ መከላከያ ተቋም ውስጥ ያለው ሚና ከተራ ጉዳዮች እንዲዘል ፍቃደኛ ኣይሆንም፤ ለምሳሌ ከሌላው ብሄር ኣባላት ይልቅ በወታደሩ ክፍል በእዝ ጣቢያዎች ከኣማራ ክልል የሚሄዱ ወታደሮች መረጃ እንዳያገኙ ራዲዮ እንዳይሰሙ ጫና ሲደረግ ግንባር ላይ በፊት መስመር ለፈንጂ ማምከኛና ለጣላት ጥይው ሲያይ የሚሆኑት እነሱ ናቸው፤ኣማሮች።

ወደ ወቅታዊው ሁነታዎች ስንመለስ የኣማራ ተቃውሞ ተከትሎ የሕወሓት ጡንቻ ያረፈው መጅመሪያ በሚዲያዎች ላይ ነው ልክ እንደ ኦሮሞ ተቃውሞ በጋዜተኞች ላይ እርምጃ እንደተወሰደው ኣሁም የኣማራውን ሚዲያ ማሽመድመድ ነው የኣማራ ጋዜጠኞችን እንዳያስር መዘዙ ሌላ እንደሆነ የደረሰበት ሕወሓት ለማስፈራራትና ዝም ለማሰኘት እንዲረዳው ሚዲያውን መምታት ከዚህ በመቀጠል ወደ ግምገማ ይዞራል የኣማራ ክልል ተቃውሞ እንደ ኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ ሁሉ ሕዝባዊ ነው፥ የኣማራው ሕዝብ ከወልቃይት ማንነት ጀምሮ ብዙ ጥያቄዎችን ያነገበ ነው ብ አዴን ይህን የሕዝብ ጥያቄ ተከትሎ ከሕወሓት እንዳያፈነግጥ በጣም ያስፈራል የሚሉ እደምታዎች ኣሉኝ።ሆኖም ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ይቀናጅ ይሆናል ድብልቅ ኣመጽን በሕወሓት ላይ ይፈጥር ይሆናል የሚለው የማይታሰብ ነው።ቀጣዩ የሕወሓት እርምጃ መካከለኛና ዝቅተኛ የብ አዴን ባለስልጣናትን ከነካድሬዎቻቸው መምታት ሲሆን እንደ ኦሕዴድ ባንዴ ሳይሆን በሂደት ይፈጽመዋል፤ በደህንነትና መከላከያ ተቋማት ውስጥ የሚውተረተሩ ኣማሮች ተፈናቅለው ወደ ሲቪል የመንግስት ሰራተኝነት ይዞራሉ፤ከፍተኛ ባለስልጣናትም በሂደት ይፐወዛሉ ኣስፈላጊ ናቸው የተባሉ ደግሞ ግምገማን ተከትሎ በሙስና ይወነጀላሉ የሚወነጀል ካሌለ በገንዘብ የተወሰኑ ካድሬዎች ይገዙናበፊት በር እስር ቤት ገብተው በጀርባ ይወጣሉ። ይህ ነው ያለው ውነት።‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

በሕወሓት የንግድ ድርጅቶች መጠቀም አስጊ ከመሆኑም በላይ ለነገ አስተማማኝ ዋስትና የለውም::

በሕወሓት የንግድ ድርጅቶች መጠቀም አስጊ ከመሆኑም በላይ ለነገ አስተማማኝ ዋስትና የለውም::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎PeopleDisobedient‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎Amharaprotests‬

Minilik Salsawi - mereja.com -እንደ ሰላም ባስ ባሉ የሕወሓት የትራንስፖርት ድርጅቶች ክመጠቀም ሌላ አማራጭ መጠቀም የተሻለ ሆኖ ተገኝቷል:: እንዲሁም በሕወሓት ባንኮች ከመጠቀም በሌሎች ከሕወሓት ነጻ በሆኑ ባንኮች መገልገል ያስፈልጋል:: ሕወሓት በሕዝብ ስለተጠላ በሕወሓት የንግድ ድርጅቶች ላይ ሕዝቡ "የበይ ተመልካች አልሆም በገዛ አገሬ" በማለት እርምጃ ስለሚወስድ አስጊ ስለሆነ ዋስትና ማግኘት እየከበደ መጥቷል::በኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት የንግድ ድርጅቶችን ተከፍተው ገበያውን ከቀረጥ ነጻ በሆነና ግብር ሳይከፍሉ በከፍተኛ ብዝበዛ ላይ የተሰማሩት የሕወሓት የንግድ ድርጅቶችን መጠቀም አስጊ ከመሆኑም በላይ ለነገ አስተማማኝ ዋስትና የለውም የሚሉ የሕዝብ አስተያየቶች በስፋት እየተደመጡ ነው::የሕዝብን የለውጥ ፍላጎት ያማከለ ዘረኝነትን የሚቃወመ ሕዝባዊ ንቅናቄ በመላው ሃገሪቱ እየተቀጣጠለ ሲሆን ይህን ተከትሎ ሕዝቡ በሕወሓት የንግድ ድርጅቶች ላይ የሚወስደው እርምጃ እየጨመረ መጥቷል::ስለዚህም ይህ ሕዝባዊ የተቃውሞ እርምጃ በሕወሓት የንግድ ድርጅቶች ላለመጠቀም የተጣለ ማእቀብ በመሆኑ ለመጠቀም አስጊ መሆኑን ሕዝቡ እየገለጸ ይገኛል::

በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ብትዞሩ አተቃላይ የንግዱን እንቅስቃሴና መሬቶች ተቆጣጥረው ያሉ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የሕወሓት አባላት ናቸው::ሕዝብ በተወለደበት ቀየ ሰርቶ መኖር አልቻለም ወደ ሌላ አከባብዎች እንደ ቀድሞ ተዘዋውሮ እንዳይሰራ በጎሳ ፖለቲካ ተጠፍንጎ የበይ ተመልካች ሆኗል::ስለዚህ ለሕወሓት አባላት እና ለንብረቶቻቸው ምህረት አያደርግም::ሕወሓት ሕዝቡ መንቃቱ በፍጹም ሊገባው አልቻለም:: በሕዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴዎች በኦሮሚያ ክልል እንዲሁም በአማራ ክልል እንደ ሰላም ባስ ያሉ የሕወሓት የንግድ ድርጅቶች ንብረቶች እና በግለሰቦች ስም ሽፋን ሕወሓት የሚያስተዳድራቸው ሆቴሎች የወርቅ ቤቶች በሕዝብ ጥቃት ደርሶባቸዋል::በተጨማሪም በመንግስት ስም የሚንቀሳቀሱ ንብረቶች የጥቃቱ ሰለባ ናቸው::ይህ ሁላ ሕወሓት የፈጠረው የጎሳ ፖለቲካ ውጤት ሲሆን በከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ኢኮኖሚእን ተቆጣጥሮ ሕዝቡን የበይ ተመልካች ለማድረግ ያለመው እቅድ በሕዝቡ እምቢተኝነት ደፍርሶበታል::የተጅመረው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ የሚቀጥል ሲሆን የሕወሓት የንግድ ድርጅቶችንም ማጥቃት ስለሚቀጥል በአገልግሎቱ የሚጠቀሙ አካላት ከፍተኛ ስጋት ስለገባቸው ራሳቸው ከአደጋ እንዲጠብቁ መልእክት ተላልፎላቸዋል::

የሕወሓት የንግድ ድርጅቶች ልክ እንደ መንግስት ስልታን ሁሉ በአንድ ብሄር የተሞሉ ከመሆኑም በላይ ሌላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ የበይ ተመልካች አድርገውታል::ሕዝባዊ ንቅናቄው የሰላም ባስ የሚባለው የሕወሓት የንግድ ድርጅት ከጥቅም ውጪ ስላደረገው ሕዝቡ በዚህ የትራንስፖርት አገልግሎች መጠቀም ስጋት ሆኖበታል እንዲሁም የውጋገን ባንክ አንብሳ ባንክ ሄሎ ካሽ የመሳሰሉ የንግድ ድርጅቶች የሕወሓት ሲሆኑ ከከባባድ ካምፓኒዎች ጀምሮ እስከ ትንንሽ የንግድ ድርጅቶች ድረስ በትግራይ ተወላጅ የሕወሓት አባላት እየተመሩ ሃግሪቷን አራቁተው ሕዝቡን ስላደኽዩ እርምጃ መውሰዱን እንደሚቀጥል ሕዝቡ እየዛተ ይገኛል::ሕዝቡ ተማሯል ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለሕወሓት የጎሳ ፖለቲካ መልስ ይሰጣል::ጥቂቶች ከብረው ሕዝቡ ደህይቶ መኖር መሮታል::ስለዚህ በሕወሓት የንግድ ድርጅቶች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ይቀጥላል::በሕወሓት የንግድ ድርጅቶች መጠቀም አስጊ ከመሆኑም በላይ ለነገ አስተማማኝ ዋስትና የለውም::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬
Minilik Salsawi's photo.

ገመና ሸፋኞች ሆይ:-የተዘራ ይታጨዳል!!! የትግራይ ተወላጆችን ሽፋን አድርጎ ሕወሓትን አትንኩብኝ ነጠላ ዜማ ይቁም !!!

Minilik Salsawi - mereja.com - በግልጽ ለሚገባው ብቻ ማስረዳት ይቻላል::ሕዝቡ እኮ ሁሉን ለይቶ ያውቃል::በላቡ ያፈራውን አብሮ የኖረውን እና በብዝበዛ የከበረውን መጤ ትግሬ በደንብ ያውቃል::አንዳንድ የአረና ትግራይ ፓርቲ ወዳጆቻችንና ከአለና የተለጠፉ አዛኝ ቂቤ አንጓች ጸሃፍያን የትግራይ ሕዝብን እና ሕወሓትን እንዲለዩ እየነገሩን ነው ማን እንደቀላቀለባቸው አላውቅም እንጂ ካሁን በፊት በተደጋጋሚ እንደምንናገረው የትግራይ ሕዝብ እና ሕወሓት ልዩነት አላቸው ከዚህ ጋር በተቆላለፈ ደግሞ የትግራይ ሕዝብን ስሙን መደበቂያ አድርገው ቀሪውን የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያጥቁ የሕወሓት ካድሬዎችና የትግራይ አይሁድን ለመመስረት ( https://www.facebook.com/permalink.php?id=291169534245718&story_fbid=911626555533343 ) ደፋ ቀና የሚሉ የሕወሓት የበላይ አካላት እና ተላላኪዎቻቸው ሲልም ሕወሓት እንዲወድቅ የማይፈልጉ በተቃዋሚ ካባ የሚደሰኩሩ የጊዜ ጀግኖች በተጨማሪም ከየተቃዋሚ ፓርቲ እንደ አረና-መድረክ ተመልምለው በጥሩ ኑሮ ውስጥ የሚርመጠመጡና ቻይና አውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካ ለትምሕርት የተላኩና ተምረው የመጡ የትግራይ ወጣቶች የትግራይ ተወላጆችን ሽፋን አድርገው በጎንደሩ ሕዝባዊ ንቅናቄ ተገን ሕውሓትን አትንኩብኝ የሚል ነጠላ ዜማቸውን እየተነፈሱን ይገኛሉ::
በኦሮሞ ሕዝብ ይሁን አሁን ጎንደር ላይ በተነሳው ህዝባዊ ንቅናቄ ከፍተኛ ጉዳይ የደረሰው የሕወሓት አባላት በያዙት ንብረት እላ የሕወሓት የንግድ ድርጅቶች በሚመሩት ንብረት ላይ መሆኑ በመጀመሪያ የማወቅ ግዴታ አለብን::ሕወሓት የጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍናውን በመላው ኢትዮጵያ ሲረጭ የዘራው የማያጭድ መስሎት አስቦ ቢሆንም ካሁኑ በባሰ ሁነታ የዘራውን እንደሚያጭድ ደጋግሞ ሊያስብበት ይገባል;ከግል ካምፓኒዎች ጀምሮ እስከ መንግስት መስሪያ ቤት በሕወሓት አባላት በወረራ የተያዘው የሕዝብ ስልጣን ንብረት እና መላው አገልግሎት ሌሎች ኢትዮጵያውያንን የመኖርና የመስራት ሕልውና አሳጥቷል::በማንኛውም መስሪያ ቤቶች ለጉዳይ ሲኬድ የሕወሓት አባላት የሕዝብን ስልጣን በቁጥጥር ስር ከማዋላቸውም በላይ የፈደራሉ ቋንቋ ትግሪኛ አስመስለውታል ጎን ለጎንም ዘረፋውን አጧጡፈውታል::በዚህ አጋጣሚ ስለ እዚህ የዘረኝነት መንፈስ የሚሰራ እኩያ ስራ የሚያሳስባቸውና ተጠቃሚ ያልሆኑ የትግራይ ተወላጆችን እንዳሉ ልንገነዘብ ይገባል::የሕወሓት አባላት ተጠቀሙ ዘረፉ ገደሉ ሲባል በስመ ትግሬ ሁሉም የትግራይ ተወላጅ ወንጀለኛ ነው ማለት አይደለም::ሆኖም ሕወሓት በሚነዛው ፕሮፓጋንዳ ራሱ በሕወሓት ሴራ ከኑግ የተገኘ ሰሊጥ አብሮ ተወቅጦ ሊሆን ይችላል::
ሕወሓት ባለፉት 25 አመታት ሲዘርፍ ሲገል ዜጎችን ሲያፈናቅል ሲያሰድድ ብዙሃኑ ድምጹን ሲያሰማ በሃገር ቤት እና በውጪ ሲጮህ አንድም ትንፍሽ ያላሉ ስለ ሌላው ሰብኣዊ መብት የማይታያቸው ዛረእ ላይ በየክልሉ ሕዝቡ ብሶቱ ሲገንጽ በገዛ እትብቱ መቃብር ላይ የፖለቲካ ጠበንጃ ያነገቱ ሕወሓቶች ሲዘርፉ የበይ ተመልካች አልሆንም በማለት ሲነቃነቅ እና ስርኣቱን ሲቃውም የስርኣቱ አሸርጋጆች የሆኑና በስርኣቱ የተጠቀሙ የትግራይ ተወላጅ የሕወሓት አባላት ንብረትን ሲያወድም የሚያሞጠሙጡ ሁሉ ዘረኝነት እንዴት እንደሆነ እያሳዩን ከመሆኑም በላይ የትግራይ ተወላጆች ከላይ እስከታች ዘረፋውን ሲያጧጡፉ ሲገሉ ሲያስሩ እና ሁሉን በሞኖፖል ሶይዙ ስልጣኑን ይዘው ሆዳሞችን ሲገዙ ግን ዘረኝነት አይታያቸውም::እነሱ ሲያደርጉት ዘረኝነት የለም ሌላው ግን የበይ ተመልካች አልሆንም ብሎ ሆ ሲል ዘረኝነት የሚባልበት ምክንያት በፍጹም አይገባንም::
በትግራይ የገባውን ችጋር የፈጠረው ሕወሓት መሆኑ አይካድም::ሕወሓት ከመጀመሪያው አነሳሱ የጸረ አማራ መርሃ ግብር ነድፎ እንደሚንቀሳቀስ ነግሮናል::ጎን ለጎን ታላቋን የትግራይ ሪፑብሊክ ለመመስረት እንደሚሰራም እያሳየን ነው::ለትግራይ ሕዝብ ከፍተኛ ፋብሪካዎች ሲገነቡ ለኦሮሞ ሕዝብ ግን የዘረኝነት እና የጥላቻ ሃእልት ሲቆም የአማእ ሕዝብ ደግሞ በተለያዩ መርዘኛ ከሚካሎችና መድሃኒቶች ይፈጃል::ይህ እንግዲህ የሕወሓት ስራ ነው ሕወሓት የዘራውን ማጨድ የሚጀምርበት ቀን ሩቅ አይደለም::ገና አልተነካም::ሕወሓትን ተገን አድርገው በየክልሉ ባለሃብት የሆኑ ሁሉ የገፈቱ ቀማሽ ናቸው::ይህ ማለት የትግራይ ተወላጆች ይመታሉ ማለት አይደለም::ሕዝቡ እኮ ሁሉን ለይቶ ያውቃል::በላቡ ያፈራውን አብሮ የኖረውን እና በብዝበዛ የከበረውን መጤ በደንብ ያውቃል::ይህ ለሕዝቡ ነጋሪ አያስፈልገውም::ሁላችንም ነጋሪ አያስፈልገንም::በትግራይ ሕዝብ ስም መነገድ እንደማይቻል እነግራቹሃለሁ ከተፈለገ ደግሞ ወሓትን እና የትግራይ ሕዝብን ለይታቹ የምታውቁበት ተጨማሪ ዝርዝር ማስቀመጥ ይቻላል ሕዝቡን አፍኖ የትግራይ ሕዝብና ሕወሓት አንድ ናቸው ማለት ተቀባይነት የለውም::ሕወሓት ከሞተ አንተም ትሞታለህ እየተባለ ለትግራይ ሕዝብ የሚነገረው ፕሮፓጋንዳ ፉርሽ ነው::በየክልሉ የጥቃት ሰለባ የሆኑት የሕወሓት ሰዎች ንብረቶች መሆናቸው ሙሉ በሙሉ የተረጋገጠ ነው::እኔ ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬ አንድ ነገር እላለሁ :- ገመና ሸፋኞች ሆይ:-የተዘራ ይታጨዳል!!! የትግራይ ተወላጆችን ሽፋን አድርጎ ሕወሓትን አትንኩብኝ ነጠላ ዜማ ይቁም !!!

ሰብዓዊነትንና ፍትሕን ከማያውቀው ከሕወሓት ኣገዛዝ የሕግ የበላይነትን መጠበቅ ቅዠት ነው።

ሰብዓዊነትንና ፍትሕን ከማያውቀው ከሕወሓት ኣገዛዝ የሕግ የበላይነትን መጠበቅ ቅዠት ነው።


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በኢትዮጵያ ራሳቸውን የፍትሕ ኣካላት ብለው በሚጠሩ የሕወሓት ታዛዥ እቃዎች የሃብታሙ አያሌውን ጉዳይ ከፍትሕ ውሳኔ ይልቅ በፖለቲካ ገመድ ተብትበውት ይገኛሉ እንዲሁም በተለያዩ እስር ቤቶች የሚገኙ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች በኣደጋ ውስጥ ሆነው ሲገኙ የወያኔ ኣገዛዝ የፖለቲካ ስልጣኑን ለማስጠበቅ ለውጥ በጠየቁ ሃይሎች ላይ የሚሰራው ግፍ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ነው፤የአንድ ሃገር ህግ የህዝብን ትኩሳት እና ጥያቄዎች ይዞ መጓዝ ሲኖርበት በሃገራችን ግን የህግ የበላይነትን የፖለቲካ ትኩሳቶች እያሽመደመዱት እንዳይከበር እና እንዲደፈጠጥ እያደረጉት ይገኛሉ:; አንድ ህዝብ ባላረቀቀው እና ባላጸደቀው ህግ ሲገዛ የህግን ትርጉም እንደማያውቅ ታሳቢ አድርጎ በህዝብ ነጻነት ላይ የሚደረጉ የፖለቲካ ጨዋታዎች እንኳን በበሰለው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ይቅር እና በሌላውም ባልሰለጠነ ህዝብ ላይ ሊተገበር መድፈር ራስን እንደመናቅ ይቆጠራል:: ወያኔ ራሱ አርቅቆ እና አጽድቆ ህጎችን በማውጣት ከፈለገም በመሻር በመቀየር በመገለባበጥ በመተርጎም ህዝቦች የራሳቸውን መብት እና ነጻነት እንዳያገኙ በከፍተኛ ደረጃ መሸራረፎችን እየፈጠረ ነው::

ባለስልጣናት የወንበር ግዝፈታቸውን ተጠቅመው የተለያዩ ውሳኔዎችን ትእዛዞችን ተግባራትን በስልክ በደብዳቤ በቀላጤ ወዘተ የህግን ስርኣት ባልተከተለ መልኩ እያሽከረከሩት ከህግ የበላይነት ላይ በድንፋታና በትእቢት በመጓዝ ላይ ሲሆኑ ይህንን ያየ የበታች ካድሬ እንዲሁ ህግን እና ስራትን ባልትከተለ መንግድ የህዝቦችን ህልውና ገደል ከቶታል:: ከበላይ ባለስልጣናት ባልተናነሰ እንዲሁም በበለጠ ማለት ይቻላል የወያኔ ካድሬዎች እና ተባባሪዎቻቸው በአገሪቱ ላይ ስርኣት አልበኝነት እና ህገወጥነት እንዲሰፍን እየሰሩ ነው::ይህ ደግሞ ህዝብ በስርኣቱ ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ አድርጎታል::

ባለስልጣናት ለህግ እና ለስርኣት ተገዢ አለመሆናቸው ህግና ስርኣት ለእነሱ ተገዢ እንዲሆን ማድረጋቸው ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ነው;: የህግን የበላይነት ማረጋገጥ የተሳነው ስርኣት የወለዳቸው ስብርባሪ ህወሓት መራሽ መንግስታት የህዝቦችን የመኖር መብት ደፍጥጠዋል::በሃገራችን ውስጥ ላለፉት 25 አመታት ተንሰራፍቶ ያለው የአንድ ፓርቲ ህገወጥ አገዛዝ ለህዝቦች ነጻነት የሚከፈለውን መስእዋትነት እንደ መንግስት ሳይከፍል ህዝብን በማሸበር እና በማወናበድ የህግ የበላይነትን ደፍጥጦ ለስልጣኑ ብቻ እየተራወጠ ይገኛል::በሃገሪቱ የህግ የበላይነት የተከበረ ጊዜ ስልታንህ ያበቃል የተባለ ይመስል ከበላይ ባለስልጣናት ጀምሮ እስከ በታች ካድሬዎች ድረስ የህግን የበላይነት ክደዋል::
ከህገመንግስት እንከ ምርጫ ህግ; ከፍርድ ቤቶች ህግ እስከ ዜጎች የመኖር ህልውና አጠቃሎ የተደፈጠጠባት እና መንግስታዊ አሸባሪነት በነጻነት የሚራመድባትን ኢትዮጵያ የመላው ዜጎች አገር በማድርገ እኩልነት ፍትህ እና ሰላም የሰፈነባት አገር እንድትሆን በትግላችን የምናረጋግጥበት ጊዜ ላይ መሆናችንን አውቀን በጋራ ትብብር ተከባብረን እና ተቀናጅተን ወደ መጨረሻው ምእራፍ እንድንደርስ እና የወያኔን አምባገነን ስርአት እንድንቀብር ጥሪዬን አስተላልፋለሁ::እንዲሁም ሃብታሙ ኣያሌው ኣሁን ካለበት የሕመም ስቃይ ወጥቶ ለተሻለ ሕክምና ከሃገር እንዲወጣ ሁላችንም በመረባረብ ሕይወቱን በመታደግ የዜግነት ድርሻችንን ልንወጣ ይገባል። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬
Minilik Salsawi's photo.

ተደጋጋሚው እብደት ፦ ዜጎች በጨለማ እየኖሩ ኤሌክትሪክ ለጎረቤት ኣገር መሸጥ ያሳፍራል። በዜጎች ላይ የሚፈጸመው ሕገወጥ ደባ ነው።

#‎Ethiopia‬ ተደጋጋሚው እብደት ፦ ዜጎች በጨለማ እየኖሩ ኤሌክትሪክ ለጎረቤት ኣገር መሸጥ ያሳፍራል። በዜጎች ላይ የሚፈጸመው ሕገወጥ ደባ ነው። ‪#‎MinilikSalsawi‬
Minilik Salsawi's photo.Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - ከዚህ ቀደም የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የወያኔው ኣገዛዝ ለጎረቤት ኬንያ በስድስት ወር ውስጥ የሸጠው መብራት ሰላሳ ኣምስት ሚሊዮን ብር ሲያተርፍ በሃገር ቤት መብራት ተቋርጦባቸው ስራ ካልሰሩ ፋብሪካዎች ለሃገሪቱ ያስገባሉ ከተባለው ውስጥ ስድሳ ሚሊዮን ብር ብር ኪሳራ ደርሳል። ይህን መመዘን የኣንባቢ ድርሻ ሲሆን ባለፉት ቀናት ኬንያ የቆየው የወያኔ ኣሻንጉሊት ሃማደ ገልፋጩ የኣራት መቶ ሜጋ ዋት ሓይድሮ ፓወር ለኬንያ ለመሸጥ ውል ፈርሞ ኢትዮጵያውያንን በጨለማ በማሳደር የሃሰት ፕሮፓጋንዳውን እየነዛ ጎረቤቶቻችንን ኣድምቆ ለማኖር ቃል ገብቶ ተመልሷል፤ ይህ ኣገዛዝ ለዜጎቹ ደንታ ቢስ መሆኑን የሚያመለክት ሲሆን ከስልጣን እስካልተወገደ ድረስ በፍጹም ለውጥ እንደማያመጣ ከበፊቱ የተረጋገጠ ነው።

ይህ በወያኔ ኣገዛዝ የሚፈጸም ተደጋጋሚ እብደት ዜጎች የሚፈልጉትን የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሳያሟላ ለጎረበት ኣገር መሸጥ ለሕዝብ ያለውን ንቀት ያሳያል።እንዲሁም እንደፈለገ ወደ ኬንያ ምድር እየገባ የሚያፍናቸውን ለኣገዛዙ ተቃዋሚ የሆኑ ዜጎችን የበለጠ ለማፈን ይረዳው ዘንድ የኬንያን ኣገዛዝ ለማለሳለስ ይጠቀምበታል።ይህ የመብራት መሸጥ ጉዳይ በኬንያ ብቻ ሳይሆን ለሱዳን ለጅቡቲ ለሰሜን ሱማሊያ እና እስከ ታንዛንያ የተስፋፋ ነው።በዜጎች ላይ የሚፈጸመው ሕገወጥ ደባ መሆኑ ኣይካድም።

በሃገር ቤት የሚገኙ ፋብሪካዎች በሃይል እጥረት ኪሳራ ላይ ሲወድቁ ሰራተኞቻቸውን ሲቀንሱ ሕዝብ ለድህነት ሲዳረግ የወያኔ ባለስልጣናት የኤሌክትሪክ ሃይል ኀጠው የሚያገኙትን ዶላር ወደየ ግል ኣካውንታቸው ያዘዋውራሉ።ምንሊክ ሳልሳዊየኣፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እና የኣስር ሺዎች ዲፕሎማቶች ከተማ የሆነችው አዲስ ኣበባ በጨለማ ማስዋጥ ኣገዛዙ የሚሰራው ሕገወጥ ተግባር ሽፋን መስጫ ነው። ተማሪዎች ከትምህርት ጥራት በደል በተጨማሪ የኤሌክትሪክ ሃይል እጥረት በፈጠረው ጨለማ ውስጥ ማጥናት ኣሊያም መማር ስለማይችሉ በቂ እውቀት ማካበት እየከበደ መጥቷል። እናቶች በሃይል ማጣት እንዲሁም በማገዶ እጥረት ያቦኩትን ሊጥ ተበላሽቶ እስከመድፋት ሲደርሱ የመንግስት ስራ በደል የባንክ ሲስተምን አበላሽቶ በኪሳራ የምትኖረዋን ኣገር ለኪሳራ ዳርጓል።ይህ ተደጋጋሚው እብደት ፦ ዜጎች በጨለማ እየኖሩ ኤሌክትሪክ ለጎረቤት ኣገር መሸጥ ያሳፍራል። በዜጎች ላይ የሚፈጸመው ሕገወጥ ደባ ነው። የወያኔ ኣገዛዝ እስካልተወገደ ድረስ ዜጎች ሰላም እና እድገት ኣይኖራቸውም።‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

በተናጠል እየሄድንበት ያለው መንገድ አስጊም አደገኛም ሲልም ሊወጡት የማይችሉ አዘቅት ነው::

በተናጠል እየሄድንበት ያለው መንገድ አስጊም አደገኛም ሲልም ሊወጡት የማይችሉ አዘቅት ነው::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EthiopianOppositionparties‬ ‪#‎Change‬ ‪#‎Unity‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) አንድ ነን እያልን ራሳችንን አየሸነገልን አናታለው፤እጅለእጅ ተያይዘን ወያኔን የመጣል ታሪካዊ የትውልድ ግዴታ ኣለብን። ኢትዮጵያዊነት ችሮታ አሊያም ስጦታ ሲልም በደረጃ የሚሰጥ ዜግነት ሳይሆን የእያንዳንዱ ሕዝብ የማንነት መሰረት የተፈጥሮ ማሕተብ እና የውርስ አደራ የታላቅነት ተምሳሌት ነው - ኢትዮጵያዊነት!!! በዚህ ሀገር ፖለቲካ ውስጥ የኢትዮጵያዊነት የደረጃ መዳቢ አድርጎ እራሱን ያስቀመጠው አደገኛ የአመለካከት ቡድን እስከአሁን በመወራጨት ላይ እንዳለ ነው።በአንድነት ሽፋን ዳግም ቅኝ ግዛት የለም::የህዝብን ትግል ለማስጠበቅ የሕዝብን ነጻነት ለማረጋገጥ ሕዝቦችን ያማከለ የጋራ አንድነታችንን ማጠናከር ግድ የሚልበት እና ሃገራዊ/ህዝባዊ ሃላፊነታችንን በመወጣት ወሳኝ ወቅት ላይ መሆናችንን አውቀን የትግል ቃልኪዳናችንን በማጥበቅ ህዝባዊ ድሎችን ማረጋገጥ ሃገራዊ ግዴታችን እንደሆነ ልንገነዘብ ይገባል::
እውነትን እና ስልጡን ፖለቲካን ቢተናነቀንም እንደምንም ልንውጠው ግድ ይላል::ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል ነው::እየሄድንበት ያለው መንገድ አስጊም አደገኛም ሲልም ሊወጡት የማይችሉ አዘቅት ነው::በፈረንጅ አገር ወያኔ በግልጽም ይሁን በተዘዋዋሪ የላካቸው ባለስኮላርሺፖች አዛኝ ቂቤ አንጓች የአንድነት ሃይል መስለው ሰርገው በመግባት እየሰሩ ያለው ስራ እጅግ ያሳዝናል::ከመወራጨት ውጪ ከነአጨብጫቢዎቻቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ እንደማያመጡና የለውጥ እንቅፋት እንደሆኑ ልንነግራቸው ይገባል::የሚዲያ ተቋማት እና የድህረገጽ ውጤቶች ሕዝብን በማስተማር ሕዝብን መብቱን እና ነጻነቱን አውቆ ለሌላው እንዲያስተምር በማድረግ ረገድ አስፈላጊውን ወቅታዊ መረጃ እና መነሳሳትን በማስረጽ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል።
ያለፉ እና የከሰሙ ወሬዎችን እና አሉባልታዎችን ከመርጨት የወያኔ የፈጠራ አደናባሪ እና አዘናጊ አጀንዳዎችን እኝኝ በማለት ከማውራት ብሄር ተኮር ክፋፋይ ሃሳቦችን ከማርከፍከፍ አዛኝ መሳይ መርዝ ሃሳቦችን ከመናገር ተቆጥበን ሕዝቡን ስለመብቱ እና ነጻነቱን በማስተማር ረገድ መትጋት ከተያዘ ለውጥ የማይመጣበት ምንም ምክንያት የለም። ትችትን እና ሂስን ላለመዋጥ እውነትን ላለመቀበል የሚደረጉ ሩጫዎች ታጥቦ ጭቃ እንጂ የትም እንደማያደርሱ እንዲሁም ፓርቲዎችን እና ሰዎችን መፈረጅ እና መወንጀል ሃሳቦችን ማጣጣል ምንም ለውጥ እንደማያመጣ ካለፈው ተምረናል ። ያሳልፍነው የትግል ሂደት ከጭብጨባ እና ስብሰባ ያለፈ ፋይዳ እንዳሌለው ተገንዝበን የወሬ እና ሆይሆይ ትግል ስለማያዋጣ ጥንካሬን እና ለውጥን የምናመጣበትን የትግል ስልት በመመካከር እና በመወያየት ሃሳብን በማቻቻል መረጃ በመለዋወጥ ሃገራዊ የጋራ አጀንዳ ሊኖረን ይገባል እላለሁ።ልዩነትን በማቻቻል በጋራ መታገል ችላ የማይባል ሃገራዊ አጀንዳ ነው። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

በምርምርና በዳበረ ሃሳብ ሽፋን የሕወሓት ስልጣን እድሜ ማስረዘሚያ እና የትኩሳት መለኪያው 'ጀኔራል?' ጆቤ

በምርምርና በዳበረ ሃሳብ ሽፋን የሕወሓት ስልጣን እድሜ ማስረዘሚያ እና የትኩሳት መለኪያው 'ጀኔራል?' ጆቤ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎TPLF‬ ‪#‎Jobe‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Change‬
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ጆቤ በአሁኑ ወቅት ይዘውት እየተራመዱት የሚገኘው አስተሳሰብ ሕወሓትም በማዘናጊያ አጀንዳነት እያራገባቸው ነው::ወደ ሚዲያው እንዲወጡ የተደረገው የቀድሞ የወያኔ አየር ሃይል አዛዥ ከተንበርካኪው ቡድን ወገን እንደሆኑ የሚነገርላቸው ታጋይ አበበ ተክለሃይማኖት በሽምቅ ተዋጊነት የጄኔራልነት ማእረግ አግኝተው አየር ሃይል እንደ ፋንታ በላይ ባይመሩትም ገለውት ነበር::ሰሞኑን በወያኔ መንግስት እየተደጎሙ በሚኖሩት አዲስ አድማስ እና ሪፖርተር ጋዜጣ እዩኝ እዩኝ ያበዙት አበበ ተክለሃይማኖት አንድም ትኩሳት መለኪያ ሌላም ሕወሓት እድሜዋ እንዲረዝም እንደ መሽረፈት ሲሆኑ ጎን ለጎን ወደ ስልጣ እየተጠጋጉ መሆኑን ጽሁፎቻቸው ያሳብቃሉ::ሕወሓት በስልጣን እንዲቆይ ካላቸው ፍላጎት የተነሳ የተሻለ አምባገነንነት እንዲፈጠር እየሰሩ ሲሆን የትግል አጋሮቻቸውን የተቹ መምሰሉ የሕወሓት የማዘናጊያ እና የማደናበሪያ አንዱ ስትራተጂ መሆኑን ልንነቃ ይገባል::
Minilik Salsawi's photo.
በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በአዲስ አድማስ እንዲተነፍሱ የተደረጉት ጆቤ በሶማሊያ የሞቱ የኢትዮጵያ ወታደሮችን በተመለከተ የክብር መቃብር ጥያቄን አስመልክቶ በሰጡት መልስ ላይ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት እያለ ራሱን የሚጠራው ጦር የሚተዳደረው በሽምቅ ተዋጊነት መመሪያ ደንብ በሆነ በጫካ ሕግ መሆኑና ወታደራዊ ሳይንስ ቀመስ ሆኖ ለሀገር የተገነባ ሰራዊት ባለመኖሩ የሞቱ ወታደሮች እንደ ሽምቅ ተዋጊ ወንበዴ ክብረቢስ ሆነው በሜዳ እንዲጣሉ እና ማስታወሻ እንዳይኖራቸው መደርጉ ከትጥቅ ትግል ጋር ተያይዞ የመጣ ልምድ እደሆነ ነግረውናል::የወታደራዊ ሳይንስ ስላለእላቸው የአንድ ሃገር ሰራዊት እና የሽምቅ ተዋጊ ወንበዴዎች ሰራዊት ልዩነቱን እንዳያውቁ እያወቁ ወንጀል በመስራት ላይ ናቸው::ጆቤ ከስልጣን ባይባረሩ ኖሮ የዚህ የግፍ አመራር አንዱ አካል እንደሚሆኑም መዘንጋት የለብንም ከመጀመሪያም በቦታው ላይ በነበሩ ሰአት ወታደራዊ ሳይንስን ሳይሆን ውንብድናን በሰራዊቱና ደህንነቱ ውስጥ ሲያሰራጩ እንደነበር ባይዘነጋም በአሁኑ ወቅት ይዘውት እየተራመዱት የሚገኘው አስተሳሰብ ሕወሓትም በማዘናጊያ አጀንዳነት እያራገባቸው ነው::
ጆበ ስለ አሰብ ጉዳይ ዘግይተው እንደነቁ ሊነግሩን ይፈልጋሉ::በሻእቢያ እና ወያኔ መካከል ውጥረት መኖሩን ተከትሎ የወያኔ ካድሬዎች መከላከያ ሰራዊያችን አሰብን ማስመለስ አለበት ብለው ሲደነፉ እንደነበረው ሁሉ የጆቤም አስተሳሰብ ይህ ነው::ጆቤ እንዲያጦዙት በሩ ተከፍቶላቸው የሕወሓትን የማዘናጊያ የአሰብ ወደብ አጀንዳ አራግበውታል::ስለ አሰብ የባነንኩት ዘግይቼ ነው ቢሉም እነዶክተር ያቆብ በተናገሩበት ወቅት ለምን ሰከን ብሎ የማሰብ እድሉን ለራሳቸው እንዳልሰጡት ግን አልነገሩንም:: የአስተሳሰብ መቀየር መዳበር መብሰል እንደተጠበቀ ሆኖ ስለ አሰብ የሚያነሱ ግለሰቦችን ወደ እስር ከሚልኩ ሰዎች ጆበእ አንዱ የነበሩ ሲሆን ዛሬኤ ላይ ከአባት ፓርቲያቸው ሕወሓት ካድሬዎች ጋር ሆነው ራሳቸው ፈርመው ያስረከቡትን አሰብን እየተመኙ ይገኛሉ::ምንሊክ ሳልሳዊ
ሕወሓት በመድበለ ፓርቲ ሲስተም ውስጥ መግባት ስለማይችል እና የ97 አይነት ሽንፈት እንደሚከናነብ ስለሚያውቁ ሕወሓትን እየደከመ የሚገኘውን እስትንፋሱን ለመቀጠል በሚደረገው ሩጫ ውስጥ ተሳታፊ የሆኑት አበበ ተክለሃይማኖት ያለምክንያት በዚህ ቀውጢ ሰአት ላይ የሕወሓት እምባ ጠባቂ የፖለቲካ ተንታኝ ሆነው እያላዘኑ ይገኛሉ::ታጋይ አበበ የሚነግሩን ነገር እና ያስተላለፉት መልእክት ሁሉ የምናውቀው እና ድምጻችንን እያሰማን እየታገልንለት የምንገኘው ጉዳይ ነው ምንም አዲስ ነገር አልነገሩንም::ለሕዝብ ልጆች ሲባል ሕወሓት ስልጣኑን ይልቀቅ ቢሉ አሊያም ሁሉን አቀፍ የሽግግር መንግስት ይቋቋም ቢሉ የተሻለ አማራጭ ነበር::ይህንን አላሉም ሕገመንግስቱ በተግባር ላይ ይዋል ማለት በሌላ አነጋገር የወያኔ የፖለቲካ ፕሮግራም በተሻለ አምባገነናዊ ዘዴ ይከሰት ማለት ነው::መጀመሪያ ሕገመንግስቱ በኢሕ አዴግ እና አባሎቹ ተረቆ የጸደቀ የፖለቲካ ፕሮግራም ግልባጭ እንጂ ሕዝብ የወከላቸው ልጆቹ ያጸደቁት ሕገመንግስት ስላልሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ምም የፈየደው ነገር የለም::
ኤርትራ እና ኤርትራ ውስጥ ያሉትን ኢትዮጵያውያን ታጋዮች እደ እርኩስ መንፈስ አይቶ እንዲደመሰሱ መመኘት ሌላኛው የታጋይ አበበ እብደት ነው::ለኤርትራ ጉዳይ ተጠያቂው ሕወሓትና ሕወሓት ብቻ ነው::ከተጠያቂዎቹም አንዱ ራሳቸው ታጋይ አበበ ናቸው::ኤርትራ ሉእላዊ መንግስት ናት ብለው ለተመድ ፈርመው ያመኑ ራሳቸው ሕወሓቶች ናቸው::እስኪ ፈርመው ባመኑበት እጃቸው ቃታ ስበው የኢሳያስን መንግስት ያውርዱና ይሞክሩ::ጉራ ብቻ ፋይዳ የለውም በደቂቃዎች ውስጥ መጥፊያቸው መሆኑን ያውቁታል::ኢሳያስ በሃይል ይውረድ የምትለው የ2016 የሕወሓት የማዘናጊያ ዜማ መሆኗን ራሳቸው ተንቅቀው እያወቁ ትኩሳት ለመለካት መሮጥ ራሳቸውን ለትኩሳት ዳርጓቸውል::
ሌላው ክዚህ ጋር የሚያያዘው በኤርትራ ያሉት ኢዮጵያውያን ታጋዮች ሲሆኑ ወደ ትጥቅ ትግሉ የሄዱት በወያነእ ተገፍተው የነጻነት ምሕዳር የለውጥ ጥያቄ የፖለቲካ ምሕዳሮች ስሌተዘጋጉ በሰላማዊ መንገድ መታገል ስላልቻሉ ነው::መፍትሄውን ክመሻት በጋራ እንደ ኢትዮጵያዊ አቀራርቦ የፖለቲካ መስመር ከማሲያዝ ይልቅ ኤርትራን በአፍራሽነት መፈረጅ በኤርትራ የሚገኙ ሃገር ወዳዶችን ከመዝለፍ አይለይም::ሌሎች በሃገራቸው ጉዳይ አያገባቸውም አይነት አመለካከት ጋር እየተላተሙ የሚገኙት ታጋይ አበበ ሊያውቁት የሚገባው ወያኔ ስልጣኑን ለሕዝብ እስካላስረከበ ድረስ እንዲሁም በጫካ ሕግ ሕዝብም ማአስተዳደር እስካላቆመ ድረስ ትግሉ እየቀጠለ ይሄዳል::የወያነ አምባገነንነት ሕዝቡን አንድ እያደረገው እንጂ እየለያየው አይሄድም ማለያየት ባለፉት 25 አመታት በወያኔ ተሞክሮ አልተሳካለትm ታጋይ አበበ የሕወሓቱ ጄኔራት ልፋታቸው በዳበረ ሃሳብ ሽፋን የሕወሓትን እስትንፋስ ለማስቀጠል እና የፖለቲካ ጥኩሳቱን ለመለካት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች አንዱ የስትራቴጂ መንገድ መሆኑን ሁላችንም እንረዳዋለን::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

በኢትዮጵያ የተደረገው ጸረ - ኢሳያስ ኣፍወርቂ ሰልፍና የወያኔ ሚና

በኢትዮጵያ የተደረገው ጸረ - ኢሳያስ ኣፍወርቂ ሰልፍና የወያኔ ሚና
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Eritrea‬ ‪#‎EritreanRefugees‬ ‪#‎TPLF‬ ‪#‎demonstration‬ ‪#‎MinilikSalssawi‬
Minilik Salsawi's photo.Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) :- ጸረ - ኢሳያስ ኣፍወርቂ ሰልፍ በኣዲስ ኣበባ ሲደረግ ይህ የመጀመሪያው ኣይደለም በወያኔ ኣቀነባባሪነት አና መሪነት ብሎም ኣጃቢነት የተለያዩ ሰልፎች እና ስብሰባዎች ተስተናግደዋል፤ ወያኔ ስልጣኔን ያስረዝሙልኛል ያላቸውን ጉድጓዶች ሁሉ በመቆፈር ላይ ባለበት በዚህ ኣጣብቂኝ ወቅት ላይ የተባበሩት መንግስታትን የሰብዓዊ መብት ሪፖርት ተከትሎ ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት በ ኤርትራ ላይ አየደነፋ ከመገኘቱም በላይ ለኢትዮጵያውያን በገዛ ኣገራቸው የተከለከሉትን ሰልፍ በ ኤርትራውያን ሽፋን ለፖለቲካ ፍጆታው እየሮጠ ሲገኝ ይህን ጸረ ኢሳያስ ሰልፍ ተቃዋሚዎች ቢያዘጋጁት ኖሮ ግን ኣዲስ ኣበባ በጥይት ታምሳ ትደፈረስ ነበር ።

Minilik Salsawi's photo.


ወያኔ ለ ኤርትራ ሕዝብ እና በስደት ለሚኖረው ያዘነ በመምሰል ጸረ ኢሳያስ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ በመርጨት በኣንድ ጎኑ ደግሞ ኤርትራውያን ወደ ሶስተኛ ኣገር የሚሸጋገሩበትን የጉዞ ሰነድ ስምና ፎቶ እየቀየረ የራሱን ሰላዮች የሆኑ ትግሪኛ ተናጋሪዎችን ወደ አውሮፓና ኣሜሪካ በመላክ እያጭበረበረ ይገኛል። ኣመድ በዱቄት ይስቃል እንደሚባለው የኢትዮጵያ ኣምባገነኖች የኢሳያስን ኣምባገነንነት ሲያማርሩ ይውላሉ።የራሷ አያረረባት የሰው ታማስላለች አንደሚባለው የወያኔ ባለስልጣናት የኢትዮጵያውያን የመኖር ሕልውናና ነጻነት ገፈው ስለ ዐርትራ እና ሱማሊያ ሕዝብ ጭቆና ሲደሰኩሩ ይውላሉ። መጃመሪያ ሰልፉን ያዘጋጀው ወያኔ ሲሆን በሰልፉ ላይ ኣብዛኛው ተሳታፊዎች የ ኤርትራ ባንዲራ ያነገቡ የሕወሓት ሰዎች መሆናቸው ኣደባባይ ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ነው።ወያኔ ከፊት ኤርትራውያንን ስደተኞች ለፎቶ በማስቀደም የፖለቲካ ፍጆታውን ሲሰራ ውሏል። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

ደርግነት እያቆጠቆጠ – ዴሞክራሲው እየጨላለመ ነው – ህዝቦች ጠንቀቅ በሉ! (ሜ/ጄ አበበ ተክለሃይማኖት)

መግቢያ
የሃገራችን መንግስትና የገዢው ፓርቲ አጠቃላይ ችግር ዉስጥ በመግባታቸው ምክንያት እዚህና እዝያ እሚታዩ ችግሮች እየተስተዋሉ ነው። ሰሞኑን እንዃ ብናይ ከኦሮሞ ህዝባዉ ዓመፅ፣ ሜቴክና ስዃር ፋብሪካ፣ ከጋምቤላ ጠለፋና ግድያ፣ በኤርትራ በኩል የሚመጣ ተከታታይነት ያለው ዜጎቻችንን የማበሳበስ ሁኔታ እያስተዋልን ነው። የድርቁና በየክልሉ የሚታዩ የህዝቦች መነሳሳት ተጠቓሽ ናቸው። እነዚህ የሚፈጠሩ ነገሮች ካጠቃላይ ሕገ መንግስታዊ ማእቀፉና ከህዝቦች ፍላጎት አንፃር ማየት አለብን።
አንድ ጏደኛየ “ህወሓት የለችም ማለት የትግራይ ህዝብ የለም ማለት ነው፤ ስለዚ ህወሓት ማለት ህዝብ ነው፤ ኢህአዴግ ማለት ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ማለት ነው” ማለት ምን ማለት ነው ብሎ ጠየቀኝ። እኔም እንዲህ ብሎ ነገር የለም ከየት አመጣሀው አልኩት፤ እሱም የሃገራችን ኢታማዦር ሹሙ ናቸው የተናገሩት አለኝ በትግርኛ የግንቦት ሃያ ስብሰባ ላይ መቐለ ከተማ የተናገሩት ብሎ ሊንኩን ሰጠኝ:: ቪድዮው የ ሶስት ሰዓትና ሃያ ሁለት ደቂቃ ርዝመት ያለው ስለሆነ፤ ይህንን ሁሉ ለማየት ግዜም ፋላጎትም ላይኖራቹህ ስለሚችል ከ2ሰዓት እና 23 ደቒቃ ( 2:23)ጀምራቹህ እንድትመለከቱት እጋብዛለሁ።
ባለፈው ፁሁፌ እንደገለፅኩት የወታደራዊ ክፍሉ ጡንቻ እየፈረጠመ የመሄዱ አዝማምያ ያሰጋኝ እንደነበር ገልጬ ነበር። ይህንን ቪድዮ ሳየው ግን ወታደራዊ ታልቃ ገብነቱ ከምገምተው እና ከጠበቅኩት ፍጥነት በላይ ሆኖ ሳገኘው ደርግነት ተመልሶ እየመጣ ይሆን እንዴ? ብየ ለመጠየቅ ተገደድኩ።የዴሞክራሲ እጥረት ወይም ምህዳር መጥበብ ማለት ደርግነት መንገስ ማለት ነው፤ ሱፍም ወታደራዊ ልብስም ሊለብስ ይችላል።
Photo - Major General Abebe Teklehaimanot
Photo – Major General Abebe Teklehaimanot
ደርግነት ምንድን ነው?
ደርግነት ወታደራዊ ክፍሉ ፖለቲካዊ አመራር ከኔ በላይ የሚችለው የለም ብሎ ስልጣን መቆናጠጥ ነው። ደርግነት ሁሉም ዴሞክራስያዊ መብቶች በሃይል ለማፈን የሚደረግ አስተሳሰብ እና ድርጊት ነው። ደርግነት የኢትዮጵያ ህዝቦች አንገዛም ማለት ሲጀምሩና ፖለቲካዊ አመራሩ መምራት ሲያቅተው ወታደራዊ ክፍሉ ድሮስ ከኔ በላይ ማን አለ በሚል ትዕቢት ጠብመንጃ ቤተ መንግስትን ሲቆጣጠር ነው። ደርግነት ሲጀምር “የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ ምርጥ ልጆቹ እንደተሰበሰቡ”  ለማሳየት እንቅስቃሴ ማድረግ ነው። ደርግነት የ “አንድ ህዝብ፣  አንድ ፓርቲ፣ አንድ መሪ”  የሚሰብክ ፀረ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብና ተግባር ነው።
ደርግነት አንድ ህዝብ፣ አንድ መንግስት (One State)፣ አንድ መሪ (führer) የሚለዉን የናዚ አስተሳሰብ ተቀጥያ ነው። በኢትዮጵያም አንድ ህዝብ፣ አንድ ፓርቲ (ኢሰፓ) አንድ መሪ (መንግስቱ ሃይለ ማርያም) እንደ ማለት ነው።  በዘመናችን ደግሞ የኤርትራው ዲክቴተር እንደሚሉት “አንድ ህዝብ፣ አንድ ልብ፣ የራሳቸው አንድ የፖለቲካ ድርጅት፣ ራሳቸው ብቸኛና አንድ መሪ”፤ ከዚህ ዉጪ ያለ መሪም ሆነ ድርጅት የኤርትራ ጠላት አድርጎ የመመልከት አስተሳሰብ ነው ደርግነት። ደርግነት አለመተማመን ነው፤ አንዱ ሌላዉን የሚያሸማቅቅበት ሰርዓት ነው። ፕሬዝዳንት መንግስቱ ሃይለማርያም ቢሆኑም በመፈንቅለ መንግስት ስልጣናቸው እንዳይወሰድባቸው ተሸማቅቀው የሚሮሩበት ነው። ደርግነት ኔትዎርኪንግ ነው፤ መጠላለፍ ነው።
የፈለገ ዓይነት ችግር ቢመጣ “ያው አፍሪካዉያን ስለሆንን በወታደር እንፈታዋለን” የሚል አስተሳሰብ የደርግነት ሀሁ ነው።ፖለቲካዊ መፍትሄ የማይታየው፣ ጭንቀት የፈጠረው ገር አስተሳሰብ ወይም ሁን ተብሎ ጠባብ ጥቅምን ለማስጠበቅ የሚሰነዘር ሃሳብ ነው።ህዝብን በጉልበት እንደሚነዳ እንስሳ የሚቆጥር ኃላ ቀር አስተሳሰብ ነው። ለመጨቆን የሚደረግ መንገድ ጠረጋ ነው። ለአፈና የሚደረግ መንደርደር ነው፤ ባጭሩ የደርግነት መነሻ ነው። የኣፍሪካዊ ሰው ሰብኣዊ እኩልነት አለማመን ነው፤ የቀኝ ገዢ አስተሳሰብ ነው። አይደለምና በደሙ ደርግነትን ያሸነፉት ለኢትዮጵያ ህዝቦች ለማነኛዉም የሰዉ ፍጡር በወታደር የሚሽከረከር ሃገር ኣልመኝም፤ ምክንያቱም ሕገ መንግስታዊና ዴሞክራስያዊ ስርዓት ለመገንባት እከል ስለሚሆን። ለራሳቹህ ጠባብ ጥቅም ለመጠበቅ ስትሉ  “ኢትዮጵያዉያንን በጉልበት ነው መግዛት” እያላቹህ ወታደራዊነት እምታቀነቅኑ ፀረ ሕዝብና ፀረ ዴሞክራሲ መሆናቹህን መገንዘብ አለባቹህ፤ የኢትዮጵያ ህዝቦች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪል ማህበረሰቡ ይህንን ክፉና አደገኛ አስተሳሰብ በንጭጩ ለመቅጨት መታገል አለበት።
ደርግነት ተሻንፊነት ነው። ደርግ በጥቁር አፍሪካ አለ የሚባል ስመ ገናና ጦር ይዞ፣ በክፍተኛ ደረጃ የሰለጠኑ መኮንኖች አስልፎ፣ የራሽያ ሙሉ ድጋፍ እየተቸረው በኢትዮጵያ ህዝቦች ፊት ግን ተሸናፊ ሃይል ከመሆን አልዳነም። ለምን ቢባል የፈለገ ወታደራዊ አቅም ቢያዝ ፖለቲካዊ ምክንያት እና ሰልፍ ነው የሚያሸንፈው፤ የደርግ ጠብመንጃም በፍትሕ ፈላጊ ኢትዮጵያዉያን ፖለቲካ ተደመሰሰ። ደርግነት ፀረ ህዝብነት ነው፤ የንቀት እና የማንቛሸሽ ስርዓት ነው።
ውቅታዊ የኢትዮጵያ ፖለቲካና ደርግነት
የኢትዮጵያ ህዝቦች ከህግ ዉጪ አንገዛም ማለት ጀምረዋል። የኦሮሞ ህዝቦች ዴሞክራስያዊ እንቅስቃሴ፣ የቅማንት ህዝቦች ዴሞክራስያዊ ትግል፣ በትግራይ ደግሞ እንደ እምባሰነይቲ ዓይነት ዴሞክራስያዊ እንቅስቃሴ፣ የኮንሶ ህዝቦች ዴሞክራስያዊ ጥያቄን እንደ ምሳሌ ሊወሰዱ ይችላሉ። ገዢው ፓርቲ ቆሟል ወይም ወደ ኃላ እየነጎደ ነው፤ ባጭሩ ጥልቕ ፖለቲካዊ ችግር (political crisis) አለ። ሆኖም ይህንን ችግር መፈታት ያለበት ህገ መንግስታዊ በሆነ መንገድ እንጂ ከዛ ዉጪ በሆነ መንገዶች መሆን የለበትም።
ኢህአዴግ ዉስጣዊ ቐዉስ አጋጥሞታል፤ ወታደራዊ ክፍሉ የአመራር ክፍተትን ለሞሙላት ምን እያደረገ ነው? የሚለው ማየት ተገቢ ነው። በተለያዩ መጣጥፎቼ የዴሞክራሲ እጥረት (democratic deficiency) በሚኖርበት ሁኔታ ሕገ መንግስታዊ ተቛሞች ልፍስፍስ በሚሆኑበት ግዜ ባለጠመንጃው ሁለት ሶስት ግዜ ማስብ ይጀምራል ብየ ነበር፤ የተወሰኑ ምልክቶችም ጠቁሜ ነበር። እንደኛ ባሉ በሽግግር ላይ በሚገኙ ማህበረሰቦች፤ የዴሞክራሲና ሕገ መንግስታዊ ተቛሞች ተገቢ ስራቸዉን መስራት አለመቻላቸው ለጉልበተኛ አካል እድል መስጠታቸው ያገራችን ህልዉናና የህዝቦችን ዋስትና ሲፈታተን ይታያል። ከዚህ አንፃር አሁን ማየት የምፈልገው ወታደራዊ ክፍሉ እያሳየ ስላለው የፖለቲካዊ ፍላጎት ጭላንጭል ነው።
ፖለቲካዊ ሚና የማይኖረው ሕገ መንግስታዊ ተልእኮዉን ብቻ የሚወጣ የመከላከያ ሃይል ለመገንባት የኢትዮጵያ ህዝቦች ከፍተኛ መስዋእትነት ክፍለዋል። የሲቪሉን አስተዳደር ህዝባዊ ስልጣን አክብሮና ለሕገ መንግስቱ ተገዢ ሆኖ ግዴታዉን የሚፈፅም፣ አገሩን በብቃት የሚከላከል፣ ጥቃትን የሚያስቀር ወይም በቂ ምላሽ መስጠት የሚችል ሃይል ሆኖ መገኘት ነው መሰረታዊ ተልእኮው። አሁን ግን በከፍተኛ አመራሮቹ እየታየ ያለው ነገር አንዳንድ ስጋቶችን እየጫረ ይገኛል።
የመቐለው ፓናል
በቅርቡ ኢታማዦር ሹሙ ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ግንቦት ሃያን አስመልክተው በመቐለ ከተማ ያካሄዱት ዉይይት ላይ ያነስዋቸው ሃሳቦችና እና የተናገርዋቸው ነገሮች በጣም እሚያሳዝኑና ሕገ መንግስቱን ገድል ግባ ያሉበት መድረክ ነበር። ከ ሀ እስከ ፐ  ስለ ሲቪል አስተዳደሩ ድክመት፣ ልፍስፍስነት፣ ስለ ወታደራዊ ክፍሉ የመተካካት ልዩ ችሎታና ስለ ሰራዊቱ የአሁንና የወደፊት ጥንካሬ ሲያወሩ ላየ ጄኔራሉ ምን እያለ እንደሆነ ይገባዋል ወይ? የሚል ጥያቄ ያጭራል። “ፖለቲካዊ አመራሩ እንጂ ወታደራዊ ክፍሉ ጤነኛ ነው” እሚል መልእክት አደገኛ አካሄድ ነው፤ እኔ ልምራ አይነት አንደምታ ያለው ንግ ግር ነው። የሲቪል መንግስት በወታደራዊ ክፍሉ የሚገመገምበት አሰራርም ሆነ ሕገ መንግስታዊ መርህ ወይም ድንጋጌ የለም። ሲቪል አስተዳደሩ ወታደሩን ሊቆጣጠር ሲገባው በተገላቢጦሽ ወታደራዊ ክፍሉ ሲቪሉን አትረባም፣ ሞተሃል፣ አመራር አታዉቅም እያለው ነው።
ሲጀመር ስብሰባው ምን አላማ ታሳቢ አድርጎ በማን ለምን እንደተዘጋጀ መጠየቅ አለበት። እዉነት የግንቦት ሃያ መንፈስ ለማስረፅ ነው የተዘጋጀው? የግንቦት ሃያ መንፈስ ሕገ መንግስታዊ መርሆችና ድንጋጌዎች እየተጣሰ ነው እንዴ እሚከበረው? ሕገ መንግስቱን በግላጭ እየደረመሱ ግንቦት ሃያን ማክበር ብሎ ነገር አለ እንዴ? በዶከተር ዛይድ አወያይነት የተጀመረው የሁለቱ ንግግር ከ 1967ዓ.ም እስከ 1983 ዓ.ም የነበረዉን ፖለቲካዊና ወታሃደራዊ ሁኔታ በዝርዝር አስቀምጠዋል። አሁን ስላለው ፖለቲካዊን ችግሮች ሁለቱም ለየቅልና ተቃራኒ ሓሳቦች አስቀመጡ፤ ኢታማዦር ሹሙ በዚህ ጉዳይ መግባት ባይኖራቸዉም።
አቶ ኣባይ ፀሃየ አሁን ያሉት ፖለቲካዊ ችግሮች የዴሞክራሲ እጦት፣ የሙስና መስፋፋት እና የበላይ አመራሩ እርስበርሱ አለመታገል (አድርባይነት) ነው አሉ። መፍትሔዉም ዴሞክራሲን ማስፋፋት እና በዚህ እና በመልካም አስተዳደር ያሉትን ችግሮች የበላይ አመራሩ ያለ ማቅማማት መታገል ነው አሉ። ጄኔራል ሳሞራ ደግሞ የችግሮቹ ምንጭ ኪራይ ሰብሳቢነትና ዕድገት ነው አሉ። መፍትሔ ሲጠቁሙ ደግሞ አቶ ኣባይ ያሉትን በመፃረር ወይም የኣቶ አባይ መነሻ ሃሳብና መፍትሔ ገሸሽ በማድረግ ላይኛዉ አመራር ፕሮጀክት መምራት እና በቴሌቭዥን መታየት ስራው በማድረግ በቦታው አለመገኘቱ ነው አሉ። የፖሊሲ፣ የመመርያ፣ የአሰራር ችግሮች ዋነኞቹ ችግሮች ናቸው በሚል ያለዉን ፀረዴሞክራሲ አስተሳሰብ ለማድበስበስ ሲፈላሰፉ ታይቷል።
አመራር ማለት ፕሮጀክቶች መምራት እና በቴሌቭዢን መታየት አይደለም ብለዋል ጄኔራሉ፤ ማንን ለመምታት ይሆን? የሚለው መጠየቅ ተገቢ ነው። ሲጠቃለል የኢህአዴግ መንግስት ችግር አቶ ኣባይ ፀሃየ እንዳስቀመጡት ነው ወይስ ጄኔራሉ እንዳሉት? የአቶ አባይ ፀሃየ ፖለቲካዊ ግምገማ በጄኔራሉ ሲቪል አስተዳደሩን የማንቛሸሽ ንግግር ታጅቦ የቀረበበት ፖለቲካዊ ምክንያት ምንድን ነው? ማን ምን ቢፈልግ ነው እንዲህ አይነት ዘመቻ የተጀመረው? የሚል ጥያቄ የሚያስነሳ ነገር ነው እየታየ ያለው።
ከሁሉም በላይ የሰቀጠጠኝ ነገር ግን ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ ባጠቃላይ ስለ ትግራይ ህዝብ ደግሞ በዋናነት ያሉት ነገር ነው። ለሳቸው የትግራይ ህዝብ ማለት ህወሓት ነው፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ማለት ደግሞ ኢህአዴግ ነው። ህወሓት/ኢህወዴግ የለም ይባላል እርስዋስ ምን ይላሉ ተብለው ሳይተየቁ በራሳቸው አነሳሽነት የሃገር ኢታማዦር ሹም ምን እንዳለ ላካፍላቹህና አሉና “አንዳንድ ሰዎች ህወሓት የለም ይላሉ ፤ እንዲህ እሚሉት ሰዎች ራሳቸው ላይኖሩ ይችላሉ። ለኔ ህወሓት ማለት መስመር ነው፣ ህወሓት ማለት ህዝብ ነው፣ ሌላ አይደለም። እኔ የሚገባኝ ህወሓት የለችም ማለት የትግራይ ህዝብ የለም ማለት ነው፤ ስለዚ ህወሓት ማለት ህዝብ ነው፤ ኢህአዴግ ማለት ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ማለት ነው” ብለው ተናገሩ
በዘመናት የትዉልድ ቕብብሎሽና ዉርስ ታሪኩና ማንነቱ በክብር ያቆየዉን የኢትዮጵያ ህዝብ በዚ መልኩ ወደ ድርጅት ጀረጃ አውርዶ ማሳነሱ ሳይበቃ የዚህ ኩሩ ህዝብ ህልዉና በፖለቲካዊ ድርጅቶች ሲረጋገጥ የቆየ ይመስል ኢህአዴግ የለም ማለት የኢትዮጵያ ህዝብ የለም ማለት ነው ብሎ ንግግር ክትዕቢት (Arrogance) እንጂ ከሌላ ሊመነጭ አይችልም። ህወሓት ሆነ ኢህወዴግ እንደ መድረክ ወይም ኢዴፓ ወይም ሌሎች ፓርቲዎች አንድ የፖለቲካ ድርጅት እንጂ የትግራይን ወይም የኢትዮጵያን ህዝብ መተካት የሚችሉ የህዝብ አቻ የሆኑ መዋቅሮች አይደሉም። ሲጀመር የሚያደጉት ነገር ከሕገ መንግስት አንፃር ምን ማለት እንደሆነ ሳይገባቸው ቀርቶ ነው?
ህወሃት ማለት የትግራይ ህዝብ ነው የሚለው አነጋገር ፀረ ህዝብነቱ የሚጎላው ፀረ ሕገ መንግስታዊ ይዘቱ ስንረዳ ነው። ህብረ ፓርቲነት በሕገ መንግስትዋ ያወጀች አገር ፣ ለዛዉም በስንት መስዋእትነት በመጣ ሕገ መንግስት፣ አንድ ኢታማዦር ብድግ ብሎ ህወሓት ማለት የትግራይ ህዝብ ነው፣ ኢህአዴግ ማለት ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው ሲል ያሳፍራል። የትግራይ ህዝብ ህወሓትን ፈጠረ እንጂ ህወሓት የትግራይ ህዝብን አልፈጠረችዉም።
የትግራይ ህዝብ የጋራ የሆነ ፍላጎቶችና ክብሮች ቢኖሩትም ሁሉም ነገሩ ግን አንድ አይደለም። የትግራይ ህዝብ ስንል ገበሬው፣ ላብአደሩ፣ ተማሪና ሙሁሩ፣ ባለሃብቱ እና ወዘተ ነው። የትግራይ ህዝብ ስንል ክርስትያኑ፣ እስላሙ፣ ኩናማው ፣ኢሮቡ ፣ ወጣቱ፣ ሽማግሌው፣ ሴት፣ ወንድ ነው። የተለያየ ፍላጎትና እሴቶች አሉት። ብዙሃነትን የሚያስተናግድ ህዝብ ነው። እነዚህ የተለያዩ ጥቅሞችና እሴቶች የተለያየ መስመርና አደረጃጀቶች ሊተይቅ ይችላል። የተለያዩ ድርጅቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፤ ከሁሉም በላይ ግን አንድ መስመር የሚሉት ፀረ ዴሞክራሲ አባዜ ነው። ጥቂት የተመረጡ የበላይ አመራሮች ለህዝብ የሚጠቅመው ይህ ነው ማለታቸው ብቻ በቂ አይደለም ። የትግራይ ህዝብ ስለ ህወሃት ምን እንደሚል የህወሓት የንደፍ ሃሳብ ልሳን የሆነዉን <ወይን< ምን እንደሚል እስኪ ያንብቡት።
የአገር መከላከያ ኢታማዦር ሹም በጠራራ ፀሃይ የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 87 ( 87/4የመከላከያ ሰራዊት በማናቸዉም ግዜ ለሕገ መንግስቱ ተገዢ ይሆናል 87/5 “የመከላከያ ሰራዊት ተግባሩን ከፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ በሆነ ኣዃሃን ያከናዉናል”) እና ሌሎች ሕጎችን በመፃረር ለህወሓት ጥብቅና መቆም ምን ይባላል? ህወሓት ልክ እንደ ሌሎች የኢህአዴግ ድርጅቶች ያለዉን ቀዉስ አንዱን ወገን ደግፈው በመንግስት ገንዘብ ጊዜ ኮኮብ እየሰሩ ነው እኮ። እነዛ የተደረደሩት ኮኮቦች ሕገ መንግስቱን መጣስ ሲጀምሩ አፈር እንደሚሆኑ ዘነጉት እንዴ? በህወሓት ዉስጥ እርስዎ የሚደግፉት ወገን ህወሓት የለችም ማለት የትግራይ ህዝብ የለም ማለት ነው የሚል ከሆነ እንጦርጦሱ ይግባ።
የሁለት ትዉልዶች ወግ
ጄኔራል ሳሞራ ህወሓት የለችም የሚሉ ምናልባት ራሳቸው የሌሉ እንዳይሆኑ ካሉ በኃላ፤ በጉባኤው ተሳታፊ የነበረችው ወዛም ታደለ የተባለች አምስተኛ ዓመት የህግ ተማሪ “እኔን ጨምሮ ኣብዛኛው ወጣት ህወሓት የለም እምንለው መሬት ላይ ካለ የመልካም አስተዳደር ችግር ተነስተን ነው፤ ብዙ ነገር ጠብቀን እምንፈልገው ነገር ስለማናገኝ ነው፣ ስለዚህ የህወሓት ህልዉና ከዚ ጋር ኣያይዘው እንዲገነዘቡት ነው እምፈልገው” ብላ ትምህርት ስጥታ ጥያቄዋን ሰነዘረች። ጀግና ወጣት ናት!
ጄኔራሉ ህወሓት አለች ምክንያቱም የትግራይ ህዝብ አለ ሲሉ ጅግናዋ ልጂትም አይ ለኔ ህወሓት እምገነዘባት መሬት ላይ ካለ የመልካም አስተዳደር ሁኔታ ጋር ነው፤ ከመንግስታዊ ድርጊት ጋር ነው ብላ “በዚ መልኩ ሊገነዘቡት ይገባል” ብላ ታሪክ የማይረሳው ትምህርት ስጥታለች። በተማረው ወጣቱ ትዉልድ ያለኝኝ ተስፋ በተማሪ ወዛም ታደለ በኩል ማየቴ ብኮራም፤ በስልጣን ላይ ባለዉ ትዉልድና በሚመራው ትዉልድ መሃል ያለው የመረዳትና የእዉቀት ልዩነት ግን የሰማይና የምድር ያህል መራራቁ ግልፅ ያደረገ መድረክ ነበር።
ግለሰቦች ተቛምና የሃገር ደህንነት
የሜቴክ እና የመከላከያ ዕቃ ግዢ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች የመልካም አስተዳደር ችግር ያለው በሲቪል መንግስት ብቻ ነው፤ መከላከያው ግን በጣም ጠንካራ ነው እያሉ ፕሮፖጋንዳ ይነፋሉ። ጄኔራሉም የዚህ ፕሮፖጋንዳ ሰለባ ሆነው መከላከያን እያንቆለጳጰሱ ለአሁኑም ለወደፊቱም እንደተዘጋጁ ሲነግሩን የመንግስት ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሩን ደግሞ ትምህርት ቤት ክፍተው ስለ አመራር ለማስተማር የተዘጋጁ ይመስላሉ::
በዚህ ጉዳይ ከኣንዳንድ ሰዎች ጋር ስነጋገር ጄኔራል ሳሞራን ኣትንካ፤ የአገራችን አለኝታ ናቸው። ያለሳቸው መከላከያዉም ብሎም አገራችን ችግር ዉስጥ ትገባለች አሉኝ፤ ምን ማለት ነው? ሕገ መንግስቱና ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን በግላጭ ሲጥሱስ ብየ ጠየቅዃቸው። <ቢሆንም ይሁን< ነበር መልሳቸው።
በትጥቅ ትግል ግዜ ከጀግኖች መሪዎች አንዱ ነበሩ፤ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ም ቢሆን እንደ ፊልድ ኮማንደር ልዩ አስተዋፅኦ ነበራቸው፤ ጦርነቱ ተንገራግጮ ከዚህ በላይ መቀጠል ኣንችልም እስኪባል ድረስ። ጀግና የነበረ ሁል ግዜ ጀግና፤ ለህዝብ ተቆርቛሪ የነበረ በቀጣይነት እንደዛ ይሆናል ባይባልም ከፈተኛ ክብር ግን ይገባቸዋል። ነገር ግን የኢትዮጵያ ህዝቦች የተዋደቁለትንና በብዙ መስዋእትነት እዉን ያደረጉትን ሕገ መንግስትና ስርዓቱን በግላጭ ሲንዱ ተው መባል አለባቸው።
የኔ ተስፋ መከላከያ ተቛማዊ አስራር ገንብቶ ማንም መሪ ቢሄድ ቢመጣ ስርዓቱን ተከትሎ የሚሄድ ጠንካራ መዋቅር ሆኖ ማየት ነው። ካልሆነ ግን በግለሰቦች እሚንጠለጠል ተቛም ተሁኖ ይህን አገር መከላከል አይቻልም።
ከአስራ አምስት አመት በላይ የአገር መከላከያ ኢታማዦር ሹም ሆነው ሲያገለግሉ፣ ብዙ ጀግኖችና ብቃታቸው ያረጋገጡ ከፈተኛ መኮንኖች የነበሩት መከላከያ እሳቸው ከተነሱ አደጋ ዉስጥ የሚገባ ከሆነ እማ አስራ ኣምስት ዓመት ጥፋት ሲፈፅሙ ነበር ማለት ነው፤ እሳቸው በሌሉበት እንደ ተቛም የበለጠ ተጠናክሮ የማይሰራ ከሆነ ይች አገር በእዉነትም አደጋ ላይ ነው ያለችው።
ከዚህ ጋር የተሳሰረ ወጣቶች ያወጉኝን ላካፍላቹህ።የስዃር ኮርፖሬሽን አመራሮች ፓርላማ ቀርበው “ያሸማቁቁናል፣ ሜቴክን መቅጣት እንደማንችል ሁላቹሁም ይገባቹሃል” ባለቡት ሳምንት ሁለት ወጣቶች አግኝቼ ከሌሎች ሁሉት ጏደኞቻቸው ሆነው ሁለት ለሁለት ተከፍለው በዚህ ዙርያ የጦፈ ክርክር ማድረጋቸው ነገሩኝና ስለምን? ብየ ጠየቋቸው። ሁሉም የተማሩ ወጣት የትግራይ ልጆች ናቸው። ዉይይታቸው ፓርላማ ሜቴክን እንደዛ መጠየቁና ብልሹ አስራር መታገል እንዳለበት ቢስማሙም በተወሰነ ነጥብ እንደተለያዩ ነገሩኝ። ሁለቱ ወጣቶች እዉነታው አሳዛኝ ቢሆንም ኣላማው ትምክህተኞች ትግራይን ለመጉዳት ሆነ ብለው ያቀነባበሩት ሴራ ስለሆነ ከሚጮሆም ጋር ኣብረን መጮህ የለብንም ሲሉ የተቀሩት ሁለቱ ወጣቶች ደግሞ የለም በሴራ ሃሳብ ገብተን ሌብነትን ከብሄር ጋር እያገናኘን እማይገባቸው ከለላ መስጠት የለብንም፤ እንደዉም ለፍትህ መቅረብ አለባቸው፤ ሜቴክም አጠቃላይ አሰራሩ መፈተሽ አለበት ብለው እንደሞገትዋቸው ከሁለቱም ጎራ የነበሩ ሁለቱ ወጣቶች ነገሩኝ።
ሜቴክ አመራር ላይ በርከት ያሉ የትግራይ ተወላጆች ሊኖሩ ይችላሉ። በትግራይ ይሁን በሌላው ኢትዮጵያ እንደ ትግራይ ተቛም አድርጎ ማየቱ ( percieve  ማድረጉ) መሰረታዊ ስህተት ነው። ሜቴክ የቴክኖሎጂ ማእከል የኢትዮጵያ ሽግግር (Transformation) ሻምፒዮና የሚሆንበት ሂደት እንደ ትግራይ/ኢትዮጵያ ሁላችንንም ሕገ መንግስቱ ማእከል አድርጎ ተጠያቂነት፣ ግልፅነት፣ የሕግ የበላይነት ያለንን የሰው ሃይል እና በመቶ ቢልየኖች ቆጥቦ ሲሰራ እንኮራበታለን። እጅጉን እናመሰግነዋለን።
ሜቴክ ተጠያቂነት፣ ግልፅነት፣ የሕግ የበላይነት የማይመለከተው አካል ሆኖ የአገራችንን ከፍተኛ ሃብት ሲያጠፋፋ ግን እንደ ኢትዮጵያዉያን ራሳችንን ደፍተን እናዝናለን። እዛ ያሉ የትግራይ ተወላጆች ጥቂት ቀጣፊዎችና ከነሱ ጋር የሚቀራረቡትን ይጠቀማሉ እንጂ የትግራይ ህዝብን እየበደሉት ነው፤ ለዛዉም ባለ ሁለት ስለት በደል። ባንዱ በኩል እንደ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ የሃገራቸው ሃብት እየተዘረፈ ነው፤ በሌላ በኩል በስሙ እየነገዱ ነው፣ ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ደግሞ ወደ አላስፈላጊ ጥርጣሬ እንዲገቡ ሊያደርግ ይችላል።
ከየትኛዉም ብሄር ብሄረሰብ ወይም ህዝቦች ሕገ መንግስትን፣ ፖሊሲዎችንና ሕጎችን አክብረው በተጠያቂነትና ግልፅነት ቀንና ሌሊት ሰርተው አገራችንን በመለወጥ የድርሻቸዉን ሲወጡ እደጉ ተመንደጉ እንደምንለው ሁሉ፤ ከዚህ በተፃራሪ የሚሰሩትን ቀጣፊዎችን ደግሞ ቀጣፊዎች እንበላቸው አልዃቸው።
ስዃር ኮርፖሬሽን እና ሜቴክ በሚመለከት ጉድ የተባለለት ሪፖርት “ሾልኮ” ለፓርላማና ለህዝቡ ተገልፆ መወያያ በሆነበት ግዜ እና ፓርላማው የመጨረሻ ዉሳኔ ባልሰጠበት ሁኔታ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ቛሚ ኮሚቴ እያንዳንዱ በሜቴክ ተቛሞች እየተዘዋወረ ምስጋና እየደረደረ ነው። የሚገባቸው ከሆነ ይበል የሚያስብል ነው። ግን ደርግነት መንገስ በጀመረበት ከባቢ (Environment) ቛሚ ኮሚቴው ተሸማቆ ይሆን እንዴ እንዲህ የሚያደርገው> የሚል ጥያቄ ሰዎች ያነሳሉ።
መደምደምያ
ደርግነት በሁለት ኢ-ሕገ መንግስታዊና ስርዓት-የለሽ በሆነ መንገድ ሊከሰት ይችላል።አንደኛው በግላጭ መፈንቅለ መንግስት ማድረግ ነው። ሁለተኛው የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ብሎም የኢህአዴግ ምክር ቤት ወይም ፈፃሚዉን መመርያ በመስጠትና በማስፈራራት “እከሌ ሊቀ-መንበር እንዲሆን እከሌን አዉርዱት” ወዘተ በማለት ሊሆን ይችላል። በድርጅቱ ባለው ሁኔታ ይህ አይቻልም ማለት የዋህነት ነው። የግንቦት ሃያ በዓል አስመልክቶ የተደረገው ፓነል ይህን ለማስረገጥ እንዳይሆን መጠንቀቅ አለብን። ኢህአዴግ ዉስጥ ያለው ችግር ባልተመሰቃቀለና ሕገ መንግስታዊ በሆነ መልኩ ከህዝቦች እና ሌሎች ፓርቲዎች ተሁኖ መፈታት ያለበት ጉዳይ ነው፤ ያለ ምንም የወታደር ጣልቃ ገብነት።
የኢትዮጵያ ሰላም፣ ልማት እና ዴሞክራሲ በ ህዝቦች ተሳትፎ እና ትግል ስ ለሚረጋገጥ ሁሉም ሰው መታገል አለበት። ትልቁን የኣሜሪካን መንግስት የደገሰለትን ኢ ፍትሓዊ የጦርነት ጥሪ አልቀበልም በማለት የሚከተለዉን የቦክሰኛዉ መሓመድ ዓሊ ጥቅስ አንድ ጏደኛየ በኢሜል ልኮልኝ እኔም እጅግ ጠቃሚ ሆኖ ስላገኘሁት ላካፍላቹህ ወደድኩ።
“My conscience won’t let me go shoot my brother, or some darker people, or some poor hungry people in the mud for big powerful America. And shoot them for what? They never called me nigger, they never lynched me, they didn’t put no dogs on me, they didn’t rob me of my nationality, rape and kill my mother and father. … Shoot them for what? How can I shoot them poor people? Just take me to jail.”