የኢትዮጵያውያንን ድምጽ እንደመጋዝ ማየት የህዝብን ችግር ቸል ማለት ለማይፈታ አጣብቂኝ ይዳርጋል::


Minilik Salsawi የህዝብን የልብ ትርታ፣ የሀገር ወዳዶችንና ውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ድምጽ እንደመጋዝ ሳይሆን እንደ አጋዥ በማየት ማግባባት፣ ማስማማት፣ለሃገር ስኬት እና እድገት ለህዝብ ነጻነት እና መብት መከበር ለዜጎች ከእስር እና ስደት መዳን የሚረዳ እና ከመሪ የሚጠበቅ የብልህ እርምጃ ነው፡፡እርግጥ በኢትዮጵያ ያለው ወያኔ መራሹ አምባገነን ቡድን ማግባባትን እና መስማማትን አሊያም መደራደርን የሚጠቀመው ለመበላላት ሃገር ወዳዶችን ለማቀጨጭ አሊያም ለማጥፋት በመሆኑ በሃገሪቱ ላይ ከፍተኛ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ችግር በመፍጠሩ የሕዝብ ችግሮች አግጥጠው ከመውጣታቸውም በላይ ሃግሪቷን እርቃኗን አስቀርቷታል::

የወያኔ ሰራሹ አምባገነን መንግስት ለሃገሪቱ የኢኮኖሚ ችግሮች መፍትሔ ሳይሰጥ ወደ ውስብስብና ግዙፍ ችግርነት እንዲያድጉ በቸልተኝነት በመፍቀዱ ያለ ጥርጥር ወደ ፖለቲካዊ ችግርነት አድጓል ፡፡ የወሎ ረሃብ እንደተነናቀ ወደ አብታዊ ማዕበልነት ተለወጠ፡፡ የሚሊተሪ ዲክታተራዊ አገዛዝ መናጠጥ፣ የቢሮክራሲያዊ በደል ማጠጥ፣ የሥልጣን መባለግና ያላግባብ መበልፀግ የአማጽያንን መፈልፈልና የተቃዋሚን ቁርጠኝነት መውለዱን ወለደ፡፡በአሁኑ ወቅትን ከባለፈው በባሰ መልኩ ሕዝባዊ የለውጥ አብዮቶች በውስጥ እና በውጪ እየተቀጣጠሉ መሆኑ የማይካድ ሃቅ ነው::ይህ የሕዝብን ጥያቄ አለመመለስ የወለደው ሌላ ጥያዌ ወያኔን አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል::

ዛሬም የህዝብን ኑሮና የሀገርን ውስብስብ ችግሮች በወቅቱ የመፍታት ቅን ልቦና ከሌለ ስልጣንን ለህዝብ ለማስረከብ ፍዋደኝነት ካልታየ በሃገሪቱ የተዘጋው የፖለቲካ ምህዳር ህግን ጥላ ባደረገ መልኩ ካልተከፈተ የፍትህ አካላት ከአምባገነን ባለስልጣናት መዳፍ ስር ካልወጡ እና ተመሳሳይ የሆኑ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ችግሮች በኢትዮጵያውያን የጋራ ተሳትፎ ካልተፈቱ ዕጣ- ፈንታ ወዳዘዘው ውድቀት ማምራት ግድ ይሆናል፡፡ በዚህ ጉዳይ ስልጣኑን ይዣለሁ የሚለው አካል ዋንኛ ትኩረት በጠበንጃ የመተማመን የበላይነቱን ድርሻ ይውሰድ እንጂ የተለያዩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማህበራትና ኃላፊነት የሚሰማቸው ዜጐች ወዘተ የነገዋ አገራችን ዕጣ-ፈንታ ይመለከተናል ማለት ኤጭ የማይባል ነገር መሆኑን ልብ ማለት ደግ ነው!ገዢ ነኝ የሚለውም ወያኔ ሃገር ወዳዶችን ስለሃገራችን ያገባናል የሚሉ ዜጎችን ሁሉ ከማግለል ከማሰር እና ከማሳደድ የማይቆጠብ ከሆነ ከገባበት አጣብቂኝ መውጣት ካለመቻሉም በተጨማሪ ወደ ማይወጣው ጥልቅ ጉድጓድ እንደሚወረወር ማወቅ ግድ ይላል::

ዕጣ-ፈንታችንን አናመልጥም፡፡ የዕጣ-ፈንታችን አካል ነን፡፡ የምንለው፣ የምናቅደው፣ የምንራዕየው ሁሉ የእኛው አካል ነው፡፡ በተናገርነው እንነገርበታለን፡፡ በደነገግነው እንቀጣበታለን፡፡ በደሰኮርነው እናፍርበታለን ወይም እንኮራበታለን፡፡ በተለይ መንግስት ስንሆን ባወጣነው ህግ እከሌ ከእከሌ ሳንል፣ ወገናዊና ኢፍትሐዊ ባልሆነ መንገድ መተዳደርና መቀጣት አለብን፡፡የመንግሥትነታችን ትልቅ ቁም ነገር የህዝብን ደህንነትና የሀገርን ህልውና መታደግ ነው፡፡ ይህ ዋና ኃላፊነት ነው፡፡ ህዝብ እንዳይሸበር፣ እንዳይጠራጠር፣ ዕምነት እንዳያጣ ማድረግ፤ በአገሩ፣ በመንግሥቱና በኃላፊዎቹ ላይ የመተማመን ስሜት እንዲያድርበት ያደርገዋል፡፡የአስተዳደር ብስለታችን፣ የዲፕሎማሲያችን ጥራት፣ ስለፓርቲና ስለ ሀገር ያለን ግንዛቤ፤ የምንመራውን ህዝብ አመኔታና ተቀባይነት የሚያስገኘው ቁልፍ ነገር መሆኑን መቼም ቢሆን መቼም እንወቅ፡፡ የህዝብን የልብ ትርታ፣ የሀገር ወዳዶችንና ውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ድምጽ እንደመጋዝ ሳይሆን እንደ አጋዥ በማየት ማግባባት፣ ማስማማት፣ ለሃገር ስኬት እና እድገት ለህዝብ ነጻነት እና መብት መከበር ለዜጎች ከእስር እና ስደት መዳን የሚረዳ እና ከመሪ የሚጠበቅ የብልህ እርምጃ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ውክልና የሰጠው የፖለቲካ ድርጅትም ይሁን ግለሰብ የለም::አንዱ ሌላውን የመጋፋት መብት የለውም:: ‪


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ሃገርና ሕዝብ ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል የፖለቲካ ጥቅም እና የበላይነትን ለማስቀደም መፍጨርጨር የሕዝብን ትግል ለፖለቲካ ፍጆታ እና ለትግል ሽሚያ ማዋል ታማኝነትን ያሳታል::የስድብ የፍረጃ ሲልም እኔ ብቻ ነኝ አዋቂ የትግል መሪ የሚል የከሰረ የተነቃበት ፖለቲካ የሌላውን ትግል ማጣጣልም ከታዛቢው ሕዝብ የሚተርፈው ነገር ቢኖር ነገን በነዚህ መመራት ስለማልፈግ ልረጋጋ የሚል መልስ ብቻ ነው:: ልናውቅ የሚገባው ነገር ቢኖር የኢትዮጵያ ሕዝብ ውክልና የሰጠው የፖልርቲካ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ የለም ሲባል ማንኛውም ብሄር ይሁን ብሄረሰብም ምራኝ ታገልልኝ ብሎ ውክልና የሰጠው ድርጅትም ሆነ ግለሰብ የለም::ሕወሓት መራሹ መንግስት በራሱ ፈቃድ የሕዝብ ወኪል አድርጎ ራሱን ሾሞ በሕዝብ ላይ እየቀለደ የሚገኝ ሲሆን ሕዝብ ከዚህ ሂደት ምን ተማረ የሚለውንም ማገናዘብ ይጠይቃል::

ሕዝብን ተጠግቶ ላደራጅህ ላዋቅርህ ልምራህ ብሉ ስትራቴጂውን በሕቡእ የሰራ ይሁን ሊሰራ ያሰበ አልታየም ከወሬና ከስድብ ፖለቲአክ እርስ በእርስ ከመባላት ውጪ::ሕዝብ ይታዘበኛል የሚል የለም::ሁሉም ልክ እንደ ሰው በላው ወያኔ አይኑን በጨው አጥቦ የሕዝብ ልጅ ነኝ ይላል:: በየማህበራዊ ሚዲያ እየተከሰተ የሚያፏጨው ሁላ አንድ ነገር ሊያውቅ ይገባል መሬት ላይ ያለው የሕዝብ ሃቅ እና በዲያስፖራው ዙሪያ የሚነፍሰው ንፋስ እንደ ሰማይ እና ምድር የተራራቁ ናቸው:; የሕዝብ ፍቅር እና አንድነት ወያኔን ሰላም ነስተውታል::ወያኔ ወንጀል የሚፈጽመው ወዶ አይደለም የሕዝብ የጋራ አቋቋም ከአቅሙ በላይ ስለሆነበት ነው::በኦሮሚያ ክፍለሃገር የተነሳው የሕዝብ ንቅናቄ ሌላውን ነዋሪ እንዲያጠቃ ወያኔ ከግድያ ጀምሮ ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም ግን አልተሳካለትም::ሲልም ይህን ሕዝብ ራሱ የመራውን ንቅናቄ ራሳቸው እንደፈጠሩት እንዳደራጁት እንድመሩት አድርገው ለማቅረብ ከሞከሩ ጀምሮ እኛ ያልመራነው ትግል ስላልሆነ ርባና ቢስ ነው እስካሉ ድረስ ፖለቲከኞች ቢታዩም የኦሮሞ ሕዝብ ንቅናቄ ግን ከአለም ሚዲያዎች ጀምሮ እስከ ምእራባውያን ፖለቲከኞች ድረስ አስደምሟል::ይህ የሚያሳየው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነቱን ራሱ እንደሚፈልግ እና ውክልና የሰጠው ድርጅትም ሆነ ግለሰብ አለመኖሩን ከማረጋገጡም በላይ የድርጅቶችን እና ግለሰቦችንም እንታገላለን የሚለውን ስትራቴጂ ባዶነት በገሃድ አጋልጧል::

የኦሮሞን ሕዝብ ንቅናቄ ተከትሎ በውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሚዲያዎች ያበረከቱት ድርሻ ትልቅ ሲሆን መሬት ላይ እንዳለው ሕብረተሰብ አይታገሉ እንጂ የማህበራዊ ድህረገጾችም ሰፊ የሆነ የመረጃ ስራ ሰርተዋል::ሕዝብ ደምቆ በታየበት በዚህ ንቅናቄ ከዲያስፖራው ድጋፍ ይልቅ የኦሕዴድ አባላት ለሕዝቡ ጥያቄ ታላቅ አስታውጾ አበርክተዋል:: ለራሱ ትግል ራሱ ሙሴ የሆነው ሕዝብ የወያኔን አገዛዝ እንዳይነሳ አድርጎ አንበርክኮታል::በዙሪያው ብቻ ሳይሆን በወያኔ ውስጥ ታላቅ ሽብርን ፈጥሯል::ድል አድራጊነትን ተግጎናጽፏል::ጥቂት ጠባቦች እና ትምክተኞችም የኦሮሞን ሕዝብ ትግል የራሳቸው ለማስመሰል ሲርወጡ ተስተውሏል::ከዚህም አልፈው ሲወነጃጀሉ ታይቷል ከተራ የስም ስያሜ ጀምሮ እስከማይመለከታቸው በመዘባረቅ አለመብሰላቸውን እንድንታዘብ እንዲሁም ስንዴ ከእንክርዳድ እንድንለይ አድርገውናል::በየቋንቋው ዘባርቀዋል::ሕዝቡ ግን ውክልና የሰጠሁት ድርጅት አሊያም ግለሰብ ይህ ነው ብሎ አልተነፈሰም አልተናገረም ሁሉም በየፈርጁ ራሱን ሲኮፍስ አይተናል::በዚህ ሰሞን መነባነብ ወያኔ ቢወድቅ ኖሮ ምንኛ በታደልን ነበር:;ግን ከትዝብት ውጪ ከፕሮፓጋንዳ የጭብጨባ ፖለቲካና ከአፍራሽ ሚና ውጪ እንዲሁም ሊመራን የሚችል ስላላገኘን እንረጋጋ ከሚለው ውጪ ለወያኔ ክፍተት ከመስጠት ውጪና ተመሳሳይ ጉዳዮች በቀር አንድም የረባ ነገር ከለውጥ መሪ ሃይሉ አልተመዘገበም::ለዚህ ሁሉ ችግሩ እጅ ላይ ባሌለ ውክልና ራስን የሕዝብ መሪ አድርጎ የማሰብ ጭፍን ሃሳብ ውጤት ነው::ስለዚህ እኔም እላለሁ የኢትዮጵያ ሕዝብ ውክልና የሰጠው የፖለቲካ ድርጅትም ይሁን ግለሰብ የለም:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬
Minilik Salsawi's photo.