ብሄራዊ መግባባት የሚፈጠረው ሁሉም ዜጋ በእኩልነት ሲኖር እንጂ ምሁራንን ሰብስቦ በመጮህ አይደለም::

ብሄራዊ መግባባት የሚፈጠረው ሁሉም ዜጋ በእኩልነት ሲኖር እንጂ ምሁራንን ሰብስቦ በመጮህ አይደለም::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎EthiopianOppositionparties‬ ‪#‎Ethiopiaprotests‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi - Ethiopian DJ - አዲሱ የጊዜ መግዣ ዲስኩር - ብሄራዊ መግባባት መፍጠር - ወያኔ ሕዝብን ማታለል ልማዱ ስራው ተግባሩ አድርጎ ይዞታል::ወያኔ ምሁራንን ሲያወያይ ይህ ለመጀመሪያው አይደለም አዲስ አበባን በገበሬውና በኤምፔሪያሊዝም ድጋፍ ሲቆጣጠር ጀምሮ ምሁራን ሲያወያይይ ካለንበት የተበላሸ ፖለቲካ ላይ ደርሷል::ሁልግዝጥ እቅድ ነድፈናል ከማለት ውጪ አንድም ጠብ ያለ የተሻሻለ ነገር የለም::ዜጎች በአገራቸው ጉዳይ እንዳይሳተፉ እንዲሳቀቁ እንዲደነብሩ ወዘተ ከግድያ ጀምሮ እስከ እስር እና ማሳደድ ድረስ በፊት ለፊት ካለእፍረት ተግብሯል::ሕዝብ መንቃቱን እንኳን አንድም የማይባንነው ወያኔ ሁል ግዜ ማዘናጊያ እና ጊዜ መግዣ ብሎ የሚወስዳቸው እርምጃዎች ሁሉ ያለፈባቸው እና ችግሮችን ከማባባስ ውጪ ምንም የፈየዱት ነገር የለም::ባለንበት 21ኛ ክፍለ ዘመን ፖለቲካው በስሏል አገራት ዜጎቻቸውን መወንጀል ትተው ኢኮኖሚያቸውን ሲገነቡ እያየን ነው::እንናገረው ብንል ብዙ ማለት ይቻላል ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ይህ በፍጹም የለም::ግልጽነት እና ተጠያቂነት ስላሌለ አገሪቷ የመሃይማን እና የሌቦች መፈንጫ ሆናለች::

ወያኔ ተናግሮ እንደማይጠግበው እንደደርግ ሃገር ሊለውጡ የሚችሉ እና ተስፋ የሆኑ የተማሩ ወጣት ትውልዶችን በጠራራ ጸሃይ እየደፋ ይገኛል::የወያኔ ወንጀሎች ተነግረው አያልቁም አሁን ዋናው አትኩሮት ወንጀል እና ወንጀለኞችን ማስወገድ ያስፈልጋል የሚለው ጊዜ ላይ ደርሰናል::ወያኔ ከአገዛዝ ሂደቱ በጎሳ ፖለቲካ ከፋፍሎ መግዛት እንዳልተሳካለት እያየው ነው::በፕሮፓጋንዳ እና በሃሰት መግዛትም ሕዝቡን እንዳስመረረው እያየው ነው::ራሱም ወያኔ በራሱ ላይ መስክሯል::ታዲያ ም እየተጠበቀ ነው ማስተዳደር መምራት ካልተቻለ ስልጣን መልቀቅ አንድ እና ብቸኛ መፍትሄ ነው::መርጦኛል ያለው ሕዝብ አልመረጥኩህም ብሎ እስከ ሕይወት መስዋትነት ከፍሎ በተግባር ወያኔን እንደማይፈልገው አሳይቷል::ዝም ያለውም ሕዝብ ለውጥ ፈላጊ እደሆነ መዘንጋት የለብንም::ዝምታ በራሱ ከባድ እና አደገኛ ተቃውሞ ነው::

የሃገሪቱን ችግር ለመፍታት በሚል በሁለት በኩል የተሳለው የወያኔ ምላስ ሕዝብን ለማጭበርበር እና ጊዜ ለመግዛት የማይቧጥጠው ነገር የለም::ከዚህም አንዱ የሃስት ይቅርታውን ተከትሎ ምሁራን ከሚላቸው ጋር ስብሰባ መቀመጡ አንደናው የማዘናጊያ መገድ ነው:;የወያኔ አገዛዝ የምሁራንን ምክር ቢሰማ ኖሮ አሁን የምናያቸው ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ባልተፈጠር ግድያዎች እና እስሮች እንዲሁም ሕዝብ ማፈናቀል ማሳደድ እና መዝረፍ ሙሰኝነት በሃግሪቱ ልቀው አይገኙም ነበር::ወያኔ ካሁን በኋላ ጊዜው አልፎበታል::ያለው እድል ስልጣኑን ለሕዝብ ማስረከብ ብቻ ነው:; ዘረፋ እና የሕዝብ ደም መጠጣት የለመዱ የወያኔ ባለስልጣናት ሰይጣናዊ ባህሪያቸውን ይቀይራሉ ማለት አንድም የዋህነት ሌላም ሞኝነት ነው::ስለዚህ ይሃገሪቱ ችግሮች ብቸኛው አማራጭ ወያኔን አውርዶ ሕዝባዊ መንግስት መመስረት ብቻ ነው::ብሄራዊ መግባባት የሚፈጠረው ሁሉም ዜጋ በእኩልነት ሲኖር እንጂ ምሁራንን ሰብስቦ በመጮህ አይደለም::ጊዜ መግዣ አጀንዳ !‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

እርቃን ሲቀሩ ከሕዝብ ለመታረቅ ? በቅድሚያ እስረኞችን መፍታት የጎሳ ፖለቲካ ፖሊሲና ዜጎችን ሽብርተኛ እያሉ መፈረጅ መቆም አለበት:: ስልጣን ለሕዝብ ማስረከብን ይጨምራል:

እርቃን ሲቀሩ ከሕዝብ ለመታረቅ ? በቅድሚያ እስረኞችን መፍታት የጎሳ ፖለቲካ ፖሊሲና ዜጎችን ሽብርተኛ እያሉ መፈረጅ መቆም አለበት:: ስልጣን ለሕዝብ ማስረከብን ይጨምራል:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎Change‬
 
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - የኢትዮጵያውያን ጥያቄዎች እጅግ ብዙ ናቸው::የሕዝብን ጥያቄ ሳይመልሱ ኖሮ አሁን እመልሳለሁ ማለት በሕዝብ ላይ መቀለድ ነው::ሕወሓት የሚረግመው የሰው ደም መጣጩ ደርግ በ17 አመቱ ቆይታው እንኳን ባለፉት 25 አመታት የተፈጠሩ ችግሮችን አልፈጠረም:: በዲሞክራሲ ስም አልነገደም በግልጽ አፋኝ ነኝ ብሎ በግልጽ ነበር የዜጎችን ደም የሚጠጣው ይህ ብቻ አይደለም ዜጎችን ጸረ አብዮተኛ ብሎ ቢፈርጅም አምልጠው ስደት የሄዱትን እንኳን በፖለቲካ እምነት እንደወጡ አምኖ የተቀበለ ወታደራዊ ጁንታ ነበር::ደርግን ማንሳት በኔ ባያምርም ሕወሓቶች ራሳቸው የሚያወዳድሩት ወደፊት ከሚኬደው ሳይሆን ከተቀበረ ሬሳ ጋር ስለሆነ ምክንያቱ ይህ ነው::

ወደ ሰሞነኛው ጉዳያችን ስንገባ ሕወሓት መራሹ አገዛዝ ከትግራይ እስከ ደቡብ ጫፍ ሕዝቡ ተመሳሳይ ተቃውሞ አንስቷል በተለይ በኦሮሚያ በተግባር ዞር በሉ ብሎናል ችግሩን በመፍታት ከሕዝቡ መታረቅ አለብን:: የሚል ዲስኩር አያሰማ ነው::አገዛዙ ከሕዝብ ጋር ቅራኔ የገባው የጎሳ ፖለቲካውን በአገሪቱ ላይ ካወጀ ጀምሮ እንዲሁም ሃሳባቸውን በነጻነት በገልጹ መብታቸውን የጠየቁ ምንም ያልታጠቁ ሰላማዊ እና ደሃ ዜጎችን አሸባሪ ብለኦ ሲፈርጅ ሲያስር ሲገድል እና ተመሳሳይ ጸረ ሕዝብ እርምጃዎችን ሲወስድ መሆኑን ባለፈው 20 አማእታት አልተረዳውም:: ወያኔ ምንም ጊዜ የሚነቃው ሕዝብ ነቅቶ ከጨረሰ በኋላ ነው::ነቅቻለሁ ብሎ ፖሊሲ ቢለውጥ ጥሩ ነው ሆነኦም እያወቀ በሕዝብ እና አገር ላይ ጥፋት በተደጋጋሚ እየፈጸመ ይገኛል::ከሕዝብ ለመታረቅ በቅድሚያ እስር ቤቶች ማጽዳት(በሽብር እና በተመሳሳይ ወንጀል በሃሰት ተፈርጀው የታሰሩትን መፍታት) የጎሳ ፖለቲካ ፖሊሲና ዜጎችን ሽብርተኛ እያሉ መፈረጅ መቆም አለበት::ከዚህ በመቀጠል ስልታን በመልቀቅ ወርዶ ሕዝባዊ መንግስት መመስረት ብቸኛ መፍትሄ ነው::

በሃገራችን ጉዳይ ሁላችንም ዜጎች ይመለከተናል::ሃገር የጥቂቶች መፈንጫ ልትሆን አይገባም::በሃሰት እና በፕሮፓጋንዳ አገር ማስተዳደር ውጤት አልባ ያደርጋል ይህን ደግሞ ካለፉት 25 አመታት ሂደት መማር ግድ ይላል:: አገሪቱ ላለፉት 50 ዓመታት አይታው በማታውቀው ድርቅ ምክንያት ችግር ውስጥ የገቡ ከአሥር ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያንን መታደግ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በኦሮሚያ በርካታ አካባቢዎች ከአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የጋራ የተቀናጀ ማስተር ፕላንን በመቃወም የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ፣ በአማራ ክልል የቅማንት ማኅበረሰብ የማንነት ጥያቄ ተከትሎ የተቀሰቀሰ በጦር መሣሪያ የታጀበ ግጭት፣ በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ለመመለስ የክልሉ መንግሥትና ፓርቲ የጋራ ማስተር ፕላኑ እንዲታጠፍ መደረጉን ቢገልጹም፣ ተቃውሞው መልኩን ቀይሮ በሌሎች አካባቢዎች ቀጥሎ ይገኛል::እንዲሁም የወልቃይት ጠገዴ በሃይል ከትግራይ ክልል መጠቃለሉ ተቃውሞ አስነስቷል::የቁጫ ሕዝብ የኮንሶ ሕዝብ የመዠንገር እና የሱርማ ሕዝብ ጥያቄዎች የጋምቤላ ግጭት በተጨማሪም በመላው ሃገሪቱ ተስፋፍቶ የሚገኙ በርካታ ጥያቄዎች እና ተቃውሞዎች የፈጠራቸው የሕወሓት አገዛዝ የሚከተለው እና ስህተት ነው ብሎ ያመነበት የፖለቲካ የኢኮኖሚ እና የማህበረሰባዊ ፖሊሲዎች መሆናቸው እሙን ነው::

በአገሪቱ የተንሰራፋው የጎሳ ፖለቲካ ሕዝቦች በሃገሪት እንደ ዜጋ ተዘዋውረው የመስራት መብታቸውን ገፏል::በአንድ ብሄር የበላይነት ኢኮኖሚውን ለመቆታጠር የሚደረገው ሩጫ ሌሎች ዜጎች ደሃ እንዲሆኑ አድርጓል::ለዚህ ሁሉ ግን መፍትሄው ይቅርታ ሳይሆን ስልጣን መልቀቅ ነው::በኦሮሚያ ክልል ለተደረገው ግድያ ተጠያቂው ማነው? ከፌዴራሉም ይሁን ከክልሉ ግድያውን ያዘዘው ተጠያቂው ክፍል በአለም አቀፍ ሕግ መሰረት ለፍርድ መቅረብ አለበት::እንዲሁ መላቀቅ የለም:: እያንዳንዱዋ ጉዳይ ወደ ተግባር እንድትቀየር በተግባር መታገላችን እንቀጥላለን:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬