«የሚቆርጡንን የምንነክስበት ጊዜ ላይ ደርሰናል !!! » የእርስ በእርስ የጅምላ ፍረጃ ይቁም።ኪሳራው ከባድ ነው።

Image may contain: text and food

«የሚቆርጡንን የምንነክስበት ጊዜ ላይ ደርሰናል !!! » የእርስ በእርስ የጅምላ ፍረጃ ይቁም።ኪሳራው ከባድ ነው።

ሕወሓትን ከመታገል ይልቅ የጽንፍ ፖለቲካ ይዞ መላፋት ያሳፍራል። የትግሉ እውነታዎች እንደተጠበቁ ሆነው የትግል ሻሞ ያለ ይመስል ላም ባልዋለበት ኩበት መልቀምም ያሳፍራል።ኣደርባይነት ኣስመሳይነት እጅግ ኣደገኛ ነው። የእርስ በርስ መኮራኮም የጅምላ ፍረጃ ከሕዝብ ልብ የሚፈልቀውን ተኣማኒነት ያሳጣል።

 የወያኔ ውሸት ስልችት ብሎን ባሌበት ጊዜ የቅፈላ ፖለቲካ የሚከተሉ የለውጥ ሃይሎች ጎታችነታቸውን ገትተው የመቻቻል የመከባበርና የመደማመጥ ፖለቲካ ኣካል ሊሆኑ ይገባል። ለውጥ የሚፈልጉ ሕዝቦች በተነሱ ሰዓት ሁሉ ኣበረታቹን ተበረታቹን የምንፈርጅ ከሆነ ኣደጋ ኣለው። ያውም ከባድ ኣደጋ።

ትግል ምንም ጊዜ የሚፈልገው መቻቻልና መደማመጥ ሲሆን ፍረጃ ቅፈላ እና የውሸት ፖለቲካ ያልበሰሉ ካድሬዎች ጩኸት ስኬቱን ያኮላሸዋል፤ ዛሬ ላይ እኛ ብቻ እናውቅልሃለን ብለው ለሚናገሩ ሰዎች ደጋፊ የሆኑ ነገ ላይ ጠያቂ ሆነው መታለላቸውን መረዳታቸው ኣይቀርም።እውነት ቀኗን ጠብቃ ነጻ ትወጣለች።በግራ በቀኝም በመሃልም የቆማጩ የለውጥ ሃይሎች ከመፈራረጅና ከልፊያ ፖለቲካ ወጥታቹ ኪሳራቹን በማስላት ወደ ሕዝባዊ የጋራ ትግል ተሰባሰቡ። #MinilikSalsawi

ቆራጥ ትግል ያስፈልጋል፡፡ የሕወሓት/ኢሕኣዴግ ባለሥልጣናት ምግባረ ብልሹነት የተጠናወታቸው ስለሆኑ ወንጀል ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም፡፡

By ምንሊክ  ሳልሳዊ

ይሰማል ?? #Ethiopia : ቆራጥ ትግል ያስፈልጋል፡፡ የሕወሓት/ኢሕኣዴግ ባለሥልጣናት ምግባረ ብልሹነት የተጠናወታቸው ስለሆኑ ወንጀል ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም፡፡ #Miniliksalsawi 

Minilik Salsawi – mereja.com – መንግስታዊ ሌቦች ተራ ሌቦች አይደሉም፡፡ አደገኞች በገንዘብ የታጀቡ በሥልጣንም የተደገፉ ናቸው፡፡ የሕወሓት/ኢሕኣዴግ ሌቦች ተራ ሌቦች አይደሉም፡፡ አደገኞች ናቸው፡፡ ምክንያቱም በገንዘብ የታጀቡ ናቸው፡፡ በሥልጣንም የተደገፉ ናቸው፡፡ ምግባረ ብልሹነት የተጠናወታቸው ስለሆኑ ሕገወጥ ገንዘብና ሥልጣናቸውን ላለማጣት ሕግን ከመጣስና ወንጀል ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም፡፡ ሌላውን አስወግደው እነሱ ብቻ የሚቆጣጠሩትና የእነሱን ፍላጎት ብቻ የሚያረካ መንግሥት የተቁዋቁዋመበት ነው!!!፡፡ ጉዞው ሌቦች የበላይነት የያዙበትና የሌቦች መንግሥት የተቁዋቁዋመበት ነው!!!በቆራጥ ትግል ሕወሓት ከኢትዮጵያ ምድር እንዲወገድ እንረባረብ።

የተወገዘ የነበረው የተለመደ ሆኗል፡፡ ጉቦ መውሰድ ኃጢአትና ወንጀል መባሉ ቀርቶ ጉቦ አለመቀበል ጅልነትና ሞኝነት እየተባለ ነው፡፡ፀረ ሕዝብ፣ ስስታም፣ ስግብግብና በሙስና የተጨማለቁ ለግል ጥቅምና ክብር ሲሉ አገርንና ወገንን ከመሸጥ፣ ከመለወጥ፣ ከመካድና ከመርገጥ ወደኋላ የማይሉ ባለሥልጣናት በሥልጣን ላይ መቀመጥ የሌለባቸው፣ መሾምና መከበር የማይገባቸው ባለሥልጣናት እንደዚህ ዓይነት ባለሥልጣናትና ሹሞችን ይዞ አገርን ከአደጋ ማዳን፣ ሕዝብን ከድህነት ማላቀቅና ፍትሕና ዴሞክራሲን ማስፈን አይቻልም፡፡በቆራጥ ትግል ሕወሓት ከኢትዮጵያ ምድር እንዲወገድ እንረባረብ።

ይህን ሕዝብ ከድህነት ማላቀቅና ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን የሚሆነውና በተግባር የሚታየው፣ ሀቀኖቹ በሌቦቹ ላይ የበላይነት ሲያረጋግጡ ብቻ ነው፡፡ በተግባር ሀቀኞች በሌቦች ላይ የበላይነት ሊኖራቸው የሚችለው ደግሞ ሲታገሉና በትግሉም ዋጋ መክፈል ሊኖርባቸው እንደሚገባ አምነው ሲንቀሳቀሱ ብቻ ነው፡፡
በቃል፣ በንድፈ ሐሳብ፣ በመግለጫና በቃለ መጠይቅ የመንግሥት ሌቦች እንዳሉ መናገሩና ማውገዙ ብቻ የትም አያደርስም፡፡ እንቅፋት ናቸው ብሎ መግለጹ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ የመንግሥት ሌቦች ካልተወገዱ የሌቦች መንግሥት ይመሠርታሉ ብሎ ማመን፣ ይህ የሌቦች መንግሥት እውን እንዳይሆን ለመቅጣት፣ ለማስወገድና ለመጠራረግ ቆራጥ ትግል ያስፈልጋል፡፡በቆራጥ ትግል ሕወሓት ከኢትዮጵያ ምድር እንዲወገድ እንረባረብ።

ሌቦችን ለማስወ ቆራጥ ትግል ያስፈልጋል፡፡ የሕወሓት/ኢሕኣዴግ ባለሥልጣናት ምግባረ ብልሹነት የተጠናወታቸው ስለሆኑ ወንጀል ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም፡፡ ፡፡ ሀቀኛው በተዝናና ቁጥር ሌባው እየተጠናከረ ይመጣል፡፡ በገንዘብ ተከታዩን ይገዛል፡፡ በገንዘብ ኔትወርክ ይዘረጋል፡፡ በገንዘብ ከውጭ ጠላት ጋርም ሊተሳሰር ይችላል (ሌብነት ድንበር የለሽ ነውና)፡፡ በገንዘብ ሀቀኞችን የሚያስወግዱ ኃይሎችን በማሰማራት ሊያሸንፍ ይችላል፡፡ በገንዘብ የመገናኛ ብዙኀንን ሊቆጣጠር ይችላል፡፡አቅም ያጣውን፣ ዕውቀትና ልምድ ያነሰውን በትምህርትና በሥልጠና ማጠናከር ይቻላል፡፡ ሌባና ወንጀለኛን ግን የሥልጠና፣ የሴሚናርና የውይይት ብዛትና ዓይነት አይለውጠውም፡፡ ሕጋዊ ዕርምጃ ብቻ ነው መፍትሔው፡፡የሕዝብ፣ የአገር፣የዴሞክራሲ፣ የፍትሕና የሰላም ጠላቶችን ማስወገድ ነው፡፡በቆራጥ ትግል ሕወሓት ከኢትዮጵያ ምድር እንዲወገድ እንረባረብ። #ምንሊክሳልሳዊ

በፍርሃት የሚኖር ፈሪ ኣገዛዝ – 11,607 ሰዎች ታስረዋል።

በፍርሃት የሚኖር ፈሪ ኣገዛዝ

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ኣምባገነኑ ሕወሓት ኮማንድ ፖስት ብሎ በገዳይ ወታደሮቹ ያደራጀው ቡድን 11,607 ሰዎችን ማሰሩን ስንሰማ ስርዓቱ ምን ያህል የሕዝብ ፍራቻ ውስጥ እንደሚገኝ ቁልጭ ኣድርጎ ያሳያል። በራሳቸው የማይተማመኑ ለስልጣናቸው ጥም ሲሉ ያልታጠቁ ንጹሃንን ከየቤታቸው በመውሰድ ማጎሪያ ካምፕ ውስጥ መክተታቸው የሕዝብ ተቃውሞ ስጋት ውስጥ እንደጨመራቸው ኣመላካች ሲሆን ኣገዛዙ የሕዝብን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ ኣፈናን መፍትሄ ማድረጉ ከባድ ፍራቻ ውስጥ መዘፈቁን ይመሰክራል።

ከየቤታቸው የታፈኑ ለዝብ ተቆርቋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ ሲሆን የዞን ዘጠኝ ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ ዛሬ ማለዳ 12 30 ገደማ ኮማንድ ፓስት ይፍለግሃል በሚል ሰበብ ከመኖሪያ ቤቱ በጸጥታ ሃይሎች ተይዞ እዛው መኖሪያ ቤቱ አካባቢ በሚገኝው 06 ፖሊስ ጣቢያ መታሰሩ ታውቋል። ኣሰርነው ብለው ያመኑትን በኣስር ሺዎች ቁጥር ኣሳንሰው ሲሆን ቁጥራቸው ውስጥ ያላስገቧቸው በሺዎች የሚቆጠር የታፈኑ ወጣቶችን ቤት ይቁጠራቸው።

ኣገዛዙ በፍርሃት የሚኖር ፈሪ በመሆኑ ብቻ ኢትዮጵያውያንን እያፈሰ በየማጎሪያ ካምፑ ኣስሮ ይገኛል። የሕዝብ ንቅናቄ ቀጣይነት ለስርዓቱ ኣደጋ መሆኑን ስለሚያሳይ የሕዝብ የጋራ ተቃውሞ በርትቶ ሊቀጥል ይገባዋል። የለውጥ ፈላጊ ሕዝቦችን ንቅናቄ ግድያ እስርና ኣፈና ኣይመልሰውም። ሕዝብ ኣሸናፊ ነው ሕዝብ ትክክል ነው። ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል። #Miniliksalsawi